Thursday, 30 May 2013

ጋዜጠኛ ሙሉቀን ተስፋሁን ቤንሻንጉል-ጉምዝ ውስጥ ታስሯል

“ኢትዮ-ምኅዳር” ለሚባለው ሣምንታዊ ጋዜጣ ከአማራ ክልል ሲዘግብ የቆየው ሙሉቀን ተስፋሁን በቤንሻንጉል-ጉምዝ ፖሊስ መያዙን የጋዜጣው ምንጮች አስታወቁ።
የቤንሻንጉል-ጉምዝ ወረዳዎች


የአሜሪካ የህግ ባለሙያዎችና አኢጋን በኅብረት ስራ ጀመሩ!

ዓርብ የፖለቲካና የሙስሊም እስረኛ ጠበቆችን ያነጋግራሉ

aba nsmne


በኢትዮጵያ በግፍ የታሰሩ የፖለቲካና የህሊና እስረኞችን በተመለከተ የአሜሪካን የህግ ባለሙያዎች ማህበር (ABA – American Bar Association) ሙሉ በሙሉ ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችለውን ስራ አርብ እንደሚጀምር ተገለጸ። አዲስ አበባ ካሉ የፖለቲካና የሙስሊም ወገን እስረኞች ጠበቆች ጋር የመጀመሪያ ስብሰባ አርብ ግንቦት 23፤2005ዓም ያደርጋሉ። አቶ ኦባንግ ሜቶ የተረሱ እስረኞች ጉዳይም እንደሚካተት ጠቅሰው በፖለቲካ ጉዳዮች ዙሪያ ለታሰሩ ዜጎች ጥብቅና የቆሙ ካሉ የአዲሲቷን ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ /አኢጋን/ በቀጥታ እንዲገናኙ ጥሪ አቅርበዋል።
(ABA) በሚል ስያሜ የሚታወቀውና ከተቋቋመ 135ዓመታትን ያስቆጠረው የአሜሪካ የሕግ ባለሙያዎች ማኅበር ከ400 ሺህ በላይ የህግ ባለሙያ አባላት አሉት። ይህ በአሜሪካ ትልቅ የተባለ ማህበር በግፍ ለሚሰቃዩ ኢትዮጵያዊያን እስረኞች ድጋፍ ለማድረግ የወሰነው የአኢጋን ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ በይፋ የድጋፍ ጥያቄ ባቀረቡ በቀናት ውስጥ ሲሆን፣ በጋራ በተከናወኑ ንግግሮችና የሰነድ ውይይቶች በወር ጊዜ ውስጥ ወደ እንቅስቃሴ ለመግባት እንደተቻለ ለማወቅ ተችሏል።

Monday, 27 May 2013

የኢህአዴግና የሻዕቢያ ድርድር ተበጠሰ ኢሳያስ፣ ደሚት፣ ግብጽ፣ ኳታር፣ ኢህአዴግ


haile and esayas
ኳታር በተናጠል የጀመረችው ኢትዮጵያንና ኤርትራን የማሸማገል ሂደት መበጠሱ ተሰምቷል። ከሽምግልናው ዙሪያ የግብጽ ሚና ስለመኖሩ አመላካች ጉዳዮች አሉ እየተባለ ነው። በድርድሩ ኢህአዴግ በዋናነት እንደ ቅድመ ሁኔታ ያስቀመጠው የትግራይ ህዝባዊ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ደሚት/ ጉዳይ እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል።
አቶ መለስ የኢትዮጵያን ወደብ እንደተራ ጉዳይ አሳልፈው በመስጠት ኤርትራን እንደ አገር እውቅና በሰጡበት ወቅት ድጋፍ ለማሰማት ቀዳሚ የነረችው ኳታር ከበረሃው ትግል ጀምሮ የሻዕቢያ ወዳጅ አገር እንደሆነች ይታወቃል።
ከዚሁ የከረመ ወዳጅነት በመነሳት ኳታር በ2008 ከኢህአዴግ ጋር ተፈጥሮ የነበረውን የጸብ ግድግዳ አፍርሳ ወደ ኢትዮጵያ የመጣችው በዋናነት ሁለቱን አገሮች መልሶ ለማስታረቅ በተያዘ እቅድ ስለመሆኑ ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ይናገራሉ። በተለይም አሁን ያለው የኤርትራ አስተዳደር እጣ ፈንታ አብዝቶ ያስጨነቃት ኳታር በኤርትራ ወደብ ሊዝ በማድረግ፣ ኢንቨስትመንት ላይ በመሳተፍና ልዩ ድጎማ በማድረግ ቀዳሚውን ስፍራ ስለምትይዝ ችግር ከመፈጠሩ በፊት ላይ ታች ማለቷ እንደማይደንቅ ስምምነት አለ።
ጎልጉል ምንጭ የሆኑ ዲፕሎማት እንዳሉት ኳታር አሁን እርቁን የፈለገችው በኤርትራ መረጋጋት እንዲፈጠርና የኤርትራ ኢኮኖሚ አንዲያገግም ለማድረግ በሚል ነው። በሌላ በኩል ህወሃት የዘወትር ስጋቱ የሆነውን ሻዕቢያን ለማስወገድ ሌት ከቀን እንደሚሰራና ይህም በድርጅት ደረጃ አቋም የተያዘበት ጉዳይ በመሆኑ የኤርትራ መንግስት መሰረታዊ የአቋም ለውጥ ሳያደርግ ከኢህአዴግ ጋር የድርድር ስምምነት ላይ መድረስ አስቸጋሪ እንደሚሆን ሁሉም ወገኖች የሚረዱት ጉዳይ ነው።
ከውስጥም ከውጪም ፖለቲከኞች ትኩረት ሰጥተው እየተከታተሉት ያለው የሁለቱ አገሮች  የሰላም ድርድር ዲፕሎማቱ እንዳሉት ሁለት አብይ ጉዳዮች አሉበት። ሁለቱ አብይ ጉዳዮች ደግሞ ሊነጣጠሉ አይችሉም። በኤርትራ እለት እለት እየሰለለ የሄደው የአገሪቱ ኢኮኖሚና የኑሮ ውድነቱ የኢሳያስን አስተዳደር አናግቶታል። በተጨማሪ ሆን ተብሎ ይሁን በሌላ ምክንያት ከሃያላኑ አገራት ጋር የገጠሙት የረዥም ጊዜ ፍትጊያ የኢሣያስን ትከሻ አዝሎታል። ከዚህም በላይ እድሜ ለመለስ የፍቅር ጊዜያቸው ሲሻግት “አሸባሪ” አድርገዋቸው።

Friday, 24 May 2013

የደህንነት ሹሙ ስዊድን ይመጣሉ




eprdf1
በእንግሊዝኛው ምህጻረ ቃል NISS (National Intelligence and Security Service) የብሔራዊ ደህንነትና የደኅንነት አገልግሎት ሁለተኛ ሰው የሆኑት አቶ ኢሳያስ ወ/ጊዮርጊስ ስዊድን እንደሚመጡ ተሰማ። በስካንዲኔቪያ አገራትና በድፍን አውሮፓ በሚኖረው ዲያስፖራ ላይ የሚያተኩር “የግል” መሰል የሬዲዮ ስርጭት ለመጀመር መታሰቡም ተሰምቷል።
የጎልጉል የመረጃ ምንጮች እንዳስታወቁት አቶ ኢሳያስ ስዊድን ይመጣሉ የተባለው በመጪው የሰኔ ወር ነው። የኤርትራዊ ዜግነት ያላቸውና አቶ መለስ በእጅጉ ይተማመኑባቸው እንደነበር የሚነገርላቸው አቶ ኢሳያስ ስዊድን ከደረሱ በኋላ ሊያከናውኑ ስላሰቡት ተግባር ዝርዝር ለመረዳት ጊዜው ገና እንደሆነ ምንጮቹ አመልክተዋል።
“ሆኖም ግን” ይላሉ ምንጮቹ፣ ” ሆኖም ግን አቶ ኢሳያስ ድርጅታቸው ኢህአዴግ በስካንዲኔቪያን አገሮች በተደጋጋሚ ያጋጠመውን ውግዘት አስመልክቶ አዲስ አደረጃጀት እንደሚገነቡ ታውቋል፡፡”
የኢህአዴግና የስርዓቱ ደጋፊዎችን ለማብዛት በልዩ ልዩ ጥቅማ ጥቅም አባላትን የመመልመሉ ስራ በተጠናከረ መልክ እንደሚሰራበትና የዲያስፖራውን ማኅበረሰብ ለመጠርነፍ ይዋቀራል የተባለው አዲሱ ድር /ኔትወርክ/ ትኩረት የሚያደርገው “አብዛኛው አድፋጭ” ወይም “silent majority” ላይ እንደሆነ መረጃ ሰጪዎቹ ተናግረዋል። ይህንኑ ተግባራዊ ለማድረግ የኢትዮጵያዊያን ኮሚኒቲዎችን ማደራጀት አንዱና ዋናው የአደረጃጀቱ አግባብ እንደሆነም ተጠቁሟል።

Thursday, 23 May 2013

ከባሕር ዳሩ ግድያ ጋር በተያያዘ 22 የፖሊስ አባላት ተይዘዋል

ከአንድ ሣምንት በፊት በባህር ዳር ከተማ የተፈፀመው ግድያ የብሔር ልዩነት ጋር ግንኙነት እንደሌለው የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት መሪ ምክትል ኮማንደር ዋለልኝ ዳኘው አስታውቀዋል።

ባሕርዳር

Wednesday, 22 May 2013

ወይ መላ ነሽ አሉ ወይ መላ አባ መላ!



ከሎሚ ተራተራ

እነደምን ከርማችሁ ወዳጆች ? እኔ አምላክ ይክበር ይመሰገን ደህና ነኝ። ሰሞኑን ከወደ ትውልድ አገር የመጡን አዛውንት እንኳን ደህና መጡ፤ የሰሜን አሚሪካ አየርሰ እንዴት ተቀበሎት ለማለት ወደ ጎረቤት ቤት፤ ጎራ ብዪ ነበርና፤ አረፍ እንዳልኩ አንድ ቀደም ብሎ ባለሁበት ከተማ ለጥቂት ወራት በርቀት ዝቅ ብለው እጅ በመንሳት የሃገሬን ተናፋቂ ባህል የሚያሰታውሱኝና እጀግም የማከብራቸውን አባት ድምጥ ሰማሁ።
እንድምነ ዋላችሁ አሉ አቶ በልሁ፤ ድምጣቸውን ያለወትሮዎቸው ለዘብ አድረገው፤ ;;’’’’’ እግዚአብሒር ይመሰገን”’ እንደምን ዋልክ በልሁ ግባ፣ ምነው ? ምን አዲሰ ነገር ሰማህ ደግሞ ድምጥህ ያለወትሮው ለዘብ ብሏል አሉ አቶ ታከለ፤ የዛሪን አያረገወና ልጆቻቸውን ለማየት ወደ ሰሜን አሜሪካ ከመጡ ወዲህ ቀረ እንጂ ድሮማ ሰው ሁሉ የሚጠራቸው “ አልሞ ተኳሸ” እያለ ነበር አሉ።
አቶ በልሁና አቶ ታከለ ለረጅም ግዜ ወዳጆች ከመሆናቸውም ሌላ በወቅቱ የሀገራችን ጉዳይ ዙሪያ ዘወትር በቁጭት ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ካላቸው ሃገራዊ ፍቀር በመነሳት መደረግ ሰለሚገባው የሃገር ጉዳይ ፤ በተለይም እንዴት አንድነታቸንን መገንባት እንደሚገባን አበክረው ከሚናገሩት የአካባቢያቸን የሰሜን አሜሪካ አዛውንቷች ዋናዎቹ ናቸው።

Monday, 20 May 2013

The Corruption Game (Alemayehu G. Mariam)


by Alemayehu G. Mariam

House cleaning or window dressing?
Are they playing us like a cheap fiddle again? For a while, it was all about the Meles Dam and how to collect nickels and dimes to build it. That kind of played itself out. (Not to worry. That circus will be back in town. The public has the attention span of a gold fish. So they think.)  It’s time to change the flavor of the month. Time for a new game, a new hype. How about “corruption”? It’s a chic topic. The World Bank is talking about it. Everybody is talking about it. Even the corrupt are talking about corruption. Imagine kleptocrats calling corruptocrats corrupt? Or the pot calling the kettle black?
I have been talking and writing about corruption in Ethiopia for years. After dozens of commentaries on some aspect of corruption in Ethiopia, I am still drumbeating anti-corruption. I have been “lasing” corruption in my  commentaries in 2013. I was flabbergasted by the World Bank’s 448-page report, “Diagnosing Corruption in Ethiopia”. I am still reeling from the shocking findings in that report. In my commentary last week, “Educorruption and Miseducation in Ethiopia”, I focused on corruption in the education sector. It is one thing to steal an election or pull off a gold heist at the national bank, but robbing millions of Ethiopian youth of their future by imprisoning them in the bowels of a corrupt educational system is harrowing, downright criminal. Aarrgghh!

Sunday, 19 May 2013

የሰንደቅ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ በፖሊስ ተጠየቀ


የሰንደቅ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ፍሬው አበበ ከሰባት ወራት በፊት ስለ ወይዘሮ አዜብ መስፍን በዘገበው ዜና ትላንት በፖሊስ ተጠየቀ።

ፍሬው አበበ - የሰንደቅ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ
ፍሬው አበበ - የሰንደቅ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ

Saturday, 18 May 2013

ታሪክን የኋሊት፤ የአቶ መለስ ድንጋጤ!


 (አቤ ቶኪቻው)
እንግዲህ ይህ ከሆነ አመቱ ሆነ አይደለ… ቅዳሜም ቅዳሜ፣ እሁድም እሁድ ነው እና ምናልባት ካልተገናኘን… እንዳንረሳው፤ ከወዲሁ ቀኑን እንደሚከተለው እንዘክረው… (በቅንፍም ኤድያ እነ እንትናዬ ደግሞ ሊበሳጩብኝ ነው… (በሌላ ቅንፍ እንግዲህ ይቻሉት እኛ ስንቱን ችለነው የለ…))

Melese Zenawi
በመጀመሪያም፤
ብስጭቴ
እኔ እኮ የምለው ሰው አይኑ እያየ የሰራውን ስራ እያወቀ ወደ አሜሪካ ለዛውም ወደ ዋሽንግተን ዲሲ ይሄዳል እንዴ!? እውነቱን ለመናገር እኔ አቶ መለስ ዜናዊን ብሆን ኖሮ ዲቪ እንኳ ቢደርሰኝ ሀገር ይቀየርልኝ እላለሁ እንጂ አሜሪካ አልሄድም። እነ ቻይና ባሉበት አለም እነ ሰሜን ኮሪያ በሚኖሩበት ምድር ሰው እንዴት ወደ አሜሪካ ይሄዳል? (ይቅርታ ሰው በሚል የተጠቀሱት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችንን ነው)
ዋናው ወሬ፤
የሆነው ሆኖ ትላንት በዋሽንግተኑ ስብሰባ አቶ መለስ ዜናዊ ሲመጡ ከውጪ ያለውን የተቃውሞ ድምፅ በመከራ አልፈው የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ከገቡ በኋላ ደግሞ ጋዜጠኛ አበበ ገላው ተሰብሳቢው ፊት፤ ከውጪ ያለው ህዝብ በሰላማዊ ሰልፍ፣ እንዲሁም አዲሳባ ያለው ህዝብ ደግሞ በሰላማዊ ዝምታ በሆዱ ምን እያላቸው እንደሆነ ነጥብ ነጥቡን ነግሯቸዋል። እንደው ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነውብኝ እንጂ “እስከ ዶቃ ማሰሪያቸው ድረስ ነግሯቸዋል!” ብል የበለጠ ይገልፀዋል መሰል!
የጋዜጠኛ አበበ ገላው ድርጊት ከዚህ በፊት ጆርጅ ቡሽ ላይ ጫማ ከወረወረው ጋዜጠኛ ጋር የሚቀራረብ ይመስላል። እንደውም በቪዲዮ እንዳየኋቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ የደረሰው የቅስም ስብራት “በጫማ መመታት በስንት ጣዕሙ!” ያሰኛል።

Wednesday, 15 May 2013



Muslime feiern das Ende des Ramadans im Nationalstadium von Addis Abeba, Äthiopien
Copyright: Getachew Tedla/DW, 
19.08.2012, Addis Abeba, Äthiopien

ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች፥ ቴሌቪዥንና ባሕርዳር ዩኒቨርስቲ

የእስረኞቹ ጠበቃ እንዳስታወቁት ክሱን የመሠረቱት የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጅሐዳዊ ሐራከት በሚል ርዕስ ባሰራጨዉ ፊልም የደንበኞቻቸዉን ሥም በማጥፋቱ ነዉ።በተያያዘ ዜና የባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች በበኩላቸዉ ሐይማኖታዊ ነፃነታችንን ገፎናል ያሉት የዩኒቨርስቲዉ አስተዳደር ዉሳኔዉን ካልቀየረ እንደሚከሱ አስታወቁ።
የኢትዮጵያ መንግሥት በአሸባሪነት ከሶ ያሰራቸዉ የሙስሊሞች መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት የኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅትን፥ የፌደራል ፖሊስንና የሌሎች መስሪያ ቤት ሐላፊዎችን በሥም አጥፊነት ከሰሱ።የእስረኞቹ ጠበቃ እንዳስታወቁት ክሱን የመሠረቱት የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጅሐዳዊ ሐራከት በሚል ርዕስ ባሰራጨዉ ፊልም የደንበኞቻቸዉን ሥም በማጥፋቱ ነዉ።በተያያዘ ዜና የባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች በበኩላቸዉ ሐይማኖታዊ ነፃነታችንን ገፎናል ያሉት የዩኒቨርስቲዉ አስተዳደር ዉሳኔዉን ካልቀየረ እንደሚከሱ አስታወቁ።የባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ አስተዳደር ሐይማኖታዊ ግዴታችንን እንዳንወጣ አግዶናል በማለት በርካታ የዩኒቨርቲዉ ተማሪዎች ትምሕርታቸዉን ለማቋረጥ መገደዳቸዉ ገልፀዉ ነበር።የሁለቱን ክሶች ይዘትና ምክንያት በተመለከተ የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዝር ዝር ዘገባ ልኮልናል።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ነጋሽ መሐመድ
አርያም ተክሌ

AUDIOS AND VIDEOS ON THE TOPIC

ከሙስናው በስተጀርባ (ከኢየሩሳሌም አርአያ)


ከኢየሩሳሌም አርአያ

በሕወሐት የተፈጠረው የቀውስ ማእበል አድማሱን እየለጠጠ መሔዱን ተከትሎ «ታማኝ» ሆነው በሙስና ሲያገለግሉ የቆዩትን ጭምር እየበላ እንደሚገኝ የቅርብ ምንጮች አስታወቁ። በቀዳሚነት የሚያነሱት በጉምሩክ ቁልፍ ስልጣን የነበረውን የሕወሐት አባል ገ/ዋህድ ወ/ጊዮርጊስን ሲሆን እንዴትና በማን ወደስልጣን እንደመጣ እንዲሁም ምን-ምን ተግባራት ይፈፅምና ያስፈፅም እንደነበረ ምንጮቹ ሂደቱን እንደሚከተለው ይገልፁታል።
tplf rotten apple
ገ/ዋህድ በ1993ዓ.ም ፓርቲው ለሁለት መሰንጠቁን ተከትሎ ወደ ስልጣን እንዲመጣ ተደረገ። ከጉምሩክ ሃላፊነት በተጨማሪ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ምክትል ዳይሬክተርነት ስልጣን እንዲጨብጥ የተደረገው በአቶ መለስ በተለይ በአዜብ ይሁንታ ጭምር እንደነበረ ምንጮቹ ይጠቁማሉ። ገ/ዋህድ ለዚህ ስልጣን የበቃው ለአቶ መለስ ቡድን በከፈለው መስዋእትነት ሲሆን በክፍፍሉ ማግስት የሙስና ዘመቻ ተከፍቶ እነአባተ ኪሾና ሌሎች እስር ቤት እንዲገቡ ቀጥተኛ ትእዛዝ ከመስጠት አንስቶ ራሱ ክስ አዘጋጅ፣ምስክርና ፈራጅ..በመሆን የላቀ ሚና መጫወቱን ያስታውሳሉ። በዚህ ተግባሩ የበለጠ ታማኝነቱን በማሳየቱ ከአዜብ በሚሰጠው ቀጥታ ትእዛዝ ሙስናውን ማከናወን መቀጠሉን ምንጮቹ አያያዘው ይጠቁማሉ። በ10ሺህ ቶን የሚገመት ቡና ከአዜብ በተቀበለው ትእዛዝ በህገወጥ መንገድ ከአገር ተዘርፎ የተሸጠበትና ጉዳዩም በፓርላማ ተነስቶ በጠ/ሚ/ሩ «የሌቦቹን እጅ እንቆርጣለን» የሚል አስቂኝ ምላሽ መሰጠቱን ያስታውሳሉ። በተጨማሪ በጉምሩክ ለረጅም አመት በመምሪያ ሃላፊነት ሽፋን የተቀመጠውና የቢሮውን የበላይ ሃላፊዎች በጥብቅ ከመቆጣጠር ጀምሮ እያንዳንዱን የሙስና ተግባር ከጀርባ ሆኖ የሚያስፈፅመው የአዜብ የቅርብ ስጋ ዘመድ ፍትሃነገስት ክንደያ እንደሚጠቀስና ግለሰቡ ቀረጥ ያልተከፈለባቸው 500 ሳተላይት ዲሾች እንዲገቡና በአዜብ በበላይነት ይመራ ለነበረው የዘረፋ ቡድን ለሰባት አመታት በየወሩ 20ሚሊዮን ከቴሌ በህገወጥ መንገድ እንዲዘረፍ ያደረገና በኋላም ከነገ/ዋህድ ጋር ሆኖ በርካታ ሙስናዎችን በዋናነት በማስፈፀም እንደሚጠቀስ ያመለክታሉ።

በኢንቨስትመንት ስም የሚፈጸም የመሬት ነጠቃ፤ በኢትዮጵያ” ጥናት ትርጉም ይፋ ሆነ!!


ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን)

በኢንቨስትመንት ስም የአገር ሃብትና ትውልድን እየበላ ስላለው የመሬት ነጠቃ አስመልክቶ የኦክላንድ ተቋምና ድርጅታችን ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ በጋራ ያዘጋጁት ጥናታዊ ዘገባ ይፋ ሆነ። የጋራ ንቅናቄያችን ዋና ዳይሬክተር ጥናቱ በትክክለኛ ጭብጥ ላይ ተመስርቶ እንዲዘጋጅ ለህይወታቸው ሳይሳሱ መረጃ በመስጠት ለተባበሩ ዜጎች “ታላቅ ክብር ይሁንላችሁ። አሁን አትታወቁም። ግን ከቶውንም አትረሱም። ክብር ለማትታወቁት ግን ለማትረሱት የአገር ጀግኖች” በማለት ምስጋና አቅርበዋል።Understanding Land Investment Deals in Africa (Ethiopia)
Understanding Land Investment Deals in Africa (Ethiopia)
ኢህአዴግን በደፈናው መቃወምን ዓላማው ያላደረገው ይህ ጥናታዊ ዘገባ ዜጎችን ካደጉበት፣ ከኖሩበት፣ ከቀያቸው፣ ከህልውናቸው፣ ከርስታቸው፣ ወዘተ ያለ አንዳች ውይይት፣ ምክክርና ንግግር በማፈናቀል ለውጪ ኩባንያዎችና ለራሱ ለባለጠመንጃው አገዛዝ ሰዎችና ባለሟሎች መሬት ማከፋፈሉን በማስረጃ ያሳያል። የራሱ የኢህአዴግ አካላትም በሪፖርቱ ውስጥ በአግባቡ ድምጻቸው ተካትቷል። የሚጠቀሙባቸው አዋጆችና ህጎችም አልተዘለሉም።
“የውጪ ባለሃብቶችና ኩባንያዎች ወደ አገር ውስጥ መግባታቸው ለቴክኖሎጂ ዝውውር፣ በአገሪቱ ያለውን የምግብ እጥረት ለማስወገድ ይረዳል” የሚሉ ምክንያቶች እያቀረበ ያለው ኢህአዴግ በተግባር ሲፈተሽ ተግባሩና ዓላማው ምን እንደሆነ የሚያመለክተው ጥናቱ የስርዓቱ ሰለባዎች፣ የኢህአዴግ ባለስልጣናት፣ ኢንቨስተሮች፣ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ክፍሎች፣ የቅርብ ምስክሮች፣ የተለያዩ ከዓለምአቀፍ ተቋማት የተገኙ መረጃዎች፣ አገዛዙ ራሱ ይፋ ያደረጋቸው መረጃዎችና ለጥናቱ አስፈላጊ የተባሉ አኻዞች የተካተቱበት በመሆኑ እውነታውን ህዝብና ማናቸውም ወገኖች እውነቱን ለመረዳት ያስችላቸዋል ተብሎ በጉልህ ታምኖበታል።

Tuesday, 14 May 2013

17 ሰዎችን የገደለው የፌደራል ፖሊስ ማንነት በውል አልታወቀም




ኢሳት ዜና:- እሁድ ግንቦት4፣ 2005 ዓም ከምሽቱ 2 ሰአት ከ45 ደቂቃ ላይ ፣ የሁለት አመት ህጻንን ጨምሮ 17 ሰዎችን በባህርዳር ከተማ ቀበሌ 11 ወይም በተለምዶ አባይ ማዶ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ በግፍ የገደለው የፌደራል ፖሊስ አባል ማንነት እና የገደለበት ምክንያት በውል አለመታወቁን ተከትሎ የተለያዩ መላምቶች እየተሰነዘሩ ነው።
ወታደሩ ድርጊቱን የፈጸመው አንድ ያፈቀራት ወጣት ከእርሱ ጋር ለመቀጠል ፈቃደኛ ባለመሆኑ ነው የሚል አስተያየቶች ቢሰሙም በሌላ በኩል ደግሞ ግለሰቡ የሌላ ብሄር ተወላጅ በመሆኑ ጥላቸውን ለመግለጽ በሚል የፈጸመው ነው የሚሉ ወገኖች አሉ።
Bahirdar Ethiopia 18 killed
በባህርዳር ከተማ ሰላማዊ ዜጎችን የጨፈጨፈው የፌዴራል ፖሊስ አስክሬን
እሁድ ምሽት ወታደሩ ወደ አፈቀራት ልጅ ቤት ቢሄድም እናቷን ብቻ በማግኘቱ ተኩሶ የልጂቱን እናት መግደሉን ከዚያ በሁዋላ መንገድ ላይ ያገኛቸውን ሁሉ መግደል መጀመሩን አንዳንድ ነዋሪዎች ተናግረዋል።
በሌላ በኩል ግን ግለሰቡ ከፍተኛ ወታደራዊ ጥበቃ በሚደረግበት የብአዴን ጽህፈት ቤት እና የሰማእታት ሀውልት በሚገኙበት አካባቢ አካባቢ መሆኑ እና ሌሎች ፖሊሶችም አፋጣኝ እርምጃ ለመውሰድ አለመቻላቸው ፣ ከዚህም በተጨማሪ ገዳዩ ወታደር የሌላ ብሄር ተወላጅ ነው የሚለው ወሬ በስፋት መሰራጨት አብዛኞቹ ወጣቶች ጉዳዩ ከፖለቲካ ከፖለቲካ ጋር የተያያዘ ነው በማለት አስተያየት እንደሚሰጡ የባህርዳር ዘጋቢያችን ገልጿል።
የባህር ዳር ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን መምሪያ ሀላፊ ኮማንደር ደረጀ አቻምየለህ የገዢው ፓርቲ ልሳን ለሆነው ራዲዮ ፋና ” ግለሰቡ በውል ባልታወቀ ምክንያት በመንገድ ላይ በከፈተው ተኩስ 12 ሰዎች መገደላቸውን በሰዓቱም ወታደሩን በቁጥጥር ስር ለማዋል ፖሊስ ክትትል ሲያደርግ እንደነበርና በመጨረሻም ራሱን በወንዝ ውስጥ በመወርወር ህይወቱን እንዳጠፋ” ተናግረ= ዋል።
የፖሊስ አዛዡ “ድርጊቱን የፈፀመው ግለሰብ የፖሊስ አባል መሆኑን ገልጸው ፥ ድርጊቱን የፈፀመበት ምክንያትም ግለሰባዊ ” ነው ብለዋል።
ኢህአዴግ ድርጊቱ ከፖለቲካ ጋር የተያያዘ አለመሆኑን ለማስረዳት በከተማው ውስጥ የሚገኙ ዋና ዋና አባሎቹን በማሰማራት ከፍተኛ ቅስቀሳ እያደረገ ነው።
ይሁን እንጅ መንግስት የሟቾቹን ቁጥር 12 አድርጎ ማቅረቡ ህዝቡን ለባሰ ጥርጣሬ እንደከተተው ዘጋቢያችን ገልጿል። በርካታ የአይን እማኞች እንደሚሉት የሟቾች ቁጥር 17 ደርሷል። መንግስት ወታደሩ ራሱን እንዳጠፋ አድርጎ ቢገልጽም፣ ነዋሪዎች ግን ወታደሩ ራሱን ቢያጠፋ ኖሮ አስከሬኑ ይገኝ እንደነበር፣ በተለይም ደግሞ አባይ በአሁኑ ሰአት ከመቼውም ጊዜ በላይ ቀንሶ የሚታይበት ጊዜ በመሆኑ ወታደሩ ራሱን ወደ ውሀው ቢወረውር እንኳ የመትረፍ እድል ሊኖረው እንደሚችል በመግለጽ በመንግስትን በኩል የቀረበውን ዘገባ አልተቀበሉትም።
ከተገደሉት መካከልም አንድ የሁለት አመት ተኩል ህጻን እና ሴቶች ይገኙበታል። የ7ቱ የቀብር ስነስርአት ዛሬ በደብረ አባይ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የክልሉ ፕሬዚዳንት አያሌው ጎበዜ በተገኙበት ተፈጽሟል።
ከወራት በፊት ኮሶበር በምትባል ከተማ አንድ የፌደራል ፖሊስ አባል በርካታ ሰዎችን መግደሉን መዘገባችን ይታወሳል። የፌደራል ፖሊስ አባላት በየጊዜው በህዝቡ ላይ የሚፈጽሙት በደል እየጨመረ ቢመጣም በመንግስት በኩል እርምጃዎች ሲወሰዱ አይታይም።

Monday, 13 May 2013

ለኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የትግል አንድነት ጥሪ


ሲራጅ ደታንጎ

አዲስ አበባ ዉስጥ በግንቦት 17 ቀን 2005 በሚደረገው ሠላማዊ ሠልፍ የሁሉንም ብሶተኛ ኢትዮጵያዊ ክፍል ጥያቄዎች አንግበን በሙሉ ልብ እንሳተፍ፣ የሕዝቡን አንድነትም ለሚጠራጠሩት ሁሉ በተግባር እናረጋግጥ። በዚህ ወቅት አዲስ አበባ የሚከበረውን የአፍሪካ ኅብረት 50ኛ ዓመት፣ የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል ምክንያት ከበርካታ የአፍሪካ ሀገሮችና ከአንዳንድ ዓለም አቀፍ ድርጅቶችም እንግዶች ስለሚኖሩ፣ የህዝቡን የፍትኅና የመብት ጥያቄዎች ለዓለም ኅብረተሰብ ጭምር ልናሰማ የምንችበት ጥሩ አጋጣሚም ነው እንላለን። አፋኙንና ግፈኛውን መንግሥትም በዓለም ህዝብ ፊት ይበልጥ ለማጋለጥ ያስችለናል።
A call for demonstration in Addis Ababa, Ethiopia
ትልቁ አስፈላጊ ተግባር፣ ምላሽ የሚጠይቁት አንገብጋቢ የፍትኅ፣ የመብት (የዕምነት መከበር ጭምር)፣ የህግ የበላይነት፣ … ጥያቄዎች በግልጽና በአንድነት፣ የችግሮቹ ሰለባ በሆነው ህዝብ በራሱ በአደባባይ በሠላማዊ መንገድና በይፋም መገለጻቸው ላይ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ በገዥው አምባገነናዊ ቡድን ሙሉ መብቱንና ሠላሙን ጭምር አጥቷል። ህዝቡ ሠላም የሚያገኘው፣ ክብሩንና መብቱን ሊያስመልስ የሚችለው፣ ከእንግዴህ በተባበረና ጠንካራ ትግሉ ብቻ ነው።ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ከዓመት በላይ በከፍተኛ ቁርጠኛነትና ብልሃት በግንባር ቀደምትነት ያደሩግት ሠላማዊ ትግል ከእንግዴህ የመላው ኢትዮጵያ ሕዝብ ትግል አካል እንዲሁን ሁኔታዎች ይጠይቃሉ። የኢትዮጵያ ሕዝብ ሃሳቡን በነፃ የመግለጽ መብቱን፣ የመሠለፍና ጥያቄዎቹን በይፋ የማቅረብ መብቱን ጭምር፣ ዛሬ መልሶ ይቀዳጀው፣ ይጠቀምበትም።
ዛሬ ሀገራችን ህግና ፍትኅ የጠፉባት ሆናለች። የህግ የበላይነት፣ በነፃነት የሚሠራ የፍርድቤት፣ ደብዛቸው ጠፍቷል። አንድነትዋ የተጠበቀ፣ ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን የምንፈልግ ሁላችን ያለመወላወል ከኢትዮጵያ ህዝብ ጎን ቆመን የትግሉና የመስዋዕትነቱም ተካፋዮች ልንሆን ይገባል።
በዕምነት ተቋሞች ዉስጥ ጣልቃ በመግባት በሙስሊም ኢትዮጵያውያን ላይ እየደረሰ ያለው እመቃና ወከባ ባስቸኳይ ይቁም፣ የታሰሩት የምእመናኑ ተወካዮችና የሃይማኖት መሪዎችም ባፋጣኝ ይፈቱ!
ፓትሪያርክ ከመሾም ጀምሮ፣ ገ ዳማትን እስከ መድፈርና ማፍረስ፣ ምዕመናን መግደልና ባህታዊያኑን መደብደብ፣ ማሰርና ማሰቃየት፣ ግፍና በደል ናቸውና ያብቁ! መንግሥት በዕምነት ተቋማት ዉስጥ ጣልቃ መግባቱን ያቁም!
በአማራው ብሄረሰብ ተወላጆች፣ በጋምቤላ አኝዋኮችና በሌሎችም ዜጎች ላይ እየተፈጸመ ያሉት ከሚኖሩባቸው አካባቢዎች የማፈናቀል፣ ዘር የማጽዳት፣ ዘር የማጥፋት አሰቃቂ ተግባሮች በአስቸኳይ ይቁሙ። ካሳ ለተጎጅዎች ይከፈል! ወንጀለኞቹ ለፍርድ ይቅረቡ!
እስር ቤቶችን እያጣበቡ ያሉት የፖለቲካ እስረኞች፣ ጋዚጠኞችና ሌሎችም የኅሊና እስረኞች በሙሉ አሁኑኑ ይፈቱ!
ጸረሽብርተኝነት በሚል አሳሳች ስያሜ የወጣው ህዝብን እያሸበረ ያለው ዓዋጅ ሳይውል ሳያድር ይነሳ!
“የነጻው ፕሬስ መተዳደሪያ ሕግ” በሚል ስያሜ የወጣው አፋኝ ህግ ይሰረዝ/ይሻር!
ዕምነት የግል ሀገር ግን የጋራ ነችና  መላው ሕዝብ በአንድነት ከታገለ ያለጥርጥር ያቸንፋል!
የሕዝቡን የተባበረ ጉልበት የሚበግረው ምድራዊ ኃይል የለም!

ሙስናን በስንጥር! ከዚያስ?

ዋናዎቹ “ሌቦች” በሞቀው ሆቴላቸው አሉ!!
inter


በቀረጥ፣ በሙስናና ባለስልጣናትን የንግድ ሸሪክ በማድረግ ኢትዮጵያን እየጋለቡዋት ያሉ “ባለሃብቶችና አሽከሮቻቸው” እስካልተነኩ ድረስ ኢህአዴግ በሙስና ላይ የጀመረውን ትግል ሙሉ ሊያደርገው እንደማይችል ተገለጸ። ጅማሮው የችግሩ ቁልፍና እምብርት በሆነው ተቋም ላይ መሆኑ የሚደነቅ እንደሆነ የሚገልጹ ክፍሎች ደግሞ ድሩ ያልተበተበው የለምና የመጨረሻው አካሄድ ወዴት እንደሚያመራ ለመገመት ቢቻልም ጅምሩ ይገፋል የሚል ጥርጣሬ እንዳላቸው አስታውቀዋል።
የባለስልጣናት ሚስቶችን፣ ዘመዶችና ወዳጆችን በተቋሞቻቸው ውስጥ በማይመጥኑት ሃላፊነት በመመደብ፣  ከተለያዩ የማማለያ ሽልማቶች ጋር ከፍተኛ ደሞዝ በመክፈል፣ አንዳንዴም ውጪ አገር ድረስ የህክምና ወጪ በመሸፈን ሰበብ የአገሪቱን የአመራር በትር ጨብጠው አገሪቱን እያለቡ ያሉት ወገኖች በይፋ እንደሚታወቁ የሚገልጹ ክፍሎች “አሁን ተጀመረ የተባለውና ይፋ የተደረገው የሙስና ትግል እነዚህን ክፍሎች ብብቱ ስር ይዞ የሚቀጥል ከሆነ ከቀልድ አይዘልም” ሲሉ ጥርጣሬያቸውን ያስቀምጣሉ።
አትራፊ የሆኑ የህዝብና የአገር ተቋማትን ወደ ግላቸው ያለ ክፍያ፣ ያለ ተመጣጣኝ ዋጋ፣ በተጭበረበረ ጨረታና አሰራር ወደ ግላቸው በማዞር አቶ መለስ “ተራው ህዝብ” በማለት በሚጠሩት ህዝብ ትከሻ ላይ እንዳሻቸው የሚዘሉትን “የሙስና አባቶችን” መታገል የማይችል የጸረ ሙስና ቀረርቶ ከተራ የፖለቲካ ልዩነት የዘለለ መነሻና መድረሻ ሊኖረው እንደማይችል እነዚሁ ወገኖች ይናገራሉ።

Friday, 10 May 2013

ሲጠበቅ የነበረው የተቃውሞ ሰልፍ በደቡብ አፍሪካ ዛሬ ተካሄደ



ክራንቻ፣ ከደቡብ አፍሪካ
በዛሬው ዕለት የተደረገውን ሰልፍ ለማደናቀፍ የወያኔ መንግስት ጭፍሮች ለዲፕሎማቶች እና ለፖሊስ የሰጡት የሀሰት ውንጀላ በትላንትናው ዕለት ውድቅ ተደርጎ ዛሬ በደቡብ አፍሪካ የሰላማዊ ሰልፍ ተደርጓል።
ተቃዋሚ ሀይሎች የሚያደርጉትን የሰላማዊ ሰለፍ እጅግ የፈራው ወያኔ ሰልፉን የጠሩት አሸባሪዎች ናቸው፣ ከዚህ በፊትም ቴዎድሮስ የሚባለውን የኢትዮጵያ ባለስልጣን በደርባን ርዕሰ ከተማ የጠለፋ ሙከራ ሊያካሂዱበት ነበር የሚልና መሰል የሀሰት ውንጀላዎችን በመደርደር ቢሟገትም ጉዳዩ የሚመለከተው አካል የደቡብ አፍሪካን ዲሞክራሲያዊ ህገ-መንግስት የሚጻረር ስህተት ላለመፈጸም ሲል የሰላማዊ ሰልፉን ፈቃድ በደቡብ አፍሪካ ነዋሪ ለሆኑ ኢትዮጵያውያን ሰጥቷል።
በመሆኑን ዛሬ አርብ ሜይ 10፣ 2013 ከጥዋቱ ሁለት ሰዓት ጀምሮ በጆሀንስበርግ የተሰበሰበው ህዝብ ወደ ፕሪቶሪያ ጉዞውን በማድረግ የስብሰባው ስፍራ ተገኝቶ መልዕክቱን በቃልና በደብዳቤ ለተባበሩት መንግስታት ከፍተኛ ልዑክ እና ለደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ቃል-አቀባይ፣ በኢትዮጵያ ማህበረሰብ ተወካይ አቶ ደረጀ አማካኝነት አስረክቧል።
ሌላው በሰላማዊ ሰልፉ ወቅት የተፈጠረ አስገራሚ ነገር ቢኖር፣ የኦጋዴን ተቃዋሚ ሀይሎች በስፍራው በመገኘት “ከወያኔ እንጂ ከኢትዮጵያ ህዝብ የመገንጠል ሀሳብ የለብንም… ወያኔ ይወገድ!” ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ከ ኦጋዴን ወገኖቻችን መካከል አንዲት እህታችን ይዛ የነበረው መፈክር የብዙዎችን ቀልብ የሳበ ነበር። እንዲህ ይነበባል፣

“60% OF ETHIOPIAN GPD IS WESTERN AID TO KILL CIVILIANS”

ድል ለሰፊው ህዝብ!

Wednesday, 8 May 2013

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ቤቱን እንዲለቅ ተገደደ


ሚያዚያ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ለጋዜጠኛው ቅርበት ያላቸው ወገኖች ለኢሳት በላኩት መረጃ እንደገለጹት ጋዜጠኛ ተመስገን ተከራይቶ በሚኖርበት ቀበና አካባቢ ያለው ቤቱን እንዲለቅ በአከራዩ የተነገረው አንድ የመስተዳድሩ ባለስልጣንና አንድ ማንነቱ ያልታወቀ ግለሰብ አከራዩ ቤቱን እንዲያስለቀቁት ማስጠንቀቂያ ከሰጡዋቸው በሁዋላ ነው።
የቤት አከራዩ “  ሁለቱ ሰዎች መጥተው ለመሆኑ ተመስገን ምን እንደሚሰራ ያውቃሉ ወይ? ተመስገን ማን እንደሆነስ ጠንቅቀው ያውቃሉ ወይ?  ለማንኛውም ዛሬ የምናሳውቅዎት እርሱ ለአካባቢው ሰላም ያሰጋል፣ ከዚህ በሁዋላ እንዳያስቀጥሉት ” ብለው እንዳስጠነቀቁዋቸው ለጋዜጠኛው በመንገር በአስቸኳይ ቤት እንዲፈልግ ተማጽነዋል። ጋዜጠኛ ተመስገንም ቤቱን በፍጥነት ለቆ ለመውጣት እንደሚቸገርና የአንድ ወር የቤት መፈለጊያ ጊዜ እንዲሰጠው ጠይቋል።
የፍትህ ጋዜጣ አዘጋጆች ለራሳቸው አሲምባ የሚል ስም በሰጡት የጋዜጠኛው መኖሪያ ቤት ውስጥ የኢዲቶሪያል ስብሰባዎችን እና ጽሁፎችን ያዘጋጁ እንደነበር ለማወቅ ተችሎአል።
ጋዜጠኛ ተመስገን የሚያዘጋጀው ፍትህ ጋዜጣ በመንግስት ጫና እንዲቋረጥ ከተደረገ በሁዋላ ጋዜጠኛው ህተመቱን ሊያስቀጥል የሚችልበትን ፈቃድ እስካሁን አላገኘም። ከ106 በላይ ክሶች ያሉበት ተመስገን ፣ አሁንም ጽሁፎችን በፌስቡክና በተለያዩ ድረገጾች በመጻፍ ላይ ይገኛል።

Tuesday, 7 May 2013

አባይ፤ የኢህአዴግ አባል ነውን!?



ከአቤ ቶኪቻው
“አባይ ማደሪያ የለው ደሞዝ ይዞ ይዞራል…” የምትለው አባባል ከተፈጠረች እነሆ ሁለት አመት አለፋት፡፡ ግዜው ይሮጣል፡፡ ሶስት፣ አራት፣ እና አምስት አመትም እዝችው አጠገባችን ቁጭ ብለው የምናወራውን እየሰሙ ነው፡፡
AbeTokichaw
ከሶስት አመት በፊት መንግስታችን የትራንስፎርሜሽን እቅድ የሚባል ወደ አስማት ቀረብ የሚል ዕቅድ አውጥቶ “ወተት በቧንቧ በየቤቱ እናቀብላለን” አይነት ነገር ሲነግረን ይቺ ነገር የየትኛው “እንትን” ውጤት ትሆን ብለን ስንጨነቅ ሰንበተን ነበር፡፡ ከዛ ወድያው ትራንስፎርሜሽኑን አባይ አጥለቀለቀው፡፡ ከዛስ…. ከዛማ ትራንስፎርሜሽን ተረስታ አባይ አባይ ይዘፈን ጀመር፡፡ ከዛስ…. ምን ከዛስ አለው… አባያችን ከእያንዳንዳችንን ኪስ ውስጥ ዘው ብሎ ገባ….ታ!
ሰላም ወዳጄ እንዴት ሰነበቱልኝ አውዳመቱ እንዴት አለፈ… እንኳንስ አውዳመቱ እና ስንቱ አያልፍም የተባለ ክፉ ቀን አልፏል… አሉኝ እንዴ! አዎ ጥሩ ነገር ብለውኛል፡፡ ቀጥሎም ገና ብዙ ቀኖች ያልፋሉ ዕድሜውን የሰጠን ሰዎችም ቁጭ ብለን እንታዘባለን፡፡ ስለዚህ ዕድሜውን ይለምኑ…! በቅጡ ካወጋን እኮ ሰነባበትን መሰል…! አንዳንድ ወዳጆቼም “በአነስተኛ እና ጥቃቅን ፅሁፎች አደከምከን እኮ” ሲሉ በውስጥ መስመርም በአደባባይም ተግሳጽ ልከውልኛል፡፡ ሰዉ ቀላል ተናጋሪ ሆኗል እንዴ…!
ለማንኛውም ዛሬ በአባይ ጉዳይ ላይ ትንሽ እናውጋ ብዬ ተከስቻለሁ…! ይቺ ፅሁፍ ለላይፍ መፅሄት እና እና ለ abetokichaw.com ድረ ገጽ ተብላ የተሰናዳች መሆኗንም እናገራለሁ፡፡ ከላይ በተንደረደርኩት መሰረት ስቀጥል እባክዎን ወዳጄ አብረውኝ ይዝለቁ ብዬ በመጋበዝ ነው፡፡

Monday, 6 May 2013

ኦባንግ የኢህአዴግ ደጋፊ ስደተኞችን አስጠነቀቁ


“በአስመሳይ ስደተኞች ላይ በቂ መረጃ አለ”

obang


“ክፉን በክፉ መመከት ባያስደስትም ወቅቱ ያስገድደናል” ሲሉ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር ኦባንግ ሜቶ በተለይ ለጎልጉል ተናገሩ። አገዛዙን ሸሽተው በተለያዩ አገራት ከለላ አግኝተው በስደት የሚኖሩም ሆኑ ጉዳያቸው እየታየ ያሉ ወገኖች አካሄዳቸውን እንዲያስተካክሉ አስጠንቅቀዋል።
የአሜሪካ ከፍተኛ ባለስልጣናትና ህግ አውጪዎች፣ የጀርመን የኢሚግሬሽን ሃላፊዎችና ከፍተኛ የፖለቲካ ሰዎች፣ ከኖርዌይ የኢሚግሬሽን ጉዳይ ሃላፊዎችና ተዛማጅ ሃላፊነት ካላቸው የህግ ክፍሎች፣ በካናዳ በተለያዩ ደረጃ ካሉ ባለስልጣናትና ወትዋቾች (አክቲቪስቶች)፣ በስዊድን አንዲሁም በእንግሊዝ በተመሳሳይ ግንኙነት ፈጥረው እየሰሩ መሆኑንን ያመለከቱት አቶ ኦባንግ “አገራቱ የስደት ፈቃድ ካገኙ በኋላ ለስደት ዳረገን ከሚሉት መንግሥት ጋር በቅርብ እየሰሩ ስላሉ አስመሳይ ስደተኞች አስገራሚ መረጃዎች መሰብሰባቸውን አውቃለሁ” ብለዋል።
አቶ መለስ በሞቱ በወር ጊዜ ውስጥ ብቻ በካናዳ ቫንኮቨር 27 አንድ አይነት ቋንቋ ብቻ የሚናገሩ ወጣቶች ጥገኛነት መጠየቃቸውን ጉዳዩን በጥብቅ እየመረመሩት ካሉ ክፍሎች ማረጋገጣቸውንና የምርመራውን ውጤት በመጠባበቅ ላይ እንደሚገኙ ያመለከቱት አቶ ኦባንግ፣ “ወጣቶቹ ካናዳ የገቡት ለእያንዳንዳቸው 75 ሺህ ዶላር በማውጣት ነው። ይህን ገንዘብ ማን ሰጣቸው? እንዴት አገኙት? እንዴት ከአንድ አካባቢ (ክልል) ብቻ ሊሆኑ ቻሉ? የሚሉት ጉዳዮች ምርመራውን በያዙት ወገኖች ላይ ግራሞት የፈጠረ ትልቅ ጉዳይ ነው” በማለት የጉዳዩን አሳሳቢነት ከገንዘብ ማሸሽ ጋር በማያያዝ አመላክተዋል። ለምሳሌ አንድ ጉዳይ አነሱ እንጂ በመላው ካናዳ በተመሳሳይ የምርመራ ስራ እየተሰራ መሆኑንን ተናግረዋል።

Sunday, 5 May 2013


የዓለም የፕሬስ ነፃነት ቀን፣ ኢትዮጵያና የዓለም ማኅበረሰብ

የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት ሣይንስና ባህል ድርጅት፣ እንዲሁም ለነፃ ፕሬስ መከበር የቆሙ ሌሎች ድርጅቶች የዛሬውን ዓለምአቀፍ የፕሬስ ነፃነት ቀን ምክንያት በማድረግ የዓለም ጋዜጠኞች ደህንነት እንዲረጋገጥ ጥሪ አድርገዋል።
የዓለም የፕሬስ ነፃነት ቀን

ይህ ሰው የወያኔ ሰላይ ነው፣ መልኩን በደንብ ያጥኑት፣ ራስዎን ይከላከሉ



ECADF – የዚህን  ሰው ፊት በደንብ ይመልከቱ። ይህ ሰው በቅርቡ በወያኔ ተላላኪዎች አማካኝነት አንድ ጽሁፍ ጻፈ ተብሎ ያስነበበን ሰው ነው። ግለሰቡ ባስነበበን ጽሁፍ “በቅርቡ  ከግንቦት ሰባት ህዝባዊ ሃይል እጅግ ፈታኝ ሁኔታዎችን አምልጬ ሱዳን ገባሁ። ሱዳንም ውስጥ ሆኜ ጽሁፍ አውጥቼ  ላክሁ። ወደፊትም በቀጣይነት በሌሎች ሚድያዎች ስለግንቦት ሰባት ህዝባዊ  ሃይል ገለጻ አደርጋለሁ” ብሎናል።
EPRDF/TPLF spy in Addis Ababa
ግለሰቡ ቀደም ሲል ይኖር በነበረበት ደቡብ አፍሪካ ያሉ ኢትዮጵያውያንና ሌሎችም ግለሰቡን በቅርብ ከሚያውቁት ሰዎች ጋር ተነጋግረን እንዳጣራነው ከሆነ ይህ ሰው በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ውስጥ ያለምንም ችግር በመንቀሳቀስ ላይ ያለ መሆኑን ለማወቅ ችለናል። በተጨማሪም፣
1ኛ –  ከግንቦት 7  ህዝባዊ  ሃይልና  ከኤርትራ መንግስት አምልጦ የሄደ ሳይሆን ቀድሞውኑ ለስራ የተመደበው በሱዳን እና ኢትዮጵያ ድንበር አካባቢ እንደነበር ለመውጣትም ለመግባትም ምንም ችግር ያልነበረበት እንደነበር፣
2ኛ –  ከህዝባዊ ሃይሉ ከድቶ በ24 ሰአት ውስጥ አዲስአበባ ከተማ የደረሰ መሆኑ፣
3ኛ –  በወያኔ የደህንነት መስሪያ ቤት ሙሉ ወጭው ተሸፍኖለት በሆቴል ተቀምጦ  እንደነበር፣
4ኛ-  ይህ ሰው ጻፍኩ በማላት የወጣው ጽሁፍ እሱ በተባባሪነት እንጂ ዋናው ጸሃፊዎቹ  የወያኔ የደህንነት  ሰዎች መሆናቸውን፣
5ኛ – ጽሁፉ ወደተለያዩ ሚዲያዎች የተላከው በወያኔ የደህንነት ቢሮ  በኩል  እንደሆነ፣
6ኛ – ይህ ግለሰብ ሚያዝያ 22፣ 2005 ዓ.ም የወያኔ ደህንነት በቅርቡ ግንቦት ሰባት ህዝባዊ ሃይልን በተመለከተ ለማዘጋጀት ላሰበው አኬልዳማንና ጂሀዳዊ ሀረካትን  መሰል ድራማ ዋናው ተዋናይ እንዲሆን ኮተቤ ከሚገኘው የቤተሰቦቹ ቤት ፕሮግራሙ ወደሚሰራበት መስሪያ ቤት ተወስዶ ስራ የጀመረ መሆኑን ለማጣራት ችለናል።

Friday, 3 May 2013

Solidarity with Amharas seeking justice


by Robele Ababya, 03 May 2013

At first I thought I was going to state the obvious in expressing my solidarity with the Amharas given my background. And then I convinced myself that I have a lot to say in view of the special breed of cruel traitors in our midst bent on destroying the birth right of Amharas – the indisputable pillars of the Ethiopian civilization including the glorious era of the Akumite Kingdom, which replaced the Kushite Kingdom (1500 BC – 500 BC).
Tell me my fellow Ethiopian. What do you see in the picture above?
To the TPLF warlords that are grandchildren of loyal servants of Mussolini, the Amharas and the Oromos are targets to be systematically uprooted from the field of politics to remove bad apples – just as planned by Italian Fascists in Rome for execution by Marshall Graziani in Ethiopia. The warlords have added the Guraghes to their blacklist; I bet Kambattas and others will follow, the former for the gallant role of their ancestors in the war with the Fascists at Maichew. Tigreans will be served carrot and stick to enforce their loyalty, but in vain.

This short piece is meant to expound my rationale for solidarity with the plight of the Amharas and its consequences on our multicultural society in the following paragraphs.

Thursday, 2 May 2013


Äthiopisches Bundesgericht Logo /020513
Foto: Yohannes G/Egziabher DW Korrespondent 2013

ኢትዮጵያ

የእነ አንዱዓለም አራጌ ይግባኝና የዛሬው የፍርድ ቤት ብይን

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፤ በእነ አንዱዓለም አራጌ መዝገብና በሌሎች መዝገቦች ፤ በአሸባሪነት ተከሠው ይግባኝ የጠየቁ የፖለቲካ ፓርቲዎች የአመራር አባላትና የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን ጉዳይ መርምሮ፣ ከአንደኛው በስተቀር የሁሉንም የእሥራት ብይን እንዲጸና አድርጓል።
የክንፈ ሚካኤል በየነ እሥራት ፤ ከ 25 ዓመት ወደ 16 ዓመት ዝቅ እንዲል ወስኗል።

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በአሸባሪነት የተወነጀሉት እና ከአለፈዉ ዓመት ጀምሮ እስር ላይ ያሉትን፤ አምደኛ እና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እንዲሁም የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዉ አንዱአለም አራጌ፤ ያቀረቡትን ይግባኝ ዉድቅ አደረገ። «ብይኑ አሁንም ትክክል ነዉ፤ ምንም አይነት ቅነሳ አይኖርም ሲሉ» የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ አቶ ደጀኔ መላኩ ተናግረዋል። ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ በዲፕሎማቶች በዘመድ እና በጓደኛ በተሞላዉ ብይን ላይ ከዉሳኔዉ በኋላ « እዉነት አንድ ቀን ይወጣል» ሲል በስሜት መናገሩ ተገልጾአል።
Anwalt Abebe Guta im Prozess Journalist Eskinder Nega und Oppositionellen
Andualem Arage 020513.
Foto: Yohannes G/Egziabher DW Korrespondent 2013ጠበቃ አበበ ጉታ
እስክንድር ነጋ የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያዉቅ የምንፈልገዉ እዉነት እራሱ በግዜዉ ይወጣል፤ የግዜ ጉዳይ ብቻ ነዉ» ብሎአል። አንዱአም አራጌ እና ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ከመንግስት ተቃዋሚ ቡድን ግንቦት ሰባት ጋር ግንኙነት አላችሁ ተብለዉ ስክንድር የ 18 ዓመት ጽኑ እስራት አንዱዓለም ደግሞ የእድሜ ልክ እስራት ተበይኖባቸዋል። በአሁኑ ወቅት በእሥር ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛ እስክንድር እጎ እ 2012 ዓ,ም ዓለም አቀፉ የደራስያን ድርጅት ፔን በዓለምአቀፍ ደረጃ በሥራቸው ምክንያት ለታሠሩ ወይም አደጋ ላይ ለወደቁ ደራስያንና ጋዜጠኞች የሚበረከተዉን የመፃፍ ነፃነት ሽልማት ማግኘቱ ይታወቃል። ዝርዝሩን ዮሃንስ ገ/እግዚአብሄር ወኪላችን ተከታትሎታል።
ዮሃንስ ገ/እግዚአብሄር
ተክሌ የኋላ
ነጋሽ መሃመድ

AUDIOS AND VIDEOS ON THE TOPIC

Wednesday, 1 May 2013

የኢትዮጵያዊያኑ ሠልፍ በመንግሥታቱ ድርጅት ደጅ


የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና መሥሪያ - ኒው ዮርክ



የባለ ራዕይ ወጣቶች የመፍትሄ ጥሪ


***ACHTUNG: Das Foto darf nur für die Rubrik Der Blick aus meinem Fenster verwendet werden***
Thema: Der Blick aus meinem Fenster: Addis Abeba, Äthiopien
Foto: Solomon Mengist
.

ኢትዮጵያ

የባለ ራዕይ ወጣቶች የመፍትሄ ጥሪ

ባለራዕይ ወጣቶች ማሕበር ኢትዮጵያ ዉስጥ እየተፈጸሙ ነዉ ያላዋቸዉን የህዝብ መፈናቀል፤ የፕሪስ አፈና እና የጋዜጠኞች መታሰርን ለማስወገድ ብሄራዊ ኮሚቴ ማቋቋም እንደሚጠቅም አስታወቀ ።
ማህበሩ፤ «ሐገራችን እየገባች ካለችበት ቀዉስ ለመታደግ፤ ብሄራዊ ኮሚቴ ማቋቋም ብቸኛዉ አማራጭ ነዉ» በሚል ርዕስ መግለጫ አዉጥቷል።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮሃንስ ገ/እግዚአብሄር የማሕበሩን መሪዎች አነጋግሮ የሚከተለዉን ዘገባ ልኮልናል።

ዮሃንስ ገ/እግዚአብሄር
አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሃመድ

AUDIOS AND VIDEOS ON THE TOPIC