Tuesday, 30 April 2013

ኢህአዴግ በኖርዌይ ገንዘብ ማሰባሰብ ተሳነው



self

በስደት አገራቸውን ለቀው የወጡ ሰዎች ያለመሰለል መብት አላቸው። በህግም የተደነገገ ነው። ከለላ የሰጣቸውም አገር ይህንን የመከላከልና የመቃወም ግዳጅም አለበት። ከለላ ያገኙ ስደተኞችም ሆኑ ከለላ እንዲሰጣቸው ያመለከቱ ወገኖች ስለመሰለላቸው ተጨባጭ ማስረጃ ማቅረብ ከቻሉ ህጉን ጠቅሰው የመከራከር መብት አለቸው። ለመብታቸው ሲከራከሩ በመደራጀት ቢሆን ይበልጥ ውጤታማ ሊሆኑ እንደሚችሉ አውሮፓ በስደት ያሉ ቀድሞ የውጪ ጉዳይ የዲያስፖራ ኢንጌጅመንት ዳይሬክቶሬት ዲፓርትመንት ኤክስፐርት ይናገራሉ።
እኚሁ ሰው እንደሚሉት ከ1997 ዓ ም ምርጫ በኋላ በአቶ መለስ ቀጥተኛ ትዕዛዝ የተቋቋመው ይህ ዲፓርትመንት ለጠቅላይ ሚኒስትሩና ለወቅቱ የውጪጉዳይ ሚኒስትር አቶ ስዩም መስፍን ሪፖርት ያቀርብ ነበር። በጁላይ 2003 ስድስት አባላትን በመያዝ የተቋቋመው ዲፓርትመንት “ብዙሃን አድፋጭ” ዲያስፖራ ወይም “silent majority” የሚባሉትን ለመማረክና በስደት ውጪ አገር የሚኖሩትን የተቃዋሚ ድርጅት ዋና ደጋፊዎችንና አመራሮችን የሚከታተል ቻፕተሮች አሉት።
የአገዛዙ ደጋፊ ለሚባሉት ዲያስፖራዎች የቀረጥ ነጻ መብት በመስጠት፣ መሬት በማደል፣ በማህበራት በማደራጀት ቢቻል መታወቂያ በመስጠት፣ “ለአገር ግንባታ ደጋፊ ማድረግ” በሚል ሽፋን በያሉበት አገር ከኤምባሲ ጋር ግንኙነት እንዲፈጥሩ በማድረግ የተዘረጋው መዋቅር የአውሮፓውን የክትትል ስራ በግንባር ቀደምትነት እንዲመራ የመደበው የብራስልስ ኤምባሲን ነው። በቤልጂየም ኢትዮጵያ ኤምባሲ ካውንስለር በመሆን የሚያገለግሉት የቀድሞው የህወሃት ታጋይ ይህንኑ የአውሮፓ የክትትል ቻፕተር እንደሚመሩት የሚያስረዱት የቀድሞ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሰራተኛ የቻፕተሩን ጠርናፊ “አቶ መለስ በታመሙበት ወቅት ብራስልስ ሆነው አስፈላጊውን ሁሉ ሲያደርጉ የነበሩ የስርዓቱ ታማኝ ሰው ናቸው” ሲሉ ይገልጹዋቸዋል።

Monday, 29 April 2013

የርዕዮት ዓለሙ የጤና ሁኔታ


የታመመችውን ርዕዮትን የቃሊቲ ማረሚያ ቤት በቀጠሮዋ መሠረት ሐኪም ቤት እንደማይወስዳት አባትዋ ለዶቼቬለ ተናግረዋል ። በሌላ በኩል ጋዜጠኛ ውብሸት ታዮ ከቅሊንጦ ማረሚያ ቤት ወደ ዝዋይ እንዲዛወር መደረጉ ቤተሰቦቹና ወዳጅ ዘመዶቹ እንዳይጎበኙት እንቅፋት መሆኑ ተሰምቷል ።

የጋዜጣ ዓምደኛ የርዕዮት ዓለሙ የጤንነት ሁኔታ እንደሚያሳስባቸው ቤተሰቦቿ አስታወቁ ። የታመመችውን ርዕዮትን የቃሊቲ ማረሚያ ቤት በቀጠሮዋ መሠረት ሐኪም ቤት እንደማይወስዳት አባትዋ ለዶቼቬለ ተናግረዋል ። በሌላ በኩል ጋዜጠኛ ውብሸት ታዮ ከቅሊንጦ ማረሚያ ቤት ወደ ዝዋይ እንዲዛወር መደረጉ ቤተሰቦቹና ወዳጅ ዘመዶቹ እንዳይጎበኙት እንቅፋት መሆኑ ተሰምቷል ። የፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር የህዝብ ግንኙነት የርዕዮት ዓለሙ የህክምና ቀጠሮ እንዳልተስተጓጎለና አሁንም በጥሩ የጤና ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ ገልጾ ፣ ጋዜጠኛ ውብሸት ታዮም በማንኛውም ፍርደኛ ላይ በሚደረግ መደበኛ ዝውውር ወደ ዝዋይ ማረሚያ ቤት መወሰዱን አስታውቋል ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዝርዝር ዘገባ አለው ።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ሂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ

ግጭቱን ማን ለኮሰው? (ከኢየሩሳሌም አርአያ)


ከኢየሩሳሌም አርአያ

ቀኑ ማክሰኞ፣ ጥቅምት 22 1998 ዓ.ም፤ ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ገደማ… አንድ የከተማ አንበሳ አውቶብስ ተሳፋሪ ሳይጭን ከመርካቶ ተነስቶ ወደ ጎማ ቁጠባ አቅጣጫ በባዶ እየከነፈ
Addis Ababa, Ethiopia 2005 protest
 ቁልቁል ወርዶ ..ተ/ሃይማኖት ቤ/ክርስቲያን አደባባይን ከዞረ በኋላ ጥግ ይዞ ቆመ። ሹፌሩ አውቶብሱን ገትሮ ወዲያው ከአካባቢው ጠፋ። ለሁለት ሰዓት ገደማ አውቶብሱ እንደተገሸረ ቆየ።…በዚህ ቅፅበት አንዲት ነጭ ቶዮታ ፒካፕ (ታርጋ የሌላት ወይም ያለጠፈች) ከሱማሌ ተራ አቅጣጫ በከፍተኛ ፍጥነት እየከነፈች ከመጣች በኋላ < በላይ ተክሉ ኬክ> ቤትን አለፍ ብላ ቆመች። ከሹፌሩ ጎን ሲቪል የለበሰና ኮፍያ ያጠለቀ ሰው የተቀመጠ ሲሆን ከመኪናው ጋር ከተገጠመው ሬዲዮ መገናኛ በተጨማሪ ሁለት ተንቀሳቃሽ ስልኮችን ይዟል።… 25 ወጠምሻዎች፣ ሁሉም ረዘም- ወፈር ያሉ ዱላዎችን፣ ገሚሶቹ ደግሞ ገጀራ እንደጨበጡ እንዲሁም ከመካከላቸው ሁለቱ አነስተኛ ጀሪካን እንደያዙ…ከመኪናዋ ዘለው ወረዱ። ሁሉም የተቀዳደ ተመሳሳይ ድሪቶ አጥልቀዋል፤ « አደገኛ ቦዘኔ» መሆናቸው ነው። ነገር ግን « ሆን ተብሎ » የተዘጋጀ ድሪቶ እንደሆነ የሚያሳብቀው ….በግልፅ የሚታየው የሁሉም ፈርጣማ ጡንቻ ከጥሩ እንክብካቤ ጋር በስፖርት የዳበረና ወታደራዊ አቋም እንዲይዝ ተደርጎ የተገነባ መሆኑ ነበር።

በሳንድያጎ የወያኔዎች ስብሰባ ሳይጀመር ተበተነ


በሳንዲያጎ የወያኔ አምባሳደር ይገኝበታል ተብሎ በአባይ ግድብ ስም ቦንድ ለመሸጥ የተጠራው ስብሰባ በኢትዮጵያውያን ተቃውሞ እንዲቋረጥ ሆንዋል።

Ethiopians in San Diego Protest April 28, 2013
በቁጥር ከሁለት መቶ በላይ የተቆጡና በርካታ መፈክሮችን ያነገቡ ኢትዮጵያውያን ስብሰባው በሚደረግበት አዳራሽ የተገኙት ቀደም ብለው ነበር።

Saturday, 27 April 2013


የተመስገን ደሣለኝ ጉዳይ ተቀጠረ

በፌደራል አቃቢ ሕግ ተቃውሞ የፍትሕ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ የተመስገን ደሣለኝ ምክሥሮች ቃል ሳይሰማ ቀረ፡፡
ፍትሕ ጋዜጣና ዋና አዘጋጅዋ የተመስገን ደሣለኝ
ፍትሕ ጋዜጣና ዋና አዘጋጅዋ የተመስገን ደሣለኝ 

ኦባማ አርፍደው ወደ ኢትዮጵያ?


“በአፍሪካ ብዙ ስራ አለን” ጆን ኬሪafrica-china-us

በአፍሪካ ህብረት 50ኛ ዓመት ክብረ በዓል ላይ ከሚገኙት የተለያዩ እንግዶችና ባለስልጣናት በተጨማሪ አራት ታላላቅ መሪዎች እንደሚገኙ እየተነገረ ነው። በዋናነት የሚጠቀሱት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ኦባማ ሲሆኑ፣ የቻይና አቻቸውም ዋናውና ታላቁ እንግዳ እንደሚሆኑ ይጠበቃል።
የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ ባለፈው ረቡዕ ለአሜሪካ ኮንግረንስ ኮሚቴ የተናገሩትን በመጥቀስ ዜናውን የላኩልን ክፍሎች እንዳሉት ኦባማ ወደ ኢትዮጵያ ሊያመሩ ይችላሉ።
ውጪ ጉዳይ ሚ/ሩ ኦባማ ኢትዮጵያ ስለመሄዳቸው ፍንጭ ቢሰጡም ስለጉዞው ዝርዝር አለመናገራቸው ታውቋል። የቻይና በአፍሪካ ሚና መጉላት ውሎ አድሮ የጠዘጠዛት አሜሪካ፣ በመጪው ወር በሚካሔደው የአህጉሩ 50ኛ ዓመት ክብረ በዓል ላይ በፕሬዚዳንቷ ለመወከል መወሰኗ “ጉባኤ አድማቂ” አሰኝቷታል።
“በአፍሪካ ብዙ የምንሰራው ስራ አለን” ሲሉ የተናገሩት ኬሪ “በድግሱ” ላይ እንደሚገኙ አረጋግጠዋል። እየተጣጣመ የመጣው የአፍሪካና የቻይና ፍቅር እንዲሁም ቻይና በአፍሪካ ያላት ሰፋ ያለ ኢንቨስትመንት ለአሜሪካ አሳሳቢ ከመሆኑ ባሻገር ቻይና የምትከተለው የንግድ ስልት በአጠቃላዩ ሁኔታ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደሩን ውጪ ጉዳይ ሚ/ር ኬሪ አልሸሸጉም፡፡ ዝርዝር ከመስጠት ቢቆጠቡም ጉቦ፣ ሙስና፣ አምባገነኖችን መርዳት በማለት የተወሰኑትን በግልጽ ከመጥቀስ አላለፉም፡፡
ኦባማም ወደ ኢትዮጵያ የሚያቀኑበት ጉዳይ አሜሪካ በአፍሪካ ለምትከተለው አዲስ እቅድ ማጠናከሪያ ካስማ ለመቸንከር እንደሆነ አብዛኞች ይስማሙበታል። “ቻይናን በቅርብ ሆኖ መቆጣጠር” በሚለው መርህ  የአፍሪካን አምባገነኖች ወታደራዊ ድጋፍ በመስጠት ልቡናቸውን የመስለብ እቅድ ይዛ እየሰራች ያለችው አሜሪካ፣ የቻይናና የአፍሪካ ግንኙነት “የፓለቲካ እባጭ” የሆነባት ቻይና ድፍን የአፍሪካ መሪዎችን ቤጂንግ ጋብዛ ወዳጅነቷን አደባባይ በማውጣት ጸሐይ ካስመታቸው በኋላ ነበር። በርካታ መረጃዎችም በዚሁ ዙሪያ ቀርበዋል።

Thursday, 25 April 2013



አፍሪቃ

የኢትዮጵያ ጦርና ሶማሊያ

ኢትዮጵያ ከሶማሊያ ብትወጣ የሚፈጠረው የፀጥታ ክፍተት ለአሸባብ አመቺ ሁኔታ መፍጠሩ እንደማይቀር ተናግረዋል ። ይሁንና ኢትዮጵያ ወታደሮቿ በቅርቡ ከሶማሊያ እንደሚወጡ ብትናገርም ፣ ለራሷ የፀጥታ ጠቀሜታ ስትል እርምጃውን ትወስዳለች ተብሎ አይታሰብም ።
ኢትዮጵያ በቅርቡ እንዳስታወቀችው ወታደሮቿን ከሶማሊያ ካስወጣች በሶማሊያ ተጨማሪ የፀጥታ ችግር  ሊከሰት  እንደሚችል ተገለፀ ። በጉዳዩ ላይ ለዶቼቬለ አስተታየታታቸውን የሰጡት የምሥራቅ አፍሪቃ የፀጥታ ጉዳዮች ተመራማሪ አንድሪውስ አታ አሳሞዋ ኢትዮጵያ ከሶማሊያ ብትወጣ  የሚፈጠረው የፀጥታ ክፍተት ለአሸባብ አመቺ ሁኔታ መፍጠሩ እንደማይቀር ተናግረዋል ። ይሁንና ኢትዮጵያ ወታደሮቿ በቅርቡ ከሶማሊያ እንደሚወጡ ብትናገርም ፣ ለራሷ የፀጥታ ጠቀሜታ ስትል እርምጃውን ትወስዳለች ተብሎ አይታሰብም ።

የህወሀት ደህንነቶችን ጤና የነሳው የፌስቡክ ጦማር


በህወሀት/ኢህአዴግ ውስጥ መግባባት ጠፍቷል፣ የወያኔ ቁንጮዎች ወዴት እንደሚሄዱ አያውቁም። እንደው በደፈናው “የመለስ ዜናዊ ራዕይ” ይበሉ እንጂ ራዕዩን እነርሱም አያውቁትም። ካድሬውም ሹማምንቱም እርስ በርስ ተናንቋል። በዚህ ሁኔታ ላይ እያሉ ሁኔታቸውን ህዝብ እንዳያውቅባቸው እያደረጉ ያሉት ጥረት እምብዛም የሰራ አይመስልም። የሙስሊሞች ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው፣ በአማራ ብሄር ተወላጆች ላይ የሚደርሰው ግፍ ህዝቡን ከዳር እስከዳር አስተባብሯል/ቀስቅሷል፣ ምርጫውን ምርጫ ለማስመሰል ያደረጉት ጥረት አልተሳካም፣ ጋዜጠኞች እና የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ አለማቀፉ ማህበረሰብ እና ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ጫና ፈጥረዋል። ለዚህም ይመስላል የወያኔ የደህንነት ሹሞች የሀሰት ዜናዎችን በፌስቡክ እያሰራጩ ፋታ ለማግኘት የሚጣጣሩት። ከዚህ በታች አብረሃ ደስታ ከመቀሌ በፌስቡክ የለቀቀውን ጦማር፣ የህወሃት/ኢህአዴግን ወቅታዊ አቋቋም እንደወረደ አቅርበነዋል።

በህወሓት የጉባኤ ኣጀንዳ ዙርያ ስብሰባ ሊጠራ ነው

አብረሃ ደስታ፣ ከመቀሌ
ከኢህኣዴግ ጉባኤ በኋላ መሪዎቻችን (ከበፊቱ ብሶባቸው) መግባባት ኣቅቷቸዋል። በፌደራል ደረጃ የሚደረጉ ስብሰባዎች ያለ ዉጤት ይጠናቀቃሉ። ለምን ኣይግባቡም? (‘ቀሽም
Ethiopian blogger Abraha Desta from Tigry, Mekele
 ጥያቄ’)። የሚያግባባ ነጥብ የላቸውማ። ድሮ (ከ‘ባለራእዩ መሪ’ ዕረፍት በፊት) ሁሉም ነገር እሳቸው ይሰሩት ስለነበር) በመሪያቸው ነበር ‘የሚግባቡት’ (አብረው የሚጓዙ)። በሰው ‘ይግባባሉ’ (ሌላ ሊያግባባቸው የሚችል ሓሳብ ወይ መርህ አልነበራቸውም፣ የላቸውም)። አሁን ታድያ እንዴት ይግባቡ?

‘ባለራእዩ’ ሰውዬ መመርያ ይሰጣል፣ ‘ፖሊሲ ነው ተግብሩት’ ይላቸዋል፣ እነሱም እሱ የተናገረውን ‘ቃል’ እየደገሙ (ከላይ እስከ ታች) ይዘምራሉ። ስሕተት መሆኑ (ሊተገበር የማይችል መሆኑ) ሲረዱ ‘ስሕተቱ ያለው አፈፃፀም ላይ ነው’ ብለው ራሳቸው ያፅናናሉ። ህዝቡ በማይፈፀሙ ፖሊሲዎች ተስፋ እንዳይቆርጥ መሪዎቻችን ሁሌ ስለ አዲስ ፖሊሲ ወይ አሰራር ይሰብካሉ። ሁሌ ስለ ‘አዲስ ኣሰራር’ ወይ ዕቅድ ሲወራልን ለውጥ የመጣ ያህል እንዲሰማን ለማድረግ ያህል ነው።

Wednesday, 24 April 2013

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለ ቤንሻንጉሉ መፈናቀል ተናገሩ


በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የሚገኙ አርሦ አደሮች ሕገወጥ በሆነ መንገድ መፈናቀላቸውን የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ አረጋገጡ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለ ቤንሻንጉሉ መፈናቀል ተናገሩ
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለ ቤንሻንጉሉ መፈናቀል ተናገሩ

ኢትዮጵያ

በአፍሪቃ ቀንድ የጋዜጠኞች ይዞታ

ሶማሊያ ዉስጥ በያዝነዉ የጎርጎሮሳዊ ዓመት 2013 ከባተ የተገደሉ ጋዜጠኞች ቁጥር አምስት ደርሷል። ለጋዜጠኞች መብት የሚሟገተዉ ድንበር የለሽ ዘጋቢዎች /RSF/ ሰሞኑን አንድ የሶማሊያ ራዲዮ ጋዜጠኛ መገደሉን በማዉገዝ፤ መቅዲሾ ዛሬም ለጋዜጠኞችም ሆነ ለኗሪዎቿ ፀጥታዋ የተረጋገጠነዉ ማለት እንደማይቻል አመልክቷል።

ድርጅታቸዉ በአፍሪቃዉ ቀንድ በሚገኙ ሀገሮች የሚታየዉ የጋዜጠኞች ይዞታ እንደሚያሳስበዉ ያመለከቱት የRSF የአፍሪቃ ጉዳይ ተንታኝ አምብሩዋዝ ፒየር ቤተሰቦቹ ከሚገኙበት ወደሌላ አካባቢ መዛወሩ የተነገረዉ የጋዜጠኛ ዉብሸት ታዬ እና ህክምና ማግኘት አለመቻሏ የተሰማዉ የጋዜጣ አምደኛ ርዕዮተ ዓለሙንም ጉዳይ እየተከታተለ መሆኑን ገልፀዋል።

ሶማሊያዉ ጋዜጠኛ ሞሐመድ ኢብራሂም ራጋ ቀደም ሲል የእንገልሃለን ዛቻ ደርሶት ሀገሩን ለቆ ወደኬንያና ዑጋንዳ ተሰድዶ ቆይቷል። ያኔ የእስላማዊዉ ታጣቂ አሸባብ መቅዲሾም ሆነች በአብዛኛዉ የሶማሊያ ግዛት ጥቃቱን በየዕለቱ ይሰነዝር ነበር። ካለፉት ወራት ወዲህ ቡድኑ ጠንካራ ይዞታዉ ትባል ከነበረችዉ ኪስማዮ ሳይቀር ለቅቋል መባልን ተከትሎ ዋና ከተማዋ መቃዲሾን የተለያዩ ዓለም ዓቀፍ ተቋማት መሪዎችና የምዕራቡ ዓለም ባለስልጣናት ሲረግጧት ራጋ ሀገር ሰላም ነዉ በሚል ወደትዉልድ ስፍራዉ ተመለሰ። ዛቻዉ ግን በዛቻነት ብቻ አልቀረም ባለፈዉ እሁድ አመሻሹ ላይ ሁለት የታጠቁ ሰዎች በርካታ ጥይት ደረቱና ጭንቅላቱ ላይ ተኩሰዉ መኖሪያ ቤቱ ደጃፍ ህይወቱ አለፈ።

Tuesday, 23 April 2013

ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ-ኢትዮጵያ አሜሪካዊያን ሠልፍ በዓለም ባንክ አደረጉ



የኢትዮጵያዊያንና ትውልደ-ኢትዮጵያ አሜሪካዊያን ሠልፍ በዓለም ባንክ

የኢትዮጵያዊያንና ትውልደ-ኢትዮጵያ አሜሪካዊያን ሠልፍ በዓለም ባንክ


የሰማያዊ ፓርቲ አመራር አባላት በቡለን ወረዳ ታስረው መለቀቃቸውን አስታወቁ


የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ውስጥ የተፈናቀሉ አርሶ አደሮች የሚገኙበት ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑን የተለያዩ ተቃዋሚ ፓርቲዎች መግለፃቸውን ቀጥለዋል፡፡

አቶ ይልቃል ጌትነት - የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር
አቶ ይልቃል ጌትነት - የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር

“ማፈናቀሉ የሚካሄደው በመንግሥት ትዕዛዝ ነው፤ ወደ ክስ እናመራለን”


“በቤኒሻንጉል የህወሃት ታጋዮች ሰፋፊ እርሻ አላቸው”

Justice Gavel


በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ከ2000 ሺህ በላይ ትግሬዎች ባለይዞታ መሆናቸውንና ማንም ሳይነካቸው በሰላም እንደሚኖሩ፣ በቶጎ ወረዳ ከስልሳ በላይ ነባር የህወሃት ታጋዮች ሰፋፊ የእርሻ መሬት ወስደው በባለሃብት ደረጃ እንደሚገኙ የመኢአድ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አስታወቁ። ከሌሎች ብሔረሰቦች ተለይቶ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየተፈጸመበት ያለውን የአማራ ብሔረሰብ በድጋሚ ለማስወጣት መታቀዱንም በመረጃ ማረጋገጣቸውን ተናግረዋል።
በቦታው በመገኘት አስፈላጊውን መረጃ እንደሰበሰቡ ለአሜሪካ ሬዲዮ የገለጹት የመኢአድ ስራ አስፈጻሚ በክልሉ ከሚኖሩት የተለያዩ ብሔረሰቦች ተለይቶ የአማራ ብሔረሰብ እንዲፈናቀልና እንዲሰቃይ የሚደረገው በማዕከላዊ መንግስት ትዕዛዝ እንደሆነም አመልክተዋል።
መኢአድ ያሰራጨውን መግለጫ ተከትሎ በተዘጋጀ ጋዜጣዊ መግለጫ ማብራሪያ የሰጡት አቶ ሃይሉ ሻወል፣ ድርጊቱ በበታች የቀበሌና ወረዳ አመራር አካላት ተፈጽሟል መባሉን ተቃውመዋል።”ሰዎቹ እንዲወጡ ሲታዘዝ ያ ሁሉ ወታደር ከየት መጣ?” በማለት የጠየቁት አቶ ሃይሉ ሻወል፣ በርካታ የወያኔ ሰዎች በቦታው እያሉ አማራው ተለይቶ እንዲፈናቀል የበታች ባለስልጣናት በራሳቸው ውሳኔ ይህን ሊያደርጉ እንደማይችሉ ተናግረዋል። በማያያዝም በርካታ ተጨባጭ ማስረጃ ስለተሰባሰበ ጉዳዩን ወደ ዓለምአቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ለመውሰድ በዝግጅት ላይ እንደሚገኙ አመልክተዋል።

Monday, 22 April 2013



ኢትዮጵያ

ቤንሻንጉል የተፈናቃዮች ሁኔታ

ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ተባረዉ እንደገና እንዲመለሱ የተደረጉ የአማራ ብሄር አባላት በአስከፊ ሁኔታ እንደሚገኙ ሰማያዊ ፓርቲ መግለፁን የአዲስ አበባዉ ዘጋቢያችን የላከልን ዘገባ ያመለክታል።
ይህን ጥናት ለማድረግ ወደክልሉ የተጓዙ የፓርቲዉ አመራር አባላት ለአምስት ሰዓታት ያህል ታስረዉ መለቀቃቸዉም ታዉቋል። ዝርዝሩን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ልኮልናል
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ሸዋዬ ለገሠ
ተክሌ የኋላ

AUDIOS AND VIDEOS ON THE TOPIC

ካሩቱሪ በኢትዮጵያ

የዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት የአፍሪካ ጉዳዮች ንዑስ ኮሚቴ በመሬት መብቶችና በምግብ ዋስትና ላይ ማብራሪያዎችን አዳምጧል፡፡

ሪምክሪሽና ካሩቱሪ - የካሩቱሪ ግሎባል መሥራችና ዋና ሥራ አስፈፃሚ
ሪምክሪሽና ካሩቱሪ - የካሩቱሪ ግሎባል መሥራችና ዋና ሥራ አስፈፃሚ

The Audacity of Evil in Ethiopia


by Alemayehu G. Mariam

Triumph of Evil?
Jailed Ethiopian journalist Reeyot Alemu named winner of 2013
Imprisoned Ethiopian journalist Reeyot Alemu has been named the winner of the 2013 UNESCO-Guillermo Cano World Press Freedom Prize.
“The only thing necessary for the triumph of evil is that good men do nothing”, said Edmund Burke. But what happens when evil triumphs over a good young woman journalist named Reeyot Alemu in Ethiopia? Do good men and women turn a blind eye, plug their ears, turn their backs and stand in silence with pursed lips?
In an extraordinary letter dated April 10, 2013, the Committee to Protect Journalists pled with Berhan Hailu, “Minister of Justice” in Ethiopia, on behalf of the imprisoned 32-year old journalist urging that she be  provided urgent medical care and spared punishment in solitary confinement at the  filthy Meles Zenawi Prison in Kality just outside the capital Addis Ababa.

Sunday, 21 April 2013

ኢህአዲግ (ወያኔ) የአባይን ግድብ የቦንድ ሽያጭ በባህር ማዶ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን መተንኮሻ አድርጎታል



GUDAYACHN BLOG
ዛሬ እነሆ በኖርዌይ እንዲህ ሆነ
Ethiopians in Norway protest, April 2013
ከኖርዌይ ከተሞች ውስጥ በደቡባዊ ክፍል የምትገኘው ስታቫንገር ከተማ ዛሬ ሚያዝያ 12/2005 ዓም በስዊድን የኢትዮጵያ አምባሳደር ወ/ሮ መብራት በተገኙበት ለአባይ ግድብ ቦንድ ሽያጭ የተዘጋጀው ዝግጅት ከኦስሎ ከ ስምንት ሰዓታት በላይ በአውቶቡስ ተጉዘው በስብሰባው በተገኙ ኢትዮጵያውያን በገጠመው ከፍተኛ ተቃውሞ ሙሉ በሙሉ ዝግጅቱ ተሰርዞ አምባሳደሯ በፖሊስ ቦታውን ለቀው  እንዲሄዱ ተመክረው አዳራሹን ለቀው ወጥተዋል።
በመርሃግብሩ መክፈቻ ላይ በሥርዓት ተቀምጠው የተገኙት ኢትዮጵያውያን መርሃግብሩ ከመጀመሩ በፊት ”በዘመነ ኢህአዲግ የተገድሉትን ኢትዮጵያውያን በቅድሚያ በህሊና ፀሎት እናስብ ይህንንም ለማድረግ ሁላችንም ከተቀመጥንበት እንነሳ” በማለት አምባሳደሯም እንዲነሱ እና አብረው በፀሎት እንዲያስቡ ይጠይቃሉ።አምባሳደሯም ሆኑ አብረዋቸው የመጡት ፈቃደኛ አልሆኑም። በመቀጠል ኢትዮጵያውያኑ እንግዲያው ስለ አባይግድብ አሁን ልንነጋገር አንችልም በማለት ያስታውቃሉ።በእዚህ መሃል ከፍተኛ የተቃውሞ ድምፅ መሰማት ይጀምራል።

Saturday, 20 April 2013

Breaking News: Ethiopians in Norway Chased TPLF Ambassador


Norway police stopped meeting in Tasta Bydelshus

Source: Aftenbladet
Norway police stopped meeting in Tasta Bydelshus
The police came out with three cars and six policemen and stopped a meeting of Tasta bydelshus where the atmosphere was becoming so very irritably among the more than 300 Ethiopian origin attendees.
The 300 attendees were Ethiopian asylum seekers or people with Ethiopian background. The police feared that it would get completely out of control when people in the audience went to the hard verbal confrontation against two representatives from the Ethiopian Embassy in Stockholm who had called for and chaired the meeting.
Breaking News: Ethiopians in Norway Chased TPLF Ambassador
The police gave the first message that all protesters to leave the meeting while the two embassy people and their potential supporters can be seated. This denied the attendees protesters, and several feared it would come to an open confrontation between police and people in the audience. Then, specific efforts manager Øyvind Sveinsvoll of Rogaland police to stop the meeting and clear the room.
It was a wise decision, said several of those present protesters. They did not want the two embassy people should be left as “victors” while they were evicted.

ሰበር ዜና፣ በአባይ ስም ዶላር ለመሰብሰብ በሲውዲን የወያኔ አምባሳደር ወደ ኖርዌይ ተጉዛ ውርደት ተከናንባ ተመልሳለች


አምባሳደሯ በሁለት ወያኔዎች ታጅባ ስለ ፓስፖርትና፣ ስለ አባይ ግድብ ቦንድ መናገር ከመጀመሯ የኖርዌይ ኢትዮጵያውያን “የለም የለም ኢትዮጵያ ውስጥ በግፍ ስለታሰሩ፣ በዘራቸው ምክንያት በሀገራቸው እየተፈናቀሉ ስላሉት ወገኖቻችን በቅድሚያ ጥያቄ አለን” በማለት አምባሳደሯን ሰንገው ይይዟታል።

ስብሰባው የወያኔዋ ተወካይ ባሰበችው መንገድ መሄድ አልቻለም። ተረበሸ።
ግርግሩ በርትቶ በመጨረሻም አምባሳደሯ እና አጃቢዎቿ በፖሊሶች ታጅበው በመጡበት እግራቸው ተመልሰዋል።
ተጨማሪ ዘገባ ይኖረናል…
ተመሳሳይ ዜና
Norway Ethiopians demonstration
Ethiopians in Norway have held a great and spectacular demonstration opposing the recentevictions of ethnic Amharas from different parts of Ethiopia and demanding freedom in Ethiopia.

ሰላማዊ ሰልፍ በለንደን፣ በወገናችን በአማራው ላይ የሚደረገውን የዘር ማጥፋት እናስቁም!



እንደ አውሮፓ አቆጣጠር ኤፕሪል 23፣ ቀን 2013 በእንግሊዝ ፓርላማ ውስጥ የአማራውን ስቃይ በሚመለከት በሚስተር ዴቭ አንደርሰን (የፓርላማ አባል) ለፓርላማው ጥያቄ ስለሚቀርብ ከፓርላማው ፊት ለፊት ከ2፡00pm እስከ 6:00pm ድረስ በቁም ሰልፍ ላይ በመገኘት አማራውንና ሌሎች ወንድሞቹን ኢትዮጵያውያን በዘር በመከፋፈል ጨርሶ ለማጥፋት ቆርጦ የተነሳውን ወያኔን ማውገዝ ብቻ ሳይሆን ፀረ-ህዝብ ተግባሩን ማስቆም እንድንችል ሀገሬንና የህዝቡን አንድነት እወዳለሁ የሚል ሁሉ በቦታው እንዲገኝና በእንግሊዝ መንግስት ላይ ተጽእኖ እንዲያሳድር ይህ ጥሪ ተላልፎለታል።
እባኮትን ቀደም ብለው መጥተው ሚስተር ዴቭ አንደርሰንን ይደግፉ
Stop the Genocide and Ethnic Cleansing of Amharas by TPLF

Ethiopia: The sorry and dangerous acts of Woyane ethnic warlords and their stooges


እባቱ ዳኛ ልጁ ቀማኛ…፣ የሌባ አይነ ደረቅ መልሶ ልብ ያድርቅ…፣ አወቅሽ አወቅሸ ሲሏት የቄሱን መፅሀፍ አጠበች… ሆኖ ቀረ የወያኔ ነገር?

The ruling regime of Ethiopia, Woyane is acting comical at times and more deadly other times since their beloved ethnic peddling tyrant extraordinary departed; leaving the warlords in disarray.  Lost in the wonderland are the collections of stooges left to tend for themselves. With no one to guide them, the only thing holding them together seems the memory of the only tyrant they knew that left them in the middle of a dead-end road with no return address and the loot he help them accumulate for two decades.
Some of TPLF ‘Mafia group’ that remained to bleed the people of Ethiopia
Some of TPLF ‘Mafia group’ that remained to bleed the people of Ethiopia
It isn’t unusual for an average house of tyranny to be frightened when its self inflected demise approaches faster than it expects. Some tyrannies reverse gear and pretend to present themselves with the best behavior they can master to fool the world. Others panic and get nastier than ever and go on in a killing spree until the end. Few are in complete chaos to know what to do next and try everything; mixing nastiness and best behavior to see if they wither the storm to return back to their natural habits.

Friday, 19 April 2013

እስረኛ እንኳን እየበላ ነው የሚቀጣው” የቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የተመለከ ተዕይታ




  •  ” እስረኛ እንኳን እየበላ ነው የሚቀጣው … ፈርኦንም ሕዝቡን በምግብ አልቀጣም… ለመለመን ከኮሌጁ ግቢ ውጭ ስለተከለከልን ከውስጥ ሆነን በአጥር ስር ነው የምንለምነው ” የቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች
  • ”ምግብማ እግዚአብሔርስ እስራኤላውያንን መቼ በምግብ ቀጣ እየመገበ ነው…..” አቡነ ህዝቅኤል የቅዱስ ሲኖዶስ ፀሐፊ
  • ”ጉዳዩ እርስዎን ይመለከታል ተብዬ ነው ወደ እርስዎ የደወልኩት” የኢሳት ራድዮ ጋዜጠኛ መሳይ ለአባ ሰረቀ በአማርኛ ላቀረበላቸው ጥያቄ
  • ”አይ ውል ፋይንድ አውት” አባ ሰረቀ በአማርኛ ላቀረበላቸው ጥያቄ በእንግሊዝኛ ሲመልሱ

GUDAYACHN BLOG
በቀል ሃይማኖታዊ መሰረት የለውም
የቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች የአስተዳደር እና የመምህራን ጉዳይ ጋር በተያያዘ ባነሱት ጥያቄ ኮሌጁ በማን እንደተዘጋ አልታወቀም።ይህ ማለት በኮሌጁ አስተዳደር አይደለም ለማለት ባይቻልም ተማሪዎቹ ለቀው እንዲወጡ የተደረገበት ማስታወቂያ ፊርማ እና ስም የሌለው ግን የኮሌጁ ማህተም ብቻ ያለበት መሆኑ ተነግሯል። በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ብቻ ሳይሆን በብዙ ሌሎች ተቋማት ውስጥ እርምጃዎች ሲወሰዱ የሚመለከተው አስተዳደር ሽባ ሆኖ የማይታዩ እጆች ግን ሲያሽከረክሩት ማየት የተለመደ ነው። በቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅም የሚስተዋለው ይሄው ነው።አቡነ ህዝቅኤል የቅዱስ ሲኖዶስ ፀሐፊ ስለጉዳዩ ሲጠየቁ የማያውቁ ሆነው መቅረባቸው ከሁሉም ደግሞ ”ጉዳዩን የሚመለከተው ቦርዱ ነው ቦርዱ ስብሰባም ላይ ትናንት ተገኝቻለሁ” ብለው ”ውሳኔውን ግን አልነገሩኝም ” ማለት  አሳዛኝ ብቻ ሳይሆን ቤተክህነቱን ከሚመለከታቸው በላይ አለቆች እንዳሉባት የሚያመላክት ነው።
የኮሌጁ የኃላ ታሪክ
በ 1942 ዓም እኤአ በቀዳማዊ አፄ ሃይለስላሴ የተመሰረተው የቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ በታህሳስ 1961 ዓም እኤአ በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ስር ሆኖ አገልግሎቱን እንዲሰጥ ተደረገ።ሆኖም ግን የንጉሡ ዘመን በደርግ ስርዓት ሲተካ ኮሌጁ የመዘጋት ዕድል ገጠመው። ይሄውም በ 1970 ዓም እንደሀገራችን ዘመን አቆጣጠር ኮሌጁ ሲዘጋ በወቅቱ የነበሩት ተማሪዎች ወደ አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ እንዲዛወሩ እና የኮሌጁ ህንፃ ለአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ሳይንስ ፋክልቲ እንዲሰጥ ተደረገ። የደርግ መንግስት ወድቆ ኢህአዲግ ስልጣን እንደያዘ አቡነ ጳውሎስ መንበረ ጵጵስናውን ያዙ።አቡነ ጳውሎስ ካደረጉት ነገር አንዱ የኮሌጁ እንደገና የማስከፈት ሂደትን ”ኮሌጁ ለቤተክርስቲያኒቱ ይመለስ” የሚል የድጋፍ መጠየቅያ  ፊርማ  አሰባስቦ መንግስት ኮሌጁን እንዲመልስ መጠየቅ እና ማስመለስ ነበር።

ትላንት ወልቃይት ጠገዴ፣ በደኖ አርባጉጉና ጋምቤላ፣ ዛሬ ጉራፈርዳና ቤንሻንጉል፣ ነገስ?



ሚያዝያ 9/2005ዓ/ም (April 17, 2013)

ከውጭ ሀገር የወልቃይት ጠገዴ ተወላጅ ኢትዮጵያዊያን 

“ሰውን ሰው ውጦት” ይላሉ እናቶቻችን የእናትነትንና የወሊድን ምስጢር ሲገልፁ፡፡ በዚህ የፈጣሪ ህግጋት ተገዳ በምጥ የምትጨነቅን እናት፣ እህት፣ ወይም ሚስት በጭካኔ መኪና ላይ እንደ አልባሌ እቃ ተወርውራ ከእነ ፅንሷ ለሞት ስትዳረግ፤ ለአይን የሚያሳሱ የእግዚአብሔር ንፁሃን ህፃናት ተወልደው ከሚድሁበት ቀያቼው እንደ ትቢያ ታፍሰው በግፍ በመወርወራቸው እስትንፋሳቸው በጭንቅ ስትቋረጥ ፤ ክፉና ደጉን ለይተው የሚያውቁ(የማያውቁ አላልንም) ታዳጊ ወጣቶች ሃገሬ ከሚሏት መንደራቸውና ህይወቴና ሙያዬ ከሚሉት የትምህርት ገበታቸው በማን አለብኝነት ሲሳደዱ፤ አባወራዎች ሀገሬ ርስቴ ብለው ጫካ መንጥረው፣ የእባብና የጊንጡን ንክሻ ችለው፣ የጅብና የአንበሳውን ትግልና ንጥቂያ ተቋቁመው ከቆረቆሩትና ካለሙት ቀያቸው በልጆቻቸውና በሚስቶቻቸው ፊት እንደ ሌባ እየተገረፉ፣ እንደ መፃተኛ ሲዋከቡና ወደ ማያውቁት ስፍራ በገፍ ሲጋዙ ማየትና መስማት ይልቁንም ይህ ሁሉ ሰቆቃና ግፍ የሚፈፀምባቸው “ዐማራ” በመሆናችሁ ነው መባሉ ምንኛ ነብስያ ድረስ ያማል? እንደምን እንቅልፍ ይነሳል? እኮ ምን ያህልስ ያስቆጣል? 

ወያኔዎች ታላቋን ትግራይ ለመመስረት ካደረባቸው ጽኑ ህመም በመነሳት በ1968ዓ.ም የትግራይ ማኒፌስቶ በመቅረጽ ከተነሱበት ግዜ ጀምሮ የጎንደርንና የወሎን ለም መሬቶችን በመቆጣጠር ሲጀመር በነዚህ አካባቢዎች ውስጥ ነዋሪ የሆኑትን ጎንደሬዎች በማፅዳትና በትግራይ ህዝብ በመተካት ይጠናከርና ማቆሚያው የጠፋች ወይም እጅግ ደካማ የሆነች ኢትዮጵያን በመፍጠር ይሆናል። ይህን እኩይ ሴራ እውን ለማድረግ ወያኔ ከ1972ዓ.ም ጀምሮ ወደ ጎንደር ለም መሬቶች ወደ ወልቃይት ጠገዴና ጠለምት በመዝለቅ ዘር ማፅዳቱን ቀጥሏል፡፡ ከዚያን ግዜ ጀምሮ እስከ 1983ዓ.ም ድረስ በነበረው የመከራ ጊዜ ብቻ ከ20,000 በላይ ንፁሃን ወገኖቻችን በህወሃት “ባዶ ስድስት” እየተባለ በሚታወቀው አሰቃቂ የመሬት ውስጥ እስር ቤት ታጉረው በግፍ ያለቁ ሲሆን፣ ከ70,000 በላይ ህዝባችን የህወሃት ወራሪ ቡድን በአካባቢው የሚፈፀመውን ግፍና መከራ በመሸሸት ለስደት ተዳርጓል፡፡ ይሁን እንጂ ከዚያ እጅግ ዘግናኝና ታሪክ ይቅር ከማይለው ሰቆቃ ማምለጥ ያልቻሉ ሴቶች፣ ህፃናትና፣ አረጋውያን ባድማ ጠባቂ በመሆን ቀጣዩን የህወሃት ግፍና መከራ ለማስተናገድ ተገደዋል፡፡

እያንዳንዱ ዜጋ ከራሱ ጋር ይነጋገር” አርቲስት ታማኝ በየነ


በታም ገዳ

በኢትዮጵያ  ውስጥ እየተካሄደ ያለው አስከፊ የሰብአዊ መብት  ረገጣ ይቆም ዘንድ እያንዳንዱ ዜጋ  የበኩሉን  አሰተዋጽኦ ሊያበረክት  እንደሚገባው እና ከራሱ ጋር መነጋገር እንዳለበት
Artist Tamagne Beyene in the United States
ተገለጸ፡፡ይሄ የተገለጸው  እርቲስት  እና  እክቲቬስት ታማኝ በየነ የኢትዮጵያ  ሳተላይት  ቴሌቭዥን ኢሳት የተመሰረተበት  3ኛ  አመት  እና ጣቢያውን  ለማጠናከር  ባለፈው ቅዳሜ ሚያዚያ 13 2013 እኤአ በ አሜሪካው የካሊፎርኒያ ግዛት በሎሳንጀለስ  ከተማ በተደረገው  የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ላይ  በመገኘት  ለተሰበሳቢዎች እና  ለኢሳት  አጋሮች  በሰጠው አሰተያየቱ  ነው፡፡

በተለይ  አርቲስት ታማኝ የህብር  ራዲዮ  ዘጋቢ  ከሆነው ከዚህ ጸሃፊ (ከታምሩ ገዳ  )ጋር ከገቢ የማሰባሰብ ፕሮግራሙ በሁዋላ ባደረገው  ቃለምልልስ  “ሌላው ቢቀር  ልጆቻችን  አገራቸውን ጥለው እንዳይሰደዱ  እና በአገራቸው ተደላድለው  እንዲኖሩ ለማድረግ በአገር ቤት በመካሄድ ላይ ያለውን የግፍ ቀንበር ልንሰብረው  ይገባናል፡በሶስት  ሺህ ዘመን አለም በተለያዩ  የኢኮኖሚ  እድገት ላይ ሲገኝ እኛ ግን ከሁሉ አገር በታች በደመ ነፍስ  በሚነዳ  እና ህግ በሌለበት  ብቸኛ አገር ውስጥ እንገኛለን፡፡” ያለው  አርቲስት ታማኝ ሁሉም ዜጋ  የበኩሉን  ጥረት  ማድረግ እንዳለበት  አስረግጦ  የተናገረ ሲሆን  አስተያየቱን ሲያራዝምም  “እኛ እናልፋልን  ነገር ግን  ቢያንስ ልጆቻችን  ተድላድለው  እንዲኖሩ  ይህን በደል  የማስቆም    የሞራል ግዴታ አለብን፡ እነ ታማኝ  ወይም እነ እገሌ  ምን አደረጉ? የሚባልበት  ወቅት ሳይሆን   ለምንድን ነው  አገሬ ውስጥ ዘወትር  ችግር ብቻ የምሰማው? እንደሌሎች አገሮች  መሆን የተሳነን ለምንድን ነው?  ሲል እያንዳንዱ ዜጋ እራሱን እንደዜጋ ሊጠይቅ    ግዴታ አለበት፡፡”ብሏል፡፡
አርቲስት  እና አክቲቬስት ታማኝ በየነ
ኢሳትን የመሳሰሉ ነጻ የመረጃ ምንጮች  ይስፋፉ ዘንድ   ምን መደረግ እንዳለበት የሚያስተላልፈው  መልእክት ካለ ተብሎ ከህብር ራዲዮ ለቀረበለት ጥያቄ  አርቲስት እና አክቲቬስት
Tamagne Beyene in the US
  ታማኝ ሲመልስ”  ይህ አይነቱ ሃሳብ  ነው ሊበረታታ የሚገባው ከዛሬ ሶስት አመት  በፊት ኢሳት አልነበረም:: ዛሬ ግን ጋምቤላ ውስጥ ችግር ሲፈጠር በኢሳት  አማካኝነት  ትሰማዋለህ :፡የአማራ ክልል ተወላጆች ከተለያዩ እካባቢዎች  በግፍ  ሲባረሩ  ኢሳት ላይ  ወዲያውኑ ትሰማዋለህ:: በሙስሊም  ወገኖቻችን  ላይ  በደል ሲደርስ  እንደዚሁ ኢሳት ላይ  መረጃውን ትሰማዋለህ፡፡በመረጃ የተደገፈ ዜና ለማግኘት ህዝቡ አስተዋጽኦ ማድረግ አለበት፡፡የህቺ እንግዲህ በሶስት አመት  ውስጥ የተገኘ  የሁላችን የጥረት ውጤት ነው ፡፡ ሶስት አመት በጣም  ትንሽ ጊዜ ነው ፡፡ኢሳት የሶስት አመት ልጅ ነው ፡፡ ልጅን ስናሳድግ ደግሞ ይታመምብናል: ምግብ አይስማማውም፡ብርጭቆ ይሰብራል ይሄን ሁሉ እየተከታተልክ አይደል  ልጅህን የምታሳድገው?ኢሳትም እንዲሁ ደካማ ሊሆን ይችላል ነገር ግን ሁሉም ሰው በመተባበር የተሟላ የሚዲያ ተቋም ሊያደርገው ይችላል፡፡ለዚህ መሰሉ በጎ ተግባራት  አስተዋጽኦ ማድረግ የእያንዳንዱ ዜጋ ግዴታ ነው፡፡” ብላል፡፡   በስተመጨረሻም የተጠናከረ  ስራ ለማካሄድ ምን መደረግ አለበት? ለሚለው ጥያቄ ሲመልስ  “ አያንዳንዱ ዜጋ ከራሱ ጋር ይነጋገር:: ወደዚህ ምድር ላይ የምጣሁበት ተልኮዮ ምንድን ነው ? ምን አድርጌ ነው የምሄደው? በእየ ወሩ ለቤተሰቤ 300 ወይም 400 የአሜሪካ  ዶላር መላክ?   በ ተሻለ ቤትውስጥ  ለመኖር ወይም ዘመናዊ  መኪና ለማሽከርከር  የተሻለ ልብስ ለመልበስ ነው ወደዚህ አለም የመጣነው? እንደእኔ እምነት አገራችን ወደ ተሻለ ደረጃ እንድትሸጋገር ጥረት ማድረግ  እያንዳንዱ ዜጋ በሚችለው እና አቅሙ በፈቀደው መጠን  ብሄራዊ ግዴታውን ሊወጣ ይገባል ፡፡ቁጭ ብሎ መተችት ለውጥ አያመጣም፡፡አስተዋጽኦ  ማድረግ አለብን፡፡በምናምንበት መንገድ በምንም ይሁን  የእኔ ፍላጎት እና ስሜት የሚያደላው በዚህ  ላይ ስለሆነ እስተዋጽኦ ማድረግ እፈልጋለሁ ብሎ  በጉልበት ይሁን   በእውቀት በምክር ሊሆን ይችላል ፡፡ይሄ የጥቂት  ወገኖች እህላፊነት ተደርጎ መወስድ የለበትም ፡፡ የሁሉም ወገን እርብርቦሽ ሊሆን ይገባል ፡፡” ብሏል::

Thursday, 18 April 2013

Mr. Obang Metho’s Statement at the U.S. Congressional Briefing on Land Grabs in Africa



African Land and Natural Resource Grabs Destroy Lives and Futures of Africans

Mr. Obang Metho, from the SMNE, gives warning of the impacts on the people at the U.S. Congressional Briefing on Land Grabs in Africa

I would like to thanks Congressman Christopher Smith, Chairman of the U.S. House Subcommittee on Africa, Global Health, Global Human Rights and International Organizations and members of the subcommittees for making this briefing on land grabs in Africa possible.
I am honored to be among those invited to talk about the impact of these land and resource grabs on the people of Africa. It is a vitally important issue that needs to be confronted. To me, this is not just about land grabs, but it is inherently about life grabs. In Africa, as well as in many other places, when you take someone’s land, you take away the means to an entire family’s livelihood, wellbeing and future. I am thrilled that the World Bank is also addressing this issue and hope it will soon lead to concrete action that saves lives.  
To me and the organization I lead, the Solidarity Movement for a New Ethiopia (SMNE), the problem of land grabs is not
Mr. Obang Metho (center) at the U.S. Congressional Briefing
Mr. Obang Metho (center) at the U.S. Congressional Briefing
new. We have been actively working to expose and find solutions to these land grabs since they began in 2008 and partnered with the Oakland Institute in 2011 in a comprehensive in-country study on: Understanding Land Investment Deals in Africa: Ethiopia.[i] What is going on today is an immoral and predatory practice by African strongmen and their powerful partners that is targeting the most vulnerable people on the continent.
When I speak today, my testimony will not be as an outsider, but as a witness. When I talk about the people being displaced from the land grabs, in many cases I am speaking about people whose names I know. They include my uncle, my cousins, my nephews, my extended family, my community and my people—the people of Gambella, the people of Ethiopia, the people of Africa and the people of the world. We the people of Africa must be able to feed ourselves, but when the powerful take the food and land we have to sustain ourselves, leaving little behind for the indigenous, it is unconscionable and should be challenged. I welcome the opportunity we have to talk about this today. I request that my statement be submitted into the record in its entirety.