መስፍን ግርማ ከኖርዌይ \ጃንዋሪ 2013\
መቼም የጁ ሥራ አይደለን….፣
ያ ፈጣሪ ሁሉን ያካፈለን …፣
በጎ አይደለም ዓመሉ
እኩይ ጣይ ያወጣል አሉ
ላዋቄ፣ ለዱባውም፣ ለቅሉም ።
ይሄዋ! አፉ… ብሎ ቢጀባቸው
እንደ ምጣድ አሻሮ አመሱን
በጥቁር ምላሳቸው ቆሉን
የጊዜው ጊዜኞች… ቃላት ሰንጣቂዎች
የጊዜው ሊቀኞች… ፈጽሞ አስመሳዮች
የጊዜው ንጉሶች… ቅስም ሰባሪዎች
ይጠብሱልናል ቅቤ
ይሞጉቱናል በዱቤ
ያፊዙብናል በቅኔ
እርም የላቸውም አይፈሩ እነሱ ለኩነኔ
ያለቅሱልናል ለቅሶ…
እንደተባለው፣ መልሶ፣ አምሶ
የጊዜው ጊዜኞች… ደርሶ ፖለቲከኞች
የወሬ ቱልቱላ… በደርቁ ላጮች
የወጣቱን ወኔ ሰላቢዎች…
እንግዲህ ዘመናቹ ነጠፈ
ምላሳቹ አንድ እርምጃ አላለፈ
አላሞቀ፣ አልደገፈ፣ አላቀፈ
እንደ በልግ ቅጠል ረገፈ
ይልቅ ወጣቱ ጥሏቹ ከነፈ
የሚያዘልቀውን ደገፈ
ከወክንድ ጎን ተሰለፈ።
No comments:
Post a Comment