Friday, 19 October 2012

ሰበር ዜና!!መንግስት ለመጅሊስ አመራርነት በየወረዳዉ ተመርጠዎል የተባሉ ሙስሊሞችን በመጥራት ለሶስት ቀን የሚቆይ ስብሰባ እያካሄደ ነው
















መንግስት መገናኛ አሚቼ አካባቢ በሚገኝ አዳራሽ ዉስጥ ለመጅሊስ አመራርነት በየወረዳዉ ተመርጠዎል የተባሉ ሙስሊሞችን በመጥራት ለሶስት ቀን የሚቆይ ስብሰባ እያካሄደ እንደሚገኝ የዉስጥ ምንጮች አስታወቁ:: የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስተር ባለስልጣናት, የፌደራል ፖሊስ አመራሮች እና የመንግስት ከፍተኛ አመራሮች ስብሰባዉን እየመሩት እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል:: በዉይይቱም ላይ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ወርቅነህ ገበየዉ በመገኘት የሙስሊሙን ሰላማዊ ተቃዉሞ ህገ ወጥ መሆኑን ማብራሪያ መስጠታቸዉን ምንጮች አስታዉቀዎል::የስብሰባዉ ተሳታፊዎችም ለምን የታሰሩት ኮሚቴዎች አይፈቱም በማለት ጥያቄ ያቀረቡ ሲሆን በምላሹም መንግስት ህገ መንግስቱን የማስከበር ግዴታ ስላለበት ህግ ሲጥሱ የነበሩና ሀገሪቷን ወደ አልተፈለገ ሁከትና ረብሻ ለማስገባት ጥረት ሲያደርጉ የነበሩ ግለሰቦችን አይፈታም:: ጉዳያቸዉ በህግ የተያዘ በመሆኑ ማንም ተነስቶ ይፈቱ ስላለ አይፈቱም በማለት ምላሽ ተሰቷል:: በስብሰባዉም ላይ ሀገሪቱን እያመሱ የሚገኙት እጅግ በጣም ጥቂቶች መሆናቸዉን ደርሰንበታል:: በቅርቡም እርምጃ እንወስድባቸዎለን ብለዎል::እነዚህ ጥቂት ግለሰቦች ህዝባዊ, ዴሞክራሲያዊ የመላዉ ሙስሊሞችን ይሉኝታና አድናቆት የተቸረዉ ምርጫ ከተካሄደ ቡሀላም ምርጫዉ በግዳጅ የተካሄደ በመሆኑ አንቀበለዉም እያሉ በራሪ ወረቀቶችን እየበተኑ እንደሚገኙ ገልፀዎል::


የስብሰባ ተሳታፊዎችንም በየአካባቢያችሁ በቤተሰባችሁ የሚገኙ ፀረ ሰላም ሰዎችን አሳልፉችሁ ስጡን በማለት ጥያቄ አቅርበዎል:: ስብሰባዉ እሮብ የተጀመረ ሲሆን ዛሬና ነገ ጁምአም ሙሉ ቀን ከነ አዳሩ እንደሚቀጥል ምንጮቻችን አስታዉቀዎል:: ስብሰባዉ ከሚካሄድበት ማዕከል ወደ ዉጪ ፈፅሞ መዉጣት የማይቻል ሲሆን የስብሰባዉ ተሳታፊዎችም ለግል ጉዳያቸዉ ለመዉጣት ቢፈልጉም የሀገር ጉዳይ ስለሚቀድም አርፉቹ ተቀመጡ እየተባሉ እንደሚገኙ የዉስጥ ምንጮቻችን አስታዉቀዎል:: የምግብ አገልግሎትም እዛዉ ስለተዘጋጀ ተሰብሳቢዎች እዛዉ እየተመገቡ እንደሚገኙ የዉስጥ ምንጮቻችን አስታዉቀዎል:: በስብሰባዉም ከፍተኛ የመንግስት አመራር አካላት በመገኘት ዉይይት ያካሂዳሉ ተብሎ ይጠበቃል::

No comments:

Post a Comment