Friday, 30 November 2012
አሁንም የተሃድሶ ያለህ!!!
(ርዕሰ አንቀጽ)
“አንድነትን ስንመሰርት በቅንጅት ወቅት ስለሰራነው ጥፋትና የፖለቲካ ስህተት የገመገምነው ነገር የለም” ዶ/ር ያዕቆብ ሃ/ማርያም አንድነት ፓርቲን ከቅንጅት ጋር በማነጻጸር ከተናገሩት፡፡ በኢትዮጵያ የተቃዋሚ ፓርቲና ድርጅቶች መዋቅራዊ ጥንካሬና ደጋፊዎቻቸውን አስተባብረው ውጤት ስመዝገብ ያለመቻላቸው ጉዳይ አነጋጋሪ ነው። ተቃውሞ በኢትዮጵያ በፓርቲ መሪዎችና በገዢው ኢህአዴግ መካከል የሚደረግ እሰጥ አገባ ካልሆነ በስተቀር በደጋፊዎች ተሳትፎ ገዢውን ፓርቲ የማስገደድና እጁን የመጠምዘዝ ደረጃ ላይ ደርሶ ሊታይ አልቻለም። ከቅንጅት መፈራረስና ልዕልናው መክሰም ጋር የህዝብ ስሜትም አብሮ ተዳፍኗል የሚለው አስተያየት ሚዛን የደፋ የሚሆንባቸው የበዙት ለዚሁ ነው። በድርጅት ደረጃ ችግሩን ተመልክተው ስለመታደስ የሚያስቡ ስለመኖራቸው ግን ለረዥም ጊዜ አልሰማንም።
በኢትዮጵያ ህዝብን ለትግልና ለእምቢተኝነት የሚያነሳሱ ጉዳዮች ሞልተው የፈሰሱ ቢሆንም ህዝብ በስርዓቱ ከመበሳጨት የዘለለ እንቅስቃሴ አለማድረጉ ስርዓቱ ከዘረጋው የአፈና መዋቅር ጋር የሚያገናኙት ቢኖሩም በዋናነት የተቃዋሚዎች ድክመት ጎልቶ እንደሚታይ አሁን አሁን ይፋ እየሆነ ነው። በተለይም ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ሰሞኑን “የግል አስተያየቴ ነው” በማለት ያቀረቡት ጽሁፍ የችግሩ ቁልፍ ነውና ሁሉም ወገኖች አሰራራቸውን ሊፈትሹ እንደሚገባ ይሰማናል – አሁን!!
ህወሃት አረጋግቶ አገገመ
ብቸኛው ተቃዋሚ የንግድ ሚኒስትሩን ሹመት ኮነኑ
ኢህአዴግ “አረጋግቶ አገገመ” ከተባለው አዲሱ “ምደባ” መካከል የንግድ ሚኒስትር ተብለው በተሰየሙት ላይ ብቸኛው የፓርላማ ተወካይ አቶ ግርማ ሰይፉ ጠንካራ መከራከሪያ በማቅረብ ተቃወሙ። አቶ ግርማ የሚሾሙ ብቻ ሳይሆን የሚነሱ ባለስልጣናት ከሃላፊነታቸው የተነሱበት ምክንያትም ለህዝብ መቅረብ እንዳለበት አሳሰቡ። አቶ ሃይለማርያም ተቃውሞውን “መክረንና ገምግመን ያደረግነው ነው” ሲሉ ተከላከሉ። አቶ ግርማ ብሩ (አሁን አምባሳደር) ሲመሩት የነበረውን ሚኒስቴር መ/ቤት “ስያሜና ምልክት መለየት የማይችል” በማለት አንቋሸሹት።
ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ አገሪቱን በመሩበት ሶስት ወራት ካቢኒያቸውን በደንብ መገምገማቸውን በግምት በመግለጽ ተቃውሞ ያቀረቡት አቶ ግርማ ሰይፉ በምደባው በተወሰነ ደረጃ እንደሚስማሙ ተናግረዋል። የንግድ ሚኒስትሩ አቶ ከበደ ጫኔን ምደባ የተቃወሙት በማስረጃ ነው። የዓለም ባንክ ለንግድ ምዝገባ የማያመቹ አገሮችን ዝርዝር ጥናት ይፋ ሲያደርግ ኢትዮጵያ ከ185 አገሮች የ165ኛ ደረጃ ማግኘቷን፣ ለዚህም የዳረጉት ቀደም ሲል በተጠባባቂ ሚኒስትርነት ለረዥም ጊዜ ያገለገሉት አቶ ከበደ ጫኔ በመሆናቸው አዲሱ ሹመት እንደማይገባቸው አቶ ግርማ በተቃውሞ ተናግረዋል። በተጨማሪም ህዝብ የማወቅ መብት ስላለው ከፍተኛ ባለሥልጣናት ከሃላፊነታቸው ሲነሱ ምክንያቱ ይፋ ሊሆን እንደሚገባው ማሳሰቢያ አቅርበዋል።
አቶ ግርማ ብቻ የተቃውሞ አስተያየት ያቀረቡበት ምደባ በስፋት ሃሳብ ሲሰጥበት ለነበረው የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ወንበር መልስ በመስጠት ተጠናቋል። ምደባውን ህወሃት ሲያሸንፍ የተመደቡት ሚኒስትር አቶ መለስ በህይወት እያሉ ይተኳቸዋል የተባሉት ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ናቸው። የግራ ዘመሙን የፖለቲካ ጎዳና እምብዛም የማያውቁት ዶ/ር ቴዎድሮስ “ልምድ ያላቸው ታጋይ አይደሉም” በሚል ህወሃትን በከፍተኛ አመራርነት ስለመወከላቸው ጥያቄ የሚያቀርቡባቸው ነበሩ።
Wednesday, 28 November 2012
መንግስት በመላ አገሪቱ ሙስሊሞችን እያስገደደ ለተቃውሞ ሰልፍ ሊያስወጣ ነው
ህዳር ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ከኢህአዴግ ምንጮች የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው በአገሪቱ ውስጥ በሚገኙና መንግስት በሙስሊሙ ላይ በሚፈጽመው ኢሰብአዊ ድርጊት የተነሳ ተቃውሞ ያስነሳሉ በተባሉ አካባቢዎች በሙሉ ፣ መንግስትን የሚደግፉ ሰልፎች ይደረጋሉ።
አብዛኛው ህዝብ ተገዶ እንዲወጣ፣ የድርጅት አባላት ከፍተኛ ተልእኮ እንደተሰጣቸው ለማወቅ ተችሎአል።
በዛሬው እለትም በቅርቡ የመንግስት ታጣቂዎች 4 ሰዎችን በገደሉበት ገርባ እና ደጋን መንግስትን የሚደግፉ ሰልፎች ተደርገዋል።
የሰልፉ ዋና አላማ በፍርድ ሂደት ላይ የሚገኙት የድምጻችን ይሰማ የሙስሊም ኮሚቴ አባላት አሸባሪዎች ናቸው የሚል መልእክት ለማስተላለፍ ነው።
ኢህአዴግ በኮሚቴ አባላቱ ላይ ለፍርድ ቤቱ ጠንካራ ማስረጃ ማቅረብ ባለመቻሉ በዳኞች ላይ ተጽኖ ለመፍጠር ማሰቡን የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
Tuesday, 27 November 2012
አላማጣ ታፍነው የተወሰዱ ከ20 በላይ ሰዎች የደረሱበት አልታወቀም
ህዳር ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በራያና አዘቦ ፣ በአላማጣ ከተማ ከኤልክትሪክ መስመር መቃጠል ጋር በተያያዘ በጥርጣሬ የተያዙ ከ20 በላይ ግለሰቦች ወደ ማይጨው ከተማ ተወስደው መታሰራቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ቢናገሩም ፣ ዘመዶቻቸው እንዳይጠይቋቸው በመደረጉ ስለደህንነታቸው ሁኔታ ለማወቅ አልተቻለም።
ወጣቶች የታሰሩት ለኢንቨስተሮች ተብሎ የተዘረጋውን የኤልክትሪክ ምሰሶ አቃጥላችሁዋል በሚል ነው። የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት እንደገለጡት ታፍነው የተወሰዱት ወጣቶች በእስር ቤት ጉዳት ሳይደርስባቸው አልቀረም። በጉዳዩ ዙሪያ የመንግስት ባለስልጣናትን ለማናገር ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።በሌላ በኩል ደግሞ ስራ ለመቀጠር ወደ ጅጅጋ የሄዱ 9 ወጣቶች በፖሊስ ተዘርፈውና ተደብድበው ለልመና መዳረጋቸውን የአካባቢው ወኪላችን ገልጿል። ከባህርዳር ዩኒቨርስቲ የተመረቁት 9ኙ ወጣቶች የተነሱት ሞጣ እየተባለች ከምትጠራ በምስራቅ ጎጃም ዞን በምትገኝ ከተማ ሲሆን፣ ወደ ጂጂጋ ያቀኑትም ለመምህርነት ስራ ተወዳድረው በማሸነፋቸው ነው። መምህራኑ ወደ ምድብ ቦታቸው እስከሚሄዱ ድረስ አልጋ ተከራይተው በመጠባባቅ ላይ ሳሉ፣ ሌሊት ፖሊሶች ወደ ክፍላቸው በመግባት ከ1600 እስከ 2000 ብር እንዲሁም የሞባይል ስልኮቻቸውን በድብደባ ቀምተዋቸዋል። ፖሊሶቹ ገንዘብ አልተወሰደብንም ብላችሁ ፈርሙ በማለት ካስፈረሙዋቸው በሁዋላ የመሳፈሪያ 50 ብር በመስጠት ሀረር ወስደው ጥለዋቸዋል። መምህራኑ ወደ አካባቢያቸው የሚመለሱበት የትራንስፖርት ገንዘብ ስላጠራቸው በአሁኑ ሰአት ሀረር ከተማ ውስጥ በልመና ላይ መሆናቸውን ወኪላችን ገልጿል።
ህዳር ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በራያና አዘቦ ፣ በአላማጣ ከተማ ከኤልክትሪክ መስመር መቃጠል ጋር በተያያዘ በጥርጣሬ የተያዙ ከ20 በላይ ግለሰቦች ወደ ማይጨው ከተማ ተወስደው መታሰራቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ቢናገሩም ፣ ዘመዶቻቸው እንዳይጠይቋቸው በመደረጉ ስለደህንነታቸው ሁኔታ ለማወቅ አልተቻለም።
ወጣቶች የታሰሩት ለኢንቨስተሮች ተብሎ የተዘረጋውን የኤልክትሪክ ምሰሶ አቃጥላችሁዋል በሚል ነው። የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት እንደገለጡት ታፍነው የተወሰዱት ወጣቶች በእስር ቤት ጉዳት ሳይደርስባቸው አልቀረም። በጉዳዩ ዙሪያ የመንግስት ባለስልጣናትን ለማናገር ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።በሌላ በኩል ደግሞ ስራ ለመቀጠር ወደ ጅጅጋ የሄዱ 9 ወጣቶች በፖሊስ ተዘርፈውና ተደብድበው ለልመና መዳረጋቸውን የአካባቢው ወኪላችን ገልጿል። ከባህርዳር ዩኒቨርስቲ የተመረቁት 9ኙ ወጣቶች የተነሱት ሞጣ እየተባለች ከምትጠራ በምስራቅ ጎጃም ዞን በምትገኝ ከተማ ሲሆን፣ ወደ ጂጂጋ ያቀኑትም ለመምህርነት ስራ ተወዳድረው በማሸነፋቸው ነው። መምህራኑ ወደ ምድብ ቦታቸው እስከሚሄዱ ድረስ አልጋ ተከራይተው በመጠባባቅ ላይ ሳሉ፣ ሌሊት ፖሊሶች ወደ ክፍላቸው በመግባት ከ1600 እስከ 2000 ብር እንዲሁም የሞባይል ስልኮቻቸውን በድብደባ ቀምተዋቸዋል። ፖሊሶቹ ገንዘብ አልተወሰደብንም ብላችሁ ፈርሙ በማለት ካስፈረሙዋቸው በሁዋላ የመሳፈሪያ 50 ብር በመስጠት ሀረር ወስደው ጥለዋቸዋል። መምህራኑ ወደ አካባቢያቸው የሚመለሱበት የትራንስፖርት ገንዘብ ስላጠራቸው በአሁኑ ሰአት ሀረር ከተማ ውስጥ በልመና ላይ መሆናቸውን ወኪላችን ገልጿል።
በኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት አርማጭሆ ሳንጃ ወረዳ ልዩ ስሙ ጃንሱማ በተባለው ቦታ ወታደራዊ ጥቃት ፈጸመ
የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት በወያኔ ቅጥረኛና ምንደኛ የልዩ ሃይል ታጣቂ ቡድን ላይ የጀመረውን የማጥቃት ዘመቻ አጠናክሮ በመቀጠል ሕዳር 15-2005 ዓ.ም
አርማጭሆ ሳንጃ ወረዳ ልዩ ስሙ ጃንሱማ በተባለ ቦታ ባደረገው ውጊያ 14 የጠላት ወታደሮችን በመግደልና 12 በማቁሰል ከፍተኛ ወታደራዊ ድሎችን በማስመዝገብ ግንባሩ የተሰማራበትን ግዳጅ በድል እየተወጣ መሆኑን የግንባሩ ወታደራዊ መምሪያ አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ሕዝብ ከዘራፊውና ከነፍሰ-ገዳዩ የወያኔ አምባገነናዊ ገዥ ቡድን ለማላቀቅ ያለው ብቸኛ አማራጭ መንገድ በትጥቅ ትግል ስርዓቱን ማንበርከክ መሆኑን ጠንቅቆ ያወቀው የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ሰራዊት ሀገርንና ወገንን ለመታደግ ቆርጦ በመነሳት በሰሜኑ የሐገራችን ክፍል ወታደራዊ ስትራቴጅውን ነድፎ እየተንቀሳቀሰ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን፣ ሰሞኑን አርማጭሆ ሳንጃ ወረዳ ልዩ ስሙ ጃንሱማ በተባለው ቦታ ባደረገው የማጥቃት ዘመቻ 26 የጠላት ወታደሮችን ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ወታደራዊ የበላይነትን የተቀዳጀ ሲሆን፣ ከሞቱት 14 የልዩ ሃይል ታጣቂ ቡድን መካከል አበበ የሚባለው የቀራቅር ተወላጅና አለልኝ የሚባል የደባርቅ ተወላጅ የሆኑት ከፍተኛ አመራሮች መሞታቸውን የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር ወታደራዊ መምሪያ ገልጿል።
በራስ አሉላ ስም የተሰየመው ት/ቤት በመለስ ተቀየረ
ከኢየሩሳሌም አርአያ
በትግራይ ተምቤን – አብዪአዲ የሚገኘውና በጀግናው ራስ አሉላ አባነጋ ስም ተሰይሞ የቆየው የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ስያሜው ተቀይሮ በመለስ ዜናዊ ስም እንዲሰየም መወሰኑን ታማኝ ምንጮች አስታወቁ።
በደርግ ዘመን የተሰራውና በራስ አሉላ ስም ተሰይሞ የ 9 – 10ኛ ክፍል ተማሪዎችን ተቀብሎ ሲያስተምር ከቆየ በሑላ ከ2002 ዓ.ም ጀምሮ የት/ቤቱን አቅም ለማሳደግ በሚል የ11-12ኛ መመሪያ ክፍሎችን ለመገንባት በአገር ውስጥና በውጭ አገራት የሚገኙ የአካባቢው ተወላጆች ገንዘብ አዋጥተው ስራው መከናወኑን ምንጮቹ ጠቁመዋል። ግንባታው ተጠናቆ ባለፈው ነሃሴ ወር ለማስመረቅ በዝግጅት ላይ እንዳለ አቶ መለስ በማለፋቸው ፕሮግራሙ መሰረዙን ሲታወቅ; ከሁለት ሳምንት በፊት በተከናወነው የምረቃ ስነ-ስርአት የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት በስፍራው እንደተገኙ ማወቅ ተችሎዋል።
Monday, 26 November 2012
ወቅቱ የአገራችን የፖለቲካ ሁኔታና የወደፊት የትግል አቅጣጫ – በዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር
መግቢያ
ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ
የሁላችንም የረጅም ጊዜ ህልም፣ አንድነትዋ የተጠበቀ የበለፀገች ኢትዮጵያን ማየት ነው፡፡ ወደዚያ ለመድረስ ሁሉም ኢትዮጵያውያን አስተዋጽኦአቸውን የሚያበረክቱበት ለአገሬ
እሠራለሁ ብለው በነፃ አየር የሚተነፍሱበት ዴሞክራሲያዊ የፖለቲካ ምህዳር እንዲፈጠር ካሁኑ ጀምረው እንዲታገሉ ሁኔታን መመቻቸት ይፈልጋሉ፡፡ ስለዚህም የፖለቲካ ምህዳሩን ማየትና ወዳለምነው ግብ ለመድረስ የሚረዱንን አቅጣጫዎች መዳሰሱ ጠቃሚ ነው፡፡
ስለአገራችን የፖለቲካ ሁኔታ ሁላችሁም ታውቃላችሁ፤ ሆኖም የግለሰቦች አረዳድ ሊለያይ ስለሚችል፣ እኔ የራሴን ግንዛቤ ለመግለጽ እሞክራለሁ፡፡
- የኔን ግንዛቤ ስገልጽ የኔን ሃሳብና አመለካከት ብቻ ተቀበሉ ለማለት ሳይሆን ዛሬም ይሁን በቀጣይ በሚካሄዱ ውይይቶች የኔም ግንዛቤና አመለካከት እንደአስተዋጽኦ እንዲወሰድ ምኞቴ መሆኑን ሳልገልጽ አላልፍም፡፡
Saturday, 24 November 2012
“የኢሳያስ ልጅ አይከዳም! አናምንም”
ህወሃት የኤርትራ ጉዳይ “ይቋጭ” እያለ ነው”
ከኤርትራ ሰሞኑን የሚወጡ መረጃዎች ከጉዳዩ ባለቤቶች ማረጋገጫ ወይም ማስተባበያ ባይቀርብበትም ከኤርትራ ጋር በተያያዘ የተለያዩ አቋምና ተስፋ ባላቸው ዘንድ ከፍተኛ ትኩረት የሳበ ጉዳይ ሆኗል። አንዳንድ በብሎግ ሂሳብ የሚጫወቱ የኤርትራ መንግሥት አገልጋዮች ለጉዳዩ ጆሮ ዳባ ቢሉም በዋና በተቃዋሚነት የሚታወቁት የኢሳያስ ባላንጣዎች ለወሬዎቹ ሽፋን በመስጠት ግንባር ቀደም ሆነዋል።
የ1997 ምርጫን ተከትሎ በተፈጠረው አለመረጋጋት “ህወሃት ሰራዊቴን በመያዝ ጓዜን ጠቅልዬ ወደ ትግራይ ምድር እገባለሁ” ማለቱን አስነብቦ የነበረው ኢንዲያን ኦሽን ኒውስ ሌተር ሰሞኑን የህወሃት ሊቀመንበርን ጠቅሶ ኤርትራ ላይ ጦርነት የማወጅ ፍላጎት እንዳለ ይፋ አድርጓል። ኢንዲያን ኦሽን ከውስጥ አዋቂዎች አገኘሁ በማለት ሌላ ያሰነበበው ዜና የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ አሊ አብዶ ካናዳ ጥገኝነት መጠየቃቸውን ነው። ይህ ብቻ አይደለም ኢትዮጵያን ሪቪው ኢሳያስ ከስልጣናቸው በፍቃዳቸው ለመውረድ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን በተመሳሳይ “ታማኝ” ያላቸው ምንጮቹ እንደነገሩት ጠቅሶ ከነምክንያቱ ዜና አሰራጭቷል።
Friday, 23 November 2012
ኢህአዴግ ኢህአዴግን ማፈን ጀመረ!
የ“ንቦቹ” ፍጥጫ አቅጣጫውን እየቀየረ ነው
የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ስም ሲነሳ አቶ በረከት ስምዖን በግንባር ቀደም ይጠቀሳሉ። የአቶ በረከት ንብረት ሆኖ የመለስን አመራር በታማኝነት ሲያገለግል የኖረው ይህ ተቋም ቆርጦ በመቀጠል፣ የዜጎችን ሃሳብ በማዛባት፣ ወሬን ባለማመጣጠንና የሃሰት ፕሮፓጋንዳ በማስተላለፍ የሚታወቅ ነው። ስለሚጠየፉት የማይመለከቱት እንዳሉ አፍ አውጥተው የሚናገሩም አሉ።
ለሙያው ቅርብ የሆኑ አስተያየት ሰጪዎች “ወገንተኛ እንኳን ቢኾን መሰረታዊ የሙያው ግዴታ ሳይጣስ ሊሆን ይገባል። አንድ መገናኛ ማመጣጠን ካልቻለ በራሱ ሙት ነው። እያደር ብቻውን ይቀራል” ሲሉ ኢቲቪን ይገልጹታል። እንደነሱ አባባል ኢቲቪ ከህዝብ ሳይሆን ከራሱ ጌቶችም ጋር ተነጥሎ የአንድ ወገን (ግለሰብ) ሎሌ የሆነ በድርጅት ቅርጽ የሚከላወስ ሱቅ በደረቴ አይነት ነው።
ኢቲቪ ሃሳባቸውን፣ ንግግራቸውን፣ አቋማቸውን፣ ጥቆማቸውንና ተቃውሟቸውን እየቀረጸ በማዛባት ከህዝብና ከሚወዱዋቸው ወገኖቻቸው ጋር እሳትና ጭድ ያደረጋቸው፣ ለተራ የፖለቲካ መጠቀሚያ ሰለባ የሆኑ ወገኖች ኢቲቪን “በደለን” በማለት መውቀስ የሚችሉበት አግባብ የላቸውም። ኢቲቪ “በአልቤርጎ ውለታ” የግል ሳሎናቸው ያደረጉትን ጨምሮ “ልማታዊ” የሚባሉት በግብር ጸረ ልማት የሆኑ ውስን ጋዜጠኞች ሎሌ ሆነው እንዳሻቸው የሚንፈላሰሱበት ቤት ስለሆነ ጠያቂም ከልካይም እንደሌለባቸው ስለ ተቋሙ የሚያውቁ ይመሰክራሉ።
ዛሬ የመሪዎቻችንና ሌሎች ወንድሞቻችን ችሎት ተሰይሞ ውሏል፡፡
መሪዎቻችን ከቃሊቲ ልደታ ፍ/ቤት የገቡት ከሌሊቱ 10፡30 ነው፡፡
በልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራተኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ ተሰይሞ የዋለው ችሎት ስራውን የጀመረው ከጠዋቱ 3፡30 አካባቢ ነበር፡፡ ፖሊስ መሪዎቻችንን ማንም እንዳያገኛቸው ከሌሊቱ አስር ሰዓት ላይ ነበር ከቃሊቲ ጭኖ ልደታ ፍ/ቤት ያደረሳቸው፡፡ ከሌሊቱ 10፡40 የደረሱት ወንድሞች የችሎት መሰየምያ ጊዜው እስኪደርስ ልደታ ፍ/ቤት በሚገኘው ጊዜያዊ መቆያ እንዲጠባበቁ ተደርገው ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት በአካባቢው የሚገኘው ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ ወደ ፍ/ቤት ጊቢ ሲገቡ ሊየያቸው ሳይችል ቀርቷል፡፡ በዛሬ የችሎቱ ቀጠሮ የመሪዎቻችንና ወንድሞቻችን ጠበቆች አቃቤ ህግ ባለፈው ወር ባቀረበው ክስ ላይ የመቃወሚያ ምላሻቸውን እንደሚሰጡ ይጠበቅ የነበረ ሲሆን፤ ጠበቆቹም 28 ገጽ የሚሆነውን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያቸውን በጽሑፍ አቅርበዋል፡፡ ጭብጣቸውንም ለፍርድ ቤቱ በቃል አሰምተዋል፡፡
ጠበቆቹ በዋነኝነት አቃቤ ሕግ የመሰረተው ክስ የኢትዮጵያን ሕገ መንግስትና አገሪቷ የፈረመቻቸውን ዓለም አቀፍ ህግጋት እንዲሁም የተባበሩት መንግስታት ሲቪል እና ፖለቲካዊ መብቶች ቃል ኪዳንን የሚጥስ እንዲሁም ክሱ የሕግ ትርጓሜን የሚያስነሳ በመሆኑ ጭምር ጉዳዩ መታየት ያለበት ይህን ጉዳይ ለማየት ስልጣን ባልተሰጠው ከፍተኛው ፍ/ቤት ሳይሆን ሕገ መንግስታዊ ጉዳዮችን በሚያየው የፌዴሬሽን ም/ቤት መሆን እንዳለበት በመቃወሚያቸው ላይ አመልክተዋል፡፡ አስር አባላት ያሉት የመሪዎቻችን ጠበቆች ቡድን በጋራ ያዘጋጀውና ተራ በተራም ባቀረበው መቃወሚያ ክሱ መሠረታዊ የህግ ስህተቶች ያቀፈ፣ የተብራራ አለመሆኑን እና የቀን ግድፈትም ያለበት መሆኑን በተጨባጭ ማስረጃዎች አቅርቧል፡፡ ችሎቱ የጠበቆችን ምላሽ ካደመጠ በኋላ አቃቤ ሕግ ምላሹን እንዲያቀርብ የተጠየቀ ሲሆን አቃቤ ሕግም ምላሹን ለማቅረብ ጊዜ እንደሚያስፈልገው ጠይቆ፤ ችሎቱ የአቃቤ ህግን ምላሽ ለማድመጥ ለመጪው አርብ ኅዳር 21/2005 ቀነ ቀጠሮ ሰጥቶ ተነስቷል፡፡ በችሎቱ ጋዜጠኞችና የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ አባላት ተገኝተው ነበር፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ለዛሬ ኅዳር 13/2005 ተቀጥሮ የነበረውን ችሎት ለመታደም ከፍተኛ ቁጥር ያለው የአዲስ አበባና የአካባቢው ሕዝብ በልደታ ፍ/ቤትና አካባቢው ተገኝቶ ነበር፡፡ ከማለዳው አንድ ሰዓት ጀምሮ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ በአካባቢው መከማቸት ጀምሮ የነበረ ቢሆንም አብዛኛው ሰው ወደ ፍ/ቤቱ ቅጽር እንዳይገባ በፌዴራል ፖሊስ አባላት ተከልክሎ ነበር፡፡ እስከ ጠዋቱ 3 ሰዓት ድረስ ወደ ጊቢው መግባት ይፈቀድ የነበረ ቢሆንም ከዚያች ሰዓት በኋላ ግን የፍ/ቤት ጉዳይ ያላቸው ሰዎች ብቻ እንዲገቡናሌሎች ሰዎች ከአካባቢው እንዲርቁ ፖሊስ ድብደባ በመፈጸም ጭምር መከላለከል አድርጓል፡፡
ከፍርድ ቤቱ በታችኛው አቅጣጫ በሚገኘው ክልል በርካታ ቁጥር ያላቸው ሙስሊሞች እስከ መከላከያ መኮንኖች ክበብ ድረስ ተኮልኩለው ቆመው የነበረ ሲሆን፣ በሜክሲኮና ሞላማሩም አቅጣጫ እንዲሁም የፍርድ ቤቱን ዙሪያ ጨምሮ ያሉ መንገዶች በሰው ተሞልተው ነበር፡፡ የፌዴራል ፖሊሶች እንደተለመደው በሰላም የቆመውን ሕዝብ በማስፈራራትና በመደብደብ፣ በአካባቢው ያሉትን የንግድ ሱቆችና ካፍቴሪያዎች በማዘጋትም ጭምር አየሩን በስጋት ሊሞሉት ሲሞክሩ ታይቷል፡፡ ፖሊስ በዚህ ድርጊቱ ገፍቶበት በአካባቢው ያሉትን የተሸከርካሪ መንገዶች በሙሉ የዘጋ ሲሆን ኢስላማዊ ምልክት ያላቸውን ሰዎች ከርቀት አካባቢዎች ጭምር ወደ ልደታ አቅጣጫ እንዳይሄዱ ሲያቅብ ነበር፡፡ በሞባይል ፎቶ ግራፍ አንስታቹሀል በሚልና በሌሎችም ጥቃቅን ሰበብ አስባቦች ፌዴራል ፖሊስ ከ25 በላይ የሚሆኑ ሰዎችን አስሯል፡፡ ብዙዎቹ አመሻሽ ላይ ቢፈቱም አሁንም በእስር ላይ የሚገኙ አሉ፡፡ ሙስሊሙ ሕዝብ በየእለቱ እና በየሰዓቱ በፖሊስ ከፍ ያለ በደል እየተፈጸመበትም በሰላማዊነቱና ትእግስቱ ዘልቋል፡፡ የሚያኮራ ትውልድ!
Thursday, 22 November 2012
ቀድመዋ እመቤት ጋሻ አነሱ!
ባትወጋ ፡ እንኳን፡ በል፡ እንገፍ፡ እንገፍ፤የአባትህ፡ ጋሻ፡ ትኋኑ፡ ይርገፍ።
ይህ ለዳተኛ ልጅ የአባቱን ጅግንነት ላልተከተለ ጋሻውን ለማንሳት ላልደፈረ የተዜመ ዜማ ነበረ። የቀድመዋ ቀዳማዊት እመቤት ባለቤት አቶ መለስ ዜናዊ አዜብ መስፍንን በፓራላማቸው
ላይ ‘ቆራጥ ታጋይ’ ሲሉ አወድሰዋቸው ነበር።የዳኛ ብርቱካን መዴክሳ በታጋይነታቸው ሰማቸው በኢትዮጵያዊያ ዘንድ እየገነነ መምጣቱ፤ የባለቤታቸውን ታጋይነት ሰለአጠላበት ነው በቁጭት የተናተሩት ያሉም ነበሩ። የወያኔ ተጋዳዮችም ቀዳማዊት እመቤትን እንደ ( Popular Front for Liberation of Palestine) ‘የፍልስጤም ሕዝባዊ ነፃነት ግንባር’ አባል የሆኑትን የእውቋንና ዝነኛዋን ሌዕላአ ካህሌድ (Leila Khaled) እንደ አስራ አምስተኛው ምዕተ ዓመት ዝነኛ ፈረሳዊት ጅግኒት የካቶሊክቱ ቅድስት ጆኖ ኦፍ አርክ (Joan of Arc) ጋር ያመሳስሏቸዋል። በተለይ ራሳቸው ላይ ጣል የሚያደርጓት ሻሽ መሰል ኮታ ቁርጥ ሌዕላአ ካህሌድን አስመስሏቸዋል። (AK 47) ክላሽስኮብ ይዘው ፎቶ ተነሰተው በኢቲቪ ባለመቅረባቸው ጅግንነታቸው አልታወቀም።አፈሩን ገለባ ያድርግላቸውና ባለቤታቸው ቢሆኑ የአርጀቲናዊን ማርክሲስት ቼ ኮቬራ (Che Guevara) መለያው የሆነችውን ቆብ ደፋ ያደርጉ ነበር። ይህ ከውጪ የተጨለፈ የትግል ስልት ‘የትግራይ ሕዝብ ነፃነት ግንባር’ (ሕውሃትን) ፈጥሮልናል። በቅርቡ የድርጅቱ መስራች አቦ ሰባት ነጋም እንደነገሩን ትግራይን ለማስገንጠል ሣይሆን የአማራውንና የኦርቶዶክ ሃይማኖት ተከታዩን የኢትዮጵያ ሕዝብ አከርካሪ ለመስበር መሆኑን ነው።
አስታውሳለሁ! እንዴት እረሳለሁ!! ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም
ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ
በ ሰኔ 6-8 እና በ ህዳር 1-4 2005 (እንዳሮፓ አቆጣጠር) በ በግንቦት 2005 የተካሄደውን ምርጫ ተከትሎ ኢህአዴግ ያወጣውን ሕገ መንግሥት በማመን ባዶ እጃቸውን ወደ
አደባባይ የወጡ ንጹሃን ወንዶች፤ሴቶች፤ሕጻናት ኢትዮጵያዊያን በቅርቡ ሕይወታቸው ባለፈው በመለስ ዜናዊ ቀጥተኛ ትእዛዝና ቁጥጥር ሕይወታቸው በአሰቃቂ ሁኔታ በጥይት ተደብድበው ተገድለዋል። በአቶ መለስ ዜናዊና በፓርላማው ሕጋዊ ሆኖ የተዋቀረው የአጣሪ ኮሚሽን አጣርቶ እንደዘገበው እውነታ፤ “ባዶ እጃቸውን በሕገ መንግሥቱ ላይ በጸደቀው መብታቸው መሰረት ወደ አደባባይ ከወጡትና ሰላማዊ ሰልፍ በማካሄድ ላይ ከነበሩት መሃል 193ቱ፤ እና እንዲሁም በመንግሥት ወህኒ ቤት ታስረው ባሉት በርካታዎች ላይ ከፖሊስ በተተኮሰ ጥይት ሕይወታቸው አልፏል 763ም ቁስለኛ ሆነዋል፡፡ አጣሪ ኮሚሽኑ ሁኔታውን በአግባቡና ከወገንተኛነት ነጻ በሆነ መንፈስ በማጣራት የንጹሃኑ ደም አለ አግባብ መፍሰሱን ሕይወታቸውም መቀጠፉን ዘግቧል፡፡ ገዢው መንግሥትና የገዢው መንግሥት መገናኛ ብዙሃን፤ እንዲሁም ወንጀሉን የፈጸሙት ፖሊሶችና ሌሎች የጦሩ አባላት የሰነዘሩትን ክስ ኮሚሽኑ በማጣራት ሂደቱ ጨርሶ ተአማኒነት የሌለው ፈጠራ ነው ብሎ አጣጥሎታል፡፡ በአጣሪው ዘገባ መሰረት “በሰላማዊ ሰልፈኞቹ በንብረት ላይ የደረሰ አንዳችም ጥፋት አለመኖሩን አረጋግጧል፡፡ አንድም ሰልፈኛ ሽጉጥም ሆነ ቦምብና ሌላም መሳርያ የያዘ አልነበረም፡፡ ከመንግሥት ታጣቂ ሃይሎችም የተተኮሱት ጥይቶች ሰልፈኛውን አስፈራርቶ ለመበተን የተቃጡ ሳይሆኑ በማነጣጠር ለመግደል ሆን ተብለው መተኮሳቸውን የሚያሳየው ሟቾችና ቁስለኞች የተመቱት ደረታቸውንና ጭንቅላታቸውን መሆኑ ነው፡፡”
Wednesday, 21 November 2012
መንግስት ጋዜጠኛው የሰራው የዜና ዘገባ ያለርሱ ፈቃድ ተቆራርጦ በቴሌቭዥን መቅረቡን አስታወቀ
ህዳር ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:- የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ባልደረባ የሆነው ጋዜጠኛ አዲሱ መሸሻ በጠ/ሚኒስትሩ ጽ/ቤት ጥቅምት 23 ቀን 2005 ዓ.ም የተካሄደውንና ከፍተኛ ባለሥልጣናት የተሳተፉበት ውይይት አስመልክቶ በስፍራው በመገኘት ያጠናቀረው ፕሮግራም ያለአግባብ ተለውጦ እና ተቆራርጦ ለሕዝብ እንዲቀርብ መደረጉን አስታወቀ።
ሰንደቅ ጋዜጣ ይህንኑ አስመልክቶ ዛሬ እንደዘገበው፣ ጋዜጠኛ አዲሱ መንገሻ በዋናነት በመልካም አስተዳደር፣ በተጠያቂነት እና በሙስና ችግሮች ላይ ያተኮረውን ይህንኑ የስብሰባ ውሎ እንዲዘግብ ተመድቦ፣ ይህንኑ ውይይት በተመለከተ ከስድስት ደቂቃ በላይ የፈጀ የዜና ዘገባ ቢሰራም፣ ባላወቀው ምክኒያት እርሱ ያጠናቀረው ዜና ወደ ጎን ተትቶ፣ በስብሰባው ላይ በአካል ባልተገኘው ሌላ ባልደረባው የተሰራ ዜና ለሚድያ ፍጆታ መዋሉን አስታውቋል። ይኸው በጋዜጠኛ ሳሙዔል ከበደ የተከለሰው ፕሮግራምም ሆን ተብሎ የባለስልጣናቱ ሃሳቦች ተቆራርጠውነት ጥቅምት 27 ቀን 2005 ዓ.ም በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን እንዲተላለፍ መደረጉንም ጋዜጠኛ አዲሱ ገልጿል።
ሰመጉ መንግስት የሚያደርሰውን ዜጎችን የማፈናቀል እርምጃ አወገዘ
ህዳር ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ሰመጉ በዚህ መግለጫው በለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ ስላለው መልካም አስተዳደር ችግሮች፣የመብት ጥሰቶችና የሕዝብ ቅሬታ፣የታሰሩ ሰዎች ዝርዝር ይፋ አድርጓል፡፡ ኢሳት ዜና:- የሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ(ሰመጉ) ወይም በቀድሞው አጠራሩ ኢሰመጉ “ለሕዝብ ጥቅም ሲባል የሚወሰድ ከመሬት የማፈናቀል እርምጃ የዜግነት መብቶችን ማሳጣት የለበትም” በሚል ርዕስ 122ኛውን ልዩ መግለጫ ዛሬ አወጣ፡፡
ከአዲስ አበባ ከተማ በሰሜን ምስራቅ በኩል 21 ኪሎሜትር ርቀት ላይ የምትገኘው የለገጣፎ/ለገዳዲ ከተማ በኦሮሚያ ክልል በፊንፊኔ ልዩ ዞን ሥር በከተማ አስተዳደርነት እንድትመሰረት ተደርጓል፡፡ በአሁን ሰዓት ከተማዋ 2ሺ431 ሄክታር የመሬት ስፋት ያላት ሲሆን የተዋቀረችውም በሁለት ቀበሌዎች ነው፡፡የከተማው ማዘጋጃ ቤት ባሳተመው ወረቀት የህዝብ ብዛቷ ከ 18 ሺ እንደሚበልጥ ቢገልጽም የከተማው አስተዳደር ከንቲባ ቁጥሩ ከአምስት ሺ እንደማይበልጥ መናገራቸውን ሰመጉ በመግለጫው ጠቅሷል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ከሕዝቡ ቁጥር በላቀ መልኩ ወደሃያ ሺ የሚጠጋ ካርታ በከተማዋ ማዘጋጃ ቤት ከሌላ አካባቢ ለመጡ ሰዎች መሰጠቱ የአካባቢው ነዋሪዎች በቅሬታ መልክ ያነሳሉ ብሏል፡፡ ሰመጉ በዚሁ መግለጫው የለገጣፎ/ለገዳዲ ነዋሪ አብዛኛው ህዝብ በግብርና ይተዳደር እንደነበር በማስታወስ አካባቢው ወደከተማነት በመቀየሩ ምክንያት ገበሬው መሬቱን ሲያጣ ሌላ የገቢ ምንጭ ያልተፈጠረለት መሆኑ የመጀመሪያው ችግር መሆኑን ጠቅሷል፡፡
Sunday, 18 November 2012
በመቶ ሺዎች የሚቆጠር የአዲስ አበባና አጎራባች ከተሞች ሙስሊም ወደ ቃላቲ ጉዞውን ቀጥሏል
Seidhusen Hussen say’s
ክርስቲያን ወገኖቻችን ወደ ቃሊቲ ኮሚቲዮቻችንን ሊዘይር ለመጣው ህዝብ ከቤታቸው ውሀ በባልዲ እና በጄሪካን በማውጣት ሙስሊሙን እያጠጡ ይገኛሉ ምንም እንኳን ETV አሸባሪ ናቸው ቢልም ዉሸትነቱ የተረዱ ክርስቲያን ወገኖቻችን ሙስሊሙን በመርዳትና በማገዝ ላይ ናቸዉ አንዴ ተክቢር በሉላቸው!!
***
(ዘግይቶ በደረሰን ዜና መሰረት፣ ወደ ቃሊቲ ውስጥ መገባት ተጀምሯል፡፡)
ወያኔዎች በሙስሊሙ የሀይማኖት ጉዳይ ጣልቃ መግባታቸውን ተከትሎ የተቀሰቀሰው የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ሰላማዊ አመጽ አንደቀጠለ ነው።
አመጹን ለማስቆም እንደተለመደው ወያኔዎች የመረጡት መንገድ መግደል፣ ማሰርና በድብደባ አካላዊ ጉዳት መፈጸም ቢሆንም ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች “ወይ ፍንክች” ብለው ተቃውሟቸውን ዘዴ እየቀያየሩ ቀጥለዋል።
የመብት ተሟጋች ሙስሊሞች በሶሻል ሚድያ መረብ እየገለጹት እንዳለው ከሆነ በአሁኑ ሰዓት በሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች በቃሊቲው ማጎሪያ ፊት ለፊት እየተሰባሰቡ ነው። ረፋዱ ላይ የሙስሊሞቹ ቁጥር እጅግ ሊጨምር እንደሚችል ይገመታል። ሙስሊሞቹ ወደ ቃሊት ማጎርያ እየተመሙ ያሉት የታሰሩ መሪዎቻቸውን ብርታት ለመስጠትና ለአሳሪዎቻቸው (ወያኔዎች) ደግሞ በትግላቸው እንደሚገፉበት ለማሳሰብ ነው።
THE IMMENSE SUFFERING OF ETHIOPIAN REFUGEES IN LIBYA
November 15/2012
THE IMMENSE SUFFERING OF ETHIOPIAN REFUGEES IN LIBYA
Khadafy is gone but Ethiopian refugees and workers in Libya are being imprisoned, held in containers, tortured, raped and even killed by racist Libyan police, officials and extremists. If Khadafy’s daughter in law burnt a maid’s body with hot water others like her are doing worse things especially to Ethiopian women in Libya. Tripoli, Benghazi and El Beida are mentioned as examples of places where Ethiopians and other Africans are subjected to inhumane treatment.
SOCEPP has written a number of letters to the new Libyan authorities to respect the rights of Ethiopians and all African migrant workers and refugees but it has received no reply whatsoever. SOCEPP has received the report that hundreds of Ethiopians are detained in containers in the Libyan desert and extorted to bring money from their relatives to get a release. The suffering of Ethiopian women is particularly socking while latest reports indicate that young Ethiopian men have been gang raped in both Tripoli and Benghazi and vilified for their Christian faith.
SOCEPP is continuing to call on the new Libyan authorities to stop this criminal action and inhumane treatment and has called on the allies of the new regime to call for the respect of human rights. SOCEPP calls on Ethiopians in the Diaspora to address protest letters to the Libyan authorities and to stage demonstrations outside Libyan embassies and consulates.
Friday, 16 November 2012
“ጥቁሩ ሰው” ይናገራል!
November 16, 2012 10:49 am
“ጥቁሩ ሰው” ይሉታል። ኢትዮጵያዊያን ለሚያሽከረከራት አስፈሪ ፈተና መፍትሄው ሰብአዊነትን ማስቀደም ብቻ ነው የሚል የጸና እምነት አለው። “ከጎሳ በፊት ሰብዓዊነት” በሚል መሪ ዓላማ ከሚመስሉት ጋር በመሆን ድርጅት አቋቁሞ መሥራት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ባከናወናቸው ሥራዎች ከፍተኛ እርካታ እንደሚሰማው ያምናል። ኢትዮጵያዊያን ችግር ደርሶባቸዋል በሚባልበት ሁሉ ቀድሞ ደራሽ እንደሆነ ብዙዎች ይመሰክሩለታል። በዚህና በሰብዓዊ መብት ጉዳይ በሰራቸው ስራዎቹ ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ ደጋፊዎችና አድናቂዎች ለማፍራት ቢችልም “ከጀርባው ድብቅ ዓላማና አጀንዳ አለው፣ ብቻውን ይሮጣል” የሚሉትን ጨምሮ በግል አቋሞቹ ዙሪያ ነቀፌታ የሚሰነዝሩበትም አሉ።
የወደፊት ዕቅዱና የሚነቅፉት እንደሚሉት መቼ ፖለቲካ ፓርቲ መስርቶ ይፋ ያደርጋል? በሚሉትና በተመሳሳይ ጉዳዮች ዙሪያ ኦባንግ ሜቶ ከጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ጋር ቃለ ምልልስ አድርጓል። ኦባንግ ሜቶ (ጥቁሩ ሰው) የአንደኛ ደረጃ ትምህርቱን ጋምቤላ ተማረ። ከዚያም ሁለተኛና የዩኒቨርሲቲ ትምህርቱን ካናዳ ተከታትሎዋል። በመጀመሪያ የጋምቤላ ልማት ኤጀንሲ (GDA) የሚባል ድርጅት አቋቁሞ በርካታ ተግባራትን እያከናወነ ነበር፡፡በኋላም በጋምቤላ የዛሬ 9ዓመት አካባቢ ከ400 በላይ አኙዋኮች ሲጨፈጨፉ ህይወቱ ተቀየረ፡፡ ሁኔታው በአመለካከቱ ላይ ብቻ ሳይሆን በግል ህይወቱ ላይ ከፍተኛ ለውጥ አመጣ፡፡ ሁሉንም ትቶ ድምጽ አልባ ለሆኑት ድምጽ ለመሆን የአኙዋክ የፍትሕ ምክርቤትን በማቋቋምና በኃላፊነት በመሥራት የመለስ አገዛዝን እና የወንጀሉን ተዋናዮች በዓለምአቀፍ ፍርድርቤት ሊያስከስስ የሚችል ተግባር አከናወነ፡፡ ሆኖም ችግሩ የአኙዋክ ብቻ ሳይሆን የመላው ኢትዮጵያ መሆኑን በጥልቅ ከተረዳ በኋላ ኢትዮጵያ ነጻ ሳትወጣ አኙዋክ ብቻ ወይም ሌላው እንዲሁ በግሉ ነጻ ቢወጣ ችግሩ ፈጽሞ ሊቃለል እንደማይችል በተረዳበት ጊዜ ትግሉን ቀየረ፡፡ አዲሲቷ ኢትዮጵያ ብትመሠረት የሁላችንም ችግር መፍትሔ እንደሚያገኝ በማስተዋል ከበርካታ ኢትዮጵያውያን ጋር በመሆን ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄን (አኢጋን) (http://www.solidaritymovement.org/) በማቋቋም የትግሉን መስመር አሰፋው፡፡ “ሁላችንም ነጻ ካልወጣን ማንም ብቻውን ነጻ መሆን አይችልም” የሚለውን መሪ መፈክር በማንገብ “ከጎሣ ይልቅ ለሰብዓዊነት ቅድሚያ” እንዲሰጥ በመታገል ዓመታትን አስቆጥሯል – ኦባንግ ሜቶ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር!
Thursday, 15 November 2012
የፌድራል ፖሊሶች ህፃን በናትዋ ጀርባ ላይ እንዳለች በዱላ መተው መግደላቸው ተዘገበ
ህዳር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በሀና ማሪያም አካባቢ መንግስት የሚያደርገውን መኖሪያ ቤቶችን የማፍረስ ዘመቻ አስፈፃሚ የሆኑ የፌድራል ፖሊሶች ህፃን በናትዋ ጀርባ ላይ እንዳለች በዱላ መተው መግደላቸው ተዘገበ።
ከ30.000 ሺህ በላይ አባ ወራ በተፈናቀለበት የንፋስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 መኖሪያ ቤቶችን የማፍረስ ዘመቻ ትላንት በናትዋ ጀርባ እንዳለች በፌድራል ፖሊስ ተመታ ከሞተችው ህፃን ጋር የሞቱት ቁጥር አራት ደርሰዋል።
መጠለያም ሆነ ተለዋጭ ቤት ሳያገኙ ቤታቸውን ከነንብረታቸው በግሬደር እየተደረመሰ ያለው የወረዳ 01 ነዋሪዎች ለብርድና ለሀሩር ከመዳረጋችን አልፎ በፌድራል ፖሊሶች የሚደርስባቸው ድብደባ ፣ እስራትና ግድያ ባስቸኮይ እንዲቆምላቸው ጥሪ አድርገዋል ።
በፌድራል ፖሊስ ወደ ተገደለችው ህፃን መጠለያ ለቅሶ ለመድረስ እንኮን አልተፈቀደልንም ያሉ ነዋሪዎች መንግስት የበደል በደል እየፈፀመብን ነው ሲሉ ምሬታቸውን ገልፀዋል።
በንፋስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ከሳምንት በላይ በዘለቀው ቤቶችን የማፍረስ ዘመቻ ከ30 ሺህ በላይ ቤቶች ፈርሰው ከ100 ሺህ በላይ ሰዎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በሜዳ ላይ ወድቀው እንደሚገኙ ካአካባቢው ሰዎች የሚደርሰን መረጃ ያመለክታል።
በዚህ የማፍረስ ዘመቻ ቤተክርስቲያንና መስኪድ ሳይቀር መፍረሳቸውንም መዘገባችን ይታወሳል።
Wednesday, 14 November 2012
«ናፍቆት እኔ ብሞትም አንተ ንብረቴን ታስመልሳለህ››
እስክንድር ነጋ
ከነገ በስቲያ (ማክሰኞ ህዳር አራት) በከፍተኛው ፍርድ ቤት ሶስተኛ ወንጀል ችሎት የእስክንድር ነጋን ንብረት ለመውረስ ይሰየማል፡፡ በትላንትናው ዕለት የክስ ቻርጅና መንግስት እወርሳቸዋለሁ ያላቸውን የእስክንድር ሁለት ቤቶች ካርታ የተያያዙበት መጥሪያ ደርሶታል፡፡ (በነገራችን ላይ መንግስት ሊወስዳቸው ከተዘጋጁት ቤቶች አንዱ በእናቱ ስም ያለ ሲሆን የዛሬ ዓመት አካባቢ ባለቤቱ ጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል የቤቱን ስም ለማዞር ፈልጋ ‹‹ካርታው የለም›› በሚል አንዴ ቀበሌ፣ ሌላ ጊዜ ክፍለ ከተማ፣ ቀጥሎ አዲስ አበባ መስተዳደር ስትመላለስ ከርማ ሊገኝ ስላልቻለ ሰልችቷት ትታው ነበር፡፡
ትላንት ግን ዓቃቢ ህግ ከክስ ቻርጁ ጋር አያይዞ አቅርቦታል፤ እናም ምንአልባት ያን ግዜ ‹‹ካርታው የለም›› የተባለው ሆነ ተብሎ ተደብቆ ሊሆን ይችላል)
የሆነ ሆኖ እስክንድር ማክሰኞ ፍርድ ቤት ቀርቦ ‹‹ቤቴን አትውረሱብኝ›› ብሎ ስለማይከራከር ‹‹በዕለቱ ፍርድ ቤት መሄድ አልፈልግም›› ሲል ለማረሚያ ቤቱ ኃላፊዎች ጥያቄ ያቀረበ ቢሆንም ማረሚያ ቤቱ ግን ‹‹የግድ ማቅረብ ስላለብን ይዘንህ እንሄዳለን›› የሚል ምላሽ ሰጥተውታል፡፡
እናም እስክንድር በዕለቱ ፍርድ ቤት ሲቀርብ ምንም አይነት ምላሽ ላለመስጠት ወስኗል፡፡ ባለቤቱም ‹‹የሚስትነቴን ድርሻ አትውረሱብኝ›› ብላ አትከራከርም፡፡ ፍርድ ቤቱ የፈለገውን ይወስን የሚል አቋም ነው ያላት፡፡ በዛሬው ዕለት ሊጠይቀው ቃሊቲ የመጣውን የሰባት ዓመቱን ህፃን ልጁን ጠባቂ ፖሊሶች እየሰሙት ድምፁን ከፍ አድርጎ ‹‹ናፍቆት እኔ ብሞትም አንተ ንብረቴን ታስመልሳለህ፡፡ አይዞህ! ስርዓት ተቀያየሪ ነው፤ ንጉሱ የወረሱት በደርግ ተመልሷል፤ ደርግ የወረሰው በኢህአዴግ ጊዜ ተመልሷል፤ ኢህአዴግ የወረሰው ደግሞ ኢህአዴግ ሲወድቅ መመለሱ አይቀሬ ነው›› ብሎታል፡፡ በ1993 ዓ.ም ግምቱ ከ7 ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ የእስክንድር እናት ቤት በግፍ እንደተወረሰ ይታወቃል፡፡
እስቲ አሁ እንኳን ምንአለበት ትንሽ እንደ ሰው አስባችሁ ልጁን የሚያሳድግበትን ንብረት ብትተውለት? …ዛሬም በትላንቱ መንገድ፣ ዛሬም በመለስ ጫማ፣ ዛሬም በመለስ ራዕይ… አቤት! እንዴት ልብ የሚያደማ ነገር ነው! ይህ ምን አይነት ጭካኔ ነው?
Tuesday, 13 November 2012
በደራ ወረዳ አንዲት ሴት የባሉዋን ብልት በአደባባይ በገመድ እንድትጎትትና እንድትስም ተደረገ
ህዳር 5 (አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በኦሮሚያ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን በደራ ወረዳ በገብሮ ቀበሌ የወረዳው የአስተዳደርና ፍትህ ሀላፊ የቅርብ ዘመድ የሆነ አቶ አየለ የተባለ ከሌሎች ሁለት ግብረ አበር ፖሊሶች ጋር በመሆን በቀበሌው የሚኖርን አንድን ግለሰብ መሳሪያ ደብቀሀል በሚል ሰበብ ግለሰቡንና ባለቤታቸውን ልብሳቸውን በማስወለቅ እርቃናቸውን እንዲታሰሩ አድርገዋል።
የሚሊሺያ ዘርፍ ሀላፊውና ፖሊሶች በመቀጠልም ባልየው ብልቱ በገመድ እንዲታሰር ካስደረጉ በሁዋላ ህዝብ በተሰበሰበበት አደባባይ እርቃኑዋን የሆነቸው ባለቤቱ ብልቱን በገመድ እንድትስብ እንዲሁም ብልቱን እንድትስም አስደርገዋል። በእርግጫ በመመታቱዋም የስድስት ወር ልጅ አስወርዳለች። በድርጊቱ አልሳቃችሁም የተባሉትም ተደብድበዋል።
ድርጊቱ ይፋ የሆነው አቶ ይመሩ በተባሉ የቀበሌው የጸጥታ ዘርፍ ሀላፊ ሲሆን፣ ድርጊቱንም ይፋ ያደረጉት የዞኑና የወረዳው ባለስልጣናት በተሰበሰቡበት ወቅት ነው።
በአቡዳቢ አንድ ኢትዮጲያዊት የቤት ሰራተኛ በአሰሪዋ ተደብደባና የፈላ ውሃ ተደፍቶባት ተገደለች
ህዳር 5 (አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ለአስር ቀናት በሽቦ ታስራ በአሰሪዋ ስትደበደብ የቆየችው ኢትዮጲያዊ የቤት ሰራተኛ ስቃዩማ መከራው በዝቶባት ግርፋትና ጭካኔው ጠንክሮባት በታሰረችበት መሞቷን የተመለከተው ያሰሪዋ ልጅ ለፕሊስ ጥቆማ መስጠቱና ሞቷ መታወቁን ዘገባው አመልክቷል።
የአቡዳቢ ፍርድ ቤትን ዋቢ ያደረገው ይህ ዘገባ ጉዳዩ ፍ/ቤት ቀርባ ኢትዩጲያዊቷን ሰራተኛ አስራ መግረፏን ያመነች ሲሆን የፈላ ሲሆን የፈላ ውሃ እላዩ ላይ መድፋቷን ግን ክዳለች።
ለፖሊስ ቃላቸውን የሰጡትን የሰጡት የገዳዩ ልጆች እናታቸው ሰራተኛዋን ኢትዮጲያዊ በየቀኑ ታሰቃያትና ትገርፋት እንደነበር ተናግረዋል።
ለፍርድ ቤቱ የቀረበ የሃኪም ማሰረጃ እንዳመለከተው የኢትዮጲያዊቷ ሞት በደረሰባት ከፍተኛ ድብደባ በአጠቃላይ በሰውነቷ ላይ ያስከተለው ቁሰለት መመርቀዝ በማስከተሉ መሆኑን ከማብራራቱ በላይ በአይኗ ላይ የደረሰ ድብደባም አይኗ ውስጥ መድማትን ማስከተሉን አመልክቷል።
ኢትዮጲያዊቷ የቤት ሰራተኛ ሰነፍ በመሆኗ ደበደብኳት የምትለው ተከሳሽ ሆን ብዬ ለመግደል ያደረኩት አልነበረም ስትል ልፍርድ ቤቱ ገልጻለች።
የሟች ኢትዮጲያዊ ተከላካይ ጠበቃ ልጆቹ መጥተው የምስክርነት ቃላቸውን እንዲሰጡ ፍ/ቤት ለጠየቀው ጥያቄ የገዳዩ አውንታና እንቢታ ባይሰማም ጠበቃው ለፖሊስ የሰጡት ምስክርነት በቂ መሆኑን በመግለጽ እንደማይፈልጓቸው ገልፀዋል።
“ወይ መዓልቲ” አለ ያገሬ ሰው!
- 464
- SHAREBAR
ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ሰብአዊ መብት ኮሚሽን አባል ሀገር ሆና ተመረጠች።
የትኛዋ ኢትዮጵያ!? የትኛው ሰብአዊ መብት!? የትኛው የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን!?
እኔ የምለው ኢትዮጵያዊው የዩልኝታ ባህላችን ያለው ህብረተሰቡ ዘንድ ብቻ መሆኑ በጣም አሳሳቢ ችግር አይመስላችሁም? እንዴ መንግስት እኮ ይሉኝታ ቢኖረው ኖሮ “ተመድ የሰባዊ መብት ኮሚሽን አባል አድርጌ መርጨሀለሁ!” ሲለው… “አረ በህግ አምላክ እኔ አልሆናችሁም ሀገር ተሳስታችሁ ነው! ወይ ደግሞ ባታውቁኝ ነው የመረጣችሁኝ…!” ማለት ነበረበት። ነገር ግን መንግስቴ “ምን ይሉኝ” ያልፈጠረበት ነውና አሜን ብሎ መቀበሉ ሲገርመን፤ ጭራሽ በአደባባይ “እንዲህ ነን እኛ ሰብአዊ መብት ጠባቂዎች” ተብሎ ተነገረን!ኢቲቪ በጠቅላይ ሚኒስትሩ አስታማሚ አምባሳደር ዲና ሙፍቲን አማካይነት፤ “ድሮውንም እኛ ለሰብአዊ መብት ጥበቃ ዘብ የቆምን ሰዎች ነን!” ብሎናል።
አቶ ዲና በሚወዱት ይማሉልኝ የሚናገሩት የምርዎትን ነው!? ከማሉልኝ ዛሬ ነገ ሳልል ሀገሬ እመጣለሁ። እኔ ብቻ ሳልሆን ሁሉም የሰብአዊ መብት ጥሰቱን ፈርቶ የወጣው ኢትዮጵያዊ ሁሉ “ምን አለኝ ሀገሬ” (“ለ“ን አጥብቆ) ዘፍኖ እንደወጣው ሁሉ፤ “ምን አለኝ ሀገሬ” በሚል “ለ”ን አላልቶ ዘፍኖ ይመለሳል። ግን እርግጠኛ ነኝ በሚወዱት አይምልሉንም! ለመሆኑ የሚወዱትስ አለ…!? ወይስ ነፍስ ይማር እንበልልዎ!?
አቶ ዲና በሚወዱት ይማሉልኝ የሚናገሩት የምርዎትን ነው!? ከማሉልኝ ዛሬ ነገ ሳልል ሀገሬ እመጣለሁ። እኔ ብቻ ሳልሆን ሁሉም የሰብአዊ መብት ጥሰቱን ፈርቶ የወጣው ኢትዮጵያዊ ሁሉ “ምን አለኝ ሀገሬ” (“ለ“ን አጥብቆ) ዘፍኖ እንደወጣው ሁሉ፤ “ምን አለኝ ሀገሬ” በሚል “ለ”ን አላልቶ ዘፍኖ ይመለሳል። ግን እርግጠኛ ነኝ በሚወዱት አይምልሉንም! ለመሆኑ የሚወዱትስ አለ…!? ወይስ ነፍስ ይማር እንበልልዎ!?
የምር ግን ሰብአዊ መብት ማለት ምን ማለት ነበረ!?
“ወይ መዓልቲ” አለ ያገሬ ሰው!
Monday, 12 November 2012
ወ/ሮ አዜብ የባለቤታቸውን ምስጢር ይፋ አደረጉ
አማራ፣ ደቡብና ኦሮሚያ እንቅልፍ ውስጥ ናቸው
“የሙስና መርከብ” በሚል ስያሜ የሚጠሩት አሉ። ከተቋቋመ ጀምሮ አንድም ቀን ስለንብረቱ መጠን ለህዝብ ተገልጾ አያውቅም። ከአገሪቱ ባንኮች ትልቁ ተበዳሪ ነው።የወጋጋን ባንክ ትልቁ ባለድርሻ ነው። በአንዳንድ ከፍተኛ የንግድ ተቋማት ውስጥ የንግድ ሽርክና እንዳለው ይታማል። የወርቅ ማዕድን ፍለጋው ሰምሮለታል። የግል አስመጪዎችን በመፈታተን አነካክቶ ጥሏቸዋል። አገሪቱ ላይ የገነባው የንግድ ኢምፓየር በበርካቶች ዘንድ ቅሬታ ፈጥሯል። በሌሎች ክልሎች በተመሳሳይ የተቋቋሙትን የንግድ ተቋማት በመደፍጠጥ በፖለቲካው የበላይነቱ ሳቢያ ልዩ ተጠቃሚ በመሆኑ አይወደድም። ይህ ታላቅ የህወሃት የንግድ ግዛት ኤፈርት ነው።
የትግራይ ህዝብ “ያንተ ነው” ስለሚባለው ታላቅ የንግድ ኢምፓየር የሚያውቀው ነገር እምብዛም የለም። አስራ ሶስት ሰፋፊና ስትራቴጂክ ኩባንያዎችን ያቀፈው ኤፈርት በቅርቡ የእህት ኩባንያዎቹን ቁጥር እንደሚጨምር ምልክቶች አሉ። ኤፈርት ትግራይን የኢንዱስትሪ ማዕከል ለማድረግ እንደሚሰራ በስፋት ይነገርበታል። ከዚሁ ከሚታማበት ጉዳይ ጋር በተያያዘ ይሁን በሌላ ወ/ሮ አዜብ በድንገት ይፋ ያደረጉት ምስጢር አነጋጋሪ ሆኗል።
Friday, 9 November 2012
በላፍቶ ክፍለ ከተማ ከ17 ሺ በላይ አባወራዎች ሜዳ ላይ ተበተኑ ሁለት ህጻናትም በፖሊስ ዱላ ተገደሉ
ኢሳት ዜና:-በአዲስ አበባ ልዩ ስሙ ላፍቶ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ቤታቸው የፈረሰባቸው ከ17 ሺ በላይ በላይ አባዎራዎች የድረሱልን ጥሪ እያሰሙ ነው። የአትዮጵያን ሰንደቃላማና የአቶ መለስ ዜናዊ ፎጥቅምት ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ከ400 በላይ ነዋሪዎች ዛሬ በአንድ ላይ በመሆን ወደ ጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ ሲያመሩ፣ የጠቅላይ ሚኒስትር
ጽህፈት ቤት ወደ አዲስ አበባ መስተዳደር እንዲሄዱ አዞዋቸዋል። አዲስ አበባ መስተዳድርም ሶስት ሰዎች ተወክለው እንዲገ
ቡ ፈቅዷል። ይሁን እንጅ ከንቲባው አልገቡም በሚል ስቱዲዮ እስከገባንበት ጊዜ ድረስ መልስ አልተሰጣቸውም።
ምተዋል። የወላጆቻቸውን ቤት መፍረስ የተቃ ለኢሳት የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው ከንቲባው ሰሞኑን ወደ ስራ ሲገቡና ሲወጡ አልታዩም።ቶግራፎችን በመያዝ ወደ ጠቅላይ ሚኒስትር ቢ
ወሙ ሁለት ህጻናት በፖሊስ ዱላ ተደብድበው መገደላቸውን፣ በዛሬው እለት ደግሞ ቤቶች በሚፈርሱበት ቦታ ላይ አንዲት እናት የኤሌክትሪክ ምሰሶ ወድቆባቸው መገደላቸውን የአይን እማኞች ገልጸዋል።ሮ ቢያመሩም፣ ሰንደቃላማውንም ፎቶግራፉንም ተቀ
ምተዋል። የወላጆቻቸውን ቤት መፍረስ የተቃ ለኢሳት የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው ከንቲባው ሰሞኑን ወደ ስራ ሲገቡና ሲወጡ አልታዩም።ቶግራፎችን በመያዝ ወደ ጠቅላይ ሚኒስትር ቢ
ወሙ ሁለት ህጻናት በፖሊስ ዱላ ተደብድበው መገደላቸውን፣ በዛሬው እለት ደግሞ ቤቶች በሚፈርሱበት ቦታ ላይ አንዲት እናት የኤሌክትሪክ ምሰሶ ወድቆባቸው መገደላቸውን የአይን እማኞች ገልጸዋል።ሮ ቢያመሩም፣ ሰንደቃላማውንም ፎቶግራፉንም ተቀ
በመስተዳድሩ ዙሪያ የነበረውን ተቃውሞ እንደሚከተለው አጠናክረነዋል ፤፡ የመስተዳድሩን ባለስልጣናትን ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።
Monday, 5 November 2012
ከሳምንቱ አጫጭር ዜናዎች
የአዲግራት ወህኒ ቤት ተደረመሰ
በትግራይ ክልል ካሉት እስር ቤቶች መካከል ከ1‚300 በላይ የሚሆኑ የሕግ እስረኞችን የያዘው የአዲግራት ወህኒ ቤት ባለፈው ረቡዕ ተደርምሶ 14 እስረኞች ሲሞቱ፣ ከ35 በላይ ደግሞ በከባድ ሁኔታ መጎዳታቸውን ሪፖርተር ምንጮች እንደነገሩት ጠቅሶ አስታወቀ። እስር ቤቱ በምን ምክንያት እንደተደረመሰ ያልገለጸው ሪፖርተር እስረኞቹን ለማትረፍ ሦስት ሎደሮችና በርካታ ወታደሮች ሲረባረቡ ማየታቸውን አመልክቷል።
አደጋው ቀን ረፋድ ላይ መድረሱ በጀ እንጂ አደጋው የከፋ ሊሆን እንደሚችል ተዘግቧል። ተረፉ የተባሉት 35 ሰዎች ክፉኛ በመጎዳታቸው አዲግራት ሆስፒታል ተኝተዋል። ህይወታቸው ያለፈው 14 እስረኞች ግን ከፍርስራሹ መቀበራቸውን የሪፖርተር ዘገባ ያስረዳል። የመከላከያ ሰራዊት አባላት ያደረጉት በዶዘር የተደገፈ ርብበርብ በህይወት የተረፉትን ነፍስ እንደታደገ ተጠቁሟል። አደጋው መድረሱን የትግራይ ክልል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት አስተዳደር ማመኑን ጋዜጣው አስታውቋል።
በሌላ በኩል ይህንኑ ዜና በአዲግራት እስር ቤት የደረሰው አደጋ ከፈንጂ ጋር በተያያዘ ጥቃትና አደጋ እንደሆነ የተለያዩ ድረ ገጾች ዘግበዋል። በዘገባውም መሠረት የኢትዮጵያ አንድነት፣ ነጻነት ኃይል የተሰኘው ቡድን ስለደረሰው ጥቃት ኃላፊነቱን ስለመውሰዱ አብሮ ተዘግቧል፡፡ የኢትዮሚዲያ ድረገጽ ከቡድኑ ቃልአቀባይ ጋር በስልክ መገናኘቱንና በቃልአቀባዩ መሠረት እስረኞቹ በ1997 የምርጫ ወቅት ከጎንደር፣ ጎጃም፣ አዲስአበባ ሌሎች ቦታዎች ተጥዘው የታሰሩ መሆናቸውን ዘግቧል፡፡ የታሰሩና የአደጋውን ትክክለኛ መንስዔ በተመለከተ ከመንግስት የተባለ ነገር የለም።
Sunday, 4 November 2012
ኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ የወጣት ክንፍ ድርጅት (ኢሕአፓ ወክንድ) የአውሮፓ ክፍል Ethiopian people's Revolutionary party Youth League (EPRP YL) Europe Section
ጥቅምት 24, 2005 ዓ.ም
ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን አምርሮ የሚጠላው ጠባቡና ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ በሙስሊም ኢትዮጵያውያን ላይ
የሚያደርገውን የመብትረገጣ አፈና ግድያ ማስፈራራትና ወከባ ኢሕአፓ ወክንድ የአውሮፓ ክፍል በጥብቅ ያወግዛል።
የኢትዮጵያ ህዝብ ላለፉት በርካታታ ዓመታት ሀገሩ ውስጥ ሰብዓዊና ዴሞክራሲየዊ መብቶቹ የተከበሩበት ሥርአት ይሰፍን ዘንድ ብዙ ታግሏል። ትግሉም የብዙ እልፍ አእላፍ ታጋዮች ደም ተገብሮበታል። አጥንት ተከስክሶበታል። ህዝባችን ግን ያን ሁሉ መስዋእትነት የተከፈለለትን ያህል የተስፋ ጭላንጭል ለማየት አልታደለም።
እስካሁን በታሪካችን የምናውቀው በብልጠትም ይሁን በጠብመንጃ ኃይል የተለያዩ መንግስታት በ አገራችን ስልጣን ሲይዙ ነው። ህዝብ በማያውቀው መንገድ ስልጣን ላይ የወጡትን አገዛዞች ፍላጎታቸውንና ዓላማቸውን በህዝቡ ላይ ሲጭኑና ህዝቡንም እንደፈለጉት ሲረግጡትና ሲገዙት ዘመናት አሳልፈናል። የ 1966 ቱ የየካቲት ህዝባዊ አብዩት የአጼውን ሥርዓት ከሥሩ መንግለው ከጣሉት አንዱ የእምነት ነጻነትና የሃይማኖት እኩልነት ይከበር ጥያቄ እንደነበር ማስታወሱ ግድ ይላል:: በዚያ የህዝብ ብሶት በወለደው የለውጥ እንቅስቃሤ ብዙዎች ቤዛ ሆነው ሥርዓቱ ቢገረሰስም፤ ህዝቡ የታገለለት፣ የወደቀለት፣ የሞተለትና የተሰዋለት ድል ባለቤት እንዳይሆን በወታደራዊ አምባገነን መኰንኖች (ደርግ) ድሉን ተነጥቋል::
“አትነሳም ወይ?!”
(አናንያ ሶሪ)
“አትነሳም ወይ” በሚል በሰማያዊ ፓርቲ ድረገጽ አናንያ ሶሪ ባስነበቡት ጽሁፍ ስለ “መነሳት” የተለያዩ ሃሳቦችን በማንሳት እይታቸውን አስፍረዋል። መነሳትን ከህይወት፣ ከህይወት ክንውኖች፣ ከህይወት ስንብትና ከመቃብር እስከመውጣት ባሉ ጉዳዮች በማዋዛት አሳይተዋል።በተለይም “አትነሳም ወይ” በማለት ኢህአዴግንም ፈክረውለታል። ጎልጉል በቀጥታ ከጽሁፉ የወሰደውን በማቃመስ ዋናውን ጽሁፍ በድረገጹ ላይ ታነቡ ዘንድ ይጋብዛል።
“ … አትነሳም ወይ?! ከእንቅልፍ ነው? ከሞት ነው? ከሞት ከበረታ ድንዛዜ ነው? ፎቶ ነው? ራጂ ነው? ክርስትና ነው? … በክፉ ነው የምትነሳው? በደግ ነው የምትነሳው? በትንሳዔ-ሙታን ነው የምትነሳው? በምንድነው የምትነሳው? ለምንድነው የምትነሳው? ወዴት ነው የምትነሳው? መቼ ነው የምትነሳው? እንዴትስ ነው የምትነሳው?…
“… መቼም ኢትዮጵያውያን በባህላችን ብልፅግና የተነሳ አንድ ትልቅ ሰው ወይም አረጋዊ ከውጭ መጥቶ ወደቤት ውስጥ ሲገባ ከተቀመጥንበት ብድግ ብለን ተነስተን “ኖር! ኖር!” እንላለን፡፡ ምላሹም “በእግዜር!” አሊያም “እረ በልጆቻችን!” ይሆናል፡፡ ታዲያ አንተ ወንድሜስ ለእንዲህ ዓይነቱ የትልቅ ሰው አክብሮት የሚገባውን መነሳት ነው የምትነሳው? ማለቴ-ክብር ለሚገባው ክብርን ለመስጠት፡፡ አሊያስ ከወደቅህበት ረግረግ እና ረመጥ ውስጥ ነው የምትነሳው? …
መብት ጠያቂዎችን በአሸባሪነት መፈረጅ የሕግ የበላይነትን ይንዳል!
ድምፃችን ይሰማ
በዴሞክራሲያዊ ስርአት ውስጥ ዜጎች መሪያቸውን ከመምረጥ ባለፈ በአመራሩ ላይ የሚከሰቱ ችግሮችን የመከታተልና የማሳወቅ፣ ለመብቶቻቸውም የመታገል ሉአላዊ መብት አላቸው፡፡ የሚደርሱባቸውን አስተዳደራዊ በደሎች በሰላማዊ መንገድ መቃወምና እንዲስተካከልላቸውም አጥብቆ መጠየቅ አሌ ከማይባሉ መሰረታዊ መብቶቻቸው አንዱ ነው፡፡ ይህንን መርህ ህገ መንግስታችን በግልጽ ያጸደቀው መሆኑም ያለጥርጥር ይታወቃል፡፡ ህዝበ ሙስሊሙ ከሀምሌ 2003 ጀምሮ በመንግስትና በመጅሊስ ጥምረት በግድ እየተጫነበት የነበረውን አዲስ አህባሽ የተባለ አንጃ ‹‹አልቀበልም›› በማለት የችግሩ ምንጭ የሆነውን መንግጅሊስን (የመንግሰትና የመጅሊስ ይፋዊ ጥምረት) በመቃወም ያደረገው ትግል ከዚህ የዜጎች ሉአላዊ መብት የመነጨ ነበር፡፡ ይህንንም ከየካቲት 26 በፊት በነበረው ወቅት የመንግስት ባለስልጣናት በግልጽ እውቅና ሲሰጡት ታይተዋል፡፡
ጥያቄው የሚሊዮኖች እንደመሆኑ ሁሉም መንግስትን ሄዶ ማናገር ስለማይችል ከመካከሉ አንደበተ ርቱእና ለህዝቡ አሳቢ የሆኑ ግለሰቦችን በፔቲሽን የወከለው ህዝበ ሙስሊም ‹‹ጥያቄያችንን መመለስ ወደሚችለው መንግስት አድርሱልን!›› ከሚል ተማጽኖ ጋር ሶስት ጥያቄዎችን አስይዞ ወደመንግስት ላካቸው – ዛሬ በሽብርተኝነት የተከሰሱትን ብርቅዬ መሪዎቻችንን!ተወዳጅ ኮሚቴዎቻችን ዛሬ እንደወንጀል ከመቆጠሩ በፊት ይህንን ከህዝብ የተወከሉበትን የመብት ጥያቄ ይዘው ከከፍተኛ የአገሪቱ ባለስልጣናት ጋር ውይይት ተቀምጠዋል፡፡ የጥያቄዎቹ አቀራረብ ሰላማዊነትም በባለስልጣናቱ አፍ እንዲወደሱ አስችሎ ነበር፡፡
Ethiopia: Government continues to target peaceful Muslim protest movement
AMNESTY INTERNATIONAL
November 03, 2012
The Ethiopian authorities are committing human rights violations in response to the ongoing Muslim protest movement in
the country. Large numbers of protestors have been arrested, many of whom remain in detention. There are also numerous reports of police using excessive force against peaceful demonstrators. Key figures within the movement have been charged with terrorism offences. Most of those arrested and charged appear to have been targeted solely because of their participation in a peaceful protest movement.
Tens of thousands of Muslims have participated in regular peaceful protests throughout 2012, opposing alleged government interference in Islamic affairs. Protestors accuse the government of attempting to impose the teachings of the Al Ahbash sect of Islam on the Muslim community and of interference in elections for the Supreme Council of Islamic Affairs.
Ethiopia’s Constitution prohibits state involvement in religious affairs. The Constitution also contains an expansive provision on the right to peacefully protest, which is routinely flouted by the authorities.
Saturday, 3 November 2012
Thousands of Ethiopian migrants kidnapped, tortured, raped in Yemen
NAIROBI (AlertNet) – Migrants travelling from the Horn of Africa to Yemen in search of a better life are regularly
kidnapped, tortured and raped, according to a newreport by the Regional Mixed Migration Secretariat(RMMS).
At least 230,000 migrants have undertaken this hazardous, often lethal, journey over the last six years and the rate of migration is increasing dramatically. In the first eight months of 2012, over 70,000 African migrants entered Yemen, three quarters of whom were Ethiopian.
Kidnapping has become increasingly common in Yemen, with the majority of respondents who arrived in the last 18 months saying they were held for ransom after disembarking from smugglers boats, said the report from RMMS, working to help migrants in the Horn of Africa and across the Gulf of Aden.
Friday, 2 November 2012
የሃይለማርያም ቃለመጠይቅ በሻዕቢያ የተዘጋጀ?
ከተስፋዬ ገብረአብ
ሰሞኑን ሃይለማርያም ደሳለኝ አንድ አስገራሚ ቃለመጠይቅ ሰጥቶ ነበር። አገር ውስጥ ለሚታተም መፅሄት በሰጠው በዚሁ ቃለመጠይቅ ላይ፣ “ዘላለማዊ ክብር ለመለስ ዜናዊ” በማለቱ
ከቤተሰቡ የደረሰበትን ተቃውሞ ገልፆአል። በርግጥም ሃይለማርያም ልጆቹንና ባለቤቱን ሰብስቦ፣ “ተሳስቼያለሁ።” ብሎ ይቅርታ ጠይቆአል። ይህን እንግዲህ ከመፅሄቱ ላይ ያነበብነው ነው። የሃይለማርያም ሴት ልጅም አባቷን በዚህ መልኩ በማረሟ ታዋቂ ሆና ሰንብታለች። በርግጥም ዘላለማዊ ክብር ለአምላክ እንጂ ለሰው የሚሰጥ አልነበረም።
በዚሁ ቃለመጠይቅ ሃይለማርያም አንዳንድ አፈንጋጭ የሚመስሉ ቃላት አምልጠውታል። ያነበበው ወረቀት ከእሱ እውቅና ውጭ ተዘጋጅቶ መቅረቡን መግለፁ አነጋጋሪ ነበር። ከጀርባ ያሉትን ዘዋሪ ሾፌሮች የሚጠቁም ነበር። መለስን የሚቃወም ከሚመስሉ የሃይሌ የምላስ ወለምታዎች መካከል፣
“እኛ የአይን ቀለም አንመረምርም” ማለቱ የሚጠቀስ ነው።
መለስ የሚታወቀው የአይናችንን ቀለም በመመርመር ነበር። ሃይለማርያም ይህን የአይን ቀለም ምርመራ ካልተከተለ፣ አንድ ትልቅ ለውጥ ነው። የምላስ ወለምታም ከሆነ እናዋለን።” ብዬ በተስፋ በመጠበቅ ላይ ነበርኩ።
Thursday, 1 November 2012
Mr. Hailemariam has already made several mistakes
Is it because of multiple personality?
by MeKonnen H. Birru, PhD*
Don’t lie to each other, for you have stripped off your old sinful nature and all its wicked deeds. Colossians 3:9
Mr. Hailemarim Desalegn, 48, has been prime minister of Ethiopia not more than three months
now but has already made several serious mistakes. I was among the first who wished him good luck within his first few office days but his unchristian and copycat drama make me question his integrity. I pray God will help him.
Mr. Hailemariam is a highly educated man. He has a graduate degree in sanitation engineering. He was President of the Southern Nations, Nationalities, and People’s Region (SNNPR) for five years; then served as Deputy Prime Minister and Foreign Minister of Ethiopia for almost two years. More than that, many claim and witness, including Mr. Hailemariam, that the man is a devout Christian with uncorrupt and respectful solid Christian background. So, how such a strong, educated, dedicated, uncorrupt, and ethical personality becomes full of lies or mistakes? Some say he is a strong Christian with weakness in telling the truth. Is there such personality? If so, can we categorize him as a person with multiple personality? One who accepts tricky political games, lies, purposeful mistakes, and partisans and another personality that regrets, confesses, cries, talks smooth, and believes?
Subscribe to:
Posts (Atom)