Monday, 17 June 2013

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን እና ፊፋ

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ለዓለም የእግር ኳስ  ዋንጫ ፍጻሜ ለመድረስ ትናንት ደቡብ አፍሪቃን ከሜዳ አሸንፎ ወደ ቀጣዩ ደረጃ ቢሸጋገርም ፤ የዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን (ፊፋ) ዛሬ ያወጣዉ ዘገባ የቡድኑን ወደ ቀጣዩ ደረጃ ማለፉን አጠራጣሪ አድርጎታል።  ዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን (ፊፋ) በሶስት የአፍሪካ አገራት ተጫዋቾች ላይ ማጣራት እንደሚያደርግ የገለጸዉ ጨዋታዉ ከመጠናቀቁ ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ነበረ።  ኢትዮጵያ ፣ ቶጎ እና ኢኳቶሪያል ጊኒ ሊሰለፉ የማይገባቸዉ ተጫዋቾች የዓለም አቀፉን የእግር ኳሰ ማህበር ህግን በጣሰ መልኩ በ2014ቱ የብራዚል ዓለም ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታዎች ሜዳ ገብተዋል በሚል ነው። ኢትዮጵያ ከቦትስዋና ጋር ተጋጥማ 2 ለ 1 ያሸነፈችበት  እንዲሁም ቶጎ እና ካሚሩን የገጠሙትም ጨዋታ እንደሚጣራ ፊፋን ጠቅሶ የፈረንሳዩ የዜና አገልግሎት አዣንስ ፍራንስ ዘግቦአል። የኢትዮጵያ ብሄራዊ የእግር ኳስ ቡድን አሰልጣኝ ሰዉነት ቢሻዉ ለዶይቼ ቬለ በሰጡት ቃለ ምልልስ ግን፤ አጭበርብረን ለማሸነፍ አንዳችም ጥረት አላደረግንም ብለዋል። ዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን (ፊፋ) ህግን ጥሰዉ ለጨዋታ ተሰልፈዋል ያላቸዉን የሶስት የአፍሪካ አገራት ስም ጠቀሰ እንጂ፤ የተጫዋቾችን ስም በዝርዝር አላወጣም።  የምሽቱ የስፖርት ዝግጅታችን ሰፋ ያለ ማብራርያ ይዞ ይጠብቃችኋል 

No comments:

Post a Comment