ክንፉ አሰፋ
በኪም ጆንግ ዘመነ-መንግስት በችጋር እና በእርዛት ይጎሳቆል የነበረ አንድ የሰሜን ኮረያ ወጣት ብቻውን በአደባባይ ወጥቶ የኪም ጆንግ ኢልን መንግስት ይረግማል።
“የምንበላው የለም! የምንለብሰው የለም!… ታርዘናል፤ ደህይተናል! ኪም ጆንግ ከስልጣን ይውረድ!”…ወጣቱ ብቻውን ሲጮህና ሲቃወም የተመለከቱ የኮምኒስቱ ፓርቲ የደህንነት አባላት ወጣቱን አፍነው ወስደው፣ ጨለማ ክፍል ውሰጥ ይወረውሩታል። ለሁለት ቀን ያህል በርሃብ ከቀጡት በህዋላም የጥይት ውርጅብኝ በጆሮው ላይ በማጮህ አስፈራርተው ይለቁታል። በእስር ቤቱ ይተኮስ የነበረው እውነተኛው ሳይሆን የልምምድ ጥይት ነበርና በእስረኛው ላይ የስነ-ልቦና እነጂ የአካል ጉዳት አላደረሰበትም።
ወጣቱ ከእስር እንደተለቀቀ ወደ ቤቱ አልተመለሰም። ይልቁንም ቀድሞ ወደተያዘበት አደባባይ እንደገና በመሄድ አሁንም ተቃውሞውን ቀጠለ።
“ቀለሃ እንኳን አልቋል…ጥይትም የለንም! ኪም ጆንግ ይወረድ!”ኪም ጆንግ ሰሜንዋን ኮርያ በባዶ ሆድ የኒውክለር ባለቤት አደረጋት። አንባገነን መሪዎች ሁሉ ቅድሚያ የሚሰጡት የራሳቸው ባዶ ክብር እና ዙፋኑ ላይ የመቆየቱ ስልት ላይ እነጂ ስለ ዜጋቸው መራብ እና መራቆት ግድ አይላቸውም። ለኪም ጆንግ ኮርያን
የኒውክለር ባለቤት የማድረጉ ተግባር የኮርያ ኩራት ነው። ለራሳቸው ዜጋ ክብር ሳይሰጡ ለሃገር ክብር የማስብ ግብዝነት!? ይህ እኛም ጋ ያለ አባዜ ነው። ከስምንት ሚሊዮን ህዘብ በላይ በምግብ ገና ራሱን ሳይችል ስለ ተአምራዊው የሁለት ድጅት ኢኮኖሚ እድገት ይነግሩናል።
ሃይለማረያም ደሳለኝ ደግሞ የኢትዮጵያ ህዘብ አሁን ጤፍ መብላት መጀመሩን ነው ሰሞኑን ያበሰሩን። ሕዝቡ ጤፍ መብላት የጀመረው መካከለኛ የሚባለው የህብረተሰቡ ክፍል ጨርሶወኑ ጠፍቶ ዝቅተኛ ገቢ ካለው ክፍል በተቀላቅለበት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እድገት ላይ ነው። ያን ምስኪን ህዝብ መለስ ዜናዊ እነዲሁ እንደቀለዱበት አለፉ፤ አሁን ደግሞ እነ…። በ2011 ኪም ጆንግ 2ኛና የሊቢያዉ ኮ/ል ሙአመር ጋዳፊ ከምድራችን ለመጨረሻ ጊዜ ሲሰናበቱ አለማችን የተሸከመቻቸው አምባገነን መሪዎች ቁጥር ወደ ስምንት ዝቅ ማለቱን አለም-አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ዘግበው ነበር። የመንግስት ስልጣን ጨብጠዉ ሰብኣዊ መብቶችን በመርገጥና የፖለቲካ ጭቆና በማድረስ ላይ ከነበሩት ከስምንቱ ጨካኝና ራስ ወዳድ መሪዎቸ አነዱ የነበሩት አቶ መለስ ዜናዊ ባሳለፍነው የፈረንጆቹ አመት ሲያርፉ የአለማችን አንባገነን መሪዎቸ ቁጥር እንደገና በአንድ ተቀንሷል የሚል ተስፋ በብዙዎች ዘንድ ነበር።