Friday, 15 February 2013

(Breaking News ሰበር ዜና) ሳይመረጥ የታወቁት 6ኛው ፓትርያርክ አቡነ ሳሙኤል



  • digg
  • 984
     
    Share

(ዘ-ሐበሻ) 6ኛው ፓትርያርክ ሆነው እንዲመረጡ የታጩት ጳጳሳት ስም ዝርዝር ዘ-ሐበሻ እጅ ደረሰ። የዘ-ሐበሻ ታማኝ የቤተክህነት ምንጮች እንዳስታወቁት ለይስሙላ 5 ጳጳሳት ለ እጩነት ይቅረቡ እንጂ 6ኛው ፓትርያርክ ሆነው የሚመረጡት ፓትርያርክ አቡነ ሳሙኤል እንደሚሆኑ ከወዲሁ ታውቋል።

የትግራይ ተወላጁ አቡነ ሳሙኤል ከምንኩስናቸው ጀምሮ የወያኔ ደህንነት እንደነበሩ የሚያስታወቁት የቤተክህነት ምንጮቻችን ከ እርሳቸው ጋር ለ እጩነት የቀረቡትን ጳጳሳት ስም ይፋ አድርሰውናል።

1ኛ . አቡነ ገብርኤል – ትውልድ ወሎ
2ኛ. አቡነ ሉቃስ – ትውልድ ትግሬ
3ኛ. አቡነ ዮሴፍ – ትውልድ ኦሮሞ
4ኛ. አቡነ ማቲዎስ – ምንጃር ሲሆኑ ከ5ቱ እጩዎች ውስጥ ሁለት ከትግራይ መመረጡ አነጋጋሪ ሆኗል ያሉት ምንጮቻችን ከመንግስት ጋር በመስራት በተለይ እርቀሰላሙ እንዳይሳካ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ሲያደርጉ እንደነበሩ የሚነገርላቸው ልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ሆነው እንዲመረጡ መንግስት ከፍተኛውን ጫና እያደረገ እንደሆነ ምንጮቻችን አጋልጠዋል፡። ዘ-ሐበሻ ተጨማሪ መረጃዎችን ይዛ ትመለሳለች። በተለይም ተመላልሰው ይጎብኙን።

No comments:

Post a Comment