Thursday, 28 February 2013

BREAKING NEWS: TPLF Appointed Abune Matias of Tigre as the 6th Patiarch of EOTC


The Horn Times Breaking News 28 February 2013

by Getahune Bekele- South Africa

*Call for mass action reverberates across the globe

In a move expected to create more tensions and divisions, Ethiopia’s ruling minority junta has appointed yet another
Abbay Tsehaye installed 6th patriarch of the Ethiopian Orthodox Church, Aba Matias.
Abbay Tsehaye installed 6th patriarch of the Ethiopian Orthodox Church, Aba Matias. (Photo: from Facebook)
divisive figure as the 6th patriarch of the Ethiopian Orthodox Church – Abune Matias, otherwise known as the chief Rabbi of Tigraye republic.
The late Abune Pawlos’s chosen successor and the favorite of the ruling TPLF junta, Aba Matias was elected on Friday 28 Feb 2013 after Bishops of the illegal pro-TPLF synod in Addis Ababa voted for him under the watchful eyes of warlord Abbay Tsehaye.
Recently denounced and condemned for walking in public with Tigray republic’s self appointed grand Mufti sheik Elias Redman to show his support for the government’s crack down on current Muslim uprising in Ethiopia, Aba Matias is expected to be banned from entering some monasteries and Churches due to his controversial election against the divine cannon of the fathers by an illegally assembled unholy synod just like his predecessor the late Aba Pawlos.
According to the Horn Times reporters in Addis Ababa, Aba Matias received a whopping 500 votes out of 806 available while non-Tigre Bishops like Abune Yosefe got less than 100 votes in the stage managed scandalous election organized by habitual election thieves, the TPLF warlords.
Hastily recalled from the Holy city of Jerusalem by the TPLF and ordered to stand election amid controversy concerning his citizenship, Aba Matias will face enraged Ethiopians in the coming days.
More news and commentaries to follow shortly.
infohorntimes@gmail.com

Wednesday, 27 February 2013

ዓቃቢ ህግ ዕዳ አለበት! አዎ ዕዳ አለበት!!


ከተመስገን ደሳለኝ

እንደ ጉርሻ
በሽብርተኝነት ተከሰው በወህኒ ቤት የሚገኙ በጣም በርካታ እስረኞች የይቅርታ ፎርም እንዲሞሉ እየተደረገ ነው (ምንአልባት የሀይለማርያም መንግስት ሪፎርም /ማሻሻያ/ የማድርግ ዕቅድ ካለው በዚሁ ሊጀምር አስቦ ሊሆን ይችላል፤ አሊያም እንደተለመደው እስረኛ በመልቀቅ የፖለቲካ ማሻሻያ እንደተደረገ ለማስመሰል ይሆናል)፡፡ ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ እና ዘሪሁን ገ/እግዚአብሄርም በብዛት ከሚለቀቁት እስረኞች ጋር አብረው እንደሚፈቱ ምንጮቼ አረጋግጠውልኛል፡፡
ዓቃቢ ህግ ዕዳ አለበት! አዎ ዕዳ አለበት!!
አጀንዳችን…
ዛሬ በከፍተኛው ፍርድ ቤት የእነእስክንድር ነጋን ንብረት ለመውረስ ፍትህ ሚንስቴር የመሰረተው ክስ ሲታይ ውሎአል፡፡

እስክንድር ከዚህ ቀደም ‹‹የታሰርኩት በግፍ ስለሆነ ንብረቴን አትውረሱ ብዬ አልከራከርም፤ ዛሬውኑ ልትወስዱት ትችላላችሁ›› በማለት ያልተከራከረ ሲሆን፣ የአበበ በለውን ንብረት በሚመለከት በሌለበት ታይቷል፡፡ የአንዱአለም አራጌ ባለቤት ደግሞ በስሟ የተመዘገበው መኪና መወረሱ አግባብ እንዳልሆነ በጠበቃዋ አቶ ደርበው ተመስገን አማካኝነት ተከራክራለች፡፡ ፍርድ ቤቱም ለውሳኔ የፊታችን ሚያዚያ አስር ቀን ቀጠሮ ሰጥቷል (በእኔ ግምት ቀጠሮው እንዲህ የራቀው መጋቢት አስራ ስምንት ቀን እነእስክንድር የጠየቁት ይግባኝ የመጨረሻ ውሳኔ ስለሚሰጥበት ከዛ በኋላ የንብረቱን ጉዳይ ለመጨረስ ይመስለኛል)
የሆነ ሆኖ ዓቃቢ ህግ የእስክንድር ንብረት ተብለው ከቀረቡት ባለሁለት ፎቅ ዘመናዊ መኖሪያ ቤት፣ በባለቤቱ ጋዜጠኛ ሰርካለም ፋሲል ስም የተመዘገበ የቤት መኪና፣ እንዲሁም የእስክንድር እናት ንብረት የሆነ በአንድ ሺህ ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ መኖሪያ ቤትን ለመውረስ ጥያቄ ያቀረበ ቢሆንም፣ በዛሬው ዕለት በእናቱ ስም የተመዘገበውን ቤት እንደተወው ገልጿል (አዲስ ታይምስ መፅሄት የእናቱ ቤት ዝርዝር ውስጥ መግባቱ ተገቢ አለመሆኑን ደጋግማ መግለጿ የሚታወስ ነው)፡፡
ይህንና ዓቃቢ ህግ በእስክንድር እናት ስም የተመዘገበውን መኖሪያ ቤት ከሚወርሳቸው ዝርዝር ውስጥ በማውጣቱ ምንም አይነት ምስጋና የለኝም፡፡ ምክንያቱም እንኳን ንብረታቸው ተከሳሾቹም ምንም ጥፋት ያላጠፉ ንፁሀን ናቸው ብዬ ስለማምን፡፡ ስለዚህም አሁንም እንዲህ እላለሁ፡- ዓቃቢ ህግ ዕዳ አለብህ! አዎ እዳ አለብህ!! ንፁሀን ወንድሞቻችንን ይቅርታ ጠይቀህ እስክትለቅልን ድረስ!!!

የሕወሐት ፍጥጫ ቀጥሏል (ከኢየሩሳሌም አርአያ)



“አሁን ያለው ሕወሐት ቆዳ ነው” እነ ስብሃት
“የሕወሐት ወራሾች እኛ ነን” እነ አባይና አዜብ

(ከኢየሩሳሌም አርአያ)
ሁለት ቦታ የተከፈለው የሕወሐት አመራር ልዩነቱን በማስፋት እየተወዛገበ መሆኑን ከመቀሌ ታማኝ ምንጮች ገለፁ። ስብሃት እና አዜብ የሚመሩት ሁለቱ ቡድን አነጋጋሪ አቋም ይዞ መውጣቱን ምንጮቹ ጠቁመዋል። በስብሃት ነጋ የሚመራው ቡድን ባስቀመጠው አቋም « መለስ ሕወሐትን ገድሎ ነው የሔደው! አሁን ያለው ሕወሐት ቆዳ ነው። ጥያቄው ግልፅ ነው፤ ሕወሐት መቀጠል አለበት.. ወይስ የለበትም?» ሲሉ በድርጅቱ ቀጣይ ሕልውና ላይ ጥያቄ አሳርፈዋል። ከዚህ በተቃራኒ የቆመውና አባይ ወልዱ፣ አዜብና ከጀርባ በረከት ስምኦን ያሉበት ቡድን በበኩሉ « የሕወሐት ወራሾች እኛ ነን፤» ሲል ለነስብሃት ምላሽ መስጠቱ ታውቋል። በተጨማሪ በሁለቱም ቡድኖች በልዩነት ነጥብ ተደርጎ የተወሰደው በ1993ዓ.ም ከፓርቲው የተባረሩት አመራሮች « ይመለሱ» ፣ « አይመለሱም» የሚለው እንደሚገኝበት ተጠቁሟል። የሁለቱም ጐራ ፖለቲካዊ ግብ አንዱ ሌላኛውን ገፍትሮ ከሜዳው ማስወጣትና ፓርቲውን ብሎም አገሪቱን በፈላጭ ቆራጭነት ለመቆጣጠር ያለመ እንደሆነ አንድ የፓርቲው ቅርብ ሰው ጠቁመዋል።
በፓርቲው በተለኮሰው ስር የሰደደ ፖለቲካዊ ፍጥጫ ካድሬው ለሁለት ተከፍሎ ሲነታረክ መሰንበቱን ምንጮች ጠቁመዋል። በፓርቲው አባላት « አደገኛ» የተባለውን ይህን ፍጥጫ መሰረት በማድረግ በቴውድሮስ አድሃኖምና ብርሃነ ገ/ክርስቶስ የሚመራ ቡድን ራሱን « የአስታራቂ ሽማግሌዎች ቡድን» በሚል ሰይሞ ባለፉት ቀናት ሲነቀሳቀስ መቆየቱን ገልፀዋል። ሆኖም ሁለቱን ጎራዎች አቀራርቦ ለማነጋገርና ለማስማማት የተጀመረው ጥረት በሁለቱም በኩል በሚታየው አክራሪ አቋም ምክንያት ተስፋ ሰጪ ሁኔታ እንደማይታይ ምንጮቹ አስታውቀዋል። አሁንም ድርድሩ መቀጠሉን ምንጮቹ አልሸሸጉም።
የሕወሐት ሕልውና አጣብቂኝ ውስጥ በገባበት በአሁኑ ወቅት በሌላ ጐራ የተነሱ ወጣት የፓርቲው ካድሬዎች ባነሱት ጥያቄ ፥ ሁሉም አንጋፋ አመራሮች ከድርጅቱ እንዲለቁ ጥያቄ ማቅረባቸውንና ይህን ለማድረግ ፈቃደኛ ካልሆኑ ግን ሕወሐት ሊፈርስ እንደሚችል ማስጠንቀቂያ ጭምር መስጠታቸውን ምንጮቹ አያይዘው ገልፀዋል።
በተያያዘም « ጉባኤ ይጠራ» በሚል በካድሬዎች የቀረበውን ጥሪ እነ አባይ ወልዱና አዜብ ያሉበት ቡድን ውድቅ እንዳደረገው ታውቋል። አባይና አዜብ የሚመሩት እንዲሁም ትርፉ ኪዳነማሪያም፣ ሃድሽ ዘነበ፣ አለም ገ/ዋህድ፣ በየነ ምክሩ፣ ተክለወይኒ አሰፋና ሳሞራ የኑስ የተካተቱበት ቡድን በጉባኤው አሸናፊ ሆነው እንደማይወጡ ከወዲሁ በማመናቸውና በነስብሃት በኩል ከፍተኛ ሃይል እንደተደራጀባቸው ጠንቅቀው ስለተረዱ ነው ሲሉ የጠቆሙት ምንጮቹ አክለውም ሳሞራ በመከላከያ እጣ ፈንታቸው ተመሳሳይ መሆኑን በማመናቸው ከነአዜብ ጋር ተሰልፈው እንደሚገኙ ገልፀዋል።
የበላይነትን እየያዘ ነው የሚባለውና በስብሃት የተደራጀው እንዲሁም በደብረፂዮን የሚመራው ቡድን አብዛኛውን የማ/ኮሚቴ አመራር በዙሪያው ያሰባሰበ ሲሆን ከነዚህም፥ አዲስአለም ባሌማ፣ አርከበ እቁባይ፣ ቅዱሳን ነጋ፣ ፈትለወርቅ፣ ፀጋዬ በርሄ፣ አባዲ ዘሙ፣ ሃ/ኪሮስ ገሰሰ፣ ተ/ብርሃን…በዋንኛነት እንደሚገኙበት ምንጮቹ አመልክተዋል። የሽማግሌው ቡድን ስብስባ እንደቀጠለ ተጠቁሞዋል።

ሞት በምልጃ፤ የበረሃ ጣዕር! ማስለቀቂያ ካልተከፈለ – ኩላሊት ለገበያ



tigist gebre


“አቧራ ይጨሳል። ከዚያ ያፈኑትን ይዘው ይሰወራሉ” አስደንጋጩ ታሪክ ውስጥ ያለው ስዕላዊ ገለጻ ነው። አንድ ወቅት አዲስ አበባ የህጻናት ሌቦች ተበራክተው ነበር። በወቅቱ በርዳታ ስም ተመዝግበው የፈጣሪ ስም እየጠሩ ህጻናትን በመነገድ የከበሩ ወረበሎች በደንብ የተደራጁና የሚቀናቀናቸውን የማስወገድ አቅም ስለነበራቸው “አቧራው ጨሰ” የሚል ስያሜ የኮድ ስም ተሰጥቷቸው ነበር። አሁንም አሉ። “ህጻን እናሳድጋለን” እያሉ በዘረጉት ሰንሰለት የህጻናትን ደም የሚጠጡ “አንቱ” የተባሉ ሰዎች!! የውጪ አገር ዜጎች ጭምር … 
በሱዳን ሰዎችን በማፈን ሲና በረሃ የሚሰውሯቸው ራሻይዳዎች የተደራጁ ናቸው። ከአረብ ምድር የፈለሱ ናቸው የሚባልላቸው እነዚህ ጎሣዎች በሱዳንና በኤርትራ የሚገኙ ሲሆን በተለይ በኤርትራ ያሉቱ ከዘጠኙ ጎሣዎች መካከል የሚቆጠሩ ናቸው፡፡ አኗኗራቸው የዘላን በመሆኑ ከኤርትራ መንግሥት ቁጥጥር ውጪ እንደሆኑ ይነገርላቸዋል፡፡ እነዚህ ጎሣዎች እጅግ አሰቃቂ የሆነ የአፈናና የጭከና ድርጊት ሲፈጽሙ በወጉ ታጥቀውና ዘመናዊ ተሽከርካሪ በመያዝ ነው። የሚታፈነውን ሰው ከተቆጣጠሩ በኋላ አዋራ ይነሳል። የሚከንፉበት ተሽከርካሪ አሸዋውን ተርትሮት ሲወረወር የሚነሳው ጭስ ሲበተን እነሱ የሉም። ቀሪው ተግባር “ሚስትህን፣ ወንድምህን፣ እህትሽን፣ ዘመድሽን ለሚያርዱ የሰውነት ክፍል ሌቦች አሳልፈን ሳንሰጥ ዶላር ክፈል ወይም ክፈይ” የሚለው ድርድር ነው። ይህ ድራማ መሰል ንግድ ሲከናወን ተገደው ይሁን የንግዱ ተባባሪ በመሆን በውል በማይታወቅ ሁኔታ የድርድሩ አስተርጓሚ ሆነው የሚሰሩት ኤርትራዊያን እንደሆኑ ተሰምቷል። ኢትዮጵያዊያኖችም አሉበት ይባላል። ማንም ይስራው ማን ድርጊቱ አሰቃቂ መሆኑ ብዙዎችን አስለቅሷል። አስጨንቋል።
በደላሎች እስራኤል ለመግባት ጉዞ ከጀመሩት ወገኖች መካከል ስንቶቹ በሲና በረሃ ሟምተው እንደቀሩ መረጃ የለም። ከሱዳን ምድር ወጥተው ግብጽ በመሻገር ሲና በረሃ እንደ ከብት ተበልተው የሚጣሉት ወገኖች ስቃይ ለሰሚው ግራ ነው። ወገኖቻችን ላይ የሚደርሰው አሰቃቂ መከራ ከቀን ቀን እየተባባሰ ነው። አሰቃቂ ዜናዎች መስማት ለየእለቱ የሚያስፈልገን መሰረታዊ ጉዳይ እስኪመስል ተለመዷል። ይህ አሳሳቢ ጉዳይ “እስከመቼ በዚህ ይቀጥላል” የሚለው የሁሉም ወገን “ዳር ቋሚዎች” ጥያቄ ነው።

Monday, 25 February 2013

ከእሁድ እስከ እሁድ (የሳምንቱ አጫጭር ዜናዎች)



junedin reporter

“ጁነዲን ሳዶ ሳዑዲ ገብተዋል”
የቀድሞው የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት የነበሩትና በቅርቡ ከሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትርነታቸው የተነሱት አቶ ጁነዲን ሳዶ ወደ አረብ አገር ማምራታቸውን አውቃለሁ ሲሉ አንድ ጎልጉል ተከታታይ ተናግረዋል። ነዋሪነታቸው ሳዑዲ አረቢያ የሆነው እኚሁ ሰው ላቀረቡት ጥቆማ ማረጋገጫ አላቀረቡም። የሆነ ሆኖ አቶ ጁነዲን ኬንያ የፖለቲካ መጠየቃቸውን ኢትዮቻናል የሚባለው የመንግስት አንደበት የሆነው ጋዜጣ ይፋ አድርጓል። ኢትዮቻናልን በመጥቀስ ዜናውን በርካታ ሚዲያዎች የዘገቡት ሲሆን እስካሁን ድረስ ማስተባበያ አልቀረበም። አቶ ጁነዲን በትክክል ኬንያ የሚገኙ ከሆነ ኢህአዴግ ሊይዛቸው ስለሚችል ወደ ሌላ አገር ባስቸኳይ እንደሚያመሩ ከግምት በላይ አስተያየት ተሰጥቷል። ወደ አውሮፓና አሜሪካ ለማምራት አስቸጋሪ ሁኔታ ስለሚገጥማቸው ምን አልባትም የደንበኛችን ጥቆማ ትክክል ሊሆን ይችላል ተብሎ ቢገመትም ጎልጉል በራሱ መስመር ሊያረጋግጥ አልቻለም። አቶ ጁነዲን የሼኽ መሐመድ ሁሴን አላሙዲ የቅርብ ወዳጅ መሆናቸው ሲገለጽ የቆየ ጉዳይ ነው።
ኢህአዴግ ከዲያስፖራው ድጋፍ እንዳላገኘ ገለጸ 
(ፎቶ: ከግድቡ ድረገጽ) ዲያስፖራው ለአባይ ግድብ ቦንድ የሚፈለገውን ድጋፍ አለማድረጉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ። የሚኒስቴሩ የግማሽ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት እንደሚያስረዳው፣ ከዳያስፖራው ለአገር ልማት ሊገኝ የሚችለውን የሀብት ፍሰትና የልማት ተሳትፎ ለማሳደግ የሚያስችሉ ጥረቶች ቢደረጉም እየተገኘ ያለው ድጋፍ ግን ውስን ነው ሲል የተናገረው ሪፖርተር ነው።
በውጭ በሚገኙ ዋና ዋና ከተሞች 43 የድጋፍ አሰባሳቢና የቦንድ ሽያጭ ምክር ቤቶች አማካይነት  የድጋፍ ማሰባሰብ ሥራው በስፋት ቢሠራም ባለፉት ስድስት ወራት ለህዳሴው ግድብ የተገኘው አጠቃላይ ገቢ ግን 3.04 ሚሊዮን ዶላር ብቻ መሆኑን ሪፖርቱ አመልክቷል፡፡ ከዚህ ውስጥ 2.7 ሚሊዮን ዶላር የተገኘው ከቦንድ ሽያጭ ሲሆን፣ የተቀረው 292 ሺሕ ዶላር ደግሞ በልገሳ የተገኘ ነው። ገንዘቡ እንደሚጠበቀው ባይሆንም ጠቃሚ መሆኑንና ወደፊት በስፋት መሠራት እንዳለበት የሚጠቁም ነው ሲል ሪፖርቱ ይገልጻል፡፡ በዚህም መሠረት የዳያስፖራ ፖሊሲ በማዘጋጀትና ሌሎችንም አማራጮች በመጠቀም ዲያስፖራውን ለማነቃነቅ በስፋት ዝግጅት ላይ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል፡፡
ታዋቂው የቻይና ኩባንያ ክስ መሰረተ ፔትሮትራንስ የተሰኘው የቻይና ኩባንያ የካሉብና የሂላላ የተፈጥሮ ጋዝ መሬቶችን የኢትዮጵያ መንግሥት አላግባብ ቀምቶኛል ሲል ቅሬታውን ጄኔቭ ለሚገኘው ዓለም አቀፍ ንግድ ምክር ቤት አቀረበ፡፡

Sunday, 24 February 2013

ያላስተዋልነው የአቶ ሽመልስ ከማል ቃለ መጠይቅ



ያላስተዋልነው የአቶ ሽመልስ ከማል ቃለ መጠይቅ
ወረድ ብለው ደግሞ ግለሰቡ ሌላ አስገራሚ ነገር ጠቅሰዋል፡፡ ኮሚቴዎቻችንን አስመልክቶ የሚከተለውን ምስክርነት ሰጥተዋል፡- ‹‹…እነዚሁ የምናውቃቸው ዛሬ የሙስሊም መሪዎች ነን ምንትሴ ነን እያሉ የወጡ አክራሪዎች ናቸው – እነሱ ናቸው ይሄንን ስብከት የሚያሰራጩት – ይሄን መላው የኢትዮጵያ ሙስሊም አበጥሮ ያውቀዋል፡፡ በዚህ የሚታለል የለም – ዓላማው ይሄ እንዳልሆነ ይታወቃል›› ብለዋል፡፡ሰሞኑን በውድቅት ሌሊት የታጠቁና ፊታቸውን በጭምብል የሸፈኑ ፖሊሶች በየሰፈሩ የሙስሊሞችን ቤት ያለምንም የፍርድ ቤት ማዘዣ ዘልለው እየገቡ፣ እየደበደቡና ያገኙትን ውድ ንብረት (ወርቅና ብር) በግድ እየዘረፉ፣ ከዚያም አልፈው በቤቱ የሚገኘውን ቅዱስ ቁርአንና አረብኛ የሀዲስ መጽሀፍት ‹‹ይተረጎማሉ›› በሚል እየወሰዱ ነው የሚገኙት፤ ልክ እንደ ደርግ ዘመን! ሙስሊሙ በየቤቱ ስጋት ውስጥ ነው ያለው፤ ሽብር ውስጥ!!! እያሸበረው ያለው ደግሞ እርስዎ ‹‹ሥራው ህዝቡን ከወንጀል ሥራ እና ፍርሀት፣ ከወንጀል ሥጋት ነፃ ማውጣት ነው›› ሲሉ ያንቆጳጰሱት ‹‹ፖሊስ›› ነው፡፡ በየጁምአው የሰላማዊውን ሙስሊም ድምጽ ለማፈን ጠመንጃውን ወልውሎ ቆመጡን እየወዘወዘ የሚወጣው የእርስዎና የባልረቦችዎ ታዛዥ የፖሊስ ሀይል ነው፡፡ ነገሩ እንዲህ ተገለባብጧል… እርስዎ ደግሞ የሚነግሩን ሌላ እኛ የማናውቃት ኢትዮጵያ ያለች እንዲመስል አድርጎናል…. መንግስት በሃይማኖት ጣልቃ የማይገባባት…. ፖሊስ ህዝቡን ከስጋት የሚጠብቅባት…!!!

ጊዮን ሆቴል የተጠናቀቀው የኦህዴድ ድራማ!! ግለሰብ የሚጠመዝዘው “የህዝብ” ወኪል

opdo1
የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) ወገኛ ድርጅት ነው። “ሲያደርጉ አይታ” እንደሚባለው እንደ ኤፈርት አይነት ታላቅ የንግድ ኢምፓየር ከፈተ። ስሙንም ቱምሳ ኢንዶውመንት አለው። ቱምሳ የድርጅት ቅርጽና መልክ ተበጅቶለት ስራ ጀመረ። በበረሃ ትግል ወቅት በነበረን ሃብት መሰረትነው ለማለት ቀዳሚዎቹ የኦህዴድ ምልምሎች ሳንቲም አዋጡና ወደ ተግባር ገቡ። ቱምሳ በስሩ ዲንሾ ትሬዲንግ፣ ዲንሾ ትራንስፖርት፣ አግሮ ኢንዱስትሪና የንግስ ድርጅቱ የጀርባ አጥንት የሆነውን ቢፍቱ ገነማ የሚባል የጫት ንግድ አቋቋመ። የትራንስፖርት ዘርፉን ይመሩ የነበሩት የአቶ ኩማ ደመቅሳ ወንድም እንክት አድርገው በሉትና ከሰረ። ዲንሾ ንግድ ማዳበሪያ እነግዳለሁ ብሎ ከ60 ሚሊዮን ብር በላይ ከንግድ ባንክ ተበደረና ታሪኩን በኪሳራ ደመደመው። ዲንሾ አግሮም ከእህት ኩባንያዎቹ እንደተማረው ኪሳራ ተከናንቦ መሬት ብቻ አንቆ ቀረ። መጨረሻ ላይ በገፍ የሰበሰበውን መሬት በሽርክና ስም ለሼኽ መሐመድ ሁሴን አላሙዲ አስረክቦ እጁን ታጠበ።

Friday, 22 February 2013

መርዝ ከውጭ ይረጫል ወይም ከውስጥ ይመነጫል


ethiopia


በአለፉት ሠላሳ አምስት ዓመታት ኢትዮጵያ ችግሮችን መፈልፈያ መሣሪያ ሆናለች፤ ለብዙ ምዕተ-ዓመታት ይዘናቸው (ምናልባትም አቅፈናቸው ማለት ይሻል ይሆናል) ስንንከባለል የቆዩ ችግሮች ሞልተውናል፤ እያሰብን እነዚያን የቆዩ ችግሮቻችንን በመፍታት ፋንታ ሌሎች አዳዲስ ችግሮችን እየፈለፈልን የተቆላለፉና የተወሳሰቡ፣ ውላቸው የጠፋ ችግሮችን ፈጥረናል፤ እየፈጠርንም ነው፤ አሁን በመፈጠር ላይ ያለው አዲስ ችግር እስላማዊ መንግሥት በኢትዮጵያ የሚል ነው፤ እስቲ እንመልከተው፡፡
(Photo: mesfinwoldemariam.wordpress.com)
በሩቁ እንጀምር፤ እስላማዊ መንግሥታት ያቋቋሙ አገሮች አሉ፤ አንዳቸውም ሰላም የላቸውም፤ እስላማዊ ቡድኖች በምርጫ አሸንፈው ሥልጣን የያዙ አሉ፤ ለምሳሌ በቅርቡ በአረብ አገሮች በተጀመረው የፖሊቲካ እድገት ለውጥ በቱኒስያና በግብጽ እስላማዊ ቡድኖች አሸንፈው ሥልጣን ይዘዋል፤ በዚህም ምክንያት በቱኒስያና በግብጽ የለውጥ ጥያቄ አገርሽቶ አንደገና ሰዎች እየሞቱ ነው፤ በነዚህና በሌሎችም አገሮች የሚገኙት ወጣቶች የሚፈልጉት የሰው ልጆች ሁሉ መብቶች የሚከበሩባቸውና በሙሉ የግለሰብ ነጻነት የተረጋገጡባቸው አገሮች እንዲኖራቸውና በእኩልነት ኩሩ ዜጎች ሆነው እንዲኖሩ ነው፤ የአንድ አገር ዜጎች የተለያየ ዘር፣ የተለያየ የቆዳ ቀለም፣ የተለያየ ቁመትና ውፍረት፣ የተለያየ ጾታና ዕድሜ፣ የተለያየ ቋንቋ፣ የተለያየ ሃይማኖት፣ የተለያየ የፖሊቲካ አመለካከት፣ የተለያየ ትምህርት፣ የተለያየ ሙያና የተለያየ ገቢ ሊኖራቸው ይችላል፤ የጋራ ማንነታቸው ዜግነት ነው፤ እኩልነታቸው በዜግነታቸው ነው፤ አንድነታቸው በዜግነታቸው ነው፤ እኩልነታቸውንና አንድነታቸውን የሚያረጋግጥላቸውና ሚዛኑን የሚጠብቅላቸው ከበላይ ሆኖ ሁሉንም የሚገዛው ሕግ ነው፡፡
በቡድን ወይም በጅምላ የሚያስቡ ሰዎች የሕግን ባሕርይ አያውቁትም፤ ‹‹ክርስቲያኖች እስላሞችን እንጨርሳለን›› አሉ፤ ወይም እስላሞች ክርስቲያኖችን እንጨርሳለን›› አሉ፤ በሚል አሉባልታ ላይ ክስ ተመሥርቶ ሕጋዊ ፍርድ መጠበቅ አይቻልም፤ በየትም ሆነ በማንኛውም ጊዜ ጽንፈኛ እምነትና አስተሳሰብ ያላቸው ሰዎች ይገኛሉ፤ እነዚህ ግለሰቦች ሕልማቸውንም ሆነ ቅዠታቸውን በስውርም ሆነ በአደባባይ ይገልጻሉ፤ ለምሳሌ በአሜሪካ ጥቁሮችንና ይሁዲዎችን ከአገሩ ጠራርገን እናወጣና ንጹሕ የነጮች አገር እንፈጥራለን የሚሉ ግለሰቦች አሉ፤ ይህ እምነት ለአሜሪካ ማኅበረሰብ መርዝ ነው፤ አሜሪካ የነጻነት አገር ነው፤ የነጭ ዘረኞቹ መርዛቸውን ለመንዛት መብት አላቸው፤ የዘረኞቹን መብት ለማፈን የሚወሰድ የጡንቻ እርምጃ ሁሉ አሜሪካ የነጻነት አገር መሆኑን ይሽራል፤ ከዚያም በላይ የአሜሪካ መንግሥት በሚከተለው ዘዴ ከነጭ ዘረኞቹ የተሻለ አይሆንም ነበር፤ ስለዚህም ነጭ ዘረኞችን ለመቋቋም የሚወሰደው አርምጃ አሜሪካ የነጻነት አገር መሆኑን ሳይሽርና ነጭ ዘረኞቹም እምነታቸውን የመግለጽ መብታቸው ሳይደፈጠጥ መሆን አለበት፤ የነጻነት ትርጉሙ ይህ ብቻ ነው፡፡

ሰበር ዜና – አስመራጭ ኮሚቴው ለዕጩነት የለያቸው አምስት ሊቃነ ጳጳሳት ታወቁ !!


ሐራ ዘተዋሕዶ

  • ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል እና ብፁዕ አቡነ ገብርኤል አልተካተቱም
  • ሁሉም የኮሚቴው አባላት በውሳኔው ስለመስማማታቸው አጠራጣሪ ኾኗል
  • የፓትርያሪክነት መመዘኛ መስፈርቱ ከዕጩዎች ማንነት ጋራ በአግባቡ ይረጋገጥ
  • ‹‹ዕጩዎቹን ስታውቅ ፓትርያሪኩን ታውቃቸዋለኽ››› /ሰሞንኛ አባባል/
የስድስተኛው ፓትርያሪክ አስመራጭ ኮሚቴ ለዕጩ ፓትርያሪክነት አጣርቶ የለያቸውን አምስት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ለቋሚ ቅ/ሲኖዶሱ ማቅረቡ ተሰማ፡፡ ከየካቲት ዘጠኝ ቀን ጀምሮ የዕጩዎች ልየታ ሲያካሂድ የቆየው አስመራጭ ኮሚቴው÷ ለፓትርያሪክነት ለመመረጥ ብቁ ናቸው ብሎ ያመነባቸው የአምስቱ ሊቃነ ጳጳሳት ስም ዝርዝር፡-
1)  ብፁዕ አቡነ ማትያስ – በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ገዳማት ሊቀ ጳጳስ
2)  ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ – የወላይታ ዳውሮ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ
3)  ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ – የባሌ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ
4)  ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል – የከፋ ሸካ ቤንች ማጂ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅ/ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ
5)  ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ – የሰሜን ጎንደር ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ናቸው፡፡
የአስመራጭ ኮሚቴው አጣርቶ ሊያቀርባቸው ከሚችላቸውና የቅድሚያ ግምት ከተሰጣቸው አባቶች አራቱ በኮሚቴው የዕጩዎች ዝርዝር ውስጥ መግባታቸው የሚጠበቅ ነው፡፡ ኮሚቴው በሚያቀርባቸው ዕጩዎች ውስጥ ያልተጠበቁ አባቶች ሊታዩ እንደሚችሉም አስቀድሞ የተገመተ ነበር፡፡
ነገር ግን በብዙ ሺሕ የካህናትና ምእመናን ድምፅ የተጠቆሙትና በፓትርያሪክ ምርጫ ሕግ አንቀጽ 5 የተዘረዘረውን የዕጩ ፓትርያሪክነት መመዘኛ መስፈርቱን ያሟላሉ ተብለው የታሰቡት ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል (ከ9000 ያህል ጠቅላላ ጠቋሚዎች 7200 አግኝተዋ)

ድንቄም ምርጫ!



ከይኸነው አንተሁነኝየካቲት 21 2013


የትምህርቱ ስርአት በተጨማሪ በሕዝቦቿ መካከል  ያለው የባህል፣ የሃይማኖትና የአኗኗር መስተጋብር የሚያበረክቱት አስተዋጽኦና በዚሁ ሳቢያም የሚገኘው ቀጥተኛ ያልሆነ የእውቀትና የልምድ አቅምና ዝውውሩ የሚናቅ አይሆንም። የተረጋጋና በመከባበር የሚመራ የሃይማኖት ስርአት፣ የአንደኛው እንቅስቃሴ ሌላኛውን በመደገፍ ላይ የተመሰረተ ማህበራዊ እንቅስቃሴ፣ ጎጂ የሆኑ ብህሎችን በማስቀረት ላይ ያተኮረና የሁሉም ብህላዊ ዕሴቶቻችን አስፈላጊነት ላይ ጥያቄ የማያነሳ ማሕበረሰብ ከሁሉም በላይ ለአንዲት ሀገር እድገት አስፈላጊዎች ናቸው። ላንዲት ሀገር መሰረታዊ የእድገት ሃይል ያላት የተፈጥሮ ሃብትና የሕዝቦቿ ሁለንተናዊ ብቃት ናቸው። የሕዝቦቿን ሁለንተናዊ ብቃት ለመገንባት ደግሞ ካሏት የትምህርት ተቋማትና

Ethiopian election 2013
በሌላ በኩል ደግሞ ምንም እንኳ የተፈጥሮ ሃብትና ብቃት ያለው የሰው ህይል የእድገት መሰረቶች ናቸው ቢባልም እነዚህን ሃብቶች ስርአት ባለው መልክ አቀናጅቶና አስተባብሮ መምራት የሚችል የሕዝብ አስተዳደርም ወሳኝ መሆኑ አሌ ልባል አይገባም። ያሉንን ሃብቶች ወደ ውጤት የመቀየሩ ሂደት ሳይደናቀፍ እንዲቀጥል ደግሞ ሀገሪቱ የህግን የበላይነት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የሚቀበል ዴሞክራሲያዊ አስተዳደርና የሕዝብን የበላይነት የሚያምን ዴሞክራሲያዊ ስርአት ሊኖራት ይገባል። ይህም ሲጠቃለል ለአንዲት ሀገር ሁለንተናዊ እድገት ቀጣይነት ዴሞክራሲና ዴሞክራሲአዊ ስርአት ወሳኝ ግብአት ነቸው ማለት ነው።
አንዳንድ ሰዎች ከዴሞክራሲ ውጭ እድገት ሊመጣ እንደሚችል አንዳንድ ሀገሮችን እየጠቀሱ ቢሞግቱም በቅርብ ጊዜያት እየወጡ ያሉ ስለ እድገት የሚያወሩ ከሂዎት ልምድ የተገኙ ተሞክሮዎችና ትንተናዎች ግን የእድገት መሰረት የሆነው ማሕበረሰብ ነፃነትና ሁሉንም ያማከለ የሃብት ክፍፍል ወሳኝ እንደሆኑ ያረጋግጣሉ። ነጻነትና የተማከለ የሃብት ክፍፍል ደግሞ ከዴሞክራሲ ፍሬዎች ዋና ዋናዎቹ መሆናቸውን ልብ ይሏል።

Saturday, 16 February 2013

የአቡነ ሳሙኤል ጉዳይ የሲኖዶሱን አባላት በትውልድ ሃገር እንዲቧደኑ እያደረገ ነው



Abune samuel 6

በተለይም ለ6ኛው ፓትርያርክነት ከታጩት 5 ሰዎች ውስጥ የ4ቱ በካድሬነት (ቡድን በማሰባሰብ ደረጃ) ከአቡነ ሳሙኤል ያነሰ እንዲሆን የተደረገው ሴራ በመንግስት የታቀደ መሆኑን ያጋለጡት እነዚሁ የዘ-ሐበሻ ምንጮች ብዙ ጊዜ መንግስትን በመተቸት የሚታወቁት አቡነ ገብርኤል በእጩነት የገቡት ምርጫውን ሚዛናዊ ለማስመሰል እንደሆነ ገልጸዋል። ሌሎቹ 3 እጩ ጳጳሳት ደግሞ እንደ አቡነ ሳሙኤል ከወያኔ ጋር ለረዥም ጊዜ በመሥራት ያገኙት የደህነትና የስለላ ሥራ ልምድ የሌላቸው እንዲሆን ሆን ተብሎ መደረጉን እነዚሁ ምንጮች ገልጸው የፓትርያርክ ምርጫው “ዓይን ባለው እና በሌለው” መካከል ነው ብለዋል። ምንጮቹ ይህን ሲያብራሩም “አቡነ ሳሙኤል በደህነነት ሥራ በቆዩባቸው ጊዜያት ቡድን በማሰባሰብና በማደራጀት አሁን ከታጩት አባቶች የላቁ ናቸው፤ ስለዚህ ዓይን ያለው ሰው ፓትርያርክ ሆኖ ይመረጣል ቢባልና ለውድድር ሁለት ዓይን ያለው፣ ዓንድ አይን ያለውና አይን የሌለው ቢቀርቡ የቱ ያሸንፋል?” ይላሉ።

በተለይ መንግስት ሆን ብሎ ባደራጃቸው ቡድኖችና ግለሰቦች አማካኝነት በሕዝብ እንደተመረጡ በማስመሰል አቡነ ሳሙኤልን እጩ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆኑ በገፍ በማስጠቆም ላይ ሲሆን ይህን ጫና ተከትሎና 6ኛው ፓትርያርክ ማን እንደሚሆን ቀድሞ መታወቁ የሲኖዶሱን አባላት ወትሮም ወደነበረባቸው የዘር መከፋፈል ውስጥ ከቷቸዋል ያሉት የዘ-ሐበሻ ምንጮች በተለይ፦ 1ኛ. ፓትርያክ ከሸዋ ፓትርያርክ መመረጥ አለበት የሚሉ ጳጳሳት(ወ እጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ተብሎ ፓትርያርኩ ስለሚጠራና የአቡነ ተክለሃይማኖት መንበር ላይ ስለሚቀመጥ ከሸዋ ነው መመረጥ ያለበት በሚሉ)

Friday, 15 February 2013

ከፍተኛ ስጋት ላይ የወደቀው መንግስት ሞባይል ኔትወርክ አቋርጦ እንደነበር ታወቀ



የካቲት ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በዛሬው ዕለት ከተካሄደው ጁምአ ጸሎት ስርዓት ጋር ረብሻና ከፍተኛ ተቃውሞ ሊነሳ ይችላል በሚል ስጋት በተያያዘ በአዲስአበባ ዛሬ ማለዳ ላይ የሞይባል አገልግሎት ከአምስት ሰዓታት በላይ ተቋርጦ እንደነበር ተሰማ፡፡ በዛሬው ዕለት ሙስሊሙ ህብረተሰብ በመደበኛ የጁምአ ፕሮግራሙ እርስ በእርስ በመጠራራት እና አጫጭር የስልክ መልዕክቶችን በመለዋወጥ ከፍተኛ ተቃውሞ ሊያደርግ ይችላል በሚል ግምት ሐሙስ ለዓርብ አጥቢያ በግምት ከለሊቱ 10 ሰዓት ጀምሮ እስከ ንጋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ የተወሰኑ የሞባይል ሰልክ ቁጥሮችን ከግንኙነት ውጪ በማድረግ ወይ
ኔትወርክ በማቋረጥ እርምጃ ተወስዷል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞም የስልክ አገልግሎት በመቋረጡ የአጭር መልዕክት ልውውጥ እንዲሁም የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲቋረጥ ግድ ሆኗል፡፡ በዚህ ምክንያት በርካታ ግለሰቦችና የቢዝነስ ተቋማት የእርስ በርስ ግንኙነት ማድረግ ሳይችሉ ለማርፈድ ተገደዋል፡፡

ሁሉም የሞይባል አገልግሎት ያልተቋረጠበት ዋንኛ ምክንያት ምን እንደሆነ የተጠየቁት ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጭ የተወሰኑ የደንበኛ ጭነት ያለባቸውን መስመሮች ግንኙነት ከተቋረጠ ያልተቋረጠባቸው ስልኮች ከእነዚህ ጋር ግንኙነት ማድረግ አይችሉም ብለዋል፡፡ በተጨማሪም ሁሉም ቁጥሮች አለመቋረጣቸው ቴሌ ለሚነሳበት ቅሬታ የኔትወርክ መጨናነቅ  ነው በሚል ጉዳዩን ለማስተባበል ስለሚረዳው ሆን ተብሎ የተደረገ መሆኑን ጠቅሰው የዚህ ዓይነቱ አሰራር ሲፈጸም የመጀመሪያው አለመሆኑን አመልክተዋል፡፡ እንደምንጫችን ገለጻ ከዚህ በፊት ጠ/ሚኒስትሩ እና ሌሎች የአገር መሪዎች በከተማ ውስጥ ሲዘዋወሩ፣ሲገቡና ሲወጡ መንገዶችን ከመዝጋት ባሻገር ሸብርተኝነትን አስቀድሞ ለመከላከል በሚል የተወሰኑ የሞይባል ግንኙነቶች ለተወሰኑ ደቂቃዎች ሲቋረጡ መቆየታቸውን አስታውሰዋል፡፡

(Breaking News ሰበር ዜና) ሳይመረጥ የታወቁት 6ኛው ፓትርያርክ አቡነ ሳሙኤል



  • digg
  • 984
     
    Share

(ዘ-ሐበሻ) 6ኛው ፓትርያርክ ሆነው እንዲመረጡ የታጩት ጳጳሳት ስም ዝርዝር ዘ-ሐበሻ እጅ ደረሰ። የዘ-ሐበሻ ታማኝ የቤተክህነት ምንጮች እንዳስታወቁት ለይስሙላ 5 ጳጳሳት ለ እጩነት ይቅረቡ እንጂ 6ኛው ፓትርያርክ ሆነው የሚመረጡት ፓትርያርክ አቡነ ሳሙኤል እንደሚሆኑ ከወዲሁ ታውቋል።

የትግራይ ተወላጁ አቡነ ሳሙኤል ከምንኩስናቸው ጀምሮ የወያኔ ደህንነት እንደነበሩ የሚያስታወቁት የቤተክህነት ምንጮቻችን ከ እርሳቸው ጋር ለ እጩነት የቀረቡትን ጳጳሳት ስም ይፋ አድርሰውናል።

1ኛ . አቡነ ገብርኤል – ትውልድ ወሎ
2ኛ. አቡነ ሉቃስ – ትውልድ ትግሬ
3ኛ. አቡነ ዮሴፍ – ትውልድ ኦሮሞ
4ኛ. አቡነ ማቲዎስ – ምንጃር ሲሆኑ ከ5ቱ እጩዎች ውስጥ ሁለት ከትግራይ መመረጡ አነጋጋሪ ሆኗል ያሉት ምንጮቻችን ከመንግስት ጋር በመስራት በተለይ እርቀሰላሙ እንዳይሳካ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ሲያደርጉ እንደነበሩ የሚነገርላቸው ልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ሆነው እንዲመረጡ መንግስት ከፍተኛውን ጫና እያደረገ እንደሆነ ምንጮቻችን አጋልጠዋል፡። ዘ-ሐበሻ ተጨማሪ መረጃዎችን ይዛ ትመለሳለች። በተለይም ተመላልሰው ይጎብኙን።

በጎንደር መድሀኒዓለም ቤ/ክ የተጠለሉ 48 ባህታዊያንን ወደ መጡበት ዋልድባ መወሰዳቸው ታወቀ



የካቲት ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ባህታዊያኑ ከጥር 2 ቀን 2005 ዓም ጀምሮ በጎንደር ከተማ በሚገኝ መድሀኒአለም ቤ/ክርስቲያን ውስጥ ጥብቅ ቁጥጥር እየተደረገላቸው ተጠልለው ቆይተዋል። ትናንት ባህታዊያኑ ከቀኑ ስምንት ሰአት ላይ በአውቶቡስ ተጭነው ወደ አልታወቀ ስፍራ መወሰዳቸውን የዘገብን ሲሆን፣ ወኪላችን ሂደቱን ተከታትሎ እንደዘገበው ባህታዊያኑ የተወሰዱት ፣ ከተለያዩ የአማራ ክልል የተውጣጡ የሀይማኖት አባቶች ችግሩን በሽምግልና እንፈታዋለን የሚል ሀሳብ ካቀረቡ በሁዋላ ነው። ባህታዊያኑ በአውቶቡስ ሲጫኑ የተመለከተ አንድ የጎንደር ነዋሪ ፣ እንደገለጠው ባህታዊያኑ ከህዝቡ እንዳይቀላቀሉ ሌት ተቀን ሲጠበቁ ሰንብተዋል (10፡42-11፡45 ) 31ባህታዊያን ጥር 15 ቀን 2005 ዓም ለሰሜን ጎንደር ዞን መስተዳድር  እና ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን  በጻፉት አቤቱታ፣ ደረሰብን ያሉዋቸውን በርካታ በደሎች ዘርዝረው አቅርበዋል።

በደብዳቤው ፣ የጸለምት ወረዳ አስተዳደርን የተቆጣጠሩ ግለሰቦች ለዘመናት አንድነቱ ተከብሮና የዘር መድልዖ ሳይደረግበት ማንኛውም መናኝ በሀይማኖታዊ ምክንያቶች ብቻ ተመርምሮ ይኖርበት በነበረው ቦታ ግልጽ በሆነ መልኩ የትግራይ ክልል ተወላጅ ካልሆናችሁ በዚህ ገዳም መኖር አትችሉም በማለት ማህበረ-መነኮሳቱን መከፋፈላቸውን እንዲሁም  የአካካቢውን የሚሊሺያ ሀይል በመጠቀም የመብት ጥሰት መፈጸማቸው ፣ ተመልክቷል። ከተጠቀሱት የመብት ጥሰቶች መካከል የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ሲሳይ መረሳ ማህበረ-መነኮሳቱን በዘር በመከፋፈልና የራሳቸውን የፖሊስ ታጣቂና ሚልሻ በመጠቀም እያሰሩ በተደጋጋሚ ማስደብደባቸው ተጠቅሷል። ጥር 2 ቀን 2005 ዓም አባ ወ/ገብርኤል ገ/ስላሴ እና አባ ገ/ህይወት ተ/ማርያም የተባሉ መናንያን ከከዳሙ ተወስደው ሽፍታ መነኩሴዎች ተብለው ለ4 ቀናት መታሳራቸውን፣ የወረዳው አስተዳዳሪውም ” እናንተ ተመልሳችሁ ወደ ገዳሙ መግባት አትችሉም፣ የወጡትም አይመለሱም፣ በገዳሙ የቀሩትንም እየመነጠርን እናወጣቸዋለን፣ እንገባለን ካላችሁ ገዳያችሁን ሳታውቁ ትገደላላችሁ መባላቸውም ተመልክቷል።

Monday, 11 February 2013

አርቲስትና አክትቪስት ታማኝ በየነ በኦስሎ፣ ኖርዌይ (ልዩ አጭር ጥንቅር)


ጉዳያችን (GUDAYACHN)

የዛሬዋ የእሁድ ምሽት ከታማኝ የኦስሎ የኢሳት ገቢ ማሰባሰብያ መርሃ ግብር ጋር ያሳለፍኩት ምሽት ነበር። ምንም እንኳን መርሃግብሩን በሙሉ ለመፈፀም ባልችልም የአክትቪስት እና አርቲስት ታማኝን በቪድዮ የተደገፈ ገለፃ ግን ለመከታተል እድሉ ገጥሞኛል።
Ethiopian satellite television, norway
ኦስሎ ለኢሳት ገቢ ማሰባሰብያ መርሃግብር ከተገኘው ሕዝብ በከፊል (photo GUDAYACHN BLOG EXCLUSIVE)
ገብስማ ፀጉሩ ከነጭ ሸሚዝ እና ሽሮ መልክ የያዘ ክራቫት ጋር ታማኝን ግርማ ሞገስ አጎናፅፎታል። ታማኝ ወደ መድረኩ ሲመጣ ከታላቅ አክብሮት ጋር ከአምስትመቶ በላይ የሆነው ታዳሚ ከመቀመጫው ተነስቶ ተቀበለው። ታማኝ አፀፋውን እየመለሰ ምስጋናውን ገለፀ። ቀደም ብለው ከጎናቸው ከነበረው ሰው ጋር ይነጋገሩ የነበሩ ሰዎች በፀጥታ ወደመድረኩ ማስተዋል ጀመሩ። ታማኝ ሰላምታውን በአማርኛ ብቻ አልነበረም ያቀረበው ”አሰላም አለኩም” በማለት ለሙስሊም ኢትዮጵያውያን ያለውን አክብሮት ሲገልፅ ሞቅ ያለ ጭብጨባ ተቸረው። ላፕቶፑን አስተካክሎ ከጀርባው በኩል ወዳለው ስክሪን ተመለከተ ትክክል ነው። ንግግሩን ቀጠለ እና እንዲህ አለ-
”ላረጋግጥላችሁ የምፈልገው በስቶኮልም እና በጄኔቭ ከተመለከትቁት ሕዝብ ኦስሎ ዛሬ የበላይነቱን ይዟል።” ጭብጨባ አጀበው ቀጠለና:-
”…እኔ አርቲስት ነኝ በአርቲስትነት መኖር እችል ነበር። መፅሐፉ የሚለው ከፊትህ ውሃና እሳት ቀርቦልሃል እጅህን ወደወደድከው ጨምር ነው። እኔ እጄን ወደ ውሃ ከትቼ በአርቲስትነቴ እየደነስኩ መኖር አያቅተኝም ነበር። ነገር ግን የእውነት ጉዳይስ? የኢትዮጵያ ጉዳይስ? ዝም ብሎ የሚኖር ህሊና አለን?… እድሜዬ እንደምታዩኝ ላይሆን ይችላል። ፖለቲካ ያቃጥላል፣ ያናድዳል። ሆኖም ግን እስከመጨረሻ ለመፅናት ነው ቃል የገባሁት።”

Thursday, 7 February 2013

እስላማዊ መንግሥት በኢትዮጵያ?



-cracies


መለስ የሚሌኒየም ንግሥ እለት ተገኝተው ዘፈን ምረጡ ሲባሉ “የሱዳን ዘፈን ይሁንልኝ” ብለው ከባለቤታቸው ጋር የተምነሸነሹበት የሚሌኒየም አዳራሽ በአቶ አሊ አብዶ የከንቲባነት ዘመን ለመስጊድ ማሰሪያ ተጠይቆ እንደነበር ፣ አቶ አሊም ቦታውን ለተጠየቀው ዓላማ እንዲውል መፍቀዳቸውንና ውሳኔው ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት ኢህአዴግ ዘንድ መረጃው ደርሶ መታገዱን ውስጥ አዋቂዎች ያስታውሳሉ። ከምርጫ 97 በኋላ ደግሞ መላ ሰውነታቸውን የተሸፋፈኑ ሙስሊሞች እየበዙ በመሆኑ ጉዳዩ ሥር ሳይሰድ፣ ከጀርባው እነማን እንዳሉበት ክትትል እንዲደረግ በታዘዘው መስረት የብሔራዊ የመረጃና የደህንነት አገልግሎት አስገራሚ ሪፖርት አቅርቦ እንደነበር እነዚሁ ክፍሎች ይናገራሉ። በክትትሉ የተገኘው መረጃና የመጨረሻ ድምዳሜ ተሸፋፍነው የሚለብሱት እህቶች አብዛኞቹ ሴተኛ አዳሪዎችና የገንዘብ ችግር ያለባቸው የሌላ ሃይማኖት ተከታዮች መሆናቸውን ነበር።

የገንዘቡም ምንጭ በሳዑዲ አረቢያ የሚገኝ አንድ የርዳታ ድርጅት ሲሆን፣ ይህንን ርዳታ ያደረገው የኢትዮጵያ ሙስሊም እህቶች አለባበሳቸው በሌላው ዓለም እንደሚዘወተረው ዓይነት ባለመሆኑ ገንዘብ በመክፈል የዕምነቱን ተከታዮች ለማደፋፈርና ተሸፋፍኖ መልበስ እንዲለመድ ለማድረግ በሚል እንደሆነ የሚጠቁሙት ክፍሎች የክትትሉ መጨረሻ ለገንዘብ ሲባል የሚደረግ የድህነት ውጤት እንጂ ወደ ሌላ አቅጣጫ ሊያመራ እንደማይችል የሚተነበይ መሆኑን ያስረዳሉ። በሌላ በኩል ግን ሳዑዲ የሚቀመጠው የርዳታ ድርጅት ከተወሰኑ የመንግስት ባለስልጣናት ጋር ሳይቀር ግንኙነት እንደነበረው፣ አቶ በድሩ አደምም በዚሁ በኩል አብረው እንደሚሰሩ ተጠቁሞ ማስተባበያ እንደሰጡበት ያስታውሳሉ።

Wednesday, 6 February 2013

አንድነት ፓርቲ ጀሃዳዊ ሀረካትን አጣጣለው



ኢሳት ዜና:-ፓርቲው ” በ‹‹ጀሃዳዊ ሃረካት›› ትረካ የሙስሊሙን ማህበረሰብ ጥያቄ ማዳፈን አይቻልም!” በሚል ርእስ ባወጣው መግለጫ፣ በገዢው ፓርቲ ድርጊት ማፈሩንና ማዘኑን ገልጿል። ገዥው ፓርቲ  ዜጎች በማንኛውም መንገድ የሚያነሱትን ጥያቄ በግልጽና በውይይት መፍታት ያለመፈለጉ ግልጽ ሀገራዊ አደጋ እየሆነ መምጣቱ እየታየው ነው የሚለው አንድነት፣ “ኢትዮጵያን የምታክል ትልቅ ሀገር እያስተዳደረ ባለ መንግሥት” ማዘኑንም አልሸሸገም።
አንድነት በኢትዮጵያ ሕዝብ ግብር የሚተዳደረው ነገር ግን የገዥው ፓርቲ መሳሪያ በመሆን የሕዝብ  ጥያቄዎችን ለማፈን ተባባሪ መሳሪያ ሆኖ እያለገለ ያለው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ‹‹ጀሃዳዊ ሃረካት›› በሚል የተሰናዳና እንደተለመደው የሙስሊሙን ህዝብ ጥያቄን ለማዳፈን የተዘጋጀ አይነት ትረካ ሲያቀርብ የመጀመሪያው አለመሆኑን አስታውሷል።

ዶክመንታሪዎች የሚሰጣቸው ርዕስ ግዝፈትና የአጽመ ታሪካቸው ትረካ ልልነት ከተራ ድራማም ያነሰ ነው ሲል ፣ በኢቲቪ ትናንት የተላለፈውን ፊልም ያጣጣለው አንድነት፣ ትረካው የቀረበው  የሙስሊሙን አንድ ዓመት የዘለቀ ግልፅ ጥያቄ ፊት ለፊት ተወያይቶ በመመለስ ፋንታ በእጅ አዙር ለማድበስበስ ፣ በዜጎች ላይ የስነ-ልቡና ጫና በመፍጠር በፍርሓት ውስጥ አድርጎ ለመግዛት በማለም ፣  መንግሥት እጁን አስረዝሞ በኃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ በመግባት የሚያደርገውን የአድራጊ ፈጣሪነት ስራ ‹‹ሕግ ማስከበር›› የሚል ሽፋን በመስጠት የማደናገር ስራ ለመስራት  ነው ብሎአል፡፡

ይህ ዶክመንተሪ በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት አራተኛ ወንጀል ችሎት የዕግድ ትእዛዝ ቢተላለፍበትም በማናለብኝነትና ሥልጣንን ካለአግባብ በመጠቀም ያለምንም ይግባኝ በከፍተኛው ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት ተሽሮ ለኢትዮጵያ ህዝብ እንዲተላለፍ መደረጉን ስንመለከት፣ ራሱ ህግ የሚጥስ ገዢ ፓርቲ እንዴት የሌሎችን ህግ ሊያስከብር ይችላል በማለት ጠይቋል። 

የባለራእይ ወጣቶች ማህበር የአመራር አባላት ማደኛ ወጣባቸው



ኢሳት ዜና:-ኢሳት ከአመራሩ ለመረዳት እንደቻለው፣ የፍርድ ቤት የእስር ትእዛዝ የወጣባቸው በማህበሩ ሊ/መንበር በወጣት ሀብታሙ አያሌው፣ በምክትሉ ሚኬኤል አለማየሁ እና በህዝብ ግንኙነት ሀላፊው በብርሀኑ ተክለያሬድ ላይ ነው።ጥር ፳፱ (ሀያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም                                                                                 
 
ወጣት ብርሀኑ በፖሊስ ተይዞ እስር ቤት የገባ ሲሆን፣ ሊቀመንበሩና ምክትሉ ዜናውን እስካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ አልተያዙም። ግለሰቦቹን በግንቦት7 ስም ለመክሰስ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ለማወቅ ተችሎአል።
 
በቅርቡ የመንግስት የደህንነት ሀይሎች የማህበሩ የአመራር አባል የሆነች ወጣትን መርፌ በመውጋት አፍነው ከወሰዱዋት በሁዋላ፣ አመራሮቹ ከግንቦት7 ጋር ይገናኙ ነበር ብለሽ ተናገሪ እየተባለች መደብደቡን መዘገባችን ይታወሳል።
ኢሳት ለማረጋጋጥ እንደቻለው ከብዙ ማንገራገር በሁዋላ ሆስፒታሉ ወጣቷ በመርፌ መወጋቷን የሚያሳይ የህክምና ማስረጃ ሰጥቷታል።

    Tuesday, 5 February 2013

    የባለራዕይ ወጣቶች ማህበር ሊቀመንበር በተፈበረከ መረጃ መንግስት ሊያስረው እንደሚፈልግ ገለፀ



    February 4, 2013 8:02 am
    • digg
    • 57
       
      Share
    “የኢህአዴግ ስርአት መወገድ አለበት፤ ሙሉ ጊዜዬን ለፖለቲካ ስራ በማዋል ስርአቱን ለመታገል ተዘጋጅቻለሁ”ሀብታሙ አያሌው
    ethiopian envላለፈው አንድ አመት የባለራዕይ ወጣቶች ማህበር ሊቀመንበር የሆነው ሀብታሙ አያሌው ከአሸባሪ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት እንዳለው በማስመሰል በኢሜልና በስልክ የማያውቃቸው መልዕክቶች እየደረሱት እንደሆነ ለፍኖተ ነፃነት ገለፀ፡፡
    በፈጠራ መረጃዎች ብዙዎች እንደታሰሩ ያስታወሰው ሀብታሙ ከዚህ መልዕክት ጀርባ በስውር የሚንቀሳቀሱ የመንግስት የደህንነት ሀይሎች እጅ እንዳለበት እንደሚያምን አስረድቷል፡፡ አያይዞም ያለው ስብዕናና ሀይማኖታዊ አስተዳደግ ከሽብርና ጥፋት ሊያቀራርበው እንደማይችል ተናግሯል፡፡
    የባለራዕይ ወጣቶች ማህበር አባላትን “እንዴት ከሀብታሙ ጋር ትሆናላችሁ እሱ ከ ግንቦት ሰባት ጋር ግነኙነት አለው” በማለት በመንግስት ደህንነት ሀይሎች ሀሰተኛ ውንጀላ እየቀረበብኝ ነው በማለት አስረድቷል፡፡
    ጨምሮም የማህበሩ አባላት የመንግስት ካድሬዎችና ደህንነቶችን ሴራ ለማጋነጥ እየተዘጋጁ መሆኑን ገልጧል፡፡
    አሁን ባለው የኢትዮጵያ ሁኔታ በሲቪክ ተቋማት ተደራጅቶ ለውጥ ማምጣት ይቻላል ብሎ እንደማያምን የገለፀው ሀብታሙ አያሌው “የኢህአዴግ ስርአር መወገድ አለበት፤ ሙሉ ጊዜዬን ለፖለቲካ ስራ በማዋል ስርአቱን ለመታገል ተዘጋጅቻለሁ” ብሏል፡፡
    ከሀብታሙ አያሌው ጋር ያደረግነውን ሙሉ ቃለምልልስ በድረ ገፃችን ላይ ያገኙታል፡፡

    Monday, 4 February 2013

    የሚድሮክ ልዑክ ለአባዱላ ያቀረቡት ጥያቄ


    የአላሙዲ ድርጅቶችን የግብር እዳ ማህደሮች ዝርፊያ ድራማ
    alamudi and abadula
    February 4, 2013 09:06 am By  1 Comment

    የሚድሮክ ኢትዮጵያ የበላይ አመራሮች አባዱላ ገመዳን ለማነጋገር ቀጠሮ አስይዘው የተወሰኑ ባለስልጣናት ከሃላፊነታቸው እንዲነሱ ጠይቀው እንደነበር የጎልጉል ምንጮች አስታወቁ። በኦሮሚያ የሚገኙ የሼኽ መሀመድ ሁሴን አሊ አላሙዲ ንብረት የተባሉ ድርጅቶች ላይ የተደረጉ የሂሳብ ምርመራዎችና ግብር ታሪፍ የተሰራባቸው ሰነዶች ዝርፊያ ምርመራ ተድበስብሶ እንዲታፈን መደረጉ እስካሁን ምላሽ ያላገኘ ጉዳይ እንደሆነ ተጠቆመ።

    አባዱላ ገመዳ የኦሮሚያ ፕሬዚዳንት በነበሩበት ወቅት ሚድሮክ የሰየማቸውና በዶ/ር አረጋ የሚመራ ልዑክ ቢሯቸው የተገኘው በወቅቱ የሼክ መሀመድ ድርጅቶች ላይ ክልሉ ግብር እንዲከፍሉ ያሳለፈውን ውሳኔ ተከትሎ ነበር። የክልሉ ካቢኔ ግብር መክፈል የሚገባቸው ባለሃብቶች በሙሉ ሊከፍሉ የሚገባቸውን ውዝፍ እዳ ገቢ እንዲያደርጉ ባሳለፈው ውሳኔ መሰረት የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ክልሉ ውስጥ የሚገኙትን የንግድ ድርጅቶች መዝገብ መርምሮ ነበር።

    በወቅቱ የተላለፈውን ውሳኔና የውሳኔውን ትግበራ በቅርበት የሚያውቁ የጎልጉል የመረጃ ምንጮች እንዳሉት የሚድሮክ ሃላፊዎች አባዱላ ቢሮ በመሄድ ስም በመጥቀስ የተወሰኑ የክልሉ ቢሮ ሃላፊዎች ከሃላፊነታቸው እንዲነሱ ጠይቀዋል። ምንጮቹ እንደሚሉት በሙስና ሰበብ በእስር ላይ የሚገኙትን የገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ቀዳሚው ተጠቃሽ ናቸው።

    ታማኝነት ለህዝባዊ ፍቅር ሲሰግድ። ታማኝ ትናንትም ዛሬም!


    ሥርጉተ ሥላሴ

    02.02.2013

    ታማኝ አወቀበት ….
    ተፈጥሮበት
    የተነሳለት ዓለማ – አስከበሮ አፈራለት
    ትናት ዘርቶ – ዛሬን አፋፍቶ – አጎምርቶ – አሳመረበት፤
    ነገን ለማብራት – በተግባር ቀለም ድሮ – ጽናትን ኮለበት።
    ፍቅር ሰጥቶ ፍቅር – ለታሪክ ተቀበለበት
    በቀለበት ተቋም፤ -  አደራን ውል አዋዋለበት።
    ታማኝ አወቀበት ….
    ትውፊት አጽድቆ – ለዘመን ደረበለት
    መሆን መቻልን – ለመቀነት ደረሰለት።
    በፍቅር ስንቅ – ተስፋን አክበሮ ለራዕይ – ዳረለት
    እንደ ትናንቱ ዛሬም ታማኝ … ታመነበት ….
    በማስተዋል ድርሻን  – በድርጊት አበቀለበት።
    ሁለት እርእሰ ጉዳዮችን በአንድ የወግ ገባታ አጣምሬ ወይንም አጋብቼ ለማቅረብ አሰብኩ። ግን ይቻለኝ ይሆን? … ትታይ እሜቴ ብዕር … አዎን እኔ እርእሰ  ተሰጥቶኝ መጻፍ
    Ethiopian artist and activist Tamagne Beyene
     አልችልም። ሁልጊዜም እርእስ እምሰጠው መጨረሻ ላይ ነው። መጻፍ ለእኔ ከቧንቧ ውኃ እንደ መቅዳት እጅግ ቀላሉ ስራ ነው። ለትምክህት አይደለም። የመዳህኒትዓለምን ሥጦታ ለማክበር ነው። ችግሬና ብዙ ጊዜ የሚፈጅብኝ ግን እርእስ ከመስጠቱ ላይ ነው። እስከ ወር የሚጠብቁ ጹሑፎች ይኖሩኛል … ጋዳ ነው አይደል?! ለእኔ እርእስን ዘው አድርጎ ለጹሑፎቼ ቤተኛ ማደረግ … ዳገት ነበር። ዛሬ ግን ግድ አለና እርእሰ ጉዳዩን ካላይ ከአናቱ ጉብ አድርጌ እንተያይ አልኩት። ተጠራጠርኩት እራሴን … ግን አልገርም? እችል ይሆን? እንጃ ነው እንጃ ጉድሽ ሥርጉተ …

    ከሥነ- ምግባሮች ሁሉ የከበረው ክብር ታማኛነት ነው። ለቃል !~ ለአደራ!~ ለዕምነት!~ ለሰንደቅዓላማ!~ ለዓላማ!~ ለህዝብ የግፍ ዕንባ! … ለትዳር ጓደኛ!~ ለሙያ ሥነ-ምግባር!~ ለዕውነት ፍሬ ነገር!~ ለህዝብ ፍቅር!~
    መታመን ለታማኝነት። መታደል። ሥጦታው የመዳህኒትዓለም ነው። መክሊቱ የአማኑኤል ነው። ሳይተላለፉ መፈጸሙ ደግሞ  የእያንዳንዱ ሰብአዊ ፍጡር መብትና ግዴታ ነው። እርግብ እንኳን ለፍቅረኛዋ ታማኝ ናት! ወንዱም እርግብ ለፍቅረኛው ታማኝ ነው። የሰው ልጅ ግን ተዛነፍ ነው … ይመስለኛል።

    Sunday, 3 February 2013

    ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ በአራት የሚዲያ ተቋማት ላይ ክሥ መሠረተ



    • ክሡ ‹‹ሓላፊና ተጠያቂ የሌላቸውን አንዳንድ የመረጃ መረቦች ዋቢ በማድረግ መሠረተቢስ አሉባልታዎችንና የሐሰት ወሬዎችን በማናፈስ የሽግግር ወቅቱ በሰላም እንዳይከናወን ትርምስ መፍጠርና ሕዝብን ማደናገር›› የሚል ነው
    • ‹‹ቅዱስ ሲኖዶስ የቤተ ክርስቲያኒቱን ቀጣይ ጉዞ በማስመልከት ጉባኤዎችን በማድረግ፣ በውስጥም በውጭም ያለውን ተጨባጭ ኹኔታ በመዳሰስና በሐቅ ላይ በመመርኰዝ የ፮ው ፓትርያሪክ ምርጫ የሚካሄድበትን ኹኔታ በማመቻቸት ተግባራዊ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡›› /የሕዝብ ግንኙነት መመሪያው ለሚዲያ አካላት ካሰራጨው መረጃ/
    • የኛ ፕረስ ጋዜጣ – ዮርዳኖስ ሥዩም ሚዲያ ሓላ/የተ/የግ/ማ
    • ሎሚ መጽሔት – በዳዲሞስ ኢንትርቴይመንትና ፕሬስ ሥራዎች ሓላ/የተ/የግ/ማ
    • አርሂቡ መጽሔት – ሳንኮፋ ሓ/የተ/የግ/ማኅበር
    • ሊያ መጽሔት – ሊያ የኅትመት እና ማስታወቂያ ድርጅት የሚዘጋጁ ናቸው፡፡


    February 3, 2013   ·   0 Comments
    EOTC_HeadQuarter

    የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክን መንበረ ፓትርያሪክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የመንበረ ፓትርያሪክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ሕዝብ ግንኙነት መመሪያ‹‹የሽግግር ወቅቱን በተመለከተ በሚመለከተው አካል መግለጫ ያልተሰጠባቸውን ዘገባዎች እንደተሰጡ አድርገው በማውጣት ግልጽ የኾነ መሠረተቢስ አሉባልታ አናፍሰዋል፤ ሕዝብን አድናግረዋል›› ባላቸው አራት የሚዲያ ተቋማት ክሥ መመሥረቱን አስታወቀ፡፡ ክሥ የተመሠረተባቸው አራቱ የሚዲያ ተቋማት አንድ ሳምንታዊ ጋዜጣ እና ሦስት መጽሔቶች ናቸው፡፡ በስም ዝርዝራቸውም፤ ቅዱስ ሲኖዶስ ‹‹የሽግግር ወቅቱን በሰላም ለማሳለፍ ሌት ተቀን ደፋ ቀና›› በማለት ላይ እንዳለ የገለጸው የመምሪያው ደብዳቤ÷ ሕዝብ ክርስቲያኑን ለማደናገር ኾነ ብለው ይንቀሳቀሳሉ ያላቸው ጋዜጠኞች ዓላማ ‹‹በአባቶች መካከል ጸብና ችግር አለ ብሎ አንባቢው እንዲያምንና ቅዱስ ሲኖዶሱን መበታተን›› ነው፡፡ ደብዳቤው አያይዞም እኒህን ጋዜጠኞች ዝም ብሎ መመልከት ‹‹የጥፋታቸው ተባባሪ መኾን ነው፤›› ስለዚህም ‹‹ጉዳያቸውን ወደ ሕግ አካላት ማድረስና ቤተ ክርስቲያኒቱን ለማተራመስ እያደረጉት ላለው እንቅስቃሴ በሕግ አግባብ ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ ማድረግ የግድ ይኾናል፤›› ብሏል፡፡

    በሕዝብ ግንኙነት መመሪያ ሓላፊው አቶ እስክንድር ገብረ ክርስቶስ ኀይለ ማርያም ፊርማ ለሚዲያ አካላት የተሰራጨው ደብዳቤ እንደገለጸው÷ ክሥ የተመሠረተባቸው የግል ሚዲያ ተቋማቱ ‹‹በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትም ኾነ በሚመለከታቸው አካላት ማብራሪያና መግለጫ ያልተሰጠበትን›› ዜና የሚያወጡት÷ ‹‹ከልዩ ልዩ የመረጃ መረቦች አግኝተናል›› በሚል ነው፡፡ መመሪያው በስም ለይቶ ያልጠቀሳቸውን ‹አንዳንድ› የመረጃ መረቦች ‹‹ሓላፊና ተጠያቂ የሌላቸው›› ሲል ገልጧቸዋል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ስማቸውን ለይቶ ያልዘረዘራቸውንና ‹‹ትክክለኛ መረጃን ለሕዝቡ ለማድረስ የሚመለከታቸውን አካላት በማነጋገር እውነተኛ ዜና የሚያስተላልፉ›› የግል ሚዲያ ተቋማትን አድንቋል፤ አመስግኗል፡፡

    የፓትርያሪክ አስመራጭ ኮሚቴው ሥራውን ጀመረ



    February 3, 2013   ·   0 Comments
    • ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ በኮሚቴው ስብሰባ አልተገኙም
    • ቅ/ሲኖዶሱ የኮሚቴውን ሊቃነ መናብርት ሠይሟል
    • በኮሚቴው እና በቅ/ሲኖዶሱ ሥልጣን መካከል ጥያቄዎች ተነሥተዋል
    • ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል ወደ ዋና ጸሐፊነት ሓላፊነታቸው ተመልሰዋል
    ቅ/ሲኖዶስ ለ፮ው ፓትርያሪክ ምርጫ የሠየመው አስመራጭ ኮሚቴ የመጀመሪያ ስብሰባውን ባለፈው ሳምንት መጨረሻ አካሄደ፡፡ የኮሚቴው ቀዳሚ ስብሰባ የተካሄደው ኮሚቴው በአወዛጋቢ ውሳኔ ታኅሣሥ 6 ቀን 2005 ዓ.ም ከተሠየመ ከአንድ ወር በኋላ በእጅጉ ዘግይቶ ነው፡፡ የመዘግየቱ መንሥኤ ከምርጫው በፊት ለዕርቀ ሰላሙ ፍጻሜ ቅድሚያ ከመስጠት፣ ውጤቱን ከመጠበቅና ለውጤቱ ከመሥራት አኳያ በቅ/ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ላይ በታየው ከፍተኛ ውዝግብ ምክንያት ነው፡፡

    ጥር 6 ቀን 2005 ዓ.ም የቅ/ሲኖዶሱ አስቸኳይ የምልአተ ጉባኤ ስብሰባ ሲጀመር በሚበዙት አባቶች ከፍተኛ ድጋፍ የተሰጠው ይኸው የሰላምና አንድነት አጀንዳ በቀጣዩ የስብሰባው ቀን በውጭ ተጽዕኖ ጭምር ከተቀለበሰ በኋላ የዕርቅና ሰላም ጉባኤው ተስፋ ጨልሞ የምርጫው ሂደት እንዲቀጥል ውሳኔ ተላልፏል፡፡ ቅ/ሲኖዶሱ ታኅሣሥ 8 ቀን 2005 ዓ.ም ባጸደቀው የፓትርያሪክ ምርጫ ሕገ ደንብ አንቀጽ 6/ሀ መሠረት÷ አስመራጭ ኮሚቴው በተቋቋመ በአንድ ወር ውስጥ÷ ለሥራው የሚያስፈልጉትን ግብአቶች፣ የምርጫውን ቦታ፣ ቀንና ሌሎች ከምርጫው ጋራ የተያያዙ ጉዳዮችን በሙሉ ከዝርዝር የድርጊት መርሐ ግብር ጋራ አዘጋጅቶ ለቅዱስ ሲኖዶስ በማቅረብ አስወስኖ ተግባሩን ማከናወን ይጠበቅበታል፡፡ በዚህም መሠረት የኮሚቴው አባላት ታኅሣሥ 26 ቀን 2005 ዓ.ም በብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ በተጻፈላቸው ደብዳቤ መሠረት ጥር 8 ቀን 2005 ዓ.ም በቅ/ሲኖዶሱ ጽ/ቤት ተገኝተው ሥራቸውን እንዲጀምሩ ማሳሰቢያ የተሰጣቸው ቢኾንም የተባለው አልተፈጸመም፡፡ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ አስመራጭ ኮሚቴው የመጀመሪያ ስብሰባውን ሊያካሂድ የቻለውም ቋሚ ቅ/ሲኖዶሱ የኮሚቴውን ሊቃነ መናብርት ከሠየመ በኋላ ነው፡፡ 

    በቋሚ His Grace Abune Estifanosቅ/ሲኖዶሱ ውሳኔ መሠረት የ፮ው ፓትርያሪክ አስመራጭ ኮሚቴን በሰብሳቢነት የሚመሩት የኮሚቴውን በችኮላ መሠየም ከተቃወሙት አባቶች አንዱ የነበሩት ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ ሲኾኑየኮሚቴው ም/ሰብሳቢ ደግሞ ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ ናቸው፡፡ ኮሚቴውንበጸሐፊነት እንዲያገለግሉ የተመረጡት የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ ዋና ሓላፊ ሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ሙጩ መኾናቸው ታውቋል፡፡

    በኮሚቴው የመጀመሪያ ቀን ስብሰባ የኮሚቴው አባል የኾኑት ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ አልተገኙም፡፡ የብፁዕነታቸው በስብሰባው አለመገኘት፣ ቀድሞ በቅ/ሲኖዶሱ ምልአተ ጉባኤ ስብሰባ ላይ ካንጸባረቁት አቋም ጋራ በተገናኘ እንደኾነ ቢገመትም ሌሎች ምንጮች ደግሞ በሀ/ስብከታቸው ከተደረገ የአዲስ ቤተ ክርስቲያን ምረቃ መርሐ ግብር መደራረብ ጋራ አያይዘውታል፡፡ በፓትርያሪክ ምርጫ ሕገ ደንቡ መሠረት 13 አባላት የተሠየሙበት ኮሚቴ÷ በመጀመሪያ ቀን ስብሰባው፣ የእርስ በርስ ትውውቅና የሥራ ክፍፍል ማድረጉ ተዘግቧል፤ በቀጣይ የሚያከናውናቸውን ዝርዝር ተግባራት ከጊዜ መርሐ ግብር ጋራ የመቅረጽ ሥራም መጀመሩ ተገልጧል፡፡ ዐቃቤ መንበረ ፓትርያሪኩ ታኅሣሥ 4 ቀን 2005 ዓ.ም ለአስመራጭ ኮሚቴው አባላት በጻፉት ደብዳቤ መሠረት÷ ኮሚቴው ለ፮ው ፓትርያሪክ ዕጩ ኾነው የሚቀርቡ ከሦስት ያላነሱ ከአምስት ያልበለጡ ተወዳዳሪ ዕጩ ሊቃነ ጳጳሳትን በሕገ ደንቡ ተለይተው ከተዘረዘሩ አካላት በሚቀርቡ ጥቆማዎች አማካይነት ለይቶ እስከ ጥር 30 ቀን 2005 ዓ.ም ድረስ የማቅረብ ሓላፊነት አለበት፡፡

    Friday, 1 February 2013

    ሕዝቡ በምርጫ እንዳይሳተፍ ጥሪ ቀረበ


    ኢሳት ዜና:-መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ኢህአዴግ ሊያካሂደው ባሰበው የአካባቢ ምርጫ እንዳይሳተፍ 39ኙ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጥሪ አቀረቡ።ጥር ፳፬ (ሀያ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

    ፓርቲዎቹ ህዝባዊ ጥሪውን ያቀረቡት ”ኢህአዴግ ስለ አካባቢ ምርጫ የሰጠው መግለጫ የጥያቄዎቻችንን ትክክለኛነትና አግላይ  አቋሙን ያረጋገጠበት ነው” በሚል ርዕስ  ባወጡት መግለጫ ነው።
    የ ኢህአዴግ ምክር ቤት ጸሀፊ አቶ ሬድዋን ሁሴን ፓርቲዎቹ በምርጫ ላለመሳተፍ መወሰናቸውን አስመልክቶ በቅርቡ በሰጡት መግለጫ ፦<<እነሱ ተሳተፉ አልተሳተፉ የሚጨምሩትም፤የሚቀንሱትም ነገር የለም>> ማለታቸው ይታወሳል።
    የ አቶ ሬድዋን መግለጫ ኢህአዴግ ዛሬም በ አገራዊና ህዝባዊ ጉዳዮች ላይ ለሚነሱ ጥያቄዎች በሙሉ ወሳኝም፣ ባለመፍትሔም እኔ ብቻ ነኝ ከሚል የ እብሪት ስሜት አለመላቀቁንና ሀላፊነት በጎደለው ጭፍን ጥላቻ እየተነዳ መሆኑን ያመለክታል ብለዋል።
    ባሻገር አህአዴግ በዋና ጸሀፊው አማካይነት የሰጠው መግለጫ በውሸት የታጀለ እና እርስ በርሱ የሚጣረስ እንደሆነ ፓርቲዎቹ በርካታ አብነቶችን በመጥቀስ አመላክተዋል።
    አክለውም “ይህ አካሄድ ለማንም የማይጠቅም ከመሆኑም በላይ  ብዙ ርቀት ሊያስኬደው እንደማይችል በድጋሚ ሊገለጽ ብቻ ሳይሆን በህዝባዊ ሀይል ሊገታ የሚገባው መሆኑን እንረዳለን” ሲሉም አስጠንቅቀዋል።

    በዳውሮ ዞን ሰዎች እየታሰሩ ነው



    ኢሳት ዜና:-በዞኑ ያለው ችግር እየተባባሰ መሄዱን ተከትሎ ፣ የችግሮች ምንጭ ናቸው የተባሉ ግለሰቦች እየተያዙ ሲሆን፣ መምህር ጸጋየ ገብረመስቀል የተባሉት በቁጥጥር ስር ውለዋል። ሌሎች ሶስት ተፈላጊ መምህራን ለመሸሸግ የተገደዱ ሲሆን፣ ፖሊስ እያሳደዳቸው የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞችም አሉ።ጥር ፳፬ (ሀያ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
    ከትናንት በስቲያ በእስር ላይ ከሚገኙት ከአቶ ዱባለ ገበየሁ እና ከሁለት ጠበቆች የእስር ቦታ ማዛወር ጋር በተያያዘ የታዘዙትን ለመፈጸም ፈቃደኛ ያልሆኑ ኮንስታብል ዘነበ ዶዮ እና ኮንስታብል ሚስታ ናቸው።
    የታሳሪዎቹንና የታሰሩበትን እስር ቤት የሚያሳይ ፎቶግራፍ በፌስ ቡክ ላይ መለጠፉ ያስደነገጠው የዳውሮ ፖለቲካ ክፍል ሃላፊዎች በእስር ቤት እስረኞቹ ኮምፒተር ሳይጠቀሙ አይቀርም በሚል ሥጋት የሌሊት ጥበቃ ፖሊሶች በተጠናከረ ጥበቃ ሌሊቱን እንዲያሳልፉ ልዩ መመሪያ እንደተሰጣቸው ታውቋል።
    ኢሳት እስር ቤት እያሉ ቃለመጠይቅ ያደረገላቸውን አቶ ዱባለ ገበየሁን በልዩ ሁኔታ ክትትል እንዲደረግባቸው የወረዳው ፖሊስ ትእዛዝ ደርሶታል። ከሌሎች እስረኞች ጋር ተቀላቅለው እንዳይታሰሩና ለብቻ ተለይተው እንዲታሰሩ ተደርጓል።
    ሕዝቡን ቀስቅሰዋል በሚል ግምት የታሰሩትን ዐቃብያን ህጎች በግንቦት 7 አባልነት ለመክሰስ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም ለማወቅ ተችሎአል።
    የክልሉ ም/ል ፕሬዚዳንት አቶ አለማየሁ አሰፋ በመሩት የደህዴግ ካድሬዎች ስብሰባ ላይ አባሎቹ ችግሮችን ለማስታገስ ተብሎ የሚወሰደው የእሥራት እርምጃ ሕዝቡን ወደ ከፋ ሁኔታ ሊመራው ይችላል በማለት ስጋታቸውን ገልጸዋል።
    የኔሰው ገብሬ ራሱን አቃጥሎ ባጠፋበት የዳውሮ ዞን የሚነሱ የመብት አሁንም እንደቀጠሉ ነው።