Monday, 21 October 2013

ጀርመን፤ ስደተኞች የርሃን አድማ አቆሙ


በጀርመን -በርሊን ከተማ ስደተኞች ለአስር ቀናት ሲያካሂዱ የቆዩትን የርሃብ አድማ ማቆማቸው ተነገረ። ብራንድን ቡርገር ቶር በሚባለው ቦታ ላይ አድማ ሲያደርጉበት የሰነበቱት መጠለያ ትናንት ማታ መነሳቱን የበርሊን ከተማ የውህደት ጉዳዮች ተመልካች ባለስልጣን ዲሌክ ኮራት ዛሬ አስታውቀዋል።  ቀደም ሲል በፌዴራል የስደተኞችና ተገን ጠያቂዎች መስሪያ ቤት የሶሻል ዲሞክራቶች ፓርቲ ተወካዩ  ዲሌክ ኮራት ከረሀብ አድመኞቹ ጋር ተደራድረው እንደነበረም ተዘግቧል። ኮላት እንዳሉትም 30 የሚደርሱ፣ የኢትዮጵያ ፣ የኮንጎ ዲሞክራቲክ  ሪፐብሊክ እና የኢራን ስደተኞች እስከ መጪው ጥር ድረስ  አድማቸውን ማቆማቸው ተነግሯል። ይሁንና የረሀብ አድማ አድራጊዎቹ የስደተኝነት ማመልከቻቸው ተቀባይነት እንዲያገኝ፣ እና የስራ ፍቃድ እንዲሰጣቸው ያቀረቡትን ጥያቄ አሁንም ቀጥለውበታል።

No comments:

Post a Comment