የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ለዓለም የእግር ኳስ ዋንጫ ፍጻሜ ለመድረስ ትናንት ደቡብ አፍሪቃን ከሜዳ አሸንፎ ወደ ቀጣዩ ደረጃ ቢሸጋገርም ፤ የዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን (ፊፋ) ዛሬ ያወጣዉ ዘገባ የቡድኑን ወደ ቀጣዩ ደረጃ ማለፉን አጠራጣሪ አድርጎታል። ዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን (ፊፋ) በሶስት የአፍሪካ አገራት ተጫዋቾች ላይ ማጣራት እንደሚያደርግ የገለጸዉ ጨዋታዉ ከመጠናቀቁ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ነበረ። ኢትዮጵያ ፣ ቶጎ እና ኢኳቶሪያል ጊኒ ሊሰለፉ የማይገባቸዉ ተጫዋቾች የዓለም አቀፉን የእግር ኳሰ ማህበር ህግን በጣሰ መልኩ በ2014ቱ የብራዚል ዓለም ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታዎች ሜዳ ገብተዋል በሚል ነው። ኢትዮጵያ ከቦትስዋና ጋር ተጋጥማ 2 ለ 1 ያሸነፈችበት እንዲሁም ቶጎ እና ካሚሩን የገጠሙትም ጨዋታ እንደሚጣራ ፊፋን ጠቅሶ የፈረንሳዩ የዜና አገልግሎት አዣንስ ፍራንስ ዘግቦአል። የኢትዮጵያ ብሄራዊ የእግር ኳስ ቡድን አሰልጣኝ ሰዉነት ቢሻዉ ለዶይቼ ቬለ በሰጡት ቃለ ምልልስ ግን፤ አጭበርብረን ለማሸነፍ አንዳችም ጥረት አላደረግንም ብለዋል። ዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን (ፊፋ) ህግን ጥሰዉ ለጨዋታ ተሰልፈዋል ያላቸዉን የሶስት የአፍሪካ አገራት ስም ጠቀሰ እንጂ፤ የተጫዋቾችን ስም በዝርዝር አላወጣም። የምሽቱ የስፖርት ዝግጅታችን ሰፋ ያለ ማብራርያ ይዞ ይጠብቃችኋል
Monday, 17 June 2013
Sunday, 16 June 2013
ከፍተኛ የደህንነት ሹም ከስልጣን ተነሱ (ከኢየሩሳሌም አርአያ)
June 16, 2013
ከኢየሩሳሌም አርአያ
የሕወሐት አባልና የአገር ውስጥ ደህንነት ዋና ሃላፊ አቶ ወልደስላሴ ከስልጣናቸው እንዲነሱ መደረጉን የቅርብ ምንጮች አስታወቁ። ወ/ስላሴ ከስልጣን እንዲነሱ ያደረጉት የደህንነት ዋና ሹም አቶ ጌታቸው አሰፋ መሆናቸውን ምንጮቹ ጠቁመዋል። የሁለቱ ሹማምንት ፀብ ውስጥ ለውስጥ ሲብላላ ቆይቶ መጨረሻ መፈንዳቱ ታውቋል። በመቀሌ በተካሄደው የፓርቲው ጉባኤ አቶ ጌታቸው የፓርቲው ማ/ኮሚቴ አባል ሆነው እንዳይመረጡ ሰፊ ቅስቀሳ ሲካሂድ የቆየው ወ/ስላሴ በመጨረሻም የአባላት ምርጫ ሲካሄድ ባቀረበው ተቃውሞ ላይ «..ጌታቸው የተሰጠውን የፓርቲና መንግስታዊ ሃላፊነት በአግባቡ እየተወጣ አይደለም፤ የአልሙዲ ተላላኪና አሽከር ሆኗል… የአላሙዲ አገልጋይ ሆኖዋል… ስለዚህም በማ/ኮሚቴ አባልነት መካተት የለበትም..» ሲል መናገሩን ያወሱት ምንጮቹ፣ የወ/ስላሴ ተቃውሞ ተቀባይነት ባለማግኘቱ አቶ ጌታቸው በማ/ኮሚቴ አባልነታቸው እንዲቀጥሉ መደረጉን አያይዘው ገልፀዋል።…
አቶ ጌታቸው በቅርቡ በወሰዱት የአፀፋ እርምጃ ወ/ስላሴ ከአገር ውስጥ ደህንነት ሃላፊነታቸው እንዲነሱ በማድረግ እንደተበቀሏቸው ማወቅ ተችሏል። በጎንደር ተወልደው ያደጉትና በሰባዎቹ መጀመሪያ አመታት ሕወሐትን የተቀላቀሉት አቶ ጌታቸው በአብዛኛው አመራር « ጥሩ ሰው ነው፣ ላመነበት ነገር ወደኋላ የማያፈገፍግ..» ተብሎ እንደሚነገርላቸው ምንጮቹ ጠቁመዋል። በሟቹ የደህንነት ሹም ክንፈ ገ/መድህን ተተክተው በ1994ዓ.ም ወደስልጣን የመጡት ጌታቸው በተጨባጭ ሙስና ፈፅመዋል የሚል መረጃ እንደሌለ ያመለከቱት ምንጮቹ ነገር ግን በአብዛኛው ባለስልጣናት የሚፈፀመው መጠነ ሰፊ ዘረፋና ሙስና በተመለከተ በርካታ መረጃና ማስረጃ በጌታቸው እጅ እንደሚገኝ አያይዘው ገለፀዋል። በሌላም በኩል በ1994ዓ.ም በደህንነት ቢሮ የበታች ሹማምንት ሆነው በአቶ መለስ ከተመደቡት መካከል ኢሳያስ ወ/ጊዮርጊስና ወ/ስላሴ እንደሚገኙበት ያስታወሱት ምንጮቹ፣ አክለውም ሁለቱ የሕወሐት አባላት ከስር ሆነው ፈላጭ ቆራጭ አመራር ይሰጡ እንደነበረና በዚህ ተግባራቸው ከጌታቸው ጋር የከረረ ውዝግብ ውስጥ ገብተው መቆየታቸውን አስታውቀዋል። ኢሳያስ ከአቶ መለስና ስብሃት ጋር ስጋ ዝምድና እንዳለው ማወቅ ተችሏል። በተለይም በዚህ ጣልቃ ገብ አሰራር ተማረው የቆዩት አቶ ጌታቸው ከቅርብ አመት ወዲህ ከአቶ መለስ ጋር ጭምር አለመግባባት ፈጥረው እንደነበረ ሲታወቅ፣ አቶ መለስ የጤና ችግር ተፈጥሮቦቻው እንጂ በዛው ወቅት ከስልጣን ሊያነሷቸው ከወሰኑት ባለስልጣናት አንዱ ጌታቸው እንደነበሩና ከመለስ ህልፈት በኋላ የደህንነቱ ሹም የታቀደባቸውን እንደደረሱበት ምንጮቹ አስታውቀዋል። የጠ/ሚ/ሩን ህልፈት ተከትሎም አቶ ጌታቸው ስልጣናቸውን በማደላደል ጎልተው መውጣቸውንና በወ/ስላሴ ላይ የወሰዱት እርምጃ ማስረጃ እንደሆነ አያይዘው ገልፀዋል። ከዚህ በተጨማሪ የአቶ ጌታቸው ወንድም ዳንኤል አሰፋ የሕወሐት ማ/ኮሚቴ አባል ተደርጎ ባለፈው ጉባኤ መመረጡ ሲታወቅ፣ የዳንኤል ባለቤት የስብሃት ነጋ ዘመድ እንደሆነች ተጠቁሞዋል።
Saturday, 15 June 2013
አገር በቤተሰብ ስትዘረፍ ኢህአዴግ የት ነበር?
“አዲስ አበባ የተገተሩት ህንጻዎችስ?”
በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉት ባለስልጣናት፣ ባለሃብት፣ ደላሎችና ባለድርጅቶች በልጆቻቸውና በቤተሰቦቻቸው ስም “ዘርፈው አስቀመጡት” የተባለው ንብረታቸውና የባንክ ሂሳባቸው መታገዱ ታወቀ። የዜናውን ይፋ መሆን ተከትሎ አዲስ አበባን ያጥለቀለቋት ህንጻዎችና የንግድ ድርጅቶች ጉዳይ ለምን ዝም ተባሉ የሚል ጥያቄ እየተሰነዘረ ነው።
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ ነጋ ገብረ እግዚአብሔር 54 ተሽከርካሪዎች ተይዘውባቸዋል። ገንዘቡን ሳይጨምር 54 ተሽከርካሪዎች በስማቸው ተመዝግበው የተያዙባቸው አቶ ነጋ ፣ የወ/ሮ አዜብ መስፍን የንግድ ሽሪክ እንደሆኑ የሚያውቋቸው ይገልጻሉ። በኢህአዴግ ጉባኤዎች ላይ የማይቀሩት አቶ ነጋ በየስብሰባው ወቅት ሻይና ቡና ሲሉ ከወ/ሮ አዜብ ጋር አብረው እንደሆነ የሚገልጹት ታዛቢዎች፣ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን “አትሌት ናቸው” በሚል ወደ ውጪ በጉቦ የላካቸው ሰዎች ጉዳይም ከሳቸው ጋር እንደሚያያዝ ይጠቁማሉ። ከጨው ንግድ፣ ከካሜራ ፊልም ብቸኛ አስመጪነት ሌላ በአሁኑ ወቅት ሂልተን ጀርባ፣ አዲስ አበባ ስታዲየም ቪክ ሬስቶራንት ጎን ግዙፍ ህንጻ ያስገነቡት አቶ ነጋ ቃሊቲ ባላቸው የነዳጅ ማደያ የከፈቱት ብቸኛ የክብደት መለኪያ/የከባድ የጭነት መኪኖች የክብደት መለኪያ “የገንዘብ ማምረቻ ማሽን” አግባብነት የሌለው ቢዝነስ እንደሆነ ቅሬታ ሲቀርብበት የቆየ የግል የንግድ ተቋማቸው ነው። ቀደም ሲል ከኤርትራዊያን ጋር አብረው ሲሰሩ የነበሩት አቶ ነጋ ሃብታቸው በድንገት የተመነጠቀው ከ1991 ኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ጀምሮ እንደሆነ የሚያውቋቸው ይናገራሉ።
Tuesday, 11 June 2013
አንለያይም! I am Proud of my people, the Ethiopians!
June 11, 2013
by Teshome Debalke
I always wonder how people with such political turmoil and economic hardship ruled under a hollow ethnic tyranny as Woyane behave in exceptionally high standard of civility, discipline and impeccable class and unity never seen in the human experience.
How is it when people around the world continue to find petty excuses to divide and wage war and conflicts against each other Ethiopians remain calm and collected with such diverse ethnicities, languages and religions unlike any other nation on earth and under a ruling regime that instituted an Apartheid system to provoke and divide us? How it is the people of Ethiopia maintain their dignity and kept the brazen ethnic regime and its stooges hiding in shame?
Frankly, it defies any human experience to believe such civilized people exist in our world. For that reason, a while back I wrote ‘Civilized people uncivilized regime: how did it happen?’. With my limited knowledge about my own people like most of my compatriots I was trying to explore how uncivilized regime like Woyane and its sorry stooges ended up ruling the sea of civilized people as Ethiopians?
At the meantime, how it is the stooges, supporters and apologists of the ethnic regime behave in such uncivilized manner; defending not only a regime known for its atrocities, human right violation, corruption, treason and up to committing genocide and ethnic cleansing to stay alive but lie like a darken sailor on behalf of ethnic tyranny . Could only their greed and corruption explain their behavior of going out of their way to sustain the brazen ethnic tyranny? Could it be possible they are mercenaries doing the bidding of foreign enemy? Can racism; as the dead tyrant claimed play a role in their behavior?
Saturday, 8 June 2013
ኢህአዴግ ጣና በለስን ለምን አፈራረሰው?
"በሩ ይከፈት፣ በአባይ ጉዳይ አገራዊ አቋም እንያዝ"
በግብጽ ረዳትነት፣ በሱዳን መሪነት መንግስት ለመሆን የበቃው ህወሃት/ኢህአዴግ ግዙፉን የጣና በለስ ፕሮጀክትና ንብረቱ እንዲዘረፍ ያደረገበትን ምክንያት በማንሳት መከራከር እንደሚያስፈልግ ተጠቆመ። የግብጽ ፕሬዚዳንት ሙርሲ እንዳደረጉት በአገር ጉዳይ ሁሉንም ያሳተፈ ግልጽ አቋም እንዲያዝና አጋጣሚውን በመጠቀም ብሔራዊ ህብረት እንዲፈጠር ኢህአዴግ በሩን ሊከፍት እንደሚገባ ተገለጸ።
በተለያዩ ጉዳዮች ምክንያት ስማቸው እንዳይጠቀስ በማሳሰብ ለጎልጉል አስተያየት የሚሰጡት የኢህአዴግ ሰው እንዳሉት በርካታ ጉዶች ያሉበትን የአባይን ግድብ ተከትሎ ከግብጽ ጋር የተነሳው ውዝግብ አስቀድሞ የሚታወቅ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ ስልትና ውጤት ነው።
አሁን ድረስ አገር እየመራ በነጻ አውጪ ስም የሚጠራው ህወሃት/ኢህአዴግ አዲስ አበባ ሲገባ “ዲሞክራሲ አመጣሁ” በማለት ኢትዮጵያን መምራት እንደጀመረ የሚያወሱት የኢህአዴግ ሰው፤ አቶ መለስ ብቻቸውን ይነዱት የነበረው ኢህአዴግ እንደፈለገ ቆዳውን እየቀያየረ የተጠቀመበትንና በእስስት በመመሰል “ከሽፏል የሚሉትን” ስልት ያብራራሉ።
በዲሞክራሲ ስም የተጀመረው የኢህአዴግ አገዛዝ ቆየት ብሎ “ልማታዊ ነኝ፣ ልማት ግቡን የሚመታው በአብዮታዊ ዲሞክራሲ ቀመር ነው” በማለት ፕሮፓጋንዳውን አሰፋ። የልማት ህልመኛነቱ ሲነቃበት “የትራንስፎርሜሽን ዘመቻ” በማለት አዲስ የፕሮፓጋንዳ እቅድ ነድፎ ህዝብና አገር ሲያታልል ቆየ። ይህም አላራምድና በህዝብ የመታመን ድል ሊያስገኝለት እንደማይችል ሲታመን “የህዳሴያችን ግድብ” ተብሎ አባይ አጀንዳ እንደተደረገ ያመለከቱት ዲፕሎማት፤ “ኢህአዴግ አገር ውስጥ የሚያምታታባቸው መንገዶች ሲጠናቀቁበት የፕሮፓጋንዳውን ዘመቻ አንድ ደረጃ ከፍ አደርገው” በማለት አሁን ከግብጽ ጋር ስለተጀመረው ውዝግብ አስተያየታቸውን ይጀምራሉ።
Friday, 7 June 2013
ኦባንግ ለኃይለማርያም ግልጽ ደብዳቤ ላኩ
ለማሰር መጣድፍ እንደማያዋጣ አስጠነቀቁ
ባለፈው እሁድ በሰማያዊ ፓርቲ የተጠራውንና በሰላም የተጠናቀቀውን ሰላማዊ ሰልፍ በማስመልከት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ ለጠ/ሚ/ር ኃይለማርያም ደሳለኝ ግልጽ ደብዳቤ ላኩ፡፡ በደብዳቤው ላይ ኢህአዴግ ሰልፈኞቹንም ሆነ የፓርቲውን አመራሮች ለማሠር የሚያደርገውን ሃሳብ ከመፈጸም እንዲቆጠብ ማስጠንቀቂያ ልከዋል፡፡
አቶ ኦባንግ በደብዳቤያቸው ላይ በርካታ ጉዳዮችን የዳሰሱ ሲሆን በቅድሚያ ግን ጠ/ሚ/ር ኃይለማርያም ሠልፉን በመፍቀዳቸው ሊመሰገኑ እንደሚገባ ጠቅሰዋል፡፡ ይህንንም በማድረግ ከቀድሞው መሪ መለስ እንደሚለዩና ምናልባትም ህዝብን ለማዳመጥ ፍላጎት እንዳላቸው ጠቋሚ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ምክንያቱንም ሲያስረዱ መለስ በእንደዚህ ዓይነቱ ሠልፈኞች ላይ የህወሓት አልሞ ተኳሾች ተኩስ በመክፈት እንዲገደሉ ማድረገቸውና የፓርቲ አመራሮችን ማሳሰራቸውን እንደ ማስረጃ ጠቅሰዋል፡፡
የሕዝብ ጥያቄ በአግባቡ ምላሽ እስካላገኘ ድረስ እንዲህ ዓይነቱ የታቃውሞ ሠልፍ እየቀጠለ እንደሚሄድ የተናገሩት ኦባንግ የሕዝብን ጥያቄ ማዳመጥና ተገቢውን ምላሽ አማራጭ መፍትሔ የሌለው ጉዳይ እንደሆነ አመልክተዋል፡፡ ከዚህ ሌላ በአንዳንድ የኢህአዴግ አመራሮች ሠልፉ የጥቂቶች እንደሆነ ለማስመሰል የተወሰደው አካሄድ ፈጽሞ እንደማይሠራ ጠቁመዋል፡፡ በሠልፉ ላይ የታዩት ኢትዮጵያውያን ከሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል የተውጣጡ እንደሆኑና እነዚህም ክርስቲያን፣ ሙስሊም፣ የማያምኑ፣ ሴቶች፣ ወጣቶች፣ አረጋውያን፣ የመንግሥት ሠራተኞች፣ ሥራ የሌላቸው፣ አካለ ስንኩላን፣ የኢህአዴግ አባላት፣ ተማሪዎች፣ ወዘተ መሆናቸውን በማስረጃ አስረድተዋል፡፡
የጁምአ ግንቦት 30 አገር አቀፍ ተቃውሞ መርሐግብር ግንቦት 29/2005 (ድምፃችን ይሰማ)
የኃይል እርምጃ ለህዝብ መልስ አይሆንም!
የትግላችንን ሂደት ለመግታት መንግስት ከውስጥም ከውጪም የተለያዩ ጥቃቶችን ሲሰነዝር መቆየቱ ይታወሳል፡፡ በጥቃቱ ሙስሊሞችን ከትግሉ ሜዳ ለማስወገድ ታስቦ የነበረ ቢሆንም መንግስት የሚያስበውን ያህል ሲሳካለት ግን አልታየም፡፡ ይህ የመንግስት ጥቃት ሌት ተቀን አከብረዋለሁ ቢሎ በሚለፍፍለት፣ በተግባር ግን ሊገዛለት የማይፈቅደውን ሕገ መንግስት በመጣስ በተደጋጋሚ የተፈጸመ ነው፡፡
በሌላ በኩል የመንግስት ባለስልጣናት ባለፈው ሳምንት ተጠርቶ የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ አስታከው በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጲያዊያን ሙስሊሞች ከአንድ ዓመት በፊት ያነሱትን ሃማኖታዊ ጥያቄ ለህዝብ ያላቸውን ንቀት በሚያሳይ ሁኔታ ድብቅ አጀንዳ ያለው አድርገው ለመሳል ሞክረዋል፡፡ በነገው የተቃውሞ ትእይንታችን እነዚህን ሁለት አንኳር ሐሳቦች 18 ወራት ቆይተው ምላሽ ከተነፈጓቸው ጥያቄዎቻችን ጋር በማስተሳሰር ድምጻችንን በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች እናሰማለን፡
በቀዳሚነት በደሴ ከተማ ሙስሊሞች ላይ በቅርቡ የተወሰደውን የኃይል እርምጃ በስልጠና፣ በማስፈራራትና በመደለል አልሳካ ያለውን መንግስታዊ እስልምና (አህባሽን) በመስጂዶቻችን የማንገስ፣ ሙስሊሙን ከመስጂዱ የማፈናቀል ሴራና በግልፅ በአፈሙዝ በመታጀብ መስጂድ ድረስ መግባቱ የመንግስት ለሕግ አልገዛ ባይነት ምን ያህል እንደደረሰ ያሳያል፡፡ ይህን የተጋረጠብንን አደጋ መላው ህዝብ ይበልጥ እንዲረዳው ማድረጉ ይበልጥ ትግላችንን እንደሚያጠነክረው በማመን በደሴ የተወሰደውን እርምጃ በነገው ተቃውሟችን እናወግዛለን፡፡
Tuesday, 4 June 2013
ወደ ጀርመን በገቡት አፍሪቃዉያን ስደተኞች ምክንያት፤ የጀርመን እና የጣልያን ወዳጅነት እየተቃወሰ ነዉ። ከጥቂት ወራቶች ወዲህ በርካታ ወጣት ወንድ አፍሪቃዉያን ስደተኞች በሊቢያ የሰሜን አትላንቲክ ወታደራዊ ቃል ኪዳን ድርጅት ጦር «የ ኔቶ» ጥቃትን በመሸሽ ወደ ደቡባዊ አዉሮጳ ጣልያን ከገቡት መካከል በርካቶች ጀርመን ገብተዋል።
በጣልያን በኩል አድርገዉ የመጡት ወደ 300 የሚጠጉት አፍሪቃዉያን ስደተኞች በሰሜናዊ ጀርመን ሃምቡርግ ከተማ ያለ መጠለያ የጎዳና ተዳዳሪ በመሆናቸዉ እና ስለ ስደተኞቹ ማንም ሃላፊነትን ባለመዉሰዱ ከተማዋ መፍትሄን ለማግኘት ጥሪ አቅርባለች። ዝርዝሩን አዜብ ታደሰ ታቀርበዋለች። በሃምቡርግ ከተማ ማዕከላዊ የባቡር ጣብያ አካባቢ አፍሪቃዉያኑ ስደተኞች በሚያድሩበት አነስተኛ ድንኳን አጠገብ ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት ላይ የከተማዉ ነዋሪ ጥያቂያቸዉን እንዲያይላቸዉ በትልቁ በጽሁፍ ለጥፈዉ ይታያል። ከጥያቄዎቻቸዉ መካከል «በሰሜን አትላንቲክ ወታደራዊ ቃል ኪዳን ድርጅት፤ «ኔቶ» ጦርነት እንድንሰደድ ግድ ሆኖብናል» «መብታችን እንጠይቃለን» ይላል። ስደተኞቹ በጉዳና ላይ በሰሩት የመኖርያ ድንኳን ዉስጥ ከሚኖሩት መካከል የ 31 ዓመቱ ናይጄርያዊ ፍሪዲ ይገኛበታል። ፍሪዲ በጣልያን የሚገኘዉ የስደተኞች መጠለያ ከተዘጋ በኋላ፤ ወደ ሰሚናዊ ጀርመን ሃምቡርግ ከተማ ከገባ አንድ ወር ግድም ሊሆነዉ ነዉ። ፍሪዲ በጣልያን የሸንጌን ቪዛን እና 500 ይሮን ተቀብሎአል።
Monday, 3 June 2013
ከእሁድ እስከ እሁድ
(የሳምንቱ አጫጭር ዜናዎች)
ከእስረኞች ጠበቆች ጋር የተደረገው ውይይት ታፈነ
የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ /አኢጋን/ ከአሜሪካ የህግ ባለሙያዎች ማህበር ጋር በመሆን በኢትዮጵያ እስር ቤት ለሚገኙ የህሊናና የፖለቲካ አስረኞች ጥብቅና ከቆሙ የህግ ባለሙያዎች ጋር ለመነጋገር ያደረገው ሙከራ ታፈነ። የጋራ ንቅናቄው ለጎልጉል እንዳስታወቀው ዓርብ ሰባት ከሚሆኑ ጠበቆች ጋር ለመያየትና መረጃ ለመለዋወጥ መስመር ተዘርግቶ ነበር።
አቶ ኦባንግ ሜቶና የጋራ ንቅናቄው የሚዲያ ዴስክ፣ ከአሜሪካ የጠበቆች ማህበር አራት፣ ከአዲስ አበባ ሰባት ጠበቆች በመሆን በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር 11 ሰዓት ላይ የስካይፕ ውይይት ለመጀመር ተዘጋጅተው ነበር። የጋራ ንቅናቄው እንዳስታወቀው ውይይቱ ሲጀመር ድምጽ መስማት አልተቻለም።
በዚሁ ሳቢያ ውይይቱ መቋረጡን ያስታወቀው አኢጋን ከአሜሪካ የጠበቆች ማህበር ጋር በመነጋገር ሰኞ ቀን በውል በማይገለጽ ሰዓት በሌላ መልኩ ውይይቱን ለማካሄድ ቀጠሮ መያዙን አመልክቷል። የአሜሪካ ህግ ባለሙያዎች ማህበር ኢህአዴግ ያለ አግባብ አስሮ የሚያሰቃያቸውን ዜጎች ጉዳይ አደባባይ ለማውጣትና አስፈላጊውን ሁሉ ለማድረግ ይቻለው ዘንድ ከአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ጋር አብረው ለመስራት መስማማታቸውን መግለጻችን ይታወሳል። በዜናው አሁን የተጀመረው ስራ የስምምነቱ መጀመሪያ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።
ምርመራው ወደ አቃብያነህጉ ተዛወረ!
የሙስናው “ሻርኮች” በዒላማ ውስጥ?
* “አዲስ ነገር የለም” ጸረ ሙስና ኮሚሽን
በተለያዩ ከፍተኛ ወንጀሎች በተጠረጠሩ ሰዎች ላይ የተከፈቱ ክሶችን በማፈንና በመመሪያ ፍትህ በማዛባትና በማቋረጥ ወንጀል የተጠረጠሩ አቃቤያነህግ ላይ ምርመራ መጀመሩ ከፍተኛ ድንጋጤ መፍጠሩ ተሰማ። በተለይም ከወንጀል ጋር ቁርኝት እንዳላቸው በህዝብ የሚታወቁ ክፍሎች ክፉኛ መደናገጣቸው ተሰምቷል።
በሙስና የተጠረጠሩት የጉምሩክ ባለስልጣናት፣ ተባባሪ ነጋዴዎችና ደላሎች መታሰራቸውን ተከትሎ ከተፈጠረው ስሜት በላይ ከፍተኛ መደናገጥ የፈጠረው ዜና አዲስ አድማስ ጋዜጣ ቅዳሜ እለት ለንባብ ያበቃው ዜና ነው።
Sunday, 2 June 2013
Ethiopian human rights protesters take to streets in Addis Ababa
Demonstrators demand government releases political leaders and journalists, and tackles corruption and economic problems
(The Guardian) — Around 10,000 Ethiopians staged an anti-government demonstration on Sunday in the first large-scale protest since a disputed 2005 election ended in street violence that killed 200 people.
The demonstrators marched through Addis Ababa’s northern Arat Kilo and Piazza districts before gathering at Churchill Avenue in front of a obelisk with a giant red star perched on top, a relic of Ethiopia’s violent communist past.
Some protesters carried banners reading “Justice! Justice! Justice!” or pictures of imprisoned opposition figures. Others chanted: “We call for respect of the constitution.”
A few police officers watched the demonstration, for which the authorities had granted permission.
“We have repeatedly asked the government to release political leaders, journalists and those who asked the government not to intervene in religious affairs,” said Yilekal Getachew, chairman of the Semayawi (Blue) party, which organised the protests.
He said the demonstrators also wanted action to tackle unemployment, inflation and corruption.
“If these questions are not resolved and no progress is made in the next three months, we will organise more protests. It is the beginning of our struggle,” he said.
Ethiopian opposition parties regularly accuse the government of harassment and say their candidates are often intimidated in polls. The 547-seat legislature has only one opposition member.
Semayawi Party Demonstration, Addis Ababa (video)
ግንቦት 25፣ 2005። ብዙ ሺዎች በሰማያዊ ፓርቲ የሰላማዊ ሰልፍ ላይ ተሳትፈዋል።
Subscribe to:
Posts (Atom)