ጥቅምት 24, 2005 ዓ.ም
ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን አምርሮ የሚጠላው ጠባቡና ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ በሙስሊም ኢትዮጵያውያን ላይ
የሚያደርገውን የመብትረገጣ አፈና ግድያ ማስፈራራትና ወከባ ኢሕአፓ ወክንድ የአውሮፓ ክፍል በጥብቅ ያወግዛል።
የኢትዮጵያ ህዝብ ላለፉት በርካታታ ዓመታት ሀገሩ ውስጥ ሰብዓዊና ዴሞክራሲየዊ መብቶቹ የተከበሩበት ሥርአት ይሰፍን ዘንድ ብዙ ታግሏል። ትግሉም የብዙ እልፍ አእላፍ ታጋዮች ደም ተገብሮበታል። አጥንት ተከስክሶበታል። ህዝባችን ግን ያን ሁሉ መስዋእትነት የተከፈለለትን ያህል የተስፋ ጭላንጭል ለማየት አልታደለም።
እስካሁን በታሪካችን የምናውቀው በብልጠትም ይሁን በጠብመንጃ ኃይል የተለያዩ መንግስታት በ አገራችን ስልጣን ሲይዙ ነው። ህዝብ በማያውቀው መንገድ ስልጣን ላይ የወጡትን አገዛዞች ፍላጎታቸውንና ዓላማቸውን በህዝቡ ላይ ሲጭኑና ህዝቡንም እንደፈለጉት ሲረግጡትና ሲገዙት ዘመናት አሳልፈናል። የ 1966 ቱ የየካቲት ህዝባዊ አብዩት የአጼውን ሥርዓት ከሥሩ መንግለው ከጣሉት አንዱ የእምነት ነጻነትና የሃይማኖት እኩልነት ይከበር ጥያቄ እንደነበር ማስታወሱ ግድ ይላል:: በዚያ የህዝብ ብሶት በወለደው የለውጥ እንቅስቃሤ ብዙዎች ቤዛ ሆነው ሥርዓቱ ቢገረሰስም፤ ህዝቡ የታገለለት፣ የወደቀለት፣ የሞተለትና የተሰዋለት ድል ባለቤት እንዳይሆን በወታደራዊ አምባገነን መኰንኖች (ደርግ) ድሉን ተነጥቋል::
ለህዝባዊ መንግሥት ጥያቄና ለተለያዩ ሌሎች የዴሞክራሲ መብት ጥያቄዎች በተደረገው ፈታኝ ትግል በሀገሪቱ ከጫፍ እስከ ጫፍ ድረስ የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ሚና፣ ጀግንነት፣ ጽናትና ቁርጠኝነት በታሪክ ተመዝግቦ ያለ ከመሆኑም ባሻገር በታሪክም ሲታወስ የሚኖር ነው :: በዚያም ህዝባዊ ተጋድሎ ብዙዎች ሰማዕት ሆነው ወድቀዋል:: ከነዚህም በጥቂቱ እነ ኢ /ር ዑስማን፣ ጀሚላ፣ ከድጃ፣ አብዱ መሀመድ፣ ጀሚል ሁሴን እና ሌሎችንም ብዙዎችን ያስታውሷል ::
ዛሬ በአወልያ የተጫረው የመብት ጥያቄ በወያኔ አፈና ግድያ ሽብርና ስየል አልበረደም:: ለዚህ የመብት ጥያቄ ወያኔ ሊያጠለሽ የሚቀባውን በባዕዳን ሀይሎች የሚነዳ ጽንፈኛና አክራሪ በሚል የሚያደርገውን የማጥላላት ዘመቻ ህዝባችን የወያኔን ዕርቃን የወጣ ነጭ ውሸትና የመከፋፈል አባዜ ነቅቶ ሊጠብቅ ሊያጋልጥና ከሙስሊም ወገኖቹ ጋር በአንድነት የትግል ድጋፉንና አጋርነቱን በተግባር እንዲያሳይ የአውሮፓው የወክነድ ከፍል ጥሪውንን ያቀርባል :: ወያኔ ሥልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ በሰላም በዲሞክራሲና በሃይማኖት እኩልነት ሥም ብዙ ግፍ ፈጽሟል። ኢትዮጵያዊንን በቋንቋና በሃይማኖት በመከፋፈል ለዘመናት የቆውን እርስ በእርስ የመተማመንና የመረዳደት ባህላችንን ክፉኛ ሸርሽሯል። በወያኔ የተጫረው የዘረኝነት እሳት በተቀጣጠለባቸው አካባቢዎች የብዙ ሰላማዊ ሰዎች ህይወት አልፋል። ደም ፈሷል፣ ንበረት ወድማል፣ የዜግነት ክብር ተዋርዶ የኢትዮጵያን ጥቅም መቆርቆርና የወያኔን ጥፋት መቃወም ከወንጀል ተፈርጇል፣ አያሌ የፖለቲካና የህሊና እስረኞች ያለፍረድ በእስር ቤቶች ታጉረወል፣ በግፍ ተገድለዋል፣ የተቀሩትም ደግሞ የደረሱበት ሳይታወቅ ደብዛቸው እንደጠፋ ቀርቷል፣ ህጻናት፣ ወጣቶች፣ ጎልማሶች፣ አዛውንትና ባልቴቶች ከየማዕዘኑ አገራቸውን ለቀው በመውጣት በጎረቤት አገሮችና በሌላውም የዓለም ክፍል ተበትነው ለአስከፊ
የስደት ኑሮ ተጋልጠዋል፣ በብዙ መቶ ሺህ የሚገመቱ ሠራተኞችና የአገር መከላከያ ሠራዊት አባላት ከሥራቸው ተባረዋል፣ ቤተሰቦቻቸው ለድህነት የተጋለጡ ህጻናትና መጦሪያ ያጡ አረጋዊያን ለልመና ተዳርገዋል፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ አርሶ አደሮች መሬታቸውን እየተነጠቁ ከቀያቸው እንዲስደዱ እየተደረገ መሬታቸው ለባእዳንን ቱጃሮች በመሰጠቱ ለተደጋጋሚ ረሃብና እልቂት ተዳረገዋል፣ የአገሪቱ ወጣት ዜጎች በበሽታና በጦርነት እየረገፉ ሲሆን፣ በርካታ ወጣት ሴቶች እንደ ርካሽ ሸቀጥ ለአረብ አገር ቱጃሮች በገሃድ እየተሸጡ ናቸው፣ በጉድፈቻ ስም በነፍስ ወከፍ ሃያሽህ የአሜሪካን ዶላር እየተቀበለ በርካታ ኢትዮጽያዊን ህጻናት ለባእዳኑ እየተሸጡ ይገኛሉ።
ይህ ሁሉ የተፈጸመው በወያኔ አባላትና ደጋፊዎች፡ ወያኔን ሥልጣን ላይ ለማቆየትና ለወያኔ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ሲባል ነው። ከዚህ አገዛዝና ድርጅት ጋር መተባበር ኢትዮጵያን የበለጠ ማጥፋት እንጂ ማዳን አይቻልም። ስለዚህም ዜጎች እንደመሆናችን መጠን የአገራችንን አንድንት እንፈልጋልን፡ ከአብራኩ ተፈጥረናልና የህዝባችን ጥቃት ይሰማናል የምንል
ዜጎች ሁሉ ተደራጅተን ከመታገል ሌላ አማራጭ የለንም። በእርግጥ ለሀገር ህልውናና ለህዝብ መብት የሚደረግ ማንኛውም ትግል ቀላል አይሆንም። ትግል ግን አገርን ከማጣትና ከባርነት በበለጠ አይከብድም ። አገር ሲዋረድ የህዝብ
መሰረታዊና ዴሞክራያሲዊ መብቶቹ ሲገፈፉ ከማየት በበለጠ አይጎረብጥም። ህዝብ ተረግጦና ተዋርዶ በመከራ ሲጠበስ ከማየት በላይ አያምም። ስለሆነም እኛ ወጣቶች ታሪክ የጣለችብንን ህዘብን ከመከራ የመታደግ ክቡር አደራ የመወጣት ቲሪካዊ ሃላፊነት ስላለብን ተደራጀትን ከተበደለው ህዝባችን ጎን በመቆም ህዝባዊ ቃልኪዳናችንን ዳግም እናድስ።
ኢትዮጵያ በቆራጥ ልጆቿ ትግል በነጻነቷ ጸንታ ለዘላለም ትኖራለች!!
እናቸንፋለን!!
ኢሕአፓ ወክንድ የአውሮፓ ክፍል።
No comments:
Post a Comment