Wednesday, 26 March 2014

የስልክና ኢንተርኔት ክትትል የHRW ዘገባ

ሂዉማን ራይትስ ዎች ኢትዮጵያ ዉስጥ ይደረጋል ያለዉን የቴሌፎንና የኢንተርኔት ቁጥጥርና ስለላ የተመለከ ዘገባ ይፋ አደረገ።

Symbolbild Iran Cyberattacke Virus Wurm
ዘገባዉ በዉጭ ሀገር መንግስታት ቴክኒዎሎጂ እና በእነሱም ርዳታ እንዲሁም በደረሱበት እድገት ተደግፎ ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚንቀሳቀሱትን ሕዝባዊ ድርጅቶች፣ ጋዜጠኞችና የተቃዉሞ ፓርቲ አባላትን፣ ተማሪዎችንና የሙያ ማኅበራት አባሎችን የኢትዮጵያ መንግስት ይከታተላል የሚል ነዉ። በዉጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያንንም እንዲሁ ተከታትሎ ስልካቸዉን በመጥለፍ፣ ኮምፕዩተራቸዉን በርብሮ የግል ምስጢራቸዉን ይከታተል በማለት ሂዉማን ራይትስ ዎች ድርጊቱን ኮንኗል። የድርጅቱን ጋዜጣዊ መግለጫ የተከታተለዉ የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለሚካኤል ዝርዝሩን ልኮልናል። በርሊን የሚገኘዉ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ዓለም ዓቀፉ የመብት ተm።ጋች ድርጅት ሂዉማን ራiteስ ዎች ስላወጣዉ ዘገባ ያለዉን አስተያየት እንዲሰጥ በርሊን የሚገኘዉ ዘጋቢያችን በተደጋጋሚ ጠይቆ ነበር ሆኖም የኤምባሲዉ ባልደረቦች መልሰን እንደዉላለን ቢሉም ስቱዲዮ እስከገባንበት ጊዜ ድረስ ምላሻቸዉን አላገኘንም።
ይልማ ኃይለሚካኤል
ሸዋዬ ለገሠ
ነጋሽ መሐመድ

AUDIOS AND VIDEOS ON THE TOPIC

No comments:

Post a Comment