Monday, 10 March 2014

የስደተኞች እልቂት በየመን የባህር ዳርቻ

ትናንት ምሽትም 45 አፍሪቃውያን ስደተኞች በየመን የባህር ዳርቻ መስጠማቸውን የሃገሪቱ የመከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል ። የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ድረ ገፅ እንዳስነበበው በባህር ዳርቻዋ ከተማ በቢር አሊ ከተማ ከደረሰው ከዚሁ አደጋ 30 ሰዎችን በህይወት ማትረፍ ተችሏል ።

Reporter ohne Grenzen Fotos für die Pressefreiheit 2010

ወደ ሃብታሞቹ የአረብ ሃገራት መሻገሪያ ሆና ወደ ምትታየው የመን ለባህር ጉዞ በማይመጥኑ አነስተኛ ጀልባዎች የሚያቀኑ ስደተኞች የባህር ሲሳይ መሆናቸው ተደጋግሞ ይሰማል ። ትናንት ምሽትም 42 አፍሪቃውያን ስደተኞች በየመን የባህር ዳርቻ መስጠማቸውን የሃገሪቱ የመከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል ። የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ድረ ገፅ እንዳስነበበው በባህር ዳርቻዋ ከተማ በቢር አሊ ከተማ ከደረሰው ከዚሁ አደጋ 30 ሰዎችን በህይወት ማትረፍ ተችሏል ።

Karte Jemen
ዓለም ዓቀፉ የስደት ጉዳይ ድርጅት እንዳስታወቀው ባለፈው የጎርጎሮሳውያኑ 2013 ዓም ባህር ተሻግረው ወይም ደግሞ በረሃ አቋርጠው የመን ለመድረስ ከሞከሩ ስደተኞች መካከል ከ7 ሺህ በላይ የሚሆኑት ህይወት አልፏል ። ይህም እስከዛሬ በዚህ መንገድ ከሞቱት ስደተኞች እጅግ ከፍተኛው አሃዝ ነው ። ከመካከላቸው የአፍሪቃውያኑ ቁጥር ከ2 ሺህ እስከ 5 ሺህ ይገመታል ። ተክሌ የኋላ ስደተኞች የመን ለመድረስ ስለሚከተሉት አደገኛ የባህርና የበረሃ ጉዞ የየመኑን ወኪላችንን ግሩም ተክለ ሃይማኖትን በስልክ አነጋግሮታል ።
ግሩም ተክለ ሃይማኖት
ተክሌ የኋላ

AUDIOS AND VIDEOS ON THE TOPIC

No comments:

Post a Comment