April 9, 2015
በነሶልያና ሽመልስ የክስ መዝገብ ከጎንዬሽ ጉዳዬች ውጪ ለ25ተኛ ጊዜ (በአጠቃላይ ለ27ተኛ ጊዜ) የተሰየመው ችሎት ዛሬም የደረጃ ምስክሮችን ሲያሰማ ውሏል፡። ከሳምነትት በፌት የተሰየመው ችሎት አቃቤ ህግ 41 ምስክሮች አሉኝ ነገር ግን ላገኛቸው ስላልቻልኩ ተከሳሾቹ በማረሚያ ቤት ቆይተው ተጨማሪ ማፈላለጊያ ጊዜ ይሰጠኝ በማለት ጠይቆ ለዛሬ የተቀጠረ ቢሆንም ዛሬም “የሽብር ተግባሩ “ ዋና ምስክሮች ባለመገኘታቸው ፍተሻ ላይ ተገኝተናል ያሉ አምስት ምስክሮች ተሰምተዋል፡። የምስክሮቸን ቁጥርም 35 ነው በማለት ቀይሮታል፡፡
ባለፈው የተሰሙት 13 ምስክሮች ሲሆኑ በዛሬው ችሎት ባልተካደ ነገር ላይ ሲመሰክሩ የዋሉት የደረጃ ምስክሮች
14ተኛ ምስክር ተወዳጅ ኃ/ማርያም ይባላሉ፡፡ እድሜያቸው 34 ሲሆን የመንግስት ሰራተኛ ናቸው፡፡ የምስክርነት ቃላቸውም ‹‹የመጣሁበት ኬዝ ግንቦት 7/2006 ዓ.ም በምኖርበት ልደታ 5ኛ አካባቢ የፌደራል ፖሊስ ታዛቢ ሁነኝ ብሎ ጠይቆኝ በታዛቢነት ያየሁትን ለመመስከር ነው፡፡ ማህሌት ጤና ጥበቃ ሚ/ር ትሰራለች መሰለኝ፣ እዚያ መስሪያ ቤት ፖሊስ ማህሌት ኮምፒውተርና ጠረጴዛ ላይ ያለውን ሲበረብር አይቻለሁ፡፡ መንግስት መስሪያ ቤት የምትጠቀምበት ኮምፒውተር ላይ የተገኙ ሰነዶች ላይ ማህሌት ስትፈርም እኛ ታዛቢዎችም ፈርመናል፡፡ የፈረምነው ግንቦት 7/2007 ዓ.ም ነበር፡፡ የገጹን ብዛት አሁን አላስታውስም፤ ወደ 40 ገጽ ይሆናል፡፡ እንግሊዝኛና አማርኛ ጽሁፎች አሉበት፡፡ የተወሰነ የፖለቲካ ይዘት የነበረው አለ፡፡ የፖለቲካ ፕሮግራም ማኒፌስቶ አይቻለሁ፡፡ ፖሊስ ማህሌትን ሲጠይቃት ከኦነግ የወጣው የሌንጮ ፓርቲ ፕሮግራም ነው ብላለች፡፡ ጎስፕ ንግግሮችም አሉ›› ብሏል፡፡ ዳኛው ጎሲፕ በአማርኛ ምንድነው ሲላቸው ምስክሩ ‹‹ሽሙጥ ንግግር ነው›› ብለው መልሰዋል፡፡ ምስክሩ የተገኙ ሰነዶች ላይ ፌደራል ፖሊስ ሄደው እንደፈረሙና ይሄን ያደረጉትም ግንቦት 9/2006 ዓ.ም ነው ብለዋል፡
15ተኛ ምስክር ፀሐይ ብርሃኔ እድሜያቸው 33 የሆኑ የመንግስት ሰራተኛ ናቸው፡፡ የምስክርነት ቃላቸውም ‹‹ግንቦት 7/2006 ዓ.ም ከቀኑ 4፡00 ፌደራል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ፖሊስ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ አሳይቶ ቢሮ ሲፈተሽ ታዘብ ተብዬ ተገኝቼ ነበር፡፡ ሲ.ዲ እና ዲክሜንት ሲወሰድ አይቻለሁ፡፡ ከዚያ ፖሊስ በ9/2006 ዓ.ም ሄጄ በሶፍት ኮፒ የነበሩት ሰነዶች ፕሪንት ተደርገው ማህሌት የፈረመችባቸው ላይ ፈርሜያለሁ፡፡ በእንግሊዝኛና አማርኛ የተጻፉ ናቸው፡፡ በግምት ወደ 40 ገጽ ይሆናል፡፡ አብዛኛው የፖለቲካ ነክ ጽሑፎች ናቸው፡፡ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጽሑፎች አሉበት፡፡ ያየናቸው መረጃዎች ከእሷ ኮምፒውተር ላይ ስለመገኘታቸው አይተን ፈርመናል፡፡››