“የኢህአዴግ ስርአት መወገድ አለበት፤ ሙሉ ጊዜዬን ለፖለቲካ ስራ በማዋል ስርአቱን ለመታገል ተዘጋጅቻለሁ”ሀብታሙ አያሌው
በፈጠራ መረጃዎች ብዙዎች እንደታሰሩ ያስታወሰው ሀብታሙ ከዚህ መልዕክት ጀርባ በስውር የሚንቀሳቀሱ የመንግስት የደህንነት ሀይሎች እጅ እንዳለበት እንደሚያምን አስረድቷል፡፡ አያይዞም ያለው ስብዕናና ሀይማኖታዊ አስተዳደግ ከሽብርና ጥፋት ሊያቀራርበው እንደማይችል ተናግሯል፡፡
የባለራዕይ ወጣቶች ማህበር አባላትን “እንዴት ከሀብታሙ ጋር ትሆናላችሁ እሱ ከ ግንቦት ሰባት ጋር ግነኙነት አለው” በማለት በመንግስት ደህንነት ሀይሎች ሀሰተኛ ውንጀላ እየቀረበብኝ ነው በማለት አስረድቷል፡፡
ጨምሮም የማህበሩ አባላት የመንግስት ካድሬዎችና ደህንነቶችን ሴራ ለማጋነጥ እየተዘጋጁ መሆኑን ገልጧል፡፡
ጨምሮም የማህበሩ አባላት የመንግስት ካድሬዎችና ደህንነቶችን ሴራ ለማጋነጥ እየተዘጋጁ መሆኑን ገልጧል፡፡
አሁን ባለው የኢትዮጵያ ሁኔታ በሲቪክ ተቋማት ተደራጅቶ ለውጥ ማምጣት ይቻላል ብሎ እንደማያምን የገለፀው ሀብታሙ አያሌው “የኢህአዴግ ስርአር መወገድ አለበት፤ ሙሉ ጊዜዬን ለፖለቲካ ስራ በማዋል ስርአቱን ለመታገል ተዘጋጅቻለሁ” ብሏል፡፡
ከሀብታሙ አያሌው ጋር ያደረግነውን ሙሉ ቃለምልልስ በድረ ገፃችን ላይ ያገኙታል፡፡
ከሀብታሙ አያሌው ጋር ያደረግነውን ሙሉ ቃለምልልስ በድረ ገፃችን ላይ ያገኙታል፡፡
No comments:
Post a Comment