Saturday, 23 March 2013

“የህዳሴው ግድብ” ከግማሽ በላይ የኢትዮጵያ አይደለም


ትልቁን ድርሻ ኤፈርት ይዟል

hidassie dam


“በራሳችን መሐንዲስ፣ በራሳችን ገንዘብ፣ በራሳችን የተባበረ ክንድ እንገነባዋለን” በማለት ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በመስቀል አደባባይ ታላቅ ህዝባዊ ድጋፍና “መዓበላዊ መነቃቃት” ፈጠሩበት የተባለለት የ”ህዳሴው” ግድብ 51 በመቶ ድርሻ የኢትዮጵያ እንዳልሆነ ነዋሪነታቸው በአውሮፓ የሆነ ዲፕሎማት በተለይ ለጎልጉል ገለጹ።
ስማቸው ምስጢር እንዲሆን የጠየቁት ዲፕሎማት እንዳሉት 51 በመቶ ባለድርሻ የሆነችው አገር አውሮፓ የምትገኝ የኢትዮጵያ አጋር አገር ናት። ለጊዜው የባለድርሻዋን አገር ስም መግለጽና የውሉን ዝርዝር ይፋ ማድረግ ያልፈለጉት ዲፕሎማት ኢትዮጵያ በግድቡ ላይ የፈለገችውን ውሳኔ በራስዋ ለማስተላለፍ እንደማትችል፤ ያላት ድርሻ 49 በመቶ ብቻ በመሆኑ ድምጽን በድምጽ በሚሽረው በአብላጫ ድምጽ ህግ መሰረት በግድቡ ላይ የሚወሰነው ውሳኔ 51 በመቶ ባለድርሻ በሆነችው አውሮፓዊቷ አገር መሆኑን አብራርተዋል።
49 በመቶ ተብሎ የተገለጸው የድርሻ መጠን ጅቡቲን ጨምሮ የተለያዩ አገሮች የተቀራመቱት መሆኑን ያመለከቱት የመረጃው ባለቤት፣ አገር ውስጥ ካሉት የንግድ ተቋማት መካከል ኤፈርት ትልቁን ድርሻ መውሰዱን እንደሚያውቁ ተናግረዋል።
የመንግስት መስሪያ ቤቶች፣ የግል ባለሃብቶች፣ ማህበራት፣ ባንኮችና የተለያዩ ግለሰቦች በትዕዛዝ አክሲዮን መግዛታቸውን ያስታወሱት እኚሁ ዲፕሎማት “በግድቡ ዙሪያ ከሚፈራው የጸጥታ ችግር በላይ አስጊው ጉዳይ የባለድርሻዎች ምስጢር መሆን ነው” ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል።
መንግስት ለግንባታው የሚሆን ከፍተኛ ገንዘብ ከአውሮፓዊቷ አገር ማግኘቱን ያመለከቱት የጎልጉል ምንጭ፣ “ከአገር ውስጥ በአክሲዮን ስም የሚሰበሰበው ገንዘብ ለአገር ውስጥ በጀት ማሟያና ለመንግስት የስራ ማከናወኛ የሚውል ነው” ብለዋል።
መንግስት በተለያየ መድረክ በተደጋጋሚ ፕሮጀክቱ “በአገር ውስጥ ባለሙያ፣ በአገር ውስጥ ሃብት፣ የሚከናወን የህዳሴ መገለጫ ነው” በሚል ብሄራዊ መነቃቃት የተፈጠረበት የአቶ መለስ ማስታወሻ እንደሆነ ከመግለጽ ውጪ ስለ አክሲዮን ድርሻና አክሲዮን ስለገዙ አገራት እስካሁን የተናገረው የለም።
ግድቡ በመጀመሪያው ምዕራፍ ሲጠናቀቅ 5 ቢሊዮን ዶላር እንደሚፈጅ መገለጹ ይታወሳል። የአባይ ግድብ ከሱዳን ድንበር 10 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ቤኒሻንጉል ክልል እንደሚገኝ መንግስት የግድቡን ሥራ ይፋ ሲያደርግ ማስታወቁ አይዘነጋም።
ይህ በእንዲህ እያለ ፋና በዛሬው እለት ባሰራጨው ዜና “የወንዙን ተፈጥሯዊ የፍሰት አቅጣጫ የማስቀየሩ ስራ እየተሰራ” መሆኑን የገለጸ ሲሆን፥ “ወንዙ ይሄድበት የነበረውን ቦታ 1780 ሜትር ከፍታ ያለው ግድብ የመካከለኛው ክፍል የሚያርፍበት እንደሚሆንም” የፕሮጀክቱ ሥራአስኪያጅ  ኢንጅነር ስመኘው መናገራቸውን ጠቅሷል። “አቅጣጫውን የማስቀየሩ ስራ ከመጭው ክረምት በፊት” ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን መሃንዲሱ ጠቅሰው፥ በቅርቡም ዕውን ይሆናል ብለዋል። ግድቡ ግንባታው የተጀመረበት 1ኛ ዓመት በዓልም ከመጪው ረቡዕ ጀምሮ በአዲስ አበባ፥ እንዲሁም መጋቢት 24 ፕሮጀክቱ በሚገኝበት ስፍራ በተለያዩ ስነ ጥበባዊ ዝግጅቶችና  ‘መለስ ቃልህ ይከበራል፤ ታላቁ የህዳሴ ግድብም በህዝባችን ተሳትፎ እውን ይሆናል’ በሚል መሪ ቃል ይከበራል” በማለት የዜናው ዘገባ ገልጾዋል።

ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (http://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Tuesday, 19 March 2013

ህጻናት እየራባቸው መማር አቅቷቸዋል!


"ምሳ ያላቸው ሲበሉ እኔ የቤት ስራ እሰራለሁ"


students in addis



ህጻናት እየራባቸው ትምህርት መማር እንዳቃታቸው ሸገር አዲስ ኤፍ ኤም ያነጋገራቸው መምህራንና ተማሪዎች ተናገሩ። ሸገር ያነጋገራቸው ተማሪዎች በየተራ እንደተናገሩት በምግብ ችግር ትምህርታቸውን መከታተልና ክፍል ውስጥ ትኩረት ማድረግ ተስኗቸዋል።
“ሌሎች ምሳ ያላቸው ምሳ ሲበሉ እኔ የቤት ስራ እሰራለሁ። ወይም ቤተክርስቲያን እሄዳለሁ” በማለት አንድ ተማሪ ሲናገር፣ ሌላኛው ምሳ የሚባል ነገር እንደማያውቅ ገልጿል። በርሃብ ምክንያት ትምህርታቸውን በወጉ መከታተል ያልቻሉ ተማሪዎች ጉዳይ እንዳሳሰባቸው መምህራኑ ሲናገሩ ሸገር አስደምጧል። በሰሙት ዜና ረፍት ያጡ በርካታ ወገኖች ስልክ በመደወል ተማሪዎቹ በትምህርት ቤታቸው ውስጥ የምሳ አገልግሎት እንዲያገኙ የበኩላቸውን ለማድረግ ሲነጋገሩና ቃል ሲገቡ ለመስማት ተችሏል።
አዲስ አበባ በኑሮ ውድነት ሳቢያ የሚበሉ ያጡ፣ በክፍል ውስጥ ረሃብ እያዞረ ክፍል ውስጥ የሚጥላቸው፣ በየጥጋ ጥጉ አጥርና ጥላ ስር ቀን የሚገፉ፣ የባሰባቸው ቤተሰቦቻቸውን ለማትረፍ ያለ እድሜያቸው ስጋቸውን ለመሸጥ እንደሚገደዱና ቤተሰብ፣ በተለይም እናቶች ልጆቻቸውን ለገበያ ወሲብ ማበረታታት እየተለመደ መምጣቱን የጎልጉል የአዲስ አበባ ዘጋቢ አመልክቷል። (ፎቶ: ተማሪዎች በአንድ የአዲስ አበባ ት/ቤት)

ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (http://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Saturday, 16 March 2013

በጋምቤላ፤ አሜሪካ የዜጋዋን መቃብር ከፍታ መረመረች


የጋምቤላ “አኬልዳማ” እየተደረሰ ነው

crime scene 1
የጎልጉል የጋምቤላ መረጃ አቀባዮች እንዳሉት ጋምቤላ የደረሱት የአሜሪካ ዜጎች የሄዱበትን ጉዳይ ለማከናወን ከክልሉና ከመከላከያ ሰራዊት ባለስልጣናት ዘንድ እክል ገጥሟቸው ነበር።

(ፎቶው የማሳያ ነው)
የፎረንሲክ ባለሙያዎቹ የዜጋቸውን አሟሟት መንስኤና የጉዳት መጠን ለማጣራት ጋምቤላ እንደደረሱ አስከሬኑ በስውር የተቀበረበትን ቦታ ማወቅ እንደሚፈልጉ፣ አስከሬኑ ላይ የዲኤንኤ ምርመራ በማካሄድ የሟችን ትክክለኛ ማንነት ለማረጋገጥ፣ የጉዳቱን መጠንና በምን ያህል ጥይት እንደተደበደበ ለማጣራት፣ ከዚያም በላይ ለምርመራ ስራቸው ይረዳቸው ዘንድ የሚፈልጉትን መረጃ ለመሰብሰብ ድርጊቱ የተፈጸመበት ቦታ መሄድ እንደሚፈልጉ ጠይቀው እንደነበር ለክልሉ መንግስት ቅርብ የሆኑ ለጎልጉል ገልጸዋል።
ጥያቄውን መቀበል የተሳናቸው የመከላከያና የክልሉ ባለስልጣናት አስከሬኑ መመርመር የማይችልበት ደረጃ ላይ መድረሱን፣ ከተቀበረ የቆየ በመሆኑ ለማውጣት አስቸጋሪ እንደሆነና እንደማይቻል ለመርማሪዎቹ ገልጸው ነበር። “ስራው የኛ ነው” ያሉት መርማሪዎቹ አስከሬኑ በየትኛውም ደረጃ ላይ ቢገኝም ማየት እንደሚፈልጉ፣ ይህ አቋም እንደማይቀየር መሆኑን አመልክተው አስከሬኑ የተቀበረበት ቦታ ደርሰው የሚፈልጉትን ምርመራ ማድረጋቸው ታውቋል። አከራካሪ የነበረውና ግድያው የተፈጸመበት ቦታ የመጓዙ ጉዳይ እንደነበር የጠቆሙት የመረጃው ምንጭ፣ የቀረበው መልስ አስገራሚ እንደነበር ይገልጻሉ።
“ቦታው ላይ ደም የለም፣ ማንንም አታገኙም፣ ምን ያደርግላችኋል?” የሚሉ መከራከሪያዎችን ባለሥልጣናቱ  ቢያቀርቡም ተቀባይነት ማግኘት አልቻሉም። አጣሪዎቹ ወደ ስፍራው ከመሄዳቸው በፊት ካድሬዎች ሽማግሌዎችንና ያካባቢው ነዋሪዎችን በማባበል የቅስቀሳና ፊልም የማዘጋጀት ስራ ለመጀመር በዝግጅት ላይ መሆናቸውን የጎልጉል ምንጮች አመልክተዋል።
ምንጮቹ እንዳሉት የአካባቢውን ነዋሪዎች ለማባበል አሳ አስጋሪዎቹ ሲጨፈጨፉ የታሰሩት የቀበሌ ሊቀመንበር ከልጆቻቸው ጋር ከእስር እንዲፈቱ ተደርጓል። ከዚህም በተጨማሪ አንድ ወጣት ከእስር ነጻ እንዲሆን በተላለፈ ውሳኔ መሰረት ተለቅቋል። ይህ ሁሉ የሚደረገው የአካባቢውን ሽማግሌዎች ለማባበልና “የጋምቤላ አኬልዳማ” በማለት የሚሳለቁበት ዘጋቢ ፊልም በተሳካ ሁኔታ እንዲሰራ ለመቀስቀሻነት ነው።
በጊሎ ወንዝ ዳርቻ ወደምትገኘው አብሌን በማምራት የበጋውን ደረቅ ወቅት ከወንዝ አሳ በማስገርና ያገኙትን በማደን ቀን እየገፉ ሳለ የካቲት 21፤2005ዓም (28/2/13) በድንገት የመከላከያ ሰራዊት ከበባ አካሂዶ ተኩስ በመክፈት አስራ ሁለት የሚጠጉ ንጹሃንን መግደሉን መዘገባችን ይታወሳል። እዚህ ቦታ ደርሶ ማጣራት ማካሄድ የሚፈልጉት የፎረንሲክ ባለሙያዎች ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ሰዓት ድረስ ወደ ስፍራው አልተነቃነቁም።

Friday, 15 March 2013

በሚዲያ መረሳት ያስፈራል


“ነጻ ፕሬስ ከሌለ አገር አደጋ ላይ ነው”

the meeting


“ከምድር በታች ጨለማ ቤት ውስጥ የታሰሩትን በቀን ለ10 ደቂቃ እናያቸዋልን። ልብ የሚነካ ነው። የብርሃን ማነስ አይናቸውን እንደጎዳቸው ያስታውቃሉ … ሴቶችን በተገኘው ሰበብ ያስሯቸዋል። ምክንያት ፈልገው እስር ቤት ይከቷቸዋል። ከዚያም ይደፍሯቸዋል። በርካታ የተደፈሩ እህቶች አሉ። የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትና መንግሥት ያሰማራቸው ሚሊሻዎች ይህንን አሳዛኝ ድርጊት እንደፈጸሙ ተነግሮናል” ይህ ማዕከላዊ እስር ቤት ታስሮ፣ ችግሩ ባለበት ቦታ ተገኝቶ የነበረው ስዊድናዊ የፍሪላንሰር ጋዜጠኛ ማርቲን ካርል ሻቢዬ ቃል ነው።
ስለ ማዕከላዊ እስር ቤት መስማት ይጨንቃል። ሰዎች በሲቃ የሚያሰሙት የጣር ድምጽ ለጆሮ  የተለመደ ነው። ከመሬት በታች የጨለማ ክፍል አለ። በዚህ መታጎሪያ ውስጥ ሆነው ስቃይ የሚፈራረቅባቸው ወገኖች ጥቂት አይደሉም። ማዕከላዊ ብዙ ጉድ ያለበት ሲኦል ነው። የሰው ልጆች በግፍ ማቅቀውበታል። እየማቀቁበትም ነው። ለውጥ እስከሌለ ድረስ የሚቆም አይመስልም። በመሃላ የሚነገርለት ውርስና ይቀጥላል የሚባለው የመለስ ራዕይ አንዱ ክፍል ይህ ነው።
መጋቢት 3፤2005 (3/12/2013) በኖርዌይ ኦስሎ የሥነጽሁፍ ቤት (ሊትሬቸር ሀውስ) በተዘጋጀ የመወያያ መድረክ ላይ ሁለቱ ስዊድናውያን ጋዜጠኞች ተገኝተው ነበር። መድረኩን ያዘጋጀው ደግሞ NOAS በሚል ስያሜ የሚታወቀው የስደተኞች ተሟጋች ድርጅት ነው። የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር አን-ማግሬት ኦስቴና ሁለቱን እንግዶች ካስተዋወቁ በኋላ መድረኩን እየመሩ ውይይቱ ተካሄደ። በዚህ ውይይት ላይ ሁለቱ ጋዜጠኞች እየተፈራረቁ የደረሰባቸውንና በትክክል ያዩትን አስታወቁ።
ማርቲን ካርል ሻቢዬና ባልደረባው የፎቶ ጋዜጠኛ ጆሃን ካርል አበክረው የሚናገሩት ስለ ሙያቸው ነው። “ጋዜጠኛ ለመጻፍ ማየትና ማነጋገር አለበት። በተለያዩ አገራት ጋዜጠኞች ችግር ባለባቸው ቦታዎች ገብተው ለመዘገብ ድንበር ያቋርጣሉ። አሁን በሶሪያ፣ ቀደም ሲል በሊቢያ የሆነው ይህ ነው። በኢትዮጵያ ግን ሽብርተኛ ያሰኛል” ሲሉ ግርምታቸውን ይጀምራሉ።

ኢትዮጵያ ፊን ፊሸር ሰላዩ ቫይረስ





ፊን ፊሸር የተባለ የስለላ የኮምፕዩተር ፕሮግራም በዓለም 25 ሀገሮች ዉስጥ መሠራጨቱንና መንግስታቱም የገዛ ዜጎቻቸዉን ለመሠለል እንደሚጠቀሙበት አንድ ጥናት አመለከተ። ኢትዮጵያ ዉስጥም በሠፊዉ ሥራ ላይ እየዋለ መሆኑን ጥናቱ ይፋ አድርጓል።
የኢንተርኔት ቫይረሱ ኮምፕዩተር ዉስጥ ከገባ ግለሰቦች በኮምፕዩተራቸዉ ላይ የሚያደርጉትን የፅሁፍ የድምፅና የምስል የመልዕክት ልዉዉጦች ወደዋና መረጃ ማሰባሰቢያዉ ማዕከል ይልካል። ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች RSF ኢትዮጵያ ዉስጥ ኢንተርኔት ላይ የሚደረገዉን ቁጥጥር አስመልክቶ የተጠቀሰዉ የስለላ የኮምፕዩተር ፕሮግራም ሥራ ላይ መዋሉን ጥናቱን ጠቅሶ ለዶቼ ቬለ መግለፁን ዘግበናል። ዶቼቬለ ስለጉዳዩ የጠየቃቸው የኢትዮ ቴሌኮም የኮምንኬሽን ኦፊሰር አቶ አብዱራሂም አህመድ ኢትዮ ቴሌኮም በተጠቀሰው ፕሮግራም እንደማይገለገል በስልክ ተናግረዋል። አቶ አብዱራሂም ስለጥናቱ ውጤት እንደማያውቁ ገልፀው ሆኖም ፊን ፊሸር የተባለው የስለላ የኮምፕዩተር ፕሮግራም ኢትዮጵያ ውስጥ ሥራ ላይ ውሏል መባሉን ከዕውነት የራቀ ሲሉ አጣጥለውታል።
ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት RSF በያዝነዉ ሳምንትባወጣዉ የኢንተርኔት ቁጥጥርን የሚመለከት ዘገባ አምስት ሀገሮችን የኢንተርኔት ጠላት ሲል ፈርጇል። የሶርያ፤ ቻይና፤ ኢራን፤ ባህሬን እንዲሁም የቬትናም መንግስታት የኢንተርኔት መረጃዎችን ለመቆጣጠር ከሚሰነዝሩት የድረገፅ ጥቃት በተጨማሪ ዜጎችን ለመሰለል የግለሰቦችን የኢሜል መረጃ የሚያጠምዱ ፕሮግራሞችን በመጠቀም ግንባር ቀደም ተብለዋል። ከበርካታ ሀገሮች እነዚህ አምስቱ የተመረጡትም ለኢንተርኔት ቁጥጥሩ የሚጠቀሙበት ቴክኒዎሊጂ መራቀቅና በዚህ ስለላ መሠረትም ጋዜጠኞችና ዜጎቻቸዉን በማሰራቸዉ እንደሆነ የRSF የዘመናዊ መገናኛ ብዙሃን ዘርፍ ተመራማሪ ግሬግዋ ፑዤ ገልፀዋል። በተለይም ቻይና የኤሌክትሮኒክ መከላከያዋ ከዓለም ምናልባትም የረቀቀ ተብሎ ሲገመት ይህንኑ ቁጥጥሯን ለማጠናከር የግል ኢንተርኔት ኩባንያዎች ዜጎቿን ለመሰለል የሚረዱ ስልቶችን እንዲያቀርቡላት ማድረጓም ተገልጿል። ኢራን በበኩሏ የራሷን «ሃላል ኢንተርኔት» በሚል አቋቁማ የኢንተርኔት መረጃ ቁጥጥሯን አጠናክራለች። RSF የተራቀቀ ቴክኒዎሎጂን ሳይኖራቸዉ አምባገነን መንግስታት ዜጎቻቸዉን ለመሰለል እንደማይችሉ በማመልከት ለመጀመሪያ ጊዜ ተባባሪ የኢንተርኔት ጠላቶች ሲል የመሰለያ ፕሮግራሞችን የሚሰሩና ለሀገራቱ የሚያቀርቡ ድርጅቶችንም ስም አጋልጧል። ፈላጭ ቆራጭ መንግስታት ዜጎቻቸዉን በኢንተርኔት መረጃ ልዉዉጥ ሳይቀር እንዲቆጣጠሩና እንዲሰልሉ ስልቱን እያስተካከሉ የሚያቀርቡትን አምስት የግል ኩባንያዎችም የዘመኑ «ቅጥረኛ ነፍሰ ገዳዮች» ሲል RSF ወቅሷል።

Thursday, 14 March 2013

ኢትዮጵያ የኢንተርኔት ስለላና ቅኝት



ዘመኑ የኢንተርኔት ብሎም የመረጃ ተብሎ ቢነገርለትም በኢንተርኔት የተሰራጩ መረጃዎችን ለማገድ እርምጃ የሚወስዱ አካላት መበራከታቸዉ ይታያል። በኢንተርኔት ላይ ጥብቅ ቁጥጥርና ስለላ የሚያካሂዱ ሀገሮችን ዝርዝር ይፋ ያደረገዉ ዘገባ ቁጥጥር የሚያደርጉ መንግስታትን ብቻ ሳይሆን ለእነሱ ቴክኒዎሎጂዉን የሚያቀርቡ ኩባንያዎችንም ማንነት አጋልጧል።
ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት RSF በያዝነዉ ሳምንት ባወጣዉ የኢንተርኔት ቁጥጥርን የሚመለከት ዘገባ አምስት ሀገሮችን የኢንተርኔት ጠላት ሲል ፈርጇል። የሶርያ፤ ቻይና፤ ኢራን፤ ባህሬን እንዲሁም የቬትናም መንግስታት የኢንተርኔት መረጃዎችን ለመቆጣጠር ከሚሰነዝሩት የድረገፅ ጥቃት በተጨማሪ ዜጎችን ለመሰለል የግለሰቦችን የኢሜል መረጃ የሚያጠምዱ ፕሮግራሞችን በመጠቀም ግንባር ቀደም ተብለዋል። ከበርካታ ሀገሮች እነዚህ አምስቱ የተመረጡትም ለኢንተርኔት ቁጥጥሩ የሚጠቀሙበት ቴክኒዎሊጂ መራቀቅና በዚህ ስለላ መሠረትም ጋዜጠኞችና ዜጎቻቸዉን በማሰራቸዉ እንደሆነ የRSF የዘመናዊ መገናኛ ብዙሃን ዘርፍ ተመራማሪ ግሬግዋ ፑዤ ገልፀዋል።


በተለይም ቻይና የኤሌክትሮኒክ መከላከያዋ ከዓለም ምናልባትም የረቀቀ ተብሎ ሲገመት ይህንኑ ቁጥጥሯን ለማጠናከር የግል ኢንተርኔት ኩባንያዎች ዜጎቿን ለመሰለል የሚረዱ ስልቶችን እንዲያቀርቡላት ማድረጓም ተገልጿል። ኢራን በበኩሏ የራሷን «ሃላል ኢንተርኔት» በሚል አቋቁማ የኢንተርኔት መረጃ ቁጥጥሯን አጠናክራለች። RSF የተራቀቀ ቴክኒዎሎጂን ሳይኖራቸዉ አምባገነን መንግስታት ዜጎቻቸዉን ለመሰለል እንደማይችሉ በማመልከት ለመጀመሪያ ጊዜ ተባባሪ የኢንተርኔት ጠላቶች ሲል የመሰለያ ፕሮግራሞችን የሚሰሩና ለሀገራቱ የሚያቀርቡ ድርጅቶችንም ስም አጋልጧል።

Wednesday, 13 March 2013

መነገር ያለበት ቁጥር አምስት “መሪዎቻንን የት አሉ?”



በልጅግ ዓሊ
እኔ ምን አገባኝ የምትለው ሐረግ፣
እሱ ነው ሃገሬን ያረዳት እንደበግ፣
የሚል ግጥም ልጽፍ፣
ስሜት አንዘርዝሮኝ ብድግ አልኩኝና፣
ምን አገባኝ ብዬ ቁጭ አልኩ እንደገና ።
ኑረዲን ዒሣ
ጀርመን ፍራንክፈርት በታማኝ በየነ ስብሰባ ታምሳ ከረመች። ከብዙ ጊዜ በኋላ እንደገና ብዙ የፍራንክፈርት አካባባቢ ነዋሪዎች ተገናኝን። አልፎም ተርፎም ችግራችንን ተወያየን። በዚሁ አጋጣሚ ይህንን ዝግጅት ላዘጋጁት ለወ/ሮ አሳየሽኝና ለአቶ ጥላሁን ምስጋናየን በግሌ አቀርባለሁ።
ብዙ ተናጋሪዎች ፣ ብዙ ምርጥ ዝግጅቶች ስለነበሩ በደስታ ስንከታተል ቆየን። በመጨረሻም ታማኝ ንግግሩን ጀመረ። እኔ ማነኝ? በሚል ነበር የጀመረው። ራሱን ዝቅ አድርጎ ሃገራችን የመሪ እጦትን እንደደረሰባት አስረዳን። እሱ ስለመሪ እጦት ሲያስረዳን እኔ በሃሳብ ፍራንክፈረት ያስተናገደቻቸውን <<መሪዎቻችን>> አስባቸው ነበር። የመጀመሪው ስብሰባ የኢንጅነር ኃይሉ ሻውል ነበር። ከዛ በኋላ ብዙ ስብሰባዎች አድርገናል። ከብዙ አድካሚ ጉዞ በኋላ ነው ዛሬ በታናሽ ወንድም ታማኝ ስብሰባ ላይ የተገኘነው።
ዛሬ እነዛ ፍራንክፈርት ያስተናገደቻቸው <<መሪዎቻችን>> ሁሉ የት አሉ ? የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል። ይህንን ጥያቄ ለመመለስ ልብ ድካም የሌለበት ሰው መሆን ያስፈልጋል። <<የፍራንክፈርት የስብሰባ ታሪክ ከኃይሉ ሻውል እስከ ታማኝ ድረስ>> ብዙ ነው። ወያኔን ለመዋጋት ሠራዊት አስልፈናል ብለው የፎቶግራፍ መረጃ ይዘው ከመጡት ጀምሮ እስከ ወያኔን በቅርብ እንጥለዋለን የሚል መፈክር ያነገቡ ብዙ <<መሪዎችን>> አይተናል። ይመሩናል፣ ለድልም ያበቁናል ብለን አጨብጭበን፣ የቻልነውን አድርገን የሸኘናቸው፣ እንኳን ሁላችንን አንድ አድርገው ሊመሩን የራሳቸውን ድርጅት ሲበትኑና ሲከፋፍሉ ያየናቸው ብዙ ናቸው። ከዚህን አልፈው ወያኔን የተቀላቀሉ ትንሽ አይደሉም። ፍራንክፈርት ብዙ አይታለች። ብዙም ታዝባለች።
ከኤርትራውያን ጋር ጥርስ የተናከስንበት፣ ሁላችንም ዘብ የቆምንበት የጎሹ ወልዴ ስብሰባ ትዝ ይለኛል። ፍራንክፈርት ውስጥ መድህን ጠንካራ ከሚባሉት ድርጅቶች አንዱ ነበር። የፍራንክፈርትን የጸረ ወያኔ ትግል የመድህን መፈረካከስና ብሎም መፍረስ አዳከምው ብል ስህተት ላይ አልወድቅም። በታማኝ ስብሰባ ላይ ላገኘኋቸው የመድህን አባሎች ፊት ለፊት ስለሞገትኳቸውም አሁን ሃሜት አይሆንብኝም። አዎ ዛሬ ያ ድርጅት የለም። ቢኖርም እንዳለ አይቆጠርም። ግን አባሎቹ አሁንም ለኢትዮጵያዊነት እንደቆሙ አሉ።
ሌላው ድርጅት የቀድሞው መላው ዐማራ(መዐአድ) የአሁን መኢአድ ነበር። በአባላትም በጥንካሬም ሰፋ ያለ ነበር። ይህ ድርጅት በጸረ ወያኔ ትግል በጀርመን ውስጥ የማይካድ አስተዋጽኦ አድርጎ አልፎል። ከዚህ ድርጅት ብዙ አመራሮች ተጋብዘው ተጠርትን ነበር። ዛሬ የዚህ ድርጅት መሪዎች ማለት የመኢአድ መሪዎች ከአባላቶቻቸው ጋር እንደማይገናኙ የታወቀ ነው። ፍራንክፈርት የሚገኙ የዚህ ድርጅት አባላት አሁንም ኢትዮጵያዊነትን እንዳነገቡ ነው።

Monday, 11 March 2013

ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ሲጋለጥ





በዳዊት ሰለሞን
የፍኖተ ነጻነት ጋዜጣ ባልደረባ መሆኔ ጋዜጣዋን ማተሚያ ድርጅቱ አላትምም ያለበትን ምክንያት ከሶስተኛ ሰው እንዳልሰማ አድርጎኛል፡፡ስማቸውን እንዳንጠቅስባቸው የተማጸኑ አንድ ሃላፊ‹‹ሰዎች እየደወሉ ይህ ጋዜጣ ባለስልጣናቱን የሚሳደብ በመሆኑ ማተም የለባችሁም››ብለውናል ስለዚህ አናትምም በማለት ነግረውን ነበር፡፡የሰደብነው፣ያዋረድነው ባለስልጣን የትኛው ነው;ይህንንስ ያደረግነው በየትኛው ህትመት ነው;ሰውዬው ለዚህ ምላሽ ለመስጠት ሳይፈቅዱ ተለዩን፡፡ አሁን አንድ ወዳጄ በፌስ ቡክ ገጹ ለዚህ ተቃራኒ የሆነ የብርሃንና ሰላም ደምበኛን ይዞ ቀርቧል፡፡በምስሉ ላይ የምትመለከቱት ጋዜጣ ስያሜ ህዳሴ ሲሆን ባለቤቷ ገዢው ፓርቲ ነው፡፡የጋዜጣው የጀርባ ገጽ አንድ ሰው ሲሸለም ያሳያል (ልክ እንደ ሚሊኒየር ገበሬዎችን ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ይሸልሙ እንደነበሩት) ፡፡ሸላሚው የኢህአዴግ ጉባኤ በሚመስለው ፓርላማ ተቃዋሚዎችን በመወከል አንድ መቀመጫ ያገኙት የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉ ናቸው፡፡በግርማ የሚሸለመው ሰው ላይ‹‹ህገ መንግስቱን መጣስ››የሚል ጹሁፍ ተለጥፏል፡፡የጋዜጣው የካርቶን ስዕል መልእክት ድብቅ አይደለም፡፡ግርማና የግርማ የሆነ ሁሉ ህገ መንግስቱን የሚጥስ ነው በማለት ሽብር መፍጠር ነው፡፡አንድ የምክር ቤት አባልን እንዲህ መወንጀል ለብርሃንና ሰላም ወይም ለእነ አቶ ሽመልስ ከማል ወንጀል ያልሆነበት ምክንያት አይገባኝም፡፡




በነገራችን ላይ ፓርላማው የአባላቶቼ መልካም ስም ጎደፈ በማለት ለአዲስ ጉዳይ መጽሄት ማስጠንቀቂያ ጽ ፏል፡፡እንዴት ነው ነገሩ አቶ ግርማ የምክር ቤቱ አባል አይደሉምን ; በአደባባይ ማስረጃ በሌለበት ሁኔታ ህገ መንግስቱን መጣስን ይሸልማሉ በማለት ሲወነጅላቸው ምነው የአዲስ ጉዳይ ከሳሾች ህዳሴን ዘነጓት;

ብርሃንና ሰላም ድርጅት ኢህአዴግ ሲመታ ማልቀስ ካልዳዳው በስተቀር ደምበኞቹን በእኩል አይን መመልከት ግዴታውና ሃላፊነቱ ነው፡፡አልያ ፍኖተ ነጻነት መንግስትን ስትተች ተሳደበች እያለ መዝጋት የህዳሴን የተገለጠ ስድብ ደግሞ እንደ ምርቃት በመቁጠር ልዩነት ማድረግ ስውሩ እጅ ጋር ከማድረስ ውጪ ምንም ትርጉም አይኖረውም፡፡እርግጥ ነው የዚህ መድሃኒቱ የራስን ማተሚያ ማሽን መግዛትና ያን ግዜ ደግሞ የሚሆነውን ማየት ነው፡፡ ይብላኝለት ለብርሃንና ሰላም እንጂ እኛማ በተባበረ ርብርብ ማሽኑን ልንገዛው ነው፡፡
ተዛማጅ ፅሁፎች:


እኛና እነሱ – የሁለት ሀገር ሰዎች ነን



ከሥርጉተ ሥላሴ 10.03.2013

እም! ብዬ እያማጥኩ ጀመርኩት።
eprdf leanders in ethiopia
(ፎቶ – ከኢትዮጵያ ከረንት አፊርስ ዲስከሽን ፎረም የተወሰደ)
እኛ ማነን? እኛ የተቀመምንበት ኢትዮጵያዊነት የሚያንገበግበን። ችግሯ – ችግራችን፤ ዕንባዋ – ዕንባችን፤ መከፈቷ – መከፈታችን፤ ጉስቁልናዋ – ጉስቁልናችን፤ አንገት መድፋቷ ሃዘናችን የሆነው በዬትኛውም ዓለም የምንገኝ ልጆቿ ነን። በወያኔ መዳፍ ውስጥ አሳሩን በማዬት የሚገኘው ከስሜን እስከ ደቡብ ጫፍ፤ – ከዱቡብ ጫፍ እስከ ምዕራብ ጫፍ፤ ከምዕራብ ጫፍ እስከ ምስራቅ ጫፍ የሚገኝ ህዝብ ለሀገሩ ልዩ መለዮችን የሆነው ሥጋና ደም ነን።
እነሱስ? „የደላው ገንፎ ያላምጣል“ እንዲሉ ከማህደረ – ኢትዮጵያዊነት ትንሽ ልቅላቂ ያልፈጠረላቸው፤ አለቶች … በዕንባ ላይ ይሾማሉ፤ ይሸለማሉ …. ልጆቻቸውን አንደላቅው ያሰተምራሉ፤ ሲሰኛቸው ውጬ ልከው ዶላር አፍሰው ያዝመነምናሉ።
ባይታዋሩ ወገናችን ደግሞ ዕጣ ፈንታው … ሥራ ፍለጋ በሺህዎች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን፤ በውሃ ጥም፤ በመንገድ ጉዞ አቅም በማነስ፤ በውሃ ሙላት፤ በጾታ ጥቃት፤ በቀጣሪ ዳባ እንደተበተነ ያልቃል፤ እንዲሁም ካሰቡት ሳይደርሱ የአሞራ እራት ይሆናል። በስደቱ በእሳት የሚቀቀሉት፤ ከፎቅ ተከስከስሰው የሚሞቱት፤ በጭንቀት በሽታ አብደው አድራሻቸው ጠፍቶ የሚቀሩትንማ ስሌትም አይገታውም። እንደ ጣሊያን በመሳሰሉት ሀገሮችም መንገድ ላይ ተዳዳሪ ወገኖቻችን በሚመለከት — ቤቱ ይቁጠረው።
ሞተን እያዩ ወደ ሞት ፊት ለፊት የሚገሰግሱ፤ በልተን እንሙት ብለው ከሞት ጋር የሚፋጠጡት ሴተኛ አዳሪ እህቶቻችን ቁጥርም ከሌሎች የችግሩ ሰለባ ከሆኑት ወገኖቻችን ቁጥር
Ethiopian girl holding baby gott
(ፎቶ – ከኢትዮጵያ ከረንት አፊርስ ሆም ፔጅ – ሰርቫይቫል ኢንተርናሽናል ከሰጠው መግለጫ ትርጉም – የተወሰደ)
ቢበልጥ እንጂ ከቶውንም አያንስም። ጧሪ ጠዋሪ አጥተው ቤት እንደ ተዘጋባቸው የሚያልፉት አዛውንታት በእርግማን ለወግ ሳናበቃቸው አፈር ራታቸው፤ ድንጋይ  ትራሳቸው ሆኗል። ሊለምኑ ያፈሩ አካሎቻችን ቁጥር የትዬለሌ ነው። ከመሬት የሚፈናቀሉ ወገኖቻችን ልጆቻቸውን ለመሸጥ ነፍሳቸው እንዲሰነብት ተሰልፈዋል …. ለመራራ ስንብት፤
የጥንተ – ጥዋቱ የአባት አደሩ ወግና ባህል ቀርቶ ዛሬ በገበሬው መንደር ሳይቀር ቡና እንኳን ብቻ – ለብቻእንደ አውሮፓ የሚጠጣበት ዘመን ተድርሷል። ለቡናውም የቡና ቁርስ አሯል። እንግዲህ እኛ የዚህ እርቃኑን – መለመላውን ያለ፤ ለዕለት ጉርስና ከፈን ያልበቃ፤ መጠለያ የሌለው ወገንተኛ ነን፤ ቀኑ እራሱ የተጋጠ የተመለመለ ነው የማረተበት!

Saturday, 9 March 2013

የህወሓት ስረወመንግስት በኢሕኣዴግ ጡዘት


“የህወሃት የበላይነት በእኩልነት”

MINILIK SALSAWI (ምንሊክ ሳልሳዊ)
ተጠፍጥፈው በወያኔ የተሰሩት የኢሕኣዴግ አባል ድርጅቶት እስከዛሬ እንዳልተዋሃዱ የሚታወቅ ነው:: እንዚህ ድርጅቶች ባለፉት 20 አመታት ውስጥ ያልተዋሃዱበት እና በአንድ
tplf rotten apple
ፓርቲ እና ግለሰብ ስር እየተሽከረከሩ የኖሩበት ሁኔታ በበረሃው የመሃላ ፖለቲካ አለምብሰላቸው ወደ ሕወሓት ስረወመንግስት ውሳኔ ሰጪነት ሳያሸጋግራቸው የፖለቲካ ባሮች እንደሆኑ አሉ::ርእዮት አለሙ እጅግ ወደ ኋላ የቀረ እና የአስተሳሰብ ጥልቀቶች አለመኖር ፓርታዊ ዲሞክራሲን ማእከል አለማድረጋቸው የውህደት ምህዳሩ እንዲደፈን እና ብሔር ተኮር የውህደት አደረጃጀት ወደ ሃገራዊ ፓርቲነት እንዳይለወጡ ለውህደቱ ዚግዛግ እደምታ አስከትሎበታል::ይህ ደሞ ሕወሓት የበላይነቱን እዳያጣ እና ስረወመንግስት እንዳይደረመስ ከመፍራት በመጣ የተቀነባበረ የፖለቲካ ሴራ ነው::

በባህር ዳር ይካሄዳል ተብሎ እየተጠበቀ ያለው የኢሕኣዴግ ጉባኤ እጅግ በተጠንቀቅ እየተጠበቀ ሲሆን ፓርቲዎች ላለፉት አመታት እየተደረገባቸው ያለውን የፖለቲካ ጭቆና በተመለከተ ያፈነዱታል ተብሎ ተሰግቷል:: ለዚህን በአሁን ሰአት አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል:: የግንባሩ አባል ድርጅቶች በሕወሃት ላይ ያላቸውን ጥላቻ ያንጸባርቁበታል ድርጅታዊ መብታቸን በፋት ይጠይቁበታል የተባለለት ይህ ጉባየ ሌሎች ችግሮችንም እንደሚወልድ እየተነገረለት ነው::እነዚሁ አባል ድርጅቶች “የህወሃት የበላይነት በእኩልነት” የሚል አዲስ አስተሳሰባቸውን ይዘው ስለሚቀላቀሉ ፍራቻውን ለማስወገድ ተሳታፊ አባላት ሲመረጡ ጥንቃቄ እንዲወሰድ ስራዎች ተሰርተዋል::በግንባሩ ላይ የለውጥ ተጸኖ ያሳድራሉ የተባሉ ተሳታፊዎች ወደ ባህር ዳር እንዳይዘልቁ በመደረጉ ችግሮች እንዳመረቀዙ ነው ያሉት::

“በፌዴራል ተደብድባችሁ ትባረራላችሁ!”



benishangul asosa



“አማራ መሆን ወንጀል ነው? የሌሎች ብሔረሰብ አባላት በፈለጉበት ክልልና ስፍራ ይኖራሉ። አማራ ክልል ውስጥ ሰፊ መሬት ወስደው የሚኖሩ አሉ፤ የሚነካቸው የለም። አማራው እየተመረጠ ለስደት፣ ለመከራ፣ ለእንግልት ይዳረጋል? እስከመቼ በዚህ ይቀጥላል? ክልሉን እንመራለን፣ የአማራ ህዝብ ወኪል ነን የሚሉ የት ናቸው? ያሳዝናል፣ ለአማራው አልቅሱ፣ ለአማራው አንቡ፣ አማራው አለቀ …”  ሲል በስልክ ለጎልጉል አስተያየቱን ሰጠ። መናገር አይችልም፤ ሲቃ ልሳኑንን አንቆ ይዞታል።
ከዓመታት በፊት መተከል ዞን ፓዌ የተካሄደውን ያነሳል። 1984 – 85 ፓዌ መንደር አራት በሚባለው የገበያ ቦታ እየገበዩ የነበሩ የአማራ ተወላጆች ያላሰቡት ደረሰባቸው። በድንገት ገበያው ታወከ። የቻሉትን በቀስት፣ ሌላውን በጥይት ለቀሙት። 56 ሰዎች በቅጽበት ተረሸኑ። ይህ ሁሉ ሲደረግ አገር የሚመሩት ባለስልጣኖች ድምጻቸውን አላሰሙም ነበር። አሁንም በተቆራረጠ አንደበት አስተያየቱን ቀጠለ።
በወቅቱ ፓዌ እንደነበር ያስታወሰው አስተያየት ሰጪ “አሰፋ ኢናቦ” ሲል ስም ጠራ። አሰፋ ኢናቦ የመተከል ዞን አስተዳዳሪ ነበር። ድንገት በደረሰው ጭፍጨፋ የተበሳጩ ከመንደር አራት ስምንት ኪሎሜትር ርቆ በሚገኘው አውሮፕላን ማረፊያ አሰፋ ኢናቦን አስገድደው ወሰዱት። በመጨረሻም ሰፋሪውን እያሳዩ የበቀል ኃይላቸውን አሳረፉበት፤ ቦጫጨቁትና እዛው ተቀበረ። በስፍራው ስለተደረገው ሁሉ በቂ መረጃ ያለው መሆኑን የሚናገረው አስተያየት ሰጪ እንደሚለው በቀትር በአደባባይ ህዝብ የጨፈጨፉትና ያስጨፈጨፉት አልታሰሩም። ህግ ፊት አልቀረቡም። ለይስሙላ ታስረዋል ተብለው ተለቀዋል።

Thursday, 7 March 2013

የጉራፈርዳ ተፈናቃዮች ልጆቻቸውን ጉዲፈቻ ለመስጠት እየተማጸኑ ናቸው



  • 73
     
    Share
Guraferda
የጉራፈርዳ ተፈናቃዮች
ከደቡብ ክልላዊ መንግስት ቤንች ማጂ ዞን ጉራፈርዳ ወረዳ በመፈናቀል ላይ ያሉ ዜጎች ልጆቻቸውን በጉዲፈቻ የሚወስድላቸው አካል እንደሚፈልጉ በተለይ ለፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል አስታወቁ፡፡
‹‹በአማርኛ ተናጋሪነታችን ሠርተን የመኖር ልጆቻችንን የማሳደግ ህልውና ያጣን ነን፡፡›› የሚሉት እነዚህ ዜጎች “በተደጋጋሚ ጥቃት እየተሰነዘረብን ነው፤ ከ20 ዓመት በላይ ከኖርንበት መሬት ተፈናቅለናል፡፡ ከአውሬ ጋር እየታገልን ያለማነውን መሬት ተነጥቀናል፡፡ እነሱ የሚሉን እናንተ አማራ ስለሆናችሁ በዚህ ክልል መኖር አትችሉም፡፡ ወደ ክልላችሁ ሂዱ ይሉናል፡፡ አማራ ክልልን እንኳን ሰርተን የምንበላበት መሬት ቀርቶ ጎጆ ቀልሰን የምንኖርበት ቦታ ሊሰጡን ፈቃደኛ አይደሉም፡፡” ሲሉ ቅሬታቸውን ይገልጻሉ፡፡

ሁለት የኢትዮጵያ አትሌቶች ውድድራቸውን አቋርጠው ጠፉ




የካቲት ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም 



ኢሳት ዜና:-ሀአሬጽ የተባለው የእስራኤል ጋዜጣ እንደዘገበው ሁለቱ አትሌቶች የማራቶን ሩጫቸውን በማቋረጥ ነው ባለፈው አርብ ፣ ማርች 1፣ 2013 የጠፉት። ሜላት መኮንን እና ማህሌት ዘለቀ የተባሉ የ24 እና 25 አመት እድሜ ያላቸው አትሌቶች የጠፉት በደቡብ ቴላቪቭ ሲሆን፤ የ እስራኤል ፖሊስ አትሌቶቹ ሆን ብለው እንደጠፉ ገልጿል።
ሁለቱም አትሌቶች  ፓስፖርታቸውን  እና ሌሎች እቃዎቻቸውን ሁሉ በመተው በሩጫ ልብሳቸው መጥፋታቸውን ፖሊስ አስታውቋል። አትሌቶቹ እስካሁን ለፖሊስም ሆነ ለአካባቢው ባለስልጣናት ስለሁኔታው አላመለከቱም።

ታክሲ ውስጥ በ 1 ብር ከ 35 ሳንቲም ሳቢያ በተፈጠረ ጭቅጭቅ ረዳቱ በጥይት ተመታ



የካቲት ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም 
ኢሳት ዜና:-ከትናንት በስቲያ ቦሌ መድኃኔዓለም አካባቢ  ኪዱ ገብረሥላሴ በተባለ  የታክሲ ተሳፋሪና ረዳቱ መካከል በተፈጠረ 1.35ብር አለመግባባት ምክንያት ረዳቱ በጥይት ተመታ።
እንደ ሪፖርተር ዘገባ ድርጊቱ የተፈጸመው ቦሌ መድኃኔዓለም ከሚገኘው ካልዲስ ካፌ ፊት ለፊት ሲሆን፣ ተጠርጣሪው አቶ ኪዱ ገብረ ሥላሴ ወዲያው በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውሏል፡፡
ነጋ ንጉሡ የተባለው የታክሲው ረዳትም፤ ሃያት ሆስፒታል ለሕክምና ተወስዷል፡፡
የታክሲው አሽከርካሪ አቶ ጌትዬ ቆንጥር እንደገለጹት፣ ተሳፋሪው ሽጉጡን ሊተኩስ የቻለው የአገልግሎት ማብቂያ ቦታቸው ላይ ሲደርሱ <<ውረድ አልወርድም>> በሚል ክርክር ነው፡፡
ሾፌሩ አክለውም፦“ታክሲያችን አገልግሎት የሚሰጠው ከመርካቶ እስከ ቴሌ መድኃኔዓለም ድረስ ነው፡፡ በዚያ ቀንም ተሳፋሪዎችን ከካዛንቺስ ጭነን ወደ ቴሌ መድኃኔዓለም ለማድረስ እየተጓዝን ነበር፡፡ በስተመጨረሻም ቴሌ መድኃኔዓለም ስንደርስ ለሁሉም ተሳፋሪዎች እንዲወርዱ ስንናገር፣ ሁለቱ ግን ለመውረድ ፈቃደኛ አልሆኑም፤” ብለዋል፡፡
እንደ ጋዜጣው ዘገባ፤ከካዛንቺስ- ቴሌ መድኃኔዓለም ድረስና ከካዛንቺስ- ቦሌ ድልድይ ድረስ ታክሲዎች የሚያስከፍሉት ታሪፍ በተመሳሳይ 2.70 ብር ነው፡፡ በመሆኑም ተጠርጣሪው አቶ ኪዱ መሄድ የምፈልገው ቦሌ ድልድይ ነው በማለት ከሾፌሩና ከረዳቱ ጋር አምባጓሮ ቢፈጥርም፣ ሾፌሩም ሆኑ ረዳቱ ከዚህ በላይ መሄድ እንደማይችሉና ቢሄዱም በሕግ እንደሚጠየቁ ለተጠርጣሪው ይናገራሉ፡፡
በሁለቱም ንግግር የተበሳጨው ተጠርጣሪ ግን ምላሹ ከታክሲ መውረድ ሳይሆን በጎኑ የሰደረውን ሽጉጥ በማውጣት በሾፌሩ ላይ ማነጣጠር ነበር፡፡
ጋዜጣው እንዳለው ይህን የተመለከተው ረዳትም ሽጉጡን ከተጠርጣሪው ለማስጣል ትግል ይገጥማል ።በዚህም መካከል ተቀባብሎ ከነበረው ሽጉጥ የተተኮሰች ጥይት የረዳቱ የግራ ጎን ውስጥ ተቀርቅራለች፡፡
ረዳቱም ከተጠርጣሪው አቶ ኪዱ ሽጉጡን ታግሎ በመቀበል በቦታው ለነበረው የካልዲስ ጥበቃ እንደሰጠው ጉዳዩን የሚመረምሩት ኮንስታብል አዱኛ ገልጸዋል፡፡
ከዚያም ፖሊስ ወዲያው በአካባቢው ደርሶ ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ሥር አውሎታል፡፡
ተጠርጣሪው  በኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎ የቀን ሠራተኛ ሲሆን፣ በነፍስ ማጥፋት ሙከራ ክስ ተመስርቶበታል።  ተጠርጣሪው ኪዱ ገብረሥላሴ የያዘው መሣሪያም ፈቃድ ያለው እንደሆነ በፖሊስ የተገለጸ ሲሆን፤ ይህም ዜናውን ባነበቡት ሁሉ ዘንድ አቶ ኪዱ ገብረሥላሴ ከባለዘመነኞቹና ከአድራጊ ፈጣሪዎቹ ሹመኞች አንዱ ሳይሆን አይቀርም የሚል ግምት አሳድሯል።
ታክሲ ውስጥ በተፈጠረ ተራ ንትርክ    የእለት ጉርሱን ለማግኘት የሚለፋን ደሀ ረዳት በሽጉጥ መምታት ጥጋብና እብሪት ካልሆነ በስተቀር ምን ሊባል ይችላል? ብለዋል በጉዳዩ ላይ በፌስቡክ አስተያየታቸውን የሰጡ በርካታ ኢትዮጵያውያን።
የታክሲ ረዳቱ ነጋ በሃያት ሆስፒታል ሕክምናውን እየተከታተለ ሲሆን፣ በሰውነቱ ውስጥ ያለውን ጥይት ለማውጣት ኦፕራሲዮን ሊሆን እንደሚችል ምንጮች  ተናግረዋል፡፡

Monday, 4 March 2013

ኢህአዴግ አሣ አስጋሪዎችን ጨፈጨፈ


የአሜሪካዊው አስከሬንና አሟሟት ሊመረመር ነው

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ (http://www.goolgule.com/)
የመከላከያ ሰራዊት በድንገተኛ ከበባ ከገደላቸው ንጹሃን ዜጎች መካከል የአሜሪካ ዜግነት ያላቸውን የአቶ ኡሞት ኡዶል ግድያ አስመልክቶ የአሜሪካ መንግስት አስፈላጊውን ሁሉ ምርመራ እንደሚያደርግ አስታውቋል። ግድያው ከተፈጸመ በኋላ የሰራዊቱ አባላት አስከሬን አደባባይ በማውጣት ለህዝብ እያሳዩ ደስታቸውን ሲገልጹ የተመለከቱ የጋምቤላ ከተማና አካባቢው ነዋሪዎች ክፉኛ መበሳጨታቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡
በጋምቤላ የደረቁን ወቅት ወይም በጋውን በወንዞች ዳር ውሃ ተንተርሶ መኖር የተለመደ ነው። ከቋሚ የመኖሪያ ቀዬ ወደ ወንዝ ዳርቻ በመሄድ አድኖ መመገብና አሳ አስግሮ ዕለትን ማሳለፍ የባህል ያህል ነው። በአገሬው ልምድ መሰረት ከቋሚ መኖሪያቸው ወደ ውሃ ዳር የሚሄዱት ወንዶች ሲሆኑ ጉዞውም የሚደረገው በቡድን ነው።
Gambella
በዚሁ መሰረት በጋምቤላ ክልል የጎክዲፓች ነዋሪዎች የደረቁን ወቅት ለማሳለፍ በጊሎ ወንዝ ዳርቻ ወደምትገኘው አብሌን ያመራሉ። በቡድን ወደ አብሌን ያመሩት ሰዎች ከወንዝ አሳ በማስገርና ያገኙትን በማደን ቀን እየገፉ ሳለ የካቲት 21፤2005ዓም (28/2/13) በድንገት የመከላከያ ሰራዊት ከበባቸው። ተኩስ ተከፈተ። ለጊዜው ስድስት ሰዎች ህይወታቸው ማለፉንና የቆሰሉ እንዳሉ ለተጎጂዎቹ ቅርበት ያላቸው ያስረዳሉ።
ሰዎቹ ከጋምቤላ ከተማ 120 ኪሜ ርቀት ላይ በምትገኘው አብሌን ተቀምጠው ኑሯቸውን እየገፉ ሳለ በድንገት የተከበቡት በጥቆማ እንደሆነ ለጎልጉል የደረሰው መረጃ ያመለክታል። “አቶ ኡሞት ኡዶል እና ሌሎች መሳሪያ የታጠቁ አብሌን ታይተዋል” የሚል ጥቆማ የደረሰው ኢህአዴግ፤ ሰራዊቱን ሰዎቹ በቋሚነት ወደሚኖሩበት ጎክዲፓች በመላክ ቤተሰቦቻቸውን በመያዝ፣ በማሰርና፣ በመግረፍ ሰዎቹ ያሉበትን ቦታ እንዲያሳዩ አስገደዱ።

Friday, 1 March 2013

በጅጅጋ የአማራ ተወላጆች ቤታቸው እየተነጠቁ ለጎዳና ተዳዳሪነት መዳረጋቸውን ገለጡ



የካቲት ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም 

ኢሳት ዜና:-በክልሉ የሚገኙ የአማራ ተወላጆች ለኢሳት እንደገለጡት ፣ ካለፉት 40 አመታት ጀምሮ በሶማሊ ክልል በጅጅጋ ከተማ ይኖሩ የነበሩ የአማራ ተወላጆች ቤቶቻቸውን እያስረከቡ ለጎዳና ህይወት ተዳርገዋል። 
እስካሁን ድረስ በከተማዋ ውስጥ ዋና ዋና የንግድ ቦታዎች የነበሩዋቸው የአማራ ተወላጆች፣ ለሶማሊ ተወላጆች እንዲያስረክቡ በመዳረጋቸው ብዙዎች ድርጅቶቻቸውን አስረክበው ወደ መሀል አገር ሄደዋል። 
ተወልደው ያደጉበትን ቦታ አንለቅም በማለት እስካሁን የቆዩትም በተለያዩ አስተዳዳራዊ ጫናዎች ከተማዋን ለቀው እንዲወጡ በደብዳቤ እና በቃል ተነግሯቸዋል።

በጅጅጋ ከተማ የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ለኢሳት በጻፉት ደብዳቤ ” የአንድ ብሄር የበላይነት በሰፈነበት መልኩ አማራ ወይም ሀበሻ የሚል መጠሪያ ተደርጎልን እነሆ ከህጻናት እስከ ትልቅ በመንገድም በቢሮም  እየተሰደብንና እየተተፋብን መኖራችን ሳያንስ፣ አሁን ደግሞ ያለምንም ልዋጭ ቤታችን ተቀምቶ ጎዳና ላይ ተጥለን እንገኛለን።” ብለዋል። 
ነዋሪዎቹ አክለውም ” የእኛ ልጆች እንደልብ በመንገድ ላይ መሄድ አይችሉም፣ ሱሪ የለበሰች ሴት በፖሊስ ዱላ ትደበደባለች፣ ማን ፖሊስ ማን ሀላፊ እንደሆነ በማናውቀው ሁኔታ፣ የሸሪያ ፍርድ ቤት የሚል ተቋቁሞ ቤታችንን እንድንለቅ እያስገደደን ነው። ተወልደን ባደግንበት አገር እንደ ሁለተኛ ዜጋ እንደቆሻሻ እየታየን ነው” ብለዋል። 
አንድ ስማቸው እንዳይገለጥ የፈለጉ የከተማው ነዋሪ በክልሉ የመኖር ተስፋቸው መሟጠጡን ተናግረዋል 
ኢሳት በጅጅጋ ከተማ በአማራ ተወላጆች ላይ የሚደርሰውን በደል በተደጋጋሚ ቢዘግብም መንግስት ዝምታን መርጧል።