Thursday, 27 February 2014

ሀይለመድህን አበራ፦ የታፈነ ብሶተኛ ወይንስ የሚያደርገውን የማያውቅ የአእምሮ በሽተኛ?


February 27, 2014
አሰፋ (ከዳላስ)

መንግስትና የመንግስት ደጋፊዎች ነን ባዮች ማምታታቱን ትተው አንዱን መምረጥ አለባቸው

የሰሞኑ ትኩስ ዜና በሆነው የረዳት አብራሪ ሀይለመድህን አበራ የሚያበረውን አውሮፕላን ጠልፎ ስዊዘርላንድ ማሳረፉን በተመለከተ የተለያዩ አስተያየቶች እየተሰነዘሩ ነው:: በተለይ የኢትዮጵያው አገዛዝ እና እሱን አውቀውም ይሁን ሳያውቁ ለመደገፍ የሚፈልጉ ሰዎች የሚስጡዋቸው መላምቶች የሚያስገርሙና እርስ በርሳቸው የሚጋጩ ናቸው:: ከነዚህ አስተያየቶች መካከል ሁለቱን ልጥቀስ:: በአንድ  በኩል ሀይለመድህን የአእምሮ ችግር አለበት ሲሉ በሌላ በኩል ደግሞ የሀገሪቱንም ሆነ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ስም ያጎደፈ በማለት ለመውቀስ ይዳዳቸዋል::
Ethiopian Airlines pilot Hailemeden Abera Tegegn
እንግዲህ እኔ እስከሚገባኝ ድረስ እነዚህ ሁለቱ ግምቶችና ወቀሳዎች በአንድ ግዜ እና በአንድ ላይ እውነት ሊሆኑ አይችሉም:: አንዱ እወነት ከሆነ ሌላው ሀሰት ይሆናል:: ይህም ማለት ሀይለመድህን የአእምሮ በሽተኛ ከሆነ የኢትዮጵያንም ሆነ የአየር መንገዱን መልካም ገፅታ በማቆሸሽ ሊወቀስ አይችልም:: ምክንያቱም አንድ ሰው የአእምሮ ህመም አለበት ከተባለ በአእምሮ ህመም ውስጥ ሆኖ ለሚፈፅመው ድርጊት ሀላፊነት ሊወስድ አይጠበቅም:: አመዛዝኖና አስቦ ያደረገው ስላልሆነ:: ድርጊቱ በሰውየው እንደተፈፀመ ተደርጎ አይታሰብም:: ምክንያቱም ከግለሰቡ ቁጥጥር ውጪ በሆነ ሀይል ተፅእኖ ስር ሆኖ ያደረገው የተከናወነ በመሆኑ:: በዚህም የተነሳ መልካም ነገር ቢሰራም ሊመሰገንና ሊሸለም እንደማይችል ሁሉ ክፉ ነገር ቢያደርግም ሊወቀስ እና ሊፈረድበት አይገባም:: ይህ ካልሆነ ግን የአእምሮ በሽተኛ የሚለውን ማንሳቱ ብዙም ትርጉም ሊኖረው አይችልም:: ስለዚህ መንግስትና የመንግስት ደጋፊዎች ነን ባዮች ማምታታቱን ትተው አንዱን መምረጥ አለባቸው::

“ግብረሰዶማውያን ከተፈጥሮ ውጪና አጸያፊ ናቸው”


ዑጋንዳ የጸረ ግብረሰዶማውያን ሕግ አጸደቀች!
musevini


የዑጋንዳው ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ “አከራካሪ” ሲባል የቆየውን የጸረ ግብረሰዶማዊ ህግ በፊርማቸው አጸደቁ፡፡ ግብረሰዶማውያንን “ከተፈጥሮ ውጪ የሆኑ” እና “አጸያፊ” ሲሉ ገልጸዋቸዋል፡፡ ግብረሰዶማዊነት በምዕራቡ ዓለም አማካኝነት ወደ አፍሪካ እየተስፋፋ የመጣ ነው ብለዋል፡፡
ለበርካታ ዓመታት አከራካሪ ሆኖ የቆየውን የጸረ ግብረሰዶማዊነት ሕግ ትላንት ዑጋንዳ አጽድቃለች፡፡ ከምዕራቡ ዓለም እና ሰዶማዊነት የመብት ጉዳይ እንደሆነ ከሚከራከሩ ተቋማት የደረሰባትን ውትወታ ወደ ጎን በማለት ዑጋንዳ በሕግ ማጽደቋ የበርካታ ዓለምአቀፍ መገናኛ ብዙሃንን ሽፋን የሰጡበት ርዕስ ሆኗል፡፡ የሕጉን መጽደቅ አስመልክቶ ጥቂት ዑጋንዳውያን ተቃውሞ ሰልፍ የወጡ ሲሆን በርካታዎች ደግሞ ድጋፋቸውን ለፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል፡፡
uganda 1ሕጉን በፊርማቸው ያጸደቁት ዩዌሪ ሙሴቪኒ ሲኤንኤን ላይ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ ግብረሰዶማውያን “አጸያፊ ሰዎች ናቸው፤ ምን ዓይነት ድርጊት ይፈጽሙ እንደሆነ አላውቅም ነበር፤ በቅርቡ የሰማሁት ግን በጣም አስደንጋጭ ነው፤ ጸያፍ ነው” ብለዋል፡፡ ፕሬዚዳንቱ ሲቀጥሉም ሰዶማውያን ሲወለዱ ጀምሮ እንደዚሁ ናቸው ስለተባለ ሁኔታውን እውነት አድርገው በመውሰድ ቸል ሊሉት እንደነበር ሆኖም ግን እስካሁን ምንም ሳይንሳዊ ማስረጃ እንዳልቀረበበት ተናግረዋል፡፡
ሙሴቪኒ ሕጉን እንዲያጸድቁ ያደረጋቸውን አንዱን ምክንያት ሲጠቅሱም፤ ግብረሰዶማዊነት ከጄኔቲክስ ጋር በተያያዘ ከውልደት ጀምሮ የሚመጣ የተፈጥሮ ጉዳይ ነው በማለት ይገምቱ እንደነበር ሆኖም የአገራቸው ሳይንቲስቶች ይህንን መከራከሪያ ውድቅ ማድረጋቸውን ጨምረው ገልጸዋል፡፡
ሕጉ በፕሬዚዳንቱ ፊርማ ከጸደቀ በኋላ ወዲያውኑ በሥራ ላይ የዋለ ሲሆን ግብረሰዶማዊ ወሲብ ሲፈጽም የተገኘ ማንኛውም ሰው እስከ ዕድሜ ይፍታህ በሚደርስ እስራት እንደሚቀጣ ይደነግጋል፡፡ በወንጀሉ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘ በ14ዓመት እስር ይቀጣል፡፡ በተደጋጋሚ ወንጀሉን ሲፈጽሙ የተገኙ፣ ዕድሜያቸው ካልደረሱ ጋር እንዲሁም ከአካለ ስንኩል ወይም ከኤችአይቪ ተጠቂ ጋር ወንጀሉን የፈጸሙ በዕድሜ ልክ እስራት እንዲቀጡ ሕጉ ያዛል፡፡

Sunday, 23 February 2014

Hailemariam Desalegn’s Confused Statements


February 22, 2014
by Amanuel Biedemariam
On February 10, Prime Minister Hailemariam Desalegn of Ethiopia gave reporters access and conducted a press conference. The statements of Hailemariam are fraught with inconsistencies and telling that there is a serious leadership vacuum and lack of direction in Ethiopia. The statements lack principle, direction and strategy. The messages are inconsistent and contradictory to previous statements.
Prime Minister Hailemariam Desalegn of Ethiopia gave reporters access
On an interview with Africa Confidential January edition, when asked what’s your Eritrea policy? PM Hailemariam Desalegn said,
“Our Eritrea policy is very clear. These two peoples are very friendly; the normalizing of relations, also with the governments, should come as soon as possible. We have accepted unconditionally the rulings [on the border] and so this has to implemented but with a discussion because the implementation process needs something on the ground since it is a colonial rather than a people’s boundary.” Emphasis added.
For a while, Ethiopians have been expressing anger and concern about the border issue between Ethiopia and Sudan claiming that the minority TPLF regime has unlawfully ceded huge chunks of Ethiopian territories to Sudan. The tenet of their argument is that the signatures of Meles Zenawi and Hailemariam Desaleng are unlawful, null and void based on Article 55(12) of Ethiopian constitution which demands accountability and ratification by parliament. On a recent article, “Save Ethiopia From Chopping Block”,  Dr.Alemayehu G. Mariam wrote,
“It is important to understand and underscore the fact that the “agreement” Meles and Bashir “signed”, by Meles’ own description  and admission, has nothing to do with the so-called Gwen line of 1902 (“Anglo-Ethiopian Treaty of 1902” setting the “frontier between the Sudan and Ethiopia”). It also has nothing to do with any other agreements drafted or concluded by the imperial government prior to 1974, or the Derg regime between 1975 and 1991 for border demarcation or settlement. Meles’ “agreement”, by his own admission, deals exclusively with border matters and related issues beginning in 1996, when presumably the occupation of Sudanese land by Ethiopians took place under Meles’ personal watch.”
Citing Wikileaks, Dr. Al Mariam writes,
“Former TPLF Central Committee member and former Defense Minister Seeye Abraha told” American embassy officials in Addis Ababa that in a move to deal with “on-going tensions between Ethiopia and Sudan”, Meles had turned over land to the Sudan “which has cost the Amhara region a large chunk of territory” and that Meles’ regime had tried to “sweep the issue under the rug.”

ከ15 ሺህ ህዝብ በላይ የተሳተፈበት ሰላማዊ ሰልፍ በባህር-ዳር [ፎቶ]


February 23, 2014


የተለያዩ መፈክር ያነገቡ ሰልፈኞች በባህር ዳር የአንድነት ፓርቲ ጽ/ቤት አካባቢ በመገኘት ሰልፉን ሲጠባበቁ ነበር በአሁኑ ሰዓት ከ15 ሺህ የሚበልጥ ህዝብ ሰልፉን ተቀላቅሏል:: የአንድነት ፓርቲ ፕሬዝዳንት ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው፣ የመኢአድ ፕሬዝዳንት አቶ አበባው መሃሪ እንዲሁም የትብብር ለዴሞክራሲ ሰብሳቢ አቶ ግርማ በቀለ እንዲሁም የአንድነት ፓርቲ ብሄራዊ ምክር ቤት አባል የሆኑት አንጋፋው ፖለቲከኛ ዶ/ር ኃይሉ አርአያን ጨምሮ ሰልፉን በቀዳሚነት እየመሩ ይገኛሉ::
በአማራ ክልል የክልሉ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የብአዴን ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አለምነው መኮንን በአማራ ህዝብ ላይ የሰነዘሩትን ዘለፋ በመቃወም ነው የባህር ዳር ሕዝብ በነቂስ ወጥቶ ሰላማዊ ሰልፍ ያደረገው።
ድል የህዝብ ነው!! ኢትዮጵያዊ አንድነታችን ከልዩነታችን በላይ ነው!!  ከባዶ ጭንቅላት ባዶ እግር ይሻላል!!  ብአዴን የአማራውን ሕዝብ አፍኖ መግዛት ያቁም!! የኢሀደግ አምባገነን አገዛዝ ሰልችቶናል!! የሚሉ መፈክሮችን እያሰሙ ይገኛሉ።

Saturday, 22 February 2014

የሸፍጥ ክርክር የሃሰት ክምር የታሪክን እውነታ አይቀይርም! (ከኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ)


February 22, 2014

ከኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ

የካቲት 15 ቀን 2006 ዓ/ም ( February 22, 2014 )

I. መግቢያ:
የካቲት 3 ቀን 2006 ዓ/ም የወያኔ/ኢሕአዴግ ሊቀ-መንበርና የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ለአገር-ውስጥ ጋዘጤኞች በሰጡት መግለጫ ላይ የኢትዮ-ሱዳን ድንበር ጉዳይን በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ በድፍረት የሰጡት ምላሽ የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴን ብቻ አይደለም መላውን የኢትዮጵያ ሕዝብ በእጅጉ ያሳዘነና ያሳፈረ ሆኖ አግኝተነዋል። በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ እግር የተተኩት አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የተረከቡት የመንግሥት ሥልጣንን ብቻ ሣይሆን ለኢትዮጵያ ሕዝብ ከበሬታ-አልባነትንም በሚመስል መልክ ነው ይህንን በጣም የተምታታ፤ በተቃርኖዎች የተሞላና በእጅጉ ኃላፊነት-የጎደለው ጋዜጣዊ-መግለጫ የሰጡት።
የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ ባደረገው ያላሰለሰ ክትትል የወያኔ/ኢሕአዴግ መንግሥት ከሱዳን መንግሥት ጋር የሕዝብን መሠረታዊ-ሉዓላዊነት በሚዳፈርና ዘለቄታዊ ጥቅሙን ለባዕድ አሣልፎ በሚሰጥ ሁኔታ እየሸረበ ያለውን ደባና እየፈጸመ ያለውን አሣፋሪ ድርጊት በተገቢ ጥናትና በጠራ-መረጃ ላይ ተመሥርቶ በተከታታይ ባወጣቸው መግለጫዎች እንዲሁም በልዩ-ልዩ መገናኛ-ብዙኃን አማካይነት ለኢትዮጵያ ሕዝብ፤ ለወያኔ/ኢሕአዴግ መሪዎችና ልዩ-ልዩ ተቋማት፤ ለሱዳን መንግሥትና ለዓለም-አቀፉ ማኅበረሰብ ጭምር ሲያሳውቅ መቆየቱ ይታወቃል። የወያኔ/ኢሕአዴግ መሪዎች ግን አሁንም በዚህ የአገር ድንበርን በሚያክል ከባድ ጉዳይ ላይ ከዋናው ባለ-ጉዳይ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጀርባ የጀመሩትን እኩይ ተግባር እየገፉበት አንደሆነ ከራሣችው አንደበት እየሰማን ነው።
II. የመግለጫው ዓላማ፤
የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ በሚከተሉት ምክንያቶች ከላይ የተጠቀሰውን የአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ንግግር በተመለከተ ይህንን መግለጫ ማውጣት አስፈላጊ ሆኖ አግኝቶታል።
ሀ). ከማንኛውም አገርና መንግሥት መሪ በተለይም የውጭ ግንኙንትን በተመለከተ የሚሰነዘር አስተያየትም ሆነ የሚሰጥ መግለጫ የአገር አቋም ተደርጎ የሚወሰድና በዋቢነትም የመጠቀስ መዘዝን ያዘለ በመሆኑ በዝምታ ሊታለፍም ሆነ ‘አጉል-መዘላበድ’ ተደርጎ ችላ ሊባል የሚችል ጉዳይ ባለመሆኑ፤
ለ). በዚህ የወያኔ/ኢሕአዴግ መንግሥት ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጀርባ እየፈጸመ ባለው በአገር-ክህደት የሚያስጠይቅ፤ ሕዝብን የናቀ የድፍረት አርምጃና ሕገ-ወጥ ድርጊት አገራችን ኢትዮጵያ አንጡራ መሬቷ ለባዕድ አሣልፎ እየተሰጠ መሆኑ ምንም ዓይነት ተቀባይነትም ሆነ አግባብነት የሌለው ብቻ ሣይሆን የማንኛውም ኢትዮጵያዊ ጉዳይና ሁሉም በግልጥ ሊረዳው የሚገባ መሆኑን ከአሁን በፊት በተደጋጋሚ መግልጫዎች የሰጠነበት ቢሆንም አሁንም በድጋሜ ማሳሰቡ አስፈላጊ ስለሆነ፤
ሐ). አፄ ቴዎድሮስ፤ ንጉሥ ተክለ-ኃይማኖትና አፄ ዮሐንስን የመሳሰሉ ታላላቅ መሪዎች እየታገሉና ክቡር መስዋዕትነት እየከፈሉ አስከብረውት የቆየውንና በአካባቢው ሕዝብ የመረረ ተጋድሎ ታፍሮና ተጠብቆ የኖረውን የሱዳን ወሰን በድብቅ ስምምነት ለባዕድ አሣልፎ ለመስጠት የሚደረግ ሕገ-ወጥ ውል ውሎ-አድሮ የሚያስከትለው መዘዝ በቀላሉ የማይታይ ከመሆኑም በላይ፤ ይህንን በመሰለ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጀርባ በተፈጸመ ውል ድንበር ለማካለል የሚወሰድ እርምጃ ሁለቱን እህትማማች አገሮች ወደ-አይቀሬ ጦርነት የሚወስድና ይህም ኢትዮጵያና ሱዳን በመልካም ጉርብትና መርኅ ተከባብረው እንዳይኖሩ፤ የውስጥ ሰላማቸውንና እድገታቸውን ወደሚያደናቅፍ ያላስፈላጊ ችግር ውስጥ ከማስገባት አልፎ ለአካባቢው ሰላምና መረጋጋት ከፍተኛ ጠንቅ እንደሚሆን ሁሉም ሊያውቀው ስለሚገባ፤
መ). የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ የወያኔ/ኢሕአዴግ መሪዎች በሱዳን በኩል ያለውን የአገር ወሰን በተመለከተ በድብቅ የሚያደርጉትን የክህደት ተግባር በወቅቱ ማጋለጥና ማክሸፍ ተገቢና የማንኛውም ኢትዮጵያዊ የዜግነት ግዴታ እንደሆነ በተደጋጋሚ የሚያሳስበውና የሚታገለው፤ ይህ ሕገ-ወጥ እርምጃ በሌሎች አካባቢዎች ያሉ ድንበሮቻችን እንዲደፈሩና አገራችን ኢትዮጵያ አንጡራ መሬቶቿን በተመሣሣይ ሁኔታ እንድታጣ በር-ከፋች ማስረጃ ሊሆን እንዳይችል ለማድረግም ጭምር ስለሆነ፤

የኢትዮጵያ አየር መንገድ መጠለፍ እና ወያኔ

February 21, 2014

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን በረዳት አብራሪ ሃይለመድህን አበራ መጠለፉን ተከትሎ የአየር መንገዱ ተጠቃሚዎች ቁጥር ይቀንሳል ተብሎ ይገመታል። ይህን የተረዱት የወያኔ ሹማምንት መክረው ዘክረው የደረሱበት ስልት ቢኖር የረዳት አብራሪውን ቤተሰቦች በማስፈራራትና በማግባባት ረዳት አብራሪው አእምሮው የታወከ “እብድ” እንደሆነ እንዲናገሩ ማድረግ ነው።
የረዳት አብራሪው እህት “ወንድምሽ ጭቅላቱን ያመው ነበር ብለሽ ከተናገርሽ በንጻ ይለቀቃል” የሚል ምክር በተላኩ የደህንነት ሰዎች እንዲደርሳት የተደረግ ሲሆን ሌሎችም የቤተሰቡ አባላት እሷ የተናገረችውን እንዲደግፉ ወያኔ ጫና እያደረገባቸው ነው።
በዚሁ መሰረት ጫና ተደርጎባችው ይሁን የብአዴን አባል በምሆናቸው ምክንያት ዶ/ር እንዳላማው የተባሉ የረዳት አብራሪው ወንድም ቪኦኤ ላይ ቀርበው ምንም እንኳን ወንድማቸው የአእምሮ ሁከትም ሆነ ጭንቀት እንዳለበት እሳቸው ባያውቁም እህቱ ያለችውን ግን ሙሉ ለሙሉ እውነት ነው ብለው ደግፈዋል። (ወይንም እንዲደግፉ ተደርገዋል)።
እንደተለመደው በቪኦኤ በኩል “ረዳት ፓይለቱ አእምሮው የታወከ፣ እብድ ነው” የሚለውን ዜና የሰራው ጋዜጠኛ ሄኖክ ሰማእግዜር መሆኑ የዘገባው መልዕት በወያኔዎች እንደተጠነሰሰ ይበልጥ የሚያረጋግጥ ነው።
ይህ በዚህ እንዳለ በጀርመን ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ረዳት አብራሪ ሀይለመድህን እንደ ወንጀለኛ እንዳይታይና ጥገኝነትም እንዲሰጠው በሚል የድጋፍ ሰላማዊ ሰልፍ ሊያደርጉ መዘጋጀታቸውን አሳውቀዋል።
Ethiopian Airlines flight hijacked by it's pilot

Friday, 21 February 2014

መሬትና ዉሃ ቅርምት በኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ ዉስጥ የመሬትና ዉሃ ቅርምት ማኅበረሰቡን እየጎዳ እንደሚገኝ ዓለም ዓቀፉ የመብት ተሟጋች ሂዉማን ራይትስ ዎች አመለከተ። ድርጅቱ ይህን አመልክቶ ባወጣዉ ዘገባ በዚህ ምክንያትም ኢትዮጵያና ኬንያ ዉስጥ 500,000 አርብቶ አደሮች ለችግር መጋለጣቸዉን ገልጿል።

ሂዉማን ራይትስ ዎች፤ ኢትዮጵያ፤ የመሬትና ዉሃ ቅርምት ማኅበረሰቦችን ጎዳ በሚል ዛሬ ባወጣዉ ዘገባ፤ አዳዲስ ከሳተላይት የተገኙ ምስሎች በታችኛዉ ኦሞ ሸለቆ አካባቢ ነባር ማኅበረሰቦች ይጠቀሙበት የነበረዉን መሬት ለስኳር ልማት በስፋት መመንጠሩን ማሳየታቸዉን አመልክቷል። ላለፉት አምስት ወራትም 7,000 የሚሆኑ የቦዲ ጎሳ አባላት ጋ በቂ ምክክር ሳይደረግ ተግባሩ መከናወኑን ዘርዝሯል። የድርጅቱ የአፍሪቃ ጉዳይ ምክትል ዳይሬክተር ሌስሊ ሌፍኮ፤ ድርጅታቸዉ በUNESCO በዓለም ቅርስነት በተመዘገበዉ አካባቢ ለበርካታ ዓመታት የሚከናወነዉን እንደሚከታተል በማመልከት፤
«የኢትዮጵያ መንግስት በርካታ ግድቦችን በኦሞ ወንዝ አካባቢ በመገንባት ላይ ይገኛል። የወንዙ ዉሃም ለስኳር ተክሉ ወደግድቦች ለመስኖ ተቀልሷል። እናም ባጠቃላይ እነዚህ ሁሉ እንቅስቃሴዎች በኦሞ ሸለቆ በሚገኙ ነባር ኗሪዎች ህይወት ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ አስከትለዋል። እዚያ ወደሁለት መቶ ሺህ ሰዎች ይኖራሉ። አብዛኞቹም እዚያ መሬታቸዉ ሲመነጠር አይተዋል፤ ወደሌላ ስፍራ አንዳንዴም ወደመንደሮች ተወስደዉ በግዳጅ እንዲሰፍሩ ተደርገዋል። እናም የኑሯቸዉ ሁኔታ እጅግ በአሳሳቢ ሁኔታ ላይ ነዉ።»

“ድምፁ የእኔ ነው ስድቡ ግን የእኔ አይደለም” አቶ አለምነው መኮንን (አቤ ቶኪቻው)


February 21, 2014
አቶ አልምነው“ድምፁ የእኔ ነው ስድቡ ግን የእኔ አይደለም” አቶ አለምነው መኮንን
አንድነት እና መኢአድ የተሳዳቢው ባለስልጣን አቶ አለምነው መኮንን እንጀራ እናት የሆነችውን ብአዴንን ለመቃውም እሁድ በባህር ዳር ሰልፍ መጥራታቸው እንደተስማ፤
በኬኒያ የስደት “ኬዝ” ጋገራ
እኒያ የአማራ ህዝብ ምንትስ ነው… ቅብርጥስ ነው… ብለው በሞቅታ ውስጥ ያለ ሰው እንኳ የማይሞክረውን የስድብ ውርጂብኝ “በመረጣቸው” ህዝብ ላይ ያወረዱት ሰውዬ፤ ዛሬ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ቀርበው። “ድምፁ የእኔ ነው ስድቡ ግን የእኔ አይደለም… ይህ የተደረገው በኮምፒውተር ቆርጦ ቀጥል ቴክኖሎጂ ነው…” ብለው መግለጫ ሰጥተዋል መባሉን ስሰማ ሮጬ ወደ ኢቲቪ ድረ ገጥ ሄጄ ያሉትን ለመስማት ሞከርኩ።
“ድምጹ የእኔ ነው…” የሚለው ከንግግራቸው ውስጥ ተቆርጦ ውጥቷል። “ተሳደበ ይሉኛል… እንዴት እሳደባለሁ… መራጮቼን… ወላጆቼን… ዘመዶቼን… ወገኖቼን… ምን በወጣኝ እና ምን ቆርጦኝ እሳደባለሁ…???” ብለው እኛኑ ሲጠይቁ የሚያሳየው ንግግራቸውን ግን ሰማሁት።
እንግዲያስ አቶ አለምነህ፤
አንደኛ የብዙሃኑም ጥያቄ ይሄው ነው… ይሄ ህዝብ ቅጥ ባጣ ድህነት እንዲኖር የተፈረደበት አንሶ ምን በድሎ ምን አጥፍቶ ይብጠለጠላል… ምን በወጣውስ ይሰደባል…???
ሁለትኛ አዩት አይደል መቁረጫ እና መቀጠያ ቴክኖሎጂው ያለው ኢቲቪ ቤት ነው…! በአደባባይ ተናግረው ዞር ከማለትዎ “ድምጹ የእኔ ነው” የሚለው የእምነት ቃልዎ ተስረዘልዎ!
ሶሰት… አራት…አምስት…. መቶ፤ ይሄንን ለሁሉም ኢህአዴጎች ንገሩልኝ፤
ወይ ልቦና ግዙ! ንስሃም ግቡ እና ተንበርከካችሁ ይሄን ህዝብ ይቅርታ ጠይቁ፤ ወይ ደግሞ “ማስተዳደሩን” ርግፍ አድርጋችሁ ትታችሁ ማደሪያችሁን ፈልጉ!

አንድነት እና መኢአድ፤ በባዶ እግራቸው በመሆን በባህርዳር ቅስቀሳ እያደረጉ ነው።


February 21, 2014
አቤ ቶኪቻው
አንድነት እና መኢአድ፤ በባዶ እግራቸው በመሆን በባህርዳር ቅስቀሳ እያደረጉ ነው።
የአማራ ክልሉ ባለስልጣን፤ “አማራው በባዶ እግሩ ነው የሚሄደው…” ብለው እጅግ የከፋ ዘለፋ ካሰሙ ብኋላ ህዝቡ በያለበት ስለ ሰውዬው ያፈረላቸው ቢሆንም እርሳቸው ግን ሳያፈሩ ትላንት በቴሌቪዥን መስኮት ተከስተው ሲያስቁን ነበር።
ዛሬ እንደሰማነው እና እንዳየነው፤ የመኢአድ እና አንድነት አባላት እሁድ ለጠሩት ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ፤ በባዶ እግራቸው በመሆን ባደረጉት ቅስቀሳ “እኛም ጫማ የለንም፤ እኛም በባዶ እግራችን ነው የምንሄደው ቢሆንም ግን የሞራል ለዕልና አለን” የሚል ቅስቀሳ ሲያሰሙ ውለዋል።
በቅስቅሳው ወቅት ፖሊስ ጉልቤውን ሊያሳያቸው ቢሞክርም ህዝቡ ከበባ እያደረግ ሲከላከላቸው አንድነት ዛሬ ከለቀቀው ቪዲዮ አይተናል።
ድረ ገጻችን፤
…የምር ግን ህዘብ እየተዘለፈም እየተዘረፈም እንዴት ይችለዋል…. ???ብላ በትልቁ እየጠየቀች፤ አንድነት ያሰራጨውን ቪዲዮ ላላዩት እንድሚከተለው ታሳያለች።

ኢትዮጵያዊቷ በሱዳን ብትደፈርም ተፈረደባት

ሱዳን መዲና ካርቱም ውስጥ በ6 ጋጠወጦች የተደፈረችው ኢትዮጵያዊት ስደተኛ፣ ወጣት፣ ነፍሰጡር ለአንድ ወር እስር ቤት እንድትቆይ እና 950 ዶላር እንድትቀጣ ትናንት ተበየነባት። ወጣቷ ኢትዮጵያዊት ስትደፈር 7ኛው ወንጀለኛ ድርጊቱን በሞባይል ቀርፆ በማኅበራዊ መገናኛ ዘርፍ ማሰራጨቱም ተነግሯል። ወጣቷ በአሁኑ ወቅት እስር ቤት ነው የምትገኘው።

የ18 ዓመት ወጣት የሆነች ኢትዮጵያዊት ስደተኛ ሱዳን መዲና ካርቱም ውስጥ በ6 ጋጠወጦች ተደፍራ ድርጊቱ በማኅበራዊ መገናኛ ዘርፍ ቢሰራጭም፤ ወጣቷ በጥፋተኝነት ቅጣት ተበየነባት። ወንጀሉ ሲፈጸምባት የሶስት ወር ነፍሰጡር የነበረችው ኢትዮጵያዊቷ ወጣት 950 ዶላር ገደማም እንድትከፍል ተፈርዶባታል። ወጣቷ እስር ቤት ውስጥ ነው የምትገኘው። የሴቶች መብት አስከባሪ ተቋም በእንግሊዘኛ ምኅፃሩ SIHA የአፍሪቃ ቀንድ ኃላፊ የሆኑት ወይዘሪት ሐላ ኧልካሪብ።

«እስር ቤት ውስጥ ለአንድ ወር እና ከእዛ በላይ ቆይታለች። የደረሰች ነፍሰጡር በመሆኗ በማንኛውም ጊዜ ልትገላገል ትችላለች። የፈፀምሽው ኢ-ግብረገባዊ ድርጊት ነው በሚል ለአንድ ወር እንድትታሰር ትናንት ተፈርዶባት ነበር። ሆኖም እስር ቤት ወስጥ አስቀድም አንድ ወር ስለቆየች ያ ተነስቶ ለእዛ ተመጣጣኝ የተባለ ወደ 950 ዶላር ግድም እንድትከፍል ተበይኖባታል። ገንዘቡ ቢከፈልም፣ አሁንም ድረስ አልለቀቋትም»

ወጣቷ በግፍ ስትደፈር የሚያሳየው ቪዲዮ ውስጥ ደፋሪዎቹ በአረቢኛ ቋንቋ ሲነጋገሩ፣ ሲስቁ እና በየመሀከሉም ሁለት ጣቶቻቸውን በድል አድራጊነት ምልክት፣ የመሀል ጣታቸውን ደግሞ ለስድብ ካሜራው ፊት ሲቀስሩ ይታያሉ። ለመሆኑ ወጣቷ እንዲህ ጭካኔ በተሞላበት ሁናቴ በ6 ጋጠወጦች እንዴት ልትደፈር ቻለች? ወጣቷ ይላሉ ወይዘሪት ሐላ ኧልካሪብን፤ ወጣቷ ካርቱም ውስጥ መኖሪያ ቤት ለመከራየት ትፈልጋለች። እናም አንድ ደላላ ነኝ ያለ ሰው የሚከራይ ቤት ሊያሳያት ይዟት ይሄዳል። ወጣቷ ክፍሎቹን ስትመለከት እሱ 6 ጓደኞቹን በስልክ በአፋጣኝ ይጠራና ወጣቷን አስገድደው በመድፈር በስልክ ይቀርፃታል።

Thursday, 20 February 2014

“Co-pilot hijacked plane to expose brutal rule in Ethiopia” – Cousin


February 19, 2014
by Abraha Belai, Ethiomedia.com
SEATTLE – Amid a flurry of government propaganda to label the hijacker of an Ethiopian Airlines plane as mental patient, a family member of the co-pilot says her cousin was an activist who has been resentful of the stifling political repression in Ethiopia.
Ethiopian Airlines plane hijacker
Speaking to the Ethiopian Satellite TV (ESAT) by phone on Wednesday, a female cousin of co-pilot Hailemedhin Abera Tegegn, who landed the passenger airliner in Geneva early on Monday and sought asylum there, said the measure was politically motivated, and not any other reason.
“He was living a comfortable life, and was a frequent traveler to the US and Europe. If he had the desire to live in the West, he had plenty of chances. But he was an activist who very much resented the gross human rights violations that the government is committing in the country,” she said.
The woman, who didn’t reveal her identity for fear of political retribution, said 31-year-old Hailemedhin Abera Tegegn and she would call each other frequently, and the co-pilot was very much opposed to the government because of lack of freedom, including harassing airlines employees to be members of the ruling party or lose their jobs.

Monday, 17 February 2014

እየተዋረዱ መገዛት እስከመቼ!?


February 17, 2014
በቅዱስ ዬሃንስ
አለምነው መኮነን የተባለ የብአዴን ወኪልና የባንዳ አስፈፃሚ የአለቆቹን የዘወትር አባባል በማስረገጥእመራዋለሁ የሚለውን የአማራ ህዝብ <<ሰንፋጭ የሆነ ትምክህተኝነት የተጠናወተው፤ ትምክህተኝነቱንያልተው፤ በባዶ እግሩ እየሄደ መርዝ ንግግር የሚናገር ወዘተ>> ካለ በኋላ <<የትምክህት ልጋጉን ማራገፍአለበት>> በማለት እንደሌሎች ብሄረሰቦች ሁሉ ደከመኝ፡ ሰለቸኝ ሳይል ዋጋ የከፈለውን የአማራ ህዝብ ዋጋበማሳጣት የሌሎቹ ጠላት አድርጐ በማቅረብ፡ የዘረኞች ተባባሪነቱን አስመስክሯል። 
የአማራው ህዝብ የወያኔ ዘረኞች ዋነኛ ዒላማ ሆኖ የአገዛዙን የግፍ ፅዋ ያለማቋረጥ መጋት ከጀመረ ድፍን 23 አመታት ተቆጠሩ። ፋሽስቱ ወያኔ የኢትዮጵያን ህዝብ ብሔራዊ ስሜት በማምከን ፣ የዘመናት ተገዥነቱን ለማረጋገጥ በቅድሚያ የአማራን ሕዝብ ማንነት ማጥፋት ፣ የአማራን ሕዝብ ስነ ልቦናዊ ጥንካሬ መስለብ እና አንገቱን ማስደፋት አስፈላጊ መሆኑን በጽናት ያምናል። ይህ በመሆኑም ፣ በአማራ ህዝብ ላይ በወያኔ የሚፈፀመው ግፍ እና በደል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ ስር እየሰደደና እየከፋ በግልፅም በስውርም በተቀነባበረ መንገድ ቀጥሏል።
ይህ የህወሀት የጸረ አማራ ፕሮፓጋንዳ ማሽን የሚመራው በዋና ዋናዎቹ የወያኔ  ሹሞች ቢሆንም ወያኔ የአማራን ህዝብ የሚገድለዉ፤ የሚያዋርደዉና የሚያሳደድዉ አማራ ነን በሚሉ ነገር ግን የአማራን ህዝብ በጅምላ በሚሰድቡና አማራዉ ሲገደል፤ ሲታሰርና ሲፈናቀል ይበልህ በሚሉ በእነ አለምነው መኮንን አይነት ወፍ ዘራሽ ካድሬዎች ነው። አንበሳ ሲያረጅ የዝንብ መጫወቻ ይሆናል እንዲሉ፡ የአማራው ህዝብ ዛሬ ቀን ጣለውና፣ በጠላቶቹ እጅ ወደቀ፣ የድፍን ስድና መረን ያደገ ዋልጌ ሁሉ የስድብና የዘለፋ አፍ ማሟሻ የመሆን ዕጣ ደረሰው። አለምነው መኮነን የተባለ የብአዴን ወኪልና የባንዳ አስፈፃሚ የአለቆቹን የዘወትር አባባል በማስረገጥ እመራዋለሁ የሚለውን የአማራ ህዝብ <<ሰንፋጭ የሆነ ትምክህተኝነት የተጠናወተው፤ ትምክህተኝነቱን ያልተው፤ በባዶ እግሩ እየሄደ መርዝ ንግግር የሚናገር ወዘተ>> ካለ በኋላ <<የትምክህት ልጋጉን ማራገፍ አለበት>> በማለት እንደሌሎች ብሄረሰቦች ሁሉ ደከመኝ፡ ሰለቸኝ ሳይል ዋጋ የከፈለውን የአማራ ህዝብ ዋጋ በማሳጣት የሌሎቹ ጠላት አድርጐ በማቅረብ፡ የዘረኞች ተባባሪነቱን አስመስክሯል።

Wednesday, 12 February 2014

መንታ መንገድ – የኢህአዴግና የአሜሪካ ወዳጅነት ወዴት?


ቻይና ኢህአዴግን ትታደጋለች? ወይስ ኢህአዴግ ይታዘዛል?
eprdf china usa

አሜሪካኖች ነጻ እንድታወጡን አንጠይቃችሁም። የኢትዮጵያ ህዝብ እንዴት ነጻ እንደሚወጣ ያውቃል። እናንተ ግንበነጻነት መንገዱን ላይ ዕንቅፋት አትሁኑበት … ዶናልድ ያማሞቶ  ከዛሬ ስምንት ዓመት በፊት ኢትዮጵያ በመንታመንገድ ላይ ነች ብለኸን ነበር መቼ ነው መንገዱን የምናቋርጠውከመንገዱ ላይ ገለል በሉልን” አቶ ኦባንግ ሜቶ
እንዴት እዚህ ተደረሰ?
የኢህአዴግን የአገዛዝ ዘመን ተቃዋሚዎችን አጃቢ አድርጎ የህግ ሽፋን በመስጠት የሚያራዝመው ዋና ተቋም ምርጫ ቦርድ፣ የፕሬስ ነጻነት፣ የመናገርና የመሰብሰብ ነጻነት፣ የህግ የበላይነት፣ ሕግን የማክበርና የማስከበር ሃላፊነት፤ ወዘተ በኢትዮጵያ ነጻ ከሆኑ ኢህአዴግ ከፊትለፊቱ ካለው ምርጫ የመዝለል አቅም እንደሌለው ይታመናል። ስለዚህም እነዚህን ጉዳዮች ለድርድር አያቀርባቸውም። ኢህአዴግ ከጅምሩ በህዝብ የማይታመነውና እውቅና የሚነፈገው ራሱን በነጻ አውጪ ስም (ህወሃት) የሰየመ መንግስት ስለሆነ ነው። ነጻ አውጪ እየተባለ አገር መምራቱም አቅዶ፤ ተልሞና መድረሻውን አስልቶ የሚጓዝ ስለመሆኑ ያሳብቅበታል። ለዚህም ይመስላል ስርዓቱ በሙስና የሸተተ፣ በግፍ የገለማ፣ የሚመራውን ህዝብ የሚገል፣ የሚያስር፣ የሚያሰቃ፣ መንግስት ሆኖ የሚሰርቅ፣ ብሔራዊ ክብርን የሚጠላ፣ ህብረትንና አንድነትን የሚጠየፍ፣ ጎሳና ጠባብ አመለካከት ላይ የተቀረጸ፣ በተራና በወረደ ተግባሩ ለመንግስትነት የማይመጥን መሆኑን የተረዱት አጋሮቹ አሁን ያመረሩበት ደረጃ ስለመዳረሳቸው ምልክቶች እንዳሉ አቶ ኦባንግ ሜቶ ለጎልጉል ተናግረው ነበር።
ኢህአዴግ ከአሜሪካ ጋር የመሰረተው ግንኙነት ከቶውንም ንፋስ እንደማይገባው ተከታዮቹ ሙሉ በሙሉ ያምናሉ። በተለይም የህወሃት ሰዎች አሜሪካ ከህወሃት ጋር ያሰረችው ቀለበት የሚወይብ አይመስላቸውም። የአሜሪካና የ”ህወሃት ፍቅር” ትምክህት የሆነባቸው የአሜሪካን ባለስልጣናት ህወሃት ኢትዮጵያን እስከ ዘላለም እንዲመራ ልዩ ቅባት እንደቀቡት የሚናገሩም አሉ። አሜሪካ ለህወሃት/ኢህአዴግ የምትሰጠው ጭፍን ድጋፍ ሊጤን እንደሚገባው በማሳሰብ ተስፋ ሳይቆርጡ የታገሉና የሚታገሉ ደግሞ ይህ ትምክህት አንድ ቀን እንደሚተነፍስ በእምነት ሲናገሩ ቆይተዋል።

ትግራዊ ማንነት ካለ ኢትዮጵያዊ ማንነትም አለ! (አብርሃ ደስታ)


February 12, 2014
“ኢትዮጵያዊ ነኝ፤ ኢትዮጵያዊ ማንነት አለኝ” ብዬ ስል የራሴ (የግሌ) ማንነት የለኝም ማለት አይደለም። የአከባቢ ማንነት የለኝም ማለት አይደለም። የክልል (የብሄር) ማንነት የለኝም ማለት አይደለም። ወይም እነዚህ የተለያየ ደረጃ ያላቸው ማንነቶቼ መጥፋት አለባቸው ማለት አይደለም። እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ ስል የራሴን ማንነት አልቀበልም ማለት አይደለም። የራሴ ማንነት ስላለኝ ነው ኢትዮጵያዊ ማንነት ሊኖረኝ የቻለው። እኔ የግል ማንነት ባይኖረኝ ኑሮ ኢትዮጵያዊ አልሆንም ነበር። ምክንያቱም የግል ማንነት ከሌለኝ የሀገር ማንነት ሊኖረኝ አይችልም። እያንዳንዱ ሰው የግሉ የሆነ ማንነት አለው። የግሉ ማንነት ስላለው ነው ኢትዮጵያዊ ማንነት ያለው። ኢትዮጵያዊ ማንነት ራሱ የቻለ የሁላችን የጋራ ማንነት ነው።
Abraha Desta the facebook
አብረሃ ደስታ
የትግራይ ማንነት ካለን የኢትዮጵያ ማንነት ለምን አይኖረንም? “ትግራዮች አንድ ነን” ካልን “ኢትዮጵያውያን አንድ ነን” ብንል ችግሩ ምንድነው? ኢትዮጵያዊነትኮ ከብሄር (ከክልል) ሰፋ ያለ ሀገራዊ ማንነት ነው። ሀገራዊ ማንነታችንን ብንቀበል ችግሩ ምንድነው?
ኢትዮጵያውያን አንድ አይደለንም አትበሉኝ። ምክንያቱም ኢትዮጵያውያን አንድ ካልሆንን ትግራዮችም አንድ አይደለንም፤ አማራዎችም አንድ አይደለንም፣ ኦሮሞዎችም አንድ አይደለንም። አንድ የሆነ አይኖርም።
“ኢትዮጵያውያን አንድ አይደለንም ምክንያቱም የተለያየ ታሪክና ባህል አለን” አትበሉኝ። ምክንያቱም እያንዳንዱ ግለሰብ፣ አውራጃ፣ ክልል (ብሄር) ወዘተ…ም የተለያየ ታሪክና ባህል ሊኖረው ይችላል። ኢትዮጵያውያን የተለያየ ባህልና ታሪክ ስላለን አንድ አይደለንም ካላችሁኝ ኦሮሞዎችም አንድ አይደሉም እላቸዋለሁ፤ ምክንያቱም የወለጋ ኦሮሞዎች፣ የሸዋ ኦሮሞዎችና የአርሲ ኦሮሞዎች የተለያየ ታሪክና ባህል አላቸው።
ኢትዮጵያውያን የተለያየ ባህልና ታሪክ ስላለን አንድ አይደለንም ካላችሁኝ አማራዎችም አንድ አይደሉም እላቸዋለሁ፤ ምክንያቱም ወለየዎች፣ ጎጃሞችና ጎንደሬዎችም የተለያየ ታሪክና ባህል አላቸው።