Tuesday, 23 June 2015

እነ ወይንሸት ሞላ ከእስር እንደተለቀቁ ታፈነው ታሰሩ


  • 183
     
    Share
9271_728586630600331_5995106938468341166_n
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
መንግስት አይ ኤስ አይ ኤስን ለመቃወም በጠራው ሰልፍ ሰበብ ታስረው ሰኔ 15/2007 ዓ.ም በቄራ ፍርድ ቤት በዋለው ችሎት እንዲፈቱ የተወሰነላቸው ወንይሸት ሞላ፣ ኤርሚያስ ፀጋዬ፣ ዳንኤል ተስፋዬና ቤትሄልየም አካለ ወርቅ ዛሬ ሰኔ 16/2007 ከእስር ተፈትተው ሲወጡ በፖሊስና ደህንነቶች ታፍነው ታስረዋል፡፡
ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ታስረው የነበሩት ኤርሚያስ ፀጋዬና ዳንኤል ተስፋዬ ከእስር ከተፈቱ በኋላ የ6ኛ ፖሊስ ጣቢያ ፖሊሶች ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በር ላይ ጠብቀው ያፈኗቸው ሲሆን ፖሊሶቹ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንዳልያዙ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በተመሳሳይ የ6ኛ ፖሊስ ጣቢያ ፖሊሶች ወይንሸት ሞላንና ቤትሄልየም አካለ ወርቅ ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት አፍነው መልሰው እንዳሰሯቸው ታውቋል፡፡
የቄራ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት በትናንትናው ዕለት ወይንሸት ሞላ፣ ዳንኤል ተስፋዬና ቤትሄልየም አካለ ወርቅ ላይ የሁለት ወር እስር ፈርዶ፤ ከሚያዝያ 14/ 2007 ጀምሮ ሁለት ወር ከአንድ ቀን የታሰሩ በመሆኑ ከእስር እንዲፈቱ ወስኖ ነበር፡፡ ኤርሚያስ ፀጋዬንም በነፃ እንዲለቀቅ ወስኖለት ነበር፡፡ ይሁንና ፖሊስና ደህንነቶች የፍርድ ቤቱን ውሳኔ በመጣስ አፍነው እንደገና አስረዋቸዋል፡፡
- See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/44561#sthash.t5AGQMgy.dpuf

Wednesday, 17 June 2015

Ethiopia Opposition Candidate Dies After Attack in Northwest


June 16, 2015
Samuel Awoke Opposition Candidate
Samuel Awoke (PHOTO: NegereEthiopia)
(Bloomberg) – An Ethiopian parliamentary candidate for the opposition Blue Party died after being assaulted in Debre Markos, a town in the country’s northwest, the group said.
Two people attacked Samuel Awoke, 29, with a club and knife as he returned home alone from a night out with friends, spokesman Yonatan Tesfaye said by phone Tuesday from the capital, Addis Ababa.
“We are trying to figure out who are the killers and the reasons,” he said, citing suspicions it was politically motivated. Ethiopian Communications Minister Redwan Hussien said in a text message that a suspect has been apprehended and the attack may have stemmed from a legal dispute.

የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ለምንድን ነው የእራሱን ጥላ አይቶ የሚደነብረው? (ፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም)

June 17, 2015
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም

ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

እ.ኤ.አ በ2015 ለምንድን ነው የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የፍርኃት፣ የአጠቃላይ በፍርሀት የመርበድበድ እና እጅግ በጣም በጭንቀት ውስጥ የመግባት አምላኮች የእራሳቸውን ጥላ የሚፈሩት?
Why Is the T-TPLF Afraid of Its Own Shadow?
እ.ኤ.አ ግንቦት 24/2015 በኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች የቅርጫ ምርጫ ለማካሄድ በዕቅድ ተይዟል፡፡ የቅርጫ ምርጫው ምንም እንኳ በሸፍጥ የታጀበ እና የተጀቦነ ቢሆንም፡፡
ከአምስት ዓመታት በፊት እ.ኤ.አ ግንቦት 23/2010 እራሱን ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት) እያለ የሚጠራው ወሮበላ አገዛዝ የፓርላሜንታዊ መቀመጫውን በ99.6 በሆነ ውጤት አሸነፈ፡፡ ይኸ የምርጫ ውጤት የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብን እ.ኤ.አ በ2002 ሳዳም ሁሴን ካስመዘገበው 100 በመቶ በትንሽ በማነስ የሁለተኛነት ደረጃን እንዲጎናጸፍ አድርጎታል፡፡
የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ እ.ኤ.አ ግንቦት 24/2015 በሚካሄደው የይስሙላ ምርጫ ቢያንስ በ99.6 በመቶ ድል ይቀዳጅ ይሆን? ጠቃጠቆ ያለባቸው ጅቦች በእርግጠኝነት ጠቃጠቆው አለባቸውን?
ሆኖም ግን የወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ በፍርሀት ተውጦ በላብ ተዘፍቆ እንደሚገኝ  የውስጥ ምንጮች ነግረውኛል፡፡ እስከ ቅርጫ ምርጫው ድረስ በፍርሀት ርዷልን?