በሊቀ ካህናት ኀይለ ሥላሴ ዓለማየሁ ከአገር መባረር ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ቁጣቸውን እየገለጹ ነውሐራ ዘተዋሕዶ
December 29, 2012
- ሊቀ ካህናት ለጉባኤው መግለጫ ይቅርታ እንዲጠይቁ ለሰዓታት ጫና ተደርጎባቸዋል
- ‹‹አጀንዳዬ ሃይማኖታዊ ነው፤ የሠራኹት ስሕተት ይኹን የምጠይቀው ይቅርታ የለም !!››
- የሰላምና አንድነት ጉባኤው መግለጫ እንደሚያወጣ ይጠበቃል
- መንግሥት በወሰደው ርምጃ የመንበረ ፕትርክና ዓላሚዎቹ ጳጳሳት እጅ እንዳለበት ታምኖበታል

ሊቀ ካህናት ኀይለ ሥላሴ ዓለማየሁ ከብፁዓን አበው ጋር በተወሰኑ ጳጳሳት ግፊትና በመንግሥት የደኅንነት ኀይሎች ርምጃ ትላንት ምሽት ከኢትዮጵያ ተገደው እንዲወጡ የተደረጉት ሊቀ ካህናት ኀይለ ሥላሴ ዓለማየሁ ከጥቂት ሰዓታት በፊት አሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ደርሰዋል፤ በሰላምና አንድነት ጉባኤው አባልም አቀባበል እንደተደረገላቸው ታውቋል፡፡ በሊቀ ካህናት ኀይለ ሥላሴ ላይ ስለተፈጸመው ተግባር መረጃው የደረሳቸው ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በአሁኑ ወቅት በጉዳዩ ላይ እየመከሩበት ሲኾን ርምጃውን አነሣስተዋል፤ ግፊት አሳድረዋል በተባሉ ግለሰቦችና ጳጳሳት ላይ ጠንካራ አቋም ይወስዳሉ ተብሎ ይጠበቃል፤ ጳጳሳቱን ያሳተፈውና ለመንግሥት ጣልቃ ገብነት ማረጋገጫ ተደርጎ የተወሰደው ይኸው ርምጃ የማክሰኞውን የቅ/ሲኖዶስ ጉባኤ እንዳያጋግለው ተፈርቷል፡፡
በቀዳሚው የዜና ዘገባችን እንዳስነበብነው÷ ሊቀ ካህናት ኀይለ ሥላሴ ትላንት ከሰዓት በኋላ ፒያሳ ከሚገኘው ቤታቸው ወደ ቦሌ ለስብሰባ ቀጠሮ ብለው ከወጡ በኋላ ነበር ታግተው ቆይተው በዚያው ‹‹ትኬት ተቆርጦላቸው›› ተገደው እንዲወጡ የተደረገው፡፡ የሰላምና አንድነት ጉባኤው ዋነኛው ሰው የኾኑት ልኡኩ በግዳጅ እንዲወጡ ከመደረጋቸው በፊት እስከ ምሽቱ ሁለት ሰዓት ድረስ ባገቷቸው የደኅንነት ኀይሎች በተለያዩ ጥያቄዎችና ተጽዕኖዎች ሲዋከቡ እንደነበር ተገልጧል፡፡ ረቡዕ ዕለት አዲስ አበባ በደረሱበት ወቅትም ሊቀ ካህናትና አብረዋቸው የነበሩት ሌላው ልኡክ በልዩ ክፍል እንዲገቡ ተደርጎ ጥብቅ ፍተሻ እንደተካሄደባቸው ታውቋል፡፡