Thursday, 30 January 2014

በጎንደር የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራር እና የቅስቀሳ ቡድን አባላት በፖሊስ ታሰሩ


January 30, 2014
ጥር 22/2006 (BlueParty Ethiopia)
እስካሁን 14 የሰማያዊ ፓርቲ አባላት በጎንደር የታሰሩ ሲሆን ከታሰሩት ውስጥ አራት ከፍተኛ የፓርቲው አመራሮች ይገኙበታል፣
1. ጌታነሀ ባልቻ (የድርጅት ጉዳዮች ሃላፊ)
2. ብርሃኑ ተ/ያሬድ (የሀዝብ ግንኙነት)
3. ዮናታል ተስፋዬ (የወጣቶች ጉዳይ ሃላፊ)
4. ይድነቃቸው ከበደ (የህግ አማካሪ)

ሁለት ሹፌሮች እና አንድ ፊልም አንሺም (Cameraman) ከታሳሪዎቹ ውስጥ ናቸው፣ በአሁኑ ስዓት ታሳሪዎቹ በወረዳ ሁለት ፖሊስ ጣብያ ሲገኙ ጌታነሀ ባልቻ (የድርጅት ጉዳዮች ሃላፊ) እና አግባው ሰጠኝ ወደ ጎንደር ከተማ ከንቲባ ጽ/ቤት ተወስደዋል።
ጥር 25 2006 ዓ.ም. የኢትዮ ሱዳን ድንበር ማካለልን ህገወጥነት በተመለከተ በጎንደር መስቀል አደባባይ የሚደረገውን ሰላማዊ ሰልፍ አስመልክቶ ከአዲስ አበባ የተጓዘው የሰማያዊ ፓርቲ የቅስቀሳ ሉኡካን ቡድን በዛሬው እለት በጎንደር ከተማ በቅስቀሳ ላይ እንዳሉ ከፍተኛ እንግልት እየደረሰባቸው ሲሆን ጎንደር የገባው ቡድን በጠቅላላ በእስር ላይ ይገኛል፡፡ የቅስቀሳው አባላት በጎንደር ከተማ እና በተለያዩ ቦታዎች ቅስቀሳውን እንደጀመሩ የፓሊስ አባላት ፈቃድ ስለሌላችሁ መቀስቀስ አትችሉም ያሏቸው ሲሆን አባላቱም በህጉ መሰረት ማሳወቅ እንጂ ማስፈቀድ የሚጠበቅብን ስላልሆነ ለሚመለከተው አካል ያሳወቅን በመሆናችን ህጋዊዎች ነን በማለታቸው ፓሊስ በማዋከብና በመደብደብ ጎንደር ከተማ በሚገኘው ሁለተኛ ፖሊስ ጣቢያ በመውሰድ በአሁኑ ሰአት ከፍተኛ መጉላላትና እንግልት እያደረሱባቸው ይገኛል፡፡ የጎንደር ከተማ ነዋሪዎችም ፖሊሶቹን ምን አደረጓችሁ በማለት እና ይህ ጉዳይ የኛም ጉዳይ ነው በማለት አባላቱን ከፖሊስ ለማስለቀቅ የተቻላቸውን ያደረጉ ሲሆን ፖሊስም ሐይል በመጨመር ህዝቡን በዱላ በማባረር የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራር እና የቅስቀሳ ቡድኑን እንዲሁም የጎንደር የፓርቲው መዋቅር አባላትን ጨምሮ አስረዋቸዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የጎንደር ነዋሪ ህዝብ የፖሊስ ጣቢያውን በመክበብ የታሰሩት እንዲፈቱ እየጠየቀ ሲሆን ሰልፉ በተያዘለት ቀን እንዲደረግ ለማድረግ ሌላኛው የሉኡካን ቡድን ከአዲስ አበባ በዛሬው እለት መንቀሳቀሱ ታውቆአል፡፡
A protest call in Gonder, Ethiopia

“ኢትዮጵያውያን ለምንድን ነው የውጭ ገበሬዎች የሚያስፈልጓቸው? ምንድን ነው ይዘውልን የሚመጡት?” አቶ ግርማ


"አንድም ሰው ከቀዬው እንዲፈናቀል አልተደረገም" ሚኒስትር ዴኤታ
displaced anuaks


  • “ሰፋፊ የእርሻ ኢንቨስትመንቶች እንደታሰቡት ውጤታማ አልሆኑም” መንግሥት
  • መንግሥት የውጭ ባለሀብቶች የመሬት ቅርምት ኢትዮጵያን አይመለከትም አለ
የውጭ ባለሀብቶች በግብርና ኢንቨስትመንት ላይ ለመሰማራት ሰፋፊ የእርሻ መሬቶችን ወስደው እያለሙ እንጂ፣ መሬት ለመቀራመት ብለው ወደ ኢትዮጵያ አልገቡም ሲል ግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
“መሬት መቀራመት ኢትዮጵያን ጭራሽ አይመለከታትም፤” ሲሉ የግብርና ሚኒስትሩ አቶ ተፈራ ደርበው ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስታውቀዋል፡፡
ሚኒስትሩ የመሥሪያ ቤታቸውን የስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ለፓርላማው ማክሰኞ ዕለት ሲያቀርቡ፣ ሰፋፊ መሬቶች ወስደው በግብርና ላይ ኢንቨስት እያደረጉ ስለሚገኙ የውጭ ባለሀብቶች ትክክለኛ ማብራሪያ እንዲሰጡ በተጠየቁበት ወቅት ነው ይህንን ያሉት፡፡
በፓርላማ ብቸኛው የተቃዋሚ ፓርቲ ተወካይ የሆኑት አቶ ግርማ ሠይፉ ለሚኒስትሩ ባቀረቡት ጥያቄ፣ የውጭ ኩባንያዎች ሰፋፊ መሬቶች አንዳንዶቹ እንደሚሉት ቤልጂየምን የሚያህል መሬት ተሰጥቶ እየተካሄደ ስላለው ኢንቨስትመንት በቂ ማብራሪያ በሪፖርቱ ስላልተካተተ እውነቱ ሊብራራ ይገባል ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

የ2014 የዓለም የመፈንቅለ መንግሥት ትንበያ

ኢትዮጵያ 25ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች

coup map


በያዝነው የአውሮጳውያን ዓመት ሊከሰቱ የሚችሉ የመፈንቅለ መንግሥት አደጋዎች ይፋ ሆኑ፡፡ በርካታዎቹ በአፍሪካ አገራት ሲሆኑ አደጋው ካንዣበበባቸው አገራት መካከል ኢትዮጵያ 25ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡
በአሜሪካ የፖለቲካ ሳይንቲስት የሆኑት ጄይ ዑልፌልደር የተለያዩ የሒሳብ ስሌቶችን በመጠቀም የ2014ዓም የመፈንቅለ መንግሥት ትንበያቸውን ሰጥተዋል፡፡ እንደ እርሳቸው ትንበያ ከሆነ 40 አገራት ቀይ የአደጋ ምልክት በርቶባቸዋል፡፡ ስለ ጉዳዩ ሲናገሩ መፈንቅለ መንግሥት እንዲሆን የሚመኙት ነገር ባይሆንም የመከሰቱ ጉዳይ ግን መነገር ያለበት ነው ይላሉ ምሁሩ፡፡
በተለያዩ የአሜሪካ አንጋፋ ጋዜጦች ላይ የተዘገበው ይኸው ጥናት እንደሚያመለክተው በዓለማችን ላይ 40 አገራት ከፍተኛ የመፈንቅለ መንግሥት አደጋ ያነጣጠረባቸው መሆናቸውን በጥናቱ ተገልጾዋል፡፡ አብዛኛዎቹም ከአፍሪካ መሆናቸው አሁንም አህጉሪቱ ለበለጠ ቀውስ የተጋለጠች መሆኗን የሚያሳይ ነው፡፡

Saturday, 25 January 2014

አብረሃ ደስታ በአዲግራት ድብደባ ተፈጸመበት


January 25, 2014
Ethiopian blogger Abraha Desta from Tigry, Mekele
አብረሃ ደስታ
(ECADF) አብረሃ ደስታ ፌስቡክን በመጠቀም ከመቀሌ (ትግራይ) በሚያሰራጫቸው ወቅታዊ መረጃዎች፣ የፖለቲካ ትንታኔዎች እና ዜናዎች በፌስቡክ ተጠቃሚዎች ዘንድ አብዝቶ ይታወቃል። የአረና-ትግራይ ፖለቲካ ፓርቲ አባል እንደመሆኑ ደግሞ የፓርቲውን ወቅታዊ እንቅስቃሴዎች ይዘግባል።
ሰሞኑን እንደተለመደው ዓረና እና መድረክ በዓጋመ (አዲግራት) ጥር 18 ስለሚያካሂዱት ህዝባዊ ስብሰባ እንዲህ በማለት ገልጾ ነበር፣
ዓረና መድረክ ከዓጋመ (ዓዲግራት) ህዝብ ጋር በፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ለመወያየት ለእሁድ ጥር 18, 2006 ዓም በዓዲግራት ህዝባዊ አዳራሽ (ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ) ቀጠሮ መያዙ ይታወቃል…
የአብረሃ ቀጣይ ዘገባ እንደሚያመለክተው፣ በተቃዋሚዎች ህዝባዊ ስብሰባ መጥራት የተሸበሩት ህወሀቶች የስብሰባው ቀን ከመድረሱ በፊት እርምጃ መውሰድ መጀመራቸውን ነበር፣
ዓረና ፓርቲ በዓዲግራት ከተማ ለእሁድ ከጠራው ህዝባዊ ስብሰባ ጋር በተያያዘ ዛሬ ዓርብ ሁለት የዓረና አመራር አባላት (አቶ ዓምዶምና መምህር ገብረጨርቆስ) በዕዳጋ ሐሙስ ከተማ ፖሊስ ታስረዋል። የታሰሩበት ምክንያት ህዝብ በስብሰባ እንዲሳተፍ ቀስቅሳችኋል የሚል ነው። ህወሓቶች በተምቤን የፈሩትን ያህል በዓጋመ ፈርተዋል። በተምቤን ተመሳሳይ የእስር ሁኔታ አጋጥሞናል። ስብሰባ ፈቅደው ስለ ስብሰባው ህዝብ እንዳይሰማ ግን ከለከሉ። ይገርማል።
በማግስቱ አብረሃ ደስታ እና ታጋይ ጓደኞቹ በህወሀት ቅጥረኛ ወንጀለኞች፣ በፖሊሶች እና በከተማው አስተዳዳሪዎች ፊት ከፍተኛ ድብደባ ተካሄደባቸው። ሁኔታውን አብረሃ እንዲህ በማለት ገልጾታል፣

Monday, 20 January 2014

ወሬ አይደለም፤ አገር ቤት አንገባለን” ሌንጮ ለታ


ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፤ “መረጃ የለኝም”
odf lencho


የኦሮሞ ነጻ አውጪ ግንባር ከፍተኛ አመራርና ጸሐፊ የነበሩት አቶ ሌንጮ ለታ አዲስ ያቋቋሙትን ድርጅት ይዘው አዲስ አበባ እንደሚገቡ አስረግጠው ተናገሩ። አቶ ሌንጮ ድርጅታቸው ኢትዮጵያ ገብቶ ለመታገል መወሰኑ ለምን ወሬ እንደሚባል እንዳልገባቸውም አመላክተዋል። በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ኢትዮጵያ መግባታቸውን ኦነግ እንደሚቀበለው ተጠይቀው “ኦነግን ጠይቅ” በሚል ጠበቅ ያለ መልስ ሰንዝረዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ እንደሌለው አመልክቷል።
ጥር 5 ቀን ከጀርመን ድምጽ የአማርኛ ፕሮግራም ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት አቶ ሌንጮ “ኖርዌይ ተቀምጠን ምን እናደርጋለን? ሃገር ቤት ገብተን እንታገላለን” ሲሉ ወደ አገር ቤት ለመመለስ መወሰናቸውን ግልጽ አድርገዋል። “ይሳካል?” በማለት ጠያቂው ላቀረበው “ይሳካል አይሳካም ተብሎ ወደ ትግል አይገባም” በማለት አቶ ሌንጮ ማምረራቸውን በሚያሳብቅ ሁኔታ መልስ ሰጥተዋል።
ህወሃት የዘረጋውን የፌዴራል ሲስተም እንደሚቀበሉትና የኦሮሞ ህዝቦች ጥያቄም በዚያው ውስጥ ሊመለስ እንደሚችል ያመለከቱት አቶ ሌንጮ፣ “በታሪክ፣ በባህል፣ በቋንቋ የተመሰረተ ሳይሆን በህግና በህገመንግሥት በተደነገገ የህዝቦች አንድነት እናምናለን” ብለዋል። የግለሰብ መብት ከብሔር መብት መቅደም አለበት፣ የብሔር መብት አስቀድሞ ሊከበር ይገባዋል በሚል ሁለት አቋም ከሚያራምዱት የተለየ ፕሮግራም እንዳላቸውም አቶ ሌንጮ አስታውቀዋል። የግለሰብም ሆነ የቡድን መብት መከበር አለበት የሚል ፕሮግራም ያለው አዲሱ ድርጅታቸው በዚህ አቋሙ ከሌሎች እንደሚለይ አመልክተዋል።
በምርጫ የመሳተፍን ጉዳይ አስመልክቶ የእሳቸው ድርጅት ብቻ ሳይሆን ሁሉም ተቃዋሚ ሃይሎች ወደ ምርጫ ቢገቡ ፍላጎታቸው መሆኑንን አቶ ሌንጮ ተናግረዋል። ይሁን እንጂ ከምርጫ በፊት ብዙ ጥያቄዎች እንዳሉ አመልክተዋል። ዴሞክራሲን ኢትዮጵያ ውስጥ ለማስፋፈት ምርጫ ብቻውን መፍትሔ እንዳልሆነም ጠቁመዋል። ህዝብን አገር ቤት ገብቶ ማስተማር፣ መቀስቀስና ማብቃት በዋናነት አስፈላጊ እንደሆነም አስምረውበታል።

“ወደው አይስቁ” (ክንፉ አሰፋ)


January 20, 2014
ክንፉ አሰፋ
የጥምቀት በዓልን ተሰባስበን በምናከብርበት አንድ ቤት ውስጥ ካለወትሮው ፓልቶክ ተከፍቷል። በዚያ የበዓል ድባብ፤ የፓልቶክ ንትርክ መከፈቱ ሳይገርመን፣ ርእሱ የሁላችንንም ቀልብ መሳቡ። በእርግጥ አንድም ቁም ነገር በንግግሩ አልሰማንም። አዲሱን ቋንቋ ልዋስና የፓልቶኩ ተናጋሪዎች ሙድ  የሚያስይዙ ነበሩ። ሰዎቹ በዚህ ከቀጠሉ የእነ ክበበው ገዳን ገበያ መዝጋት እንደሚችሉ አያጠራጥርም።
የድምጽ መነጋገርያውን የያዘው ሰው ጉሮሮውን ጠራርጎ ንግግሩን እንዲህ ሲል ጀመረ።  “የምኒሊክ ወንጀል በጡት መቁረጥ ብቻ አያበቃም። …  የወንዶች ብልትም ተቆርጧል።…”
በአኖሌ ሃውልት የምትገረሙ ነፍጠኞች ካላችሁ። በዚህ ብዙም አትደነቁ። ገና የወንድ ልጅ ሃፍረተ-ስጋ በሃውልት መልክ በአደባባይ ይቆምላችኋል። “የባሰ አታምጣ!” ነው ነገሩ። ሜንጫዎቹ ሰክረዋል። አእምሮዋቸውም ስቷል።  የሚናገሩትን አያውቁትም።  የማየውቁትን ነገር ሁሉ ይናገራሉ።  እነሱ የሚናገሩትን ደግሞ በምኒሊክ ቤተ-መንግስት ያሉ ሰዎቻቸው በተግባር ይፈጽሙላቸዋል።
ተናጋሪው የእለቱ የክብር እንግዳ መሆኑ ነው። በጉዳዩ ላይ ብዙ ጥናት እንዳደረገም አስቀድሞ ገለጻ ተደርጓል። ሰዎቹ የወንዶች ብልት መቆረጥን የፈጠራ ታሪክ ያነሱት ያለምክንያት እንዳልሆነ ግልጽ ነው። ጡትን በአደባባይ ያቆሙ እብዶች፣  የወንድ ብልትን አያቆሙም ማለት አንችልም።  “ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም!” ይላል የሃገሬ ሰው። ስለ አኖሌ የፈጠራ ውጤት በያዝነው አዲስ አመት አውርተን ሳንጨርስ፤ ይኸው የባሰ ነገር እየመጣ ነው። ምኒሊክ የወንድ ብልትምም ቆርጠዋል ነው እያሉን ያሉት – ጨዋታቸውን ሲያራዝሙት። አጼ ሚኒሊክ ለካ የጉጂ ኦሮሞ ኖረዋል።  ትንሽ ቆይተው ጉጂዎች የወንድ ብልት መቁረጥ የተማሩት ከምኒሊክ ነው ይሉናል።  እዚህ ላይ ሰዎቹ እየቀለዱ ብቻ አይደለም።  እየቀለዱብንም ነው። ወዳጆቼ ግን አሁንም ሙድ ይዘዋል።…
በነዚህ ቀልደኞች ዘና እንል ይሆናል። አንድ የዘነጋነው ነገር አለ።  የሴት ልጅ ጡት በአደባባይ ሃውልት የተሰራለት በእኛ ምድር ላይ ብቻ ነው።  ይኸውም በእኛ ዘመን። ሴት ልጅ በሃገራችን ትከበራለች። የውስጥ አካልዋ እንዲህ በአደባባይ ላይ ሲውል ክብርዋን ይቀንሰዋል። የሴትን ልጅ ጡት በአደባባይ ላይ አውለው፤ ህጻናትና አዋቂው እንዲመለከተው ማድረግ በባህላችንም እጅግ ነውር ነገር ነው።
“ምሁሩ” የታሪክ ተንታኝ ንግግሩን በዚህ አላበቃም። ማብራራቱን እንደቀጠለ ነው።  “…ይህንን ታሪክ ለማወቅ የታሪክ መጽሃፍ ማንበብ አይጠበቅባችሁም። በኢንሳይክሎፔዲያ ላይም ግዜያችሁን አታባክኑ። በቀላሉ ጉግል አደርጉና ታገኙታላችሁ… ” አለ። ጉግል ስናደርግ ይህንኑ መረጃ በራሱ ድረ-ገጽ ላይ ልናገኘው እንችል ይሆናል።

በደምና በአጥንት መስዋዕትነት ተከብሮ የቆየ የሃገራችንን ዳር ድንበር ለባዕድ አሳልፈን አንሰጥም!


January 20, 2014
ብርሃኔ አሰበ አለሁድረስ
ሀገራችን ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ሃብቷ የታደለች ፣መልካም የአየር ፀባይ ያላት፣ህዝቦቿ የራሳችን አኩሪባህልና ወግያለን፣የራሳችን መልካም መልክዓ ምድራዊና አሰፋፈር ያለን በጋራ ተሳስረን አብረን የኖርንባትና የምንኖርባት በየትኛውም ዘመን ሉአላዊነቷ ያልተደፈረ ለአፍሪካ ተምሳሌት የሆነች ሀገር ናት። በተለያየ ወቅት የተፈጥሮ ሃብቷን ለመቀራመትና ሉአላዊነቷን ለመዳፈር የሞከሩ ሃገራት ሁሉ፣በውድ ልጆቿ የተባበረ ክንድ አይቀጡ ቅጣት ተቀጥተው ኢትዮጵያን ዳግም እንዳይመኟት የተባረሩበትና የኢትዮጵያን አይበገሬነት በአፍሪካም ሆነ በአለም መድረክ ያስመሰከረች፣ አንድነቷንና ሉዓላዊነቷን ጠብቃ በማቆየት በአለም ታሪካዊ ስፍራ ያላት፣ በቀደምት ውድ ልጆቿ የደም መስዋዕትነት ሀገራችን ሉአላዊነቷ ሳይደፈር ለብዙ ሺ አመታት ቆይታለች።
Ethiopian government to hand over land to Sudan
በአሁኑ ስዓት ኢህአዴግ/ህወሃት ለግልና ለግዚያዊ የፖለቲካ ጥቅም ሲል የኢትዮጵያን አንድነት በማደብዘዝ እንሆ በእኛ ዘመን ለዘመናትተደፍሮ የማያውቀውን የኢትዮጵያን ሉአላዊነት በመጋፋት የኢትዮጵያ የሉአላዊነት ባለቤት የሆኑት ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ሳይወያዩበትና ሳያፀድቁት በጓሮ በር የኢትዮጵያን መሬት ለባዕድ ሃገር/ሱዳን ቆርሶ ለመስጠት ሽርጉዱን ተያይዞታል። ከአመታት በፊት በምዕራቡ የሃገራችን ክፍል /ድንበር በኩል/ በመሸራረፍ ለም የሰሊጥ ምርት የሚሰጥ መሬት ለሱዳን ሲሰጥ ዝም በማለታችን  እንሆ ዛሬ የኢትዮጵያን ሉአላዊነት የሚጋፋ ፣ የኢትዮጵያን ቅርጽ የሚያጠፋ ረጅም ርዝመት ያለው ለም መሬት ለሱዳን ለመስጠት ዝግጅቱ መጠናቀቁን ሰማን።
ዛሬ ላይ ሆነን ይህንን መሰሪ ተግባር አንድነታችንን አጠናክረን መግታት ካልቻልን ነገ ደግሞ በሌላኛው የኢትዮጵያ ጫፍ በኩል የኢትዮጵያ መሬትተቆርሶ ለሌሎች አጎራባች ሀገራት ላይሰጥ ምን ዋስትና አለን?

Sunday, 19 January 2014

ሾልኮ የወጣ የጥምቀት የጭፍጨፋ ድግስ ሚስጥር

January 18, 2014
ቹቸቤ
በመጀመርያ ለክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ አደረሳችሁ። እንዲያው ይሁን ብዬ እንጂ ጥምቀተ ባህር እንኳን ሙስሊም ጓደኞቻችንም አብረውን ይውሉ እንደነበር አስታውሳለሁ።የጥምቀተ ባህር ፀበል ብቻ ሳይሆን የፍቅር ፀበልም የሚረጭበት  የፍቅር በታ ነው።: በተለይ  ተረ … ተረረረ…. ረረረ የምትል ማንም ከደፈረ የሚጫወታት ሃርሞኒካ ተይዛ ከሚጨፈርበት እነ አብዱና እነ ሙስጠፋስ መች ይጠፉ ነበር። ለጥምቀት ያልሆነ ቀሚስ ይበጣጠስ ብለው ሜዳውን የሚሞሉት ኮረዶች መካከልስ ተቃቅፈው ወይ እጅ ለእጅ ተያይዘው ከሚሄዱት ሃሊማና ሩቅያስ መች ይታጡ ነበር። “ተዋዶ ያለበት እስላም ክርስትያኑ…ተዘነጋሽ እንዴ ኢትዮጵያ መሆኑ”  ያለው ቴዲ ይህን በዐይኑ አይቶ እንጂ ተረት ሰምቶ አይደለም። ደግሞም ነገም ወደፊትም አብረን እንኖራለን የማያኖሩን አይኑሩ! አሜን አላችሁ?
አሁን በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች ድህረ ገጽ ላይ ሰውነት የሚያንቀጠቀጥ ዘግናኝ የሆነ ጉዳይ በእንግሊዝኛ ተጽፎ አነበብኩ። http://ecadforum.com/2014/01/17/
terror-plot-to-turn-ethiopian-
epiphany-celebration-into-an-inferno-uncovered/


በእንግሊዝኛ መጻፉ ብቻ ሳይሆን የመልዕክቱ አስቸኳይነት እጅግ አሳሰበኝ። ለነገ የሞት ድግስ መላምት ካልሆነ አለም ሊያውቀው እኛም ሕዝቡን ልናስጥነቅቅበት የሚገባ መሆን አለበት በሚል ስሜት በድጋሚ አነበብኩት። ከሆነ በሁዋላ ከማዘን የተወራውን ማሳወቅ የታሰበ ነገርም ካለ ተነቃብን እንዲሉ ካልሆነም አስፈላጊ ጥንቃቄ እንዲደረግ ስለሚረዳ መልዕክቱን ማጮህ ይሻላል ብዬ አሰብኩ።

ክህደት ከአናት ሲጀምር፣ በቀድሞው የኢትዮጵያ አየር ኃይል ውስጥ


January 18, 2014
ከቀድሞው የኢትዮጵያ አየር ኃይል አባላት
እውነት ቤት ሥትሰራ …
ውሸት ላግዝ ካለች
ሚስማር ካቀበለች
ጭቃ ካራገጠች
ቤቱም አልተሰራ … እውነትም አልኖረች ።

… እንደዚያ ነው በባቢሎን ዘመን ።
የአንዱ ቋንቋ ከአንደኛው ይዘበራረቃል ….. መግባባትና መረዳዳት ብርቅ ይሆናል ። በጠራ አማርኛ የተጣፈውን በጉግማንጉግኛ በመተርጐም ከውስጡ የሚፈልጉትን ብቻ አለፍ አለፍ እያሉ ያነቡታል ። እናም የራሳቸውን ትርጉም ይሰጡታል ። ፍየል ወድያ ….. ቅዝምዝምም ወዲህ ይሆናል ።
ከቀድሞው የኢትዮጵያ አየር ኃይል አባላት መካከል ጥቂት አዛውንቶች ታሪክን ደልዘው በወያኒኛ አዲስ ታሪክ ስለ አየር ኃይሉ እንዲፅፉ በህውሃት እየተጠየቁ ነው ። እነዚህ ባለ ብዙ አኩሪ ታሪክ ባለቤት አዛውንቶች መንታ መንገድ ላይ ቆመዋል ። በዓለም ዙርያ ተበትነው ያሉት የቀድሞው አየር ኃይል አባላት ሃሳባቸውን እንዲደግፉና
የእርዳታ እጃቸውንም እንዲዘረጉ ለማግባባት እየሞከሩ ነው ። እኛም የቀድሞው የአየር ኃይል አባላት እንዲህ አልን ……….

“ የአየር ኃይልን ታሪክ ለትውልድ ለማስቀረት የምታደርጉት ጥረት በጐና የሚደገፍ ምግባር ነው በርቱ ፤ ነገር ግን የገዢው ፓርቲ ሞግዚትነት አያስፈልጋችሁም ። በተጨማሪም በተፅዕኖ ስር ሆናችሁ ሚዛናዊነት የሚጐድለውና የተደለዘ ታሪክ ለትውልድ እንዳታቆዩ ሥጋት ቢጤ አለችን ። (ያም ቢሆን መፅሃፉን ካነበብን በኋላ የምንታዘበው ይሆናል … አያጣላም ።)
የአየር ኃይል ቬተራን አሶሴሽንን እናቋቁማለን የምትሉትን በተመለከተ ግን ወራጅ አለ ። እጅግ ከስጋት በላይ የሆኑ ጥያቄዎች አሉን ። “ የቀድሞው አየር ኃይል ቬተራን አሶሴሽን ” እያላችሁን ከሆነ ግን እንግባባለን ።
የሚለውን ጥቅል ሃሳብ በመልዕክታችን ብንሰድላቸው በጉግማንጉግኛ በመተርጐም እኛ ፖለቲካ አንነካካም …. ፖለቲካንና ኰረንቲን በሩቁ ነው ብለናል ይሉናል ከአዲስ አባ ደብዳቤ እየፃፉ ። እነሱ ለካ የአሁኑን የህውሃትን መንደርተኛ አየር ኃይል ነው ቬተራን እያሉ የሚያንቆለጳጵሱት ። በህውሃት ሰማይ ስር ጉድ ሳይሰማ አያድርም አይደል !

Tuesday, 14 January 2014

የመረጃ ነፃነት ? …. (ይድነቃቸው ከበደ )


January 14, 2014
‹‹ ሕዝቡ እኔ ማን እንደሆንሁ ይላል ? ›› በማለት እየሱስ ክርስቶስ መረጃ ይጠይቃል ፤ ደቀመዛምርቶችም ስለሱ የተባለውን አንድም ሳያስቀሩ ይነግሩታል፡፡ እሱም መልሱ እንዲህ ይላቸዋል ‹‹ እናንተስ እኔ ማን እንደሆንሁ ትላላችሁ ? ››አላቸው ፡፡ እነሱም መለሱለት፡፡ ሙሉ ታሪኩ ሉቃስ 9ቁ 18 ላይ ይገኛል ፡፡
Yidnekachew Kebede
መረጃ አይናቅም አይደነቅም ማለት እንዲህ ነው፡፡ በመሰረቱ ክርስቶስ ሰዎች ስለሱ ምን እንዳሉ ብቻ ሳይሆን ምን እያሰብ እንደነበር የሚያውቅ አምላክ ነው፡፡ ግን መጠየቅ እና መመለስ አሳብን መግለፅ የሰው ልጅ ተፈጥሯዊ ባህሪ ነው፡፡ ለዚህም ነው ክርስቶ እንደሰው በምድር በተመላለሰበት ወቅት መረጃ ይጠይቅ የነበረው እሱም ስለራሱ መረጃ ይሰጥ የነበረው፡፡ እርግጥ ነው ክርስቶስ ይህን ሲጠይቅ የራሱ ምክንያት አለው፡፡
በመሆኑም ሃሳብ መግለፅ ተፍጥራዊ መብት ነው ወደሚለው ዓለም አቀፍ ስምምነት በመደረሱ የመናገር ሃሳብን የመግለፅ ነፃነት የዲሞክራሲ ዋና የድም ስር ነው የተባለው፡፡ ስለዚህም ተሰባስቦ መቃወም እንዲሁም መደገፍ ፣ አንድ ሰው የሚመስለውን ሃሳብ በፈለገው መንገድ መግለፅ፣ የመምረጥና የመመረጥ፣ መንግስትን የመተቸት፣ በራስ ፍቃድ የመናገረ እና ያለመናገር ፣ በዓልንና አይማኖትን መከተልና ማስፋፋት እንዲሁም ህግ ለሁሉም የሚሰራ ስለመሆኑ መረጋገጥ እና የመሳሰሉት ሁሉ ተግባራዊ የሚሆነው ተአቅቦ ያልተደረገበት የመናገርና የመረጃ መብት ልውውጥ ተግባሪዊ ሲሆን ብቻ ነው፡፡

ለመደርደሪያነት የዚህን ያኸል ከተባለ ወደ ዋናው ጉዳይ አስፈቅደን ሳይሆን ፈቅደን እንገባለን፡፡ ያነሳነው አሳብ ‹‹ መረጃ ›› እንደመሆኑ መጠን ያለማንም ጣልቃ ገብነት ተፍጥሯዊ መብታችን በፈለግነውና በፈቀድነው መንገድ እንገልፃለን፡፡ እኛ ስል ለመረጃ ነፃነት የቆምነው ሁላችንም ማለቴ ነው፡፡

Monday, 13 January 2014

Letter to Sudan and AU: Secret land grab deal with TPLF (campaign)

January 13, 2014
Embassy Of The Republic Of Sudan
2210 Massachusetts Ave
Washington DC,20008,
Ph: 202.338.8565
Fax: 202.667.2406
AFRICAN UNION/ UNION AFRICAINE/ UNIÃO AFRICANA
Addis Ababa, Ethiopia, P.O. Box: 3243
Tel.: (251 11) 5513 822
Fax: (251 11) 5519 321
Email:  situationroom@africa­-union.org;oau­-ews@ethionet.et
Subject: Secret land grab deal with Tigray People Liberation Front (TPLF)
Dear Mr. Ambassador,
Ethiopian people and Sudanese people lived in harmony for millennia, they live together sharing common values prior and post colonial era. Most of us still remember the music of late Said Khalifa, Mohamed Wardi and others. I believe Sudanese also remember the music of late Tilahun Gessese, Menilik Wesinachew, Bizunesh Bekele and others. Ethiopian and Sudanese people share not only borders but cultures and millennia long history and values. Ethiopia’s contribution on anti-colonial struggle was definitely undisputable. The defeat of Italian colonizer by Ethiopian lead by Emperor Menelik is remembered by all colonized nations who suffered under European colonization let alone Sudanese fellow citizens.
Unfortunately, current Ethiopia failed under the siege of Tigrian People’s Liberation Front (TPLF). Ethiopia’s natural resources are nationalized and the people of Ethiopia are the hostage of TPLF. TPLF, ethnocentric regime, as you well know is giving away fertile land of the country for kickbacks and also in the process of secret deal with the Sudanese government to give away large chunk of land as pay back for the help it received from Sudanese government when it was in the bush. This unholy deal conspired behind the people will only be a recipe for future instability and animosity. We concerned Ethiopians advice Sudanese government to back off from such deal. TPLF represents neither Ethiopia nor Ethiopian people. To conclude a deal with such tyrant regime is considered as a conspiracy against Ethiopian people and is a ticking time bomb that will not benefit Sudan in the   future. Any deal done behind the Ethiopian people will not be recognized and will be null and void as soon as this tyrant regime is gone. Dictators come and go but people live forever. Therefore, for the good of the Sudanese and Ethiopian people and for lasting relationship of the two nations, we urged the Sudanese government to refrain from instilling long lasting animosity between Ethiopian and Sudanese people.

Friday, 3 January 2014

አልጋ ወራሹ ማነው?


January 3, 2014
ባህር ከማል
የአንድ ወጣት እድሜ አስቆጥሯል፤ በኢትዮጵያ በስልጣን ላይ ያለው ቡድን ህወሃት/ኢህአዴግ  መግዛት ከጀመረ። በብሄርና  በሃይማኖት  እኩልነት ስም ህብረተሰቡን  በመከፋፈል ለሃያ ሶስት አመታት ስልጣኑ ላይ ከመቆየቱም በላይ፤ ጥቂቶቹ የቡድኑ አባላትና ደጋፊቆቻቸው በጉቦ በዘረፋና  ለም መሬት  በመሽጠት ጭምር ሲከብሩ፤ ብዙሃኑ ሕዝብ ግን ኑሮው ከእለት እለት እያሽቆለቆለበት ሲሄድ፤ አገዛዙ ግን በአሥራ ምናምን ከመቶ አድገሃል እያለ ሕዝቡን ሊያታልለው ይሞክራልል።
በአሳ መበላት፤ በዘራፉዎች መደብደብና  መዘረፍ ከዚያም አልፎ ተገድሎ የሆድ እቃው  መቸብቸብ እንዳለ  እያወቀ ባለሁበት ሁኜ ከሚሞት እድሌን ልሞክር በማለት ክፍት በሆነለት መንገድ ከአጋሪቷ የሚሸሸው ህዝብ ቁጥር ከፍተኛ ነው ።  ከዚህ ሁሉ መከራና ስቃይ ተርፈው   ወደ “ተፈለገበት አገር” የሚደርሱ ወገኖቻችን እዚያም ከደረሱ በኋላ የሚደርስባቸው  ስቃይና እንግልት ተነግሮ የሚያልቅ አይደለም። ለዚህም በአለም ደቻሳ በሊባኖስ፤ በሸዋዬ ሞላ በሊቢያ፤ እንዲሁም ካሜራና የድምጽ መቅረጫ ያላገኛቸው በሺዎች በሚቆጠሩ፡ ወገኖቻችን የደረሰባቸውና ዛሬም በሳውዲና እንዲሁም በደቡብሱዳ እየደረስባቸው ያለው መከራና ስቃይ በቂ ምስክርነው። በእንቅርት ላይ ጆሮደግፍ እንዲሉ ሊወክላቸው የሚገባው መንግስት ህገወጥ ስደተኖች ናቸው ብሎ ተሳልቆባቸዋል።
ከላይ እንደገለጽኩት የገዢው ቡድን ህብረተሰቡን በመከፋፈልና ያለውን ሃይል በመጠቀም ጭምር እስካሁን ስልጣን ላይ ለመቆየት በቅቶአል፡:
የዛሬው ሁኔታ ባለ መልኩ ለዘላልም ስለማይቆይ ሁሉም ነገር ያልፋልና እነሱ ሲያልፉ (በጡረታም ሆነ በደከመን ወይም በዘረፋው በቃን ሲገለሉ) ልጆቻቸውን ለመተካት ሽርጉዱ ከተጀመረ አመታት ተቆጥረዋል። መተካካት ይሉታል በነሱ ቋንቋ ።

Thursday, 2 January 2014

ኣወይ ጉዴ ወይ መላ ጉዴ (ሄኖክ የሺጥላ)


January 1, 2014
ሄኖክ የሺጥላ
ኣወይ ጉዴ ወይ መላ ጉዴ
ብቸኛው ልቤ ሰው  በመውደዴ
ነው  ያለው ኣረጋሃኝ ወራሽ ኣሁን እንደሱ ልፋትና ጥረት ቢሆን ኖሮ የኢትዮጵያ ሙዚቃ የት በደረሰ። ለነገሩ ይሄ ትውልድ የተሰራውን ሁሉ በመናድ : የተጣፈውን ሁሉ በመካድ ነው የሚታወቀው። እኔ እንኳ በዘመኔ ስንት ኣየሁ። ኣሁን ማን ይሙት ኣደይ ትርሃስ በፍራሽ መዋጥ ለሁለት ዕየከፈሉ ያጸኑት ሹሩባ የሚረሳ ሆኖ ነው “ቢዮንሴ ሄር ስታይለር ምናምን ምንምን በሚል ሰጋቱራ ሃገሩን ያጥለቀለቅነው።” እስኪ ኣሁን ምን ትውልድ ኣለ። ድሮ ቡና እንኩዋ እስከ ሶስተኛ ነበር የሚጠጣው፤ ኣሁን ግን ኢኮኖሚው በ ፲፩ ፐርሰንት ኣድጎ ቡና እንኩዋ የሚያቆመው ሰባተኛ ምናምን ላይ ነው። በውነት ፕሮፌሰር ኣልማርያም እንደሚሉት ይሄ ትውልድ ኣቦ ሸማኔ ሳይሆን ኣቦል ሸማኔ ነው። ኣያቶቻችን ለኣድዋ ጦርነት ምታ ነጋሪት ክተት ሰራዊት ሲሉ፤ መለከት: ጥሩንባ ሲነፉ  ነው ታሪክ የሚነግረን። ዛሬ ግን የመለከት እና የእንቢልታ ሪሚክስ  በየ ስርጣ ስርጡ ሺሻ መንፋት ሆኖዋል ግብራችን። የሰሞኑ መፈክር ኪንግ ኣብደላ ሼም ኦን ዩ፤ ሼም ሼም ሼም፤ ነበር ኣይደል፤ ምነው ሺሻው ተረሳ ታዲያ፤  ኣጎቶቻችን  ባርነትና ውርደት ብቻ ሳይሆን ሱሰኝነቱንም ኣወረሱን።
Ethiopian poet Henok Yeshitla
እንግሊዚኣዊው  ጋዜጠኛና ጠሃፊ Grham Hancook The sign and the Seal (The Quest for The Lost Arc of the Covenant)  በሚለው መጥሃፉ ላይ The Ethiopian slept a thousand years forgetting the world by whom they were forgotten by  ይላል :: በነገራችን ላይ የላይኛውን የኣነባበብ ዘዬ (style ) ኣንድ ነገርን ኣስታወሰኝ :: ባንድ ወቅት በስድስት ኪሎ (university ) ያስተምሩ የነበሩ መምህር  ስለ ጆነፍ ኬንዲ ሞት ለተማሪዎቻቸው ሲያስተምሩ (During the time and death of Jonneif Kennedy everybody was shocken) ኣሉ በዚህን ጊዜ ኣንድ የቅዱስ ዮሴፍ ተማሪ ሳቁን ለሞአቆጣጠር ሲታገል  ያስተዋሉ እኝሁ መምህር በነገሩ በስጨት ይሉና “ምን ያስቅሃል ሾካካ!!!” ኣሉ ኣሉ። እንግዲህ ያዙልኝ ሾክን ሾካካ ከሚለው ነው የመጣው ማለት ነው። እሺ ይሁን  ሾክንስ ከሾካካ ነው እንበል፤ ኣድርባይነት፤ ባንዳነት፤ ሆዳምነት፤ ታሪክ ሸቃይነት፤ እነዚህስ?  ኣንድ ወዳጄን በጣም በስጨት ብዬ ኣረ ባክህ እኔ ኣልገባኝም ይሄ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን መናቅ ከየት የመጣ ባህል ነው ስለው፤ ፈገግ ብሎ በርግጠኝነት ከቻይና ኣይደለም፤ ከቻይና ቢሆን ይህን ሁሉ ዘመን ኣብሮን ኣይቆይም ነበር፤ ማናልባት ከጣልያን ይሆን እንዴ ኣለኝ። ወይ ኢትዮጵይ፤ ልጆችሽ ተከብረሽ የኖርሽው ባባቶቻችን ደም የሚለውን ዘፈን  በየስብሰባው እና ሰላማዊ ሰልፉ ላይ ደጋግመው በማቀንቀናቸው ዘፈኑ ራሱ ሰልችቶት ልጆቼ ሃያ ሶስት ኣመት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳልል ተዘፈንኩላችሁ በሉ ኣሁን ሌላ ዘፈን ፈልጉ፤ እናንተን እንዳየሁዋችሁ ከሆነ ፤ እኔን እንደ ልደት ዘፈን በሻማ ከባችሁ ከማልቀስ ውጪ  ምንም የምታመጡ ኣይመስለኝም፤ እና ጡረታዬን ጠብቁልኝና እስኪ ደሞ ይቺ የቀረችው ጊዜዬን እፎይ ብዬ ልኑር ኣለ ኣሉታዲያ ምን ይዋጠን፤ ኣንቺም ዜሮ ዜሮ እንዳንል ዘፋኙ እንጀራው ላይ የቅንድብ ጠጉር ተገኝቶበት ገበያውን ገደለው፤ ምን ይበጀን፤ ምን ይሻለን።  ከማቀንቀን ውጪ ሌላ ነገር ለማድረግ ዛሬም በቅጡ የተዘጋጁ ኣይመስልም፤ በየ ዝግጅቱ ላይ ኣበው ኣባቶቻችንን በ ፩ ደቂቃ የህሊና ጸሎት ከማሰብ ውጪ ሰምሮላቸው የተሻለ ነገር ሲያደርጉ ዛሬም ኣናይም።

በናታችሁ ከዚች አገር አውጡኝ!


January 2, 2014
Alex Abreham (Facebook)
በናታችሁ ከዚች አገር አውጡኝ ! በቃ ሱማሌም ኧረ ምናምን ሱዳንም ይሁን ብቻ ኢትዮጲያ የምትባል አገር የማልሰማበት አገር ውሰዱኝ !

አሁን ቤት አከራየ መጣና የቤት ኪራይ አምስት መቶ ብር ጨምር ሲለኝ ቤት አከራየ ሳይሆን ኢትዮጲያ አስጠላችኝ !! የቤት ኪራዩ ብቻ እንዳይመስላችሁ የግፍ አገር ናት ! ምንም ፍትሃዊ ነገር የላትም ! እንደድመት ወልዳ የምትበላ ጉድ !

እስካሁን የኖርኩበትን እድሜ ቢያንስ ሶስት አራተኛውን አንገቴን ደፍቸ በመማር አሳልፊያለሁ በተማርኩት ሙያም እችን ለዛዋ የተሟጠጠ አገር አገልግያለሁ ! በምሰራው ስራ በመስሪያ ቤቴ የተመሰገንኩ ባለሙያ ነኝ ! ግን አንድ ቀበሌ ለቀበሌ እያውደለደለ በአፉ የሚኖር መሃይም የቤት ባለቤት አፉን ሞልቶ ወይ ልቀቅ ወይ አምስት መቶ ብር ኪራይ ጨምር ይለኛል! የዛሬ አራት ወር ሁለት መቶ ብር አስጨምሮኛል እውነቴን ነው በአገሬ ላይ የማልጠቅም ዜጋ የመሆን ስሜት ነው የተሰማኝ ፡፡
እኔ ማንም ብር እንዲሰጠኝ አልፈልግም ሰርቸ ማግኘት የምችል ጤነኛ የተማርኩ ወጣት በመንግስት ችግር ምክንያት እንደለማኝ መመፅወት አለብኝ እንዴ እንደገና ለፍተው ያሳደጉ ቤተሰቦቸ ለእኔ ብር መደጎም አለባቸው እንዴ እንደህፃን ልጅ ለኔ ልብስ መግዛት አለባቸው እንዴ…. ውለታየን መክፈል ቢያቅተኝ እንኳን እንዳልችል እንዴት በማንም ሆዳም እገፋለሁ መብቴን እቀማለሁ
አንድ የሱማሌ ወይም የኤርትራ ስደተኛ ከእኔ የተሸለ እኔ አገር ላይ ይኖራል ! እንደዜጋ መብራት ውሃ በስርአት አላገኝም ያውም ከፍተኛ የሚባል የስራ ግብር እየከፈልኩ ! እንደዜጋ ትክክለኛ መረጃ አላገኝም ! እንደዜጋ ደፍሬ ስለችግሬ አላወራም ! ላቤን ጠብ አድርጌ የምኖር ዜጋ አባትና እናቴ እድሚያቸውን ሙሉ በፍፁም ታማኝነትና ትጋት ያገለገሏት ኢትዮጲያ ላይ እንደሁለተኛ ዜጋ መንከራተት እጣ ፋንታየ ሁኗል …… ኧረ የምን ሁለተኛ ምንም ደረጃ የሌለኝ ውዳቂ ዜጋ ነኝ እንጅ ! በእውነት ግን እኔ ትላንት ዩኒቨርስቲ ሁኘ ኢትዮጲያን የብርሃን ኩሬ አድርጌ ሳልም የነበርኩት ልጅ ነኝ …..ኦህህህ እውነቴን ነው እንደዛሬ መሮኝ አያውቅም !

Wednesday, 1 January 2014

The accidental journalist, refugee, tourist, or the all-in-one spy?


December 30, 2013
The Free Press in Ethiopia can’t be free until the drifters, apologists and want-to-be journalists and Medias are put out of commission. It’s about time Ethiopians draw the line between the real things and those masquerading as journalist and free press to deceive the public.
by Teshome Debalke
The once celebrated ‘journalist’ and editor of Awramba Times, Dawit Kebede  sought political asylum in the USA a few years back an d abandon his protection and return home to the same regime a few month ago he gave refugee status a whole different meaning.
Dawit Kebede of Awramba, accidental journalist
When the accidental journalist, refugee, tourist and alleged spy took a daylight flight out of Addis Ababa Airport a few years ago to seek protection from a regime known for its atrocious treatment of journalists something wasn’t kosher. But, when he return back; after enjoying the privilege and throwing jabs on his compatriots he broke his sworn journalistic duty and became a gossip peddler with an extended tourist visa.
No one knows how he managed to secure a passport, exist visa and a ticket from the same regime he flee claiming to fear for his life. But, to retune to the same regime that allowed him to resume his work and interview a high ranking government official within weeks of his return not only insult journalism profession but the people that paid the price for it. It was like watching ‘Alice in the wonderland’ episode that can qualify for Grammy nomination for the best acting and directing.