Thursday, 17 December 2015

የወያኔን የጥፋት መንገዶች ማክሸፍ ይጠበቅብናል !!! – ነፃነት በለጠ



 በወያኔ/ኢሕአዴግ የሚመራዉን ስርዐት ምንነትና ማንነት በተግባርም የታየ እና ህዝቡም በሚገባ የሚያዉቀዉ ነዉ፡፡ ሆኖም ጥንቃቄ የሚያሰፈልጋቸዉን ጉዳዮች ማስገነዘብ እጅግ አስፈላጊ ነዉ፡፡ ይህ ፅሁፍ የስርዐቱን አደገኛ አካሄዶች ላይ በማተኮር፣ ሁላችንም እንድንጠነቀቅ በማስገነዘብ እና አንዳንድ እዉነታዎችን ለማሳወቅ የተዘጋጀ ጽሑፍ ነዉ፡፡ በቅድሚያ ወደ ዋናዉ ጉዳይ ከመግባቴ በፊት ስለ ወያኔ/ኢሕአዴግ መንግስት የማስተደዳር አቅም ላይ ማብራሪያ ልስጥ፡፡
የማስተዳደር አቅም ማጣት
በማርክሳዊ ሌኒናዊ አስተምህሮ መሠረት በአሁኑ ወቅት በኢትዮጲያ ህዝቡ ለለዉጥ እንዲነሳ ለማድረግ የሚያስፈልጉ ነባራዊ እና ህሊናዊ ሁኔታዎች ተሟልተዉ የሚገኙበት አብዮታዊ ወቅት ላይ እንገኛለን፡፡ ነባራዊ ሁኔታዎች የምንላቸዉ ለህዝቡ የሚያስፈልጉ መሰረታዊ አገልግሎቶች በበቂ ሁኔታ ተማልተዉ አለመቅረብ እና ከናካቴዉ አለመኖር፣ የኑሮ ዉድነት እየተባባሰ በመምጣቱ በየቤቱ ያለዉ ችግር ከሚገመተዉ በላይ መሆን (ብዙ ወላጆች ምግብ ሳይበሉ ወደ ስራ መሄዳቸዉ የተለመደ ሆኗል፤ ህፃናትም ምግብ ሳይበሉ በመሄዳቸዉ ራሳቸዉን መሳት በየጊዜዉ የሚደመጥ ነዉ)፣ ድርቁ ወደ ረሃብ ከመለወጡ በፊት መሰራት የነበረበት ስራ አለመሰራት (ለድግስ ቅድሚያ መስጠት)፣ የስራ አጡ ቁጥር ማሻቀብ (የድርጅት አባል ካልሆኑ የፈለገ ጥሩ ነጥብም ቢኖር እንኳ ስራ ማግኘት የማይቻል መሆኑ)፤ ውስጣዊ ፍልሰትና እና ከሀገር ዉጭ መሰደድ እየየተባባሰ መምጣት፣ ሙስና በከፍተኛ ደረጃ መስፋፋት (የተመቻቸላቸዉ ዋናኛዎቹ የሙስና ተዋናዮች በማይነኩበት የጨዋታዉ ሜዳ በነፃነት እየዘረፉ በአይናችን እያየን በአጭር ጊዜ ወደ ብልፅግና መሸጋገር) ፣ የተጠያቂነት ስርዐት አለመኖር (ጥፋት አጥፍተሃል ብሎ መጠየቅ ነዉር የሆነበት፣ ያወጡትን ህገ መንግሰት በአደባባይ መጣስ፣ የፍትህ ስርዐቱ ለህግ ልዕልና ሳይሆን ለወያኔ አገልጋይ መሆን፣ በየስራዉ ቦታ ህግን አክብሮ መስራት እየተዳከመ እና እየቀረ መገኘት እና ሌሎች ያልተገለፁትን ያጠቃልላል፡፡
ሕሊናዊ ሁኔታዎች የምንላቸዉ ህዝቡ ከፍርሃት መላቀቅና ስርዐቱን ፊት ለፊት ለመጋፈጥ መቁረጥ፣ እምቢ አልገዛም ማለት፣ የስርዐቱን አስከፊነት በጥልቀት መረዳት፣ ገዢዎች እንደቀድሞዉ መምራት አለመቻል እና የመሳሰሉት በግልፅ እያየናቸዉና እየተገበሩ የሚገኙ መሆናቸዉ ለዉጡ አይቀሬ መሆኑን ያመላክታል፡፡
በአሁኑ ወቅት በወያኔ/ኢሕአዴግ የሚመራዉ መንግስት የማስተዳደር አቅሙ የተሟጠጠ መሆኑ በግልፅ እየታየ ነዉ፡፡ በየትኛዉም የሲቪል ሰርቪስ መ/ቤት የሠራተኛዉ የመስራት ፍላጎት ከመቼዉም ጊዜ የወረደበት፣ በከተማ መስተዳድር / ክልል ጀምሮ ወደታች ባሉ የመንግሰት እርከኖች ያለዉ የስራ መጠንና የመስራት ፍላጎት ተዳክሞ ሲንቀሳቀሱ የሚገኙት ታክስ / ግብር የሚሰበስቡ፣ መታወቂያ፣ የልደት እና የሞት ማስረጃ የሚሰጡ እና አልፎ አልፎ ደንብ በማስከበር የሚሠሩ (ሊሞሰን የሚችል ነገር ሲያጋጥም) ክፍሎች ናቸዉ፡፡ በህግና በስርዐት ስራ የሚሰራበት ጊዜ ማለቁን በአይናችን እያነነዉ ነዉ፡፡ ጠያቂም ተጠያቂም የሌሉበት እና ወያኔ/ኢሕአዴግ አተኩሮ እየተፍጨረጨረ ያለዉ ዕድሜዉን እንዴት እንደሚያራዝምና ለዕድሜ ማራዘሚያ የሚጠቅሙ ስልቶችን ከመድረክ በስተጀርባ በጥቂት የስርዐቱ ሰዎች እየጎነጎነ መሆኑ ነዉ፡፡


ከዚህ ቀጥሎ ያለዉ ጽሁፍ የሚያተኩረዉ በወያኔ እየተደረጉና ወደፊት ሊያጋጥመን የሚችለዉን እኩይ ተግባራት ህዝቡ አስቀድሞ በመገንዘብ ለስርዐቱ መሳሪያ ሆንን ተግባራዊ እንዳናደርገዉ እና አደገኛ ጥፋቶችን እንዳንፈፅም  ለማስገነዘብ ነዉ፡፡
  1. ህዝቡን በዘር ማጋጨት
ላለፉት 24 ዓመታት ወያኔ/ኢሕአዴግ ላይ ታች ሲል የነበረዉ ዘርንና ሃይማኖትን ለዕድሜዉ ማራዘሚያ አገልግሎት እንዲሰጡት ሲያዘጋጃቸዉና ሲተግብራቸዉ እንደነበር ሁሉም የሚያዉቀዉ ነዉ፡፡ በተለይ ሁለቱን የዘር ግንዶች፡ ኦሮሞ እና አማራን እርስ በርስ ለማጋጨት እሰከዛሬም እየተሞከረ ያለ ሴራ ነዉ፡፡ በሁለቱ የዘር ግንዶች ሳይወሰን በተለያዩ የዘር ግንዶች መካከል መናቆር ወያኔ ስልጣን ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ እንደቀጠለ ነዉ፡፡ በመካከላችን በሚነሳ ግጭት በልዩነቱ አገዛዙ ዕድሜዉን ለማራዘም እየተጠቀመበት ይገኛል፡፡ በተለይ ፊደል የቆጠርነዉ ዜጎች አምነንበት ይሁን ሳናምንበት ለወያኔ መሳሪያ ሆንን ለማገልገል ላይ ታች የምንል አለን፡፡ በሁሉም  የዘር ግንዶች አለመተማመን እንዳይኖር ማድረግ፣ አንዱ አንዱን እንደናቀ አደርጎ ማራገብ፣ ሰዎችን ከሰፈሩበት ቦታ ማፈናቀል፣ ታሪክን በማጣቀስ ለልዩነት ምክንያት የሚሆኑ ነገሮች መድረክ ተሰጥቷቸአዉ እንዲራገቡ እና በሌላ ጎን የመተጋገዝ፣ የመተባበር እና ለጋራ ዓላማ የመነሳት ጉዳይ ቦታ እንዳይኖረዉ መንገዱን በማመቻቸት በጋራ እንዳንታገል ተንኮል እየተሰራ ነዉ፣ ካላከሸፍነዉ ለእኛም ሆነ ለሀገሪቱ አይበጅም፡፡

በተለይ ወያኔ የህዝብ ቁጥራቸዉ ከፍተኛ የሆኑት ኦሮሞና አማራ በመካከለቸዉ ግጭት እንዲኖር የተለያዩ ስልቶችን ስራ ላይ ያዉላል፡፡ በተለይ በወያኔ ተላላኪ በሆነዉ በኦህዴድ ካድሬዎች አማካኝነት ስስ የሆኑ ጉዳዮችን በመነካካት ልዩነቱን ማጋጋል፣ ታሪክ በማጣቀስ ግጭት መለኮስ፣ በኦሮሚያ ዉስጥ የሚኖሩ ኦሮሞ ያልሆኑትን ከቦታቸዉ እንዲፈናቀሉ ማድረግ፣ በተለያዩ የሶሻል ሚዲያዎች አንዱን ዘር የሚያንቋሽሽ ጽሁፎችን ማዉጣት (ወያኔ ሆን ብሎ ቀጥሮ ያሰማራቸዉ በዚህ መስመር ቀጥለዉበታል) እነዚህና ሌሎች በመርዝ የተለወሱ መንገዶችን ተግባራዊ ለማድረግ ወያኔ  ወደኃላ እንደማይል ልናስተዉል ይገባል፡፡

ሰለዚህ ኦሮሞዉ፣ ከንባታዉ፣ ትግሬዉ፣ አማራዉ፣ አፋሩ፣ ሱማሌዉ፣ አኝዋኩ፣ ወላይታዉ፣ ኑዌሩ፣  … ወዘተ ሆነ ሌላዉ የተማረ፣ ያልተማረ ገጠሬ ሆነ ከተሜ ይህንን መሰሪነት በእንጭጩ ካልቀጨነዉ ተመልሶ እሳቱ የሚለበልበን እኛኑ እራሳችን ነዉ፡፡ ኢትዮጲያ በጋራ ሆነን ሰንሰለፍ ብቻ ነዉ ሰላም የሰፈነባት፤ ህዝብን የሚያስቀድም መንግሥት መመስረት እና የተሻለች ሀገር መገንባት የምንችለዉ፡፡ መነታረክ እና መበጣበጥ ለማናችንም ሳይጠቅም ለግፍ አገዛዝ በመዳረግ ለወያኔ እድሜ ማራዘሚያ መሳሪያ ሆንን እናገለግላለን፡፡ ይህንን አስከፊ ሁኔታ በሀገራችን እንዳይከሰትና ህዝቦች ነፃነታቸዉ ተከብሮ ፣ በሰላም በብልፅግና እንዲኖሩ ልዪነትን ከማራገብ ተቆጥበን በአንድነት በመንቀሳቀስ ለዉጡን እዉን ማድረግ ይጠበቅብናል፡፡

  1. ሃይማኖትን መሣሪያ በማድረግ ህዝቡን ማጋጨት
የሃይማኖት ጉዳይ ሌላዉ ለስልጣን ማራዘሚያነት የወያኔ ስርዐት እየተጠቀመበት ያለ መንገድ ነዉ፡፡ በኦፊሴል ኢትዮጲያ ሃይማኖት የልዩነት መሳሪያ ሳይሆን የብዝሃነት ምልክት ነዉ ይበል እንጂ በስልጣኑ ላይ አደጋ የሚደርስ መሆኑን ካወቀ በክርስትና እና በእስልምና አማኞች መካከል ልዩነት በማራገብ አርስ በርሳችን እንድንፋጅ አያደርግም ማለት ሞኝነት ነዉ፡፡ ለዘመናት በሁሉም ሃይማኖቶች መካከል በመተሳሰብ ተጠብቆ የቆየዉን ግንኙነት (የዚህ ጽሁፍ ፀሀፊ ከልጅነቱ ጀምሮ ያደገበት እና ያየዉ እዉነታ ነዉ) ለማደፍረስ

No comments:

Post a Comment