የእስረኞቹ ጠበቃ እንዳስታወቁት ክሱን የመሠረቱት የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጅሐዳዊ ሐራከት በሚል ርዕስ ባሰራጨዉ ፊልም የደንበኞቻቸዉን ሥም በማጥፋቱ ነዉ።በተያያዘ ዜና የባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች በበኩላቸዉ ሐይማኖታዊ ነፃነታችንን ገፎናል ያሉት የዩኒቨርስቲዉ አስተዳደር ዉሳኔዉን ካልቀየረ እንደሚከሱ አስታወቁ።
የኢትዮጵያ መንግሥት በአሸባሪነት ከሶ ያሰራቸዉ የሙስሊሞች መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት የኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅትን፥ የፌደራል ፖሊስንና የሌሎች መስሪያ ቤት ሐላፊዎችን በሥም አጥፊነት ከሰሱ።የእስረኞቹ ጠበቃ እንዳስታወቁት ክሱን የመሠረቱት የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጅሐዳዊ ሐራከት በሚል ርዕስ ባሰራጨዉ ፊልም የደንበኞቻቸዉን ሥም በማጥፋቱ ነዉ።በተያያዘ ዜና የባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች በበኩላቸዉ ሐይማኖታዊ ነፃነታችንን ገፎናል ያሉት የዩኒቨርስቲዉ አስተዳደር ዉሳኔዉን ካልቀየረ እንደሚከሱ አስታወቁ።የባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ አስተዳደር ሐይማኖታዊ ግዴታችንን እንዳንወጣ አግዶናል በማለት በርካታ የዩኒቨርቲዉ ተማሪዎች ትምሕርታቸዉን ለማቋረጥ መገደዳቸዉ ገልፀዉ ነበር።የሁለቱን ክሶች ይዘትና ምክንያት በተመለከተ የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዝር ዝር ዘገባ ልኮልናል።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ነጋሽ መሐመድ
አርያም ተክሌ
No comments:
Post a Comment