ለነገው የአውፍ መባባያ ስነ ስርአት ዝግጅቶች እየተደረጉ ነው፡፡
በክልልሎችና በአዲስ አበባ የሚደረጉ የረመዳን ዝግጅቶች ተጠናክረው መቀጠላቸውን ተከትሎ መንግስት ከፍተኛ ስጋት ውስጥ በመግባቱ በሁሉም ክልሎች ስብሰባ መጥራቱን የቀጠለ ሲሆን ስብሰባዎቹም በማስፈራሪያ የታጀቡ ሆነዋል፡፡ ተቃውሞ ተባብሶ ይቀጥልባቸዋል ተብለው በሚታሰቡ አካባቢዎች በዋነኝነት እየተጠሩ ባሉት የማስፈራሪያ ስብሰባዎች በሰብሳቢነት የሚገኙት የኢሕአዴግ የየአካባቢው ተወካዮችና የመንግስታዊው መጅሊስ ተወካዮች ሲሆኑ በረመዳን ምንም አይነት ተቃውሞ እንዳይደረግና በመስጊዶች ከሰላት ውጪ መቆየት እንደማይችልም በማስጠንቀቅ ላይ ይገኛሉ፡፡ የስብሰባ ታሳታፊ ሙስሊሞች ግን ተቃውሞዋቸውን አሰምተዋል፡፡ ‹‹ድምጻችን ይሰማ›› ለምን ትላላችሁ ብለው ሰብሳቢዎቹ ጥያቄ የሚያቀርቡበት ይኸው የማስፈራሪያ ስብሰባ ብዙዎቹ ባለመስማማትና በሙስሊሙ እንቢተኝነት በመጠናቀቅ ላይ ይገኛሉ፡፡
አላሁ አክበር!
No comments:
Post a Comment