Saturday, 6 April 2013

ገረብ ገረብ ትግራይ መቃብር አምሃራይ


ቴዎድሮስ ሐይሌ (tadyha@gmail.com)

አንካሳ በምርኩዝ እውሩ በመሪ የተከተልዎ፤
እህል አይበቅልም ወይ ንጉስ በአገርዎ፤
በጽዮኗ እመቤት በጭንቅ አዛኝዎ፤
በቅዱስ ሚካኤል በጋሻ ጃግሬዎ፤
ጎጃምን ይማሩት ፈሪም አንልዎ።

ከታላቁ ንጉስ አጼ ቴዎድሮስ ሞት በኋላ የነገሱት የትግራዩ መሳፍንት ወገን የሆኑት አጼ ዮሃንስ ንግስናቸውን ለማጠናከር ጎጃምን በወረሩ ግዜ ታሪክ እንደሚለው ተከታይ ሰራዊታቸው የሃገሬውን ሃብት በጎተራ ያለ እህል በበረት ያለ መንጋ ከብት በሜዳ ላይ የነበረ ክምርና ያልታጨደ ሰብል ሳይቀር ያለ ምህረት ሙልጭ አርጎ በመዝረፍ ህዝቡንም በከባድ የአካልና የሞት ቅጣት በመፈጸም ያካሄዱትን ከፍ ያለ መከራ የተመለከተ ከስቃይ ያመለጠ ገጣሚ ያቀረበው ቁጣና ተማጽኖ ነበር።
የቀድሞዎቹ የስሁል ሚካኤል አልጋ ወራሽ ቤተሰቦች ለስልጣን ካላቸው መቋመጥ የተነሳ የሃገር ክብርና ኩራትን አሽቀንጥረው በመጣል የእንግሊዝ መንግስትን ጦር መሪ የጀነራል ናፒየርን ወራሪ ጦር መንገድ በመምራት አህያ በመንዳት ታላቁን ባለ ራዕዩንና በክፍለ ዘመናት ውስጥ እንኳ ሊተካ ያልቻለውን የስልጣኔ ጥመኛ የሃገር ፍቅር ቃልኪዳን ምርኮኛ ለእግሩ ጫማ ለኑሮው ምቾት ያልነበረውን ሃገሩን ከአውሮፓ ጋር በስልጣኔ ሊያስተካክል የተነሳ ሕልመኛ ለቅንጣት አፈሯ ቅናተኛ የነበረውን መይሳው አባታጠቅ ካሳን አፄ ቴዎድሮስን ሕልም በማጨለም ይህ ታላቅ ንጉሰ ነገስት ያለ ግዜው እንዲሞት የትግራይ መሳፍንቶች የፈጸሙት የሃገር ክህደት ወንጀል አብሮ ለመኖር ሲባል ዝም ተብሎ ቢቆይም እንዲህ ክፋታቸው ሲያይል ታሪክን ማጣቀስና ሃቁን ማስተጋባት እንድንገደድ ጭካኔያቸው ግድ ይለናል።

ታሪክ ራሱን ይደግማል እንዲሉ ምንም አጼ ዮሃንስ በዛሬዎቹ ኩታራ የባንዳ ልጆችና ግልገል ፋሽስቶች ሚዛን መሰፈር የማይገባቸው ታላቅ ኢትዮጽያዊ ንጉስ ለመሆናቸው ያለኝን አክብሮት ሳልቀንስ ታሪካዊ ኩነቱ ግን መጠቀስ ስለ አለበት ትላንት የንጉሱ ሰራዊት ሆኖ የጎጃም አማሮችን እጅና እግር እየቆረጠ ሃብታቸውን እየዘረፈ ህዝቡ ላይ መከራ አጽንቶ የነበረው ከትግራይ የመጣ ወራሪ ሠራዊት የተፈጸመው በደል በህዝቡ ይቅር ተብሎ ቂምና ቁርሾ ተወግዶ በአምቻና ጋብቻ ቤተሰባዊ እየሆነ በዘኬው በእድሩ በአድባር መንደሩ ተስማምቶ ለመኖር ሳያግደው ምዕተ ዓመት ቢያስቆጥርም የፍቅር ጠንቅ የአንድነት ተውሳክ የሆነው በአናሳነት ስነ ልቦና በዳሸቁ እንደ መለስ ባሉ የፋሽስት ጣሊያን ባንዳና ሹንባሽ ልጆች ክፉ ሃሳብ የተፈጠረው የትግሬ ነጻ አውጪ ነኝ ባዩ ወያኔ የብተና አጀንዳ ለማስፈጸም በተከተለው የጎሳ ፖለቲካ ሳቢያ ትውልዱ በአብሮነት መኖር እንዳይችል የዘር ግንብ በመትከል የተካሄደው ክፉ ዘረኛ የኢንተርሃሞይ ቅስቀሳ ሳያንስ ዜጎች በሃገራቸው ምድር ጫካ መንጥረው ከወባ ጋር ታግለው ካለሙት ምድረ በዳ ሃብት ሲያገኙ መለወጥ ሲጀምሩ ክፋትና ቅናት ተንኮልና ጥላቻ ያነገቡት የዛሬዎቹ የትግሬ ነጻ አውጪዎች የአማራውን ተወላጅ በግፍ ሃብትና ንብረቱን እየቀሙ የሚያደርጉት ማፈናቀል በእቅድና ፕላን የሚፈጸም አትግደለው እንዲሞት ግን አድርገው በሚለው የትግርኛ ብሂል አንጻር የአማራው ተወላጅ ከሞቀ ጎጆው ተፈናቅሎ ለጎዳና ፤ አርሶና ቆፍሮ እሸት በሚዘግንበት እጁ ምጽዋት እንዲለምን ፤ የማድረግ የበቀል አካሄድ ለማሰቆም በሚያስችል ደረጃ አማራው ራሱን እስካላዘጋጀ ድረስ በከፋ መልኩ የሚቀጥል ለመሆኑ ደደቢት በረሃ ተረቆ የተዘጋጀው የወያኔ ማኒፌስቶ ደረጃ በደረጃ እየተሰራበት መሆኑን አስረግጠው የሚናገሩት የቀድሞው የድርጅቱ አባላት ተጨባጭ ማረጋገጫዎች ናቸው ።
አማራው በእንዲህ ያለ ፍርደ ገምድል አረመኔያዊ ግፍ በሚፈጠምበት ሁኔታ ላይ ወያኔው የኔ ብሎ በሚጠራው የትግራይ ክልልን መጠነሰፊ በሆነ የእድገት ጎዳና እንድትራመድ ለማድረግ የተቀየሰው አስነዋሪ አፓርታይዳዊ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ አድሎ አለም አቀፍ ተቋማት ጭምር አጽዕኖት ሰጥተው በማስረጃ ጭምር እንዳረጋገጡት በአሁኑ ወቅት ከመላው የኢትዮጽያ ክልሎች በግብርና በቴክኖሎጂ በትምህርት ጥራት በኢንዱስትሪ በልማት በገቢ ቀመር በኑሮ ደረጃ በብዙ መመዘኛዎች የትግራይ ክልል በሁሉ ነገር ልቆ እንዲገኝ መደረጉን የውጭ ታዛቢዎች እንዲህ በተጣራ ሁኔታ ቢገልጹትም አይን የሚያየው ጆሮ የሚሰማው የአደባባይ ሚስጥር ሆኖ ለመቆየቱ ሕዝባችን የሚያውቀው ሃቅ ነው። ወያኔዎች እንዲህ ትግራይን በሌላው ኪሳራ ሲያደልቡ በአንጻሩ ሃገሬ ብሎ በየቦታው ተበትኖ ላቡን አፍስሶ ወዙን ጠብ አድርጎ ራሱንም ሃገሩን በመጥቀም ላይ የነበረውን በተለይ የአማራ ተወላጆች ላይ ከጊዜ ወደግዜ እየተጠናከረ የመጣው የማፈናቀልና ዘር የማጥፋት ዘመቻ ቀድሞ ወያኔው በረሃ በነበረ ግዜ “ገረብ ገረብ ትግራይ መቃብር አምሃራይ’’ በአማርኛ የትግራይ ሸለቆዎችና ኮረብቶች የአማራ መቀበሪያ ይሆናሉ እያሉ ነበር ከበሮዐቸውን ሲደልቁ የኖሩት ይህው ዛሬ ሁኔታው ሰምሮላቸው በከበሮ ፋንታ አማራውን በመከራ እየደለቁት ጮቤ ለመርገጥ በቅተዋል። እዚህ ላይ የዛሬን አያድርገውና የዛሬ 16 አመት ገደማ የቀድሞው የትግል አጋሬ ልደቱ አያሌው በተባ ብዕሩ ከላይ በተቀመጠው ርዕስ ስር የተብራራና መጪ ሁኔታዎችን ያገናዘበ ትንተናውን በአንድነት ጋዜጣ ላይ አውጥቶት አንዳንዶች ከፋፋይ ሃሳብ ነው ሲሉ ጠንካራ ትችት ሲሰነዝሩበት እንደነበር አስታውሳለሁ። ነገራችን ሁሉ የተገላቢጦሽ ሆኖ ጽሁፉን በእኔ እምነት በትንቢት ደረጃ ስወስደው ጸሃፊው ግን በተቃራኒው የገባበት የሦስተኛ ረድፈኝነት የባልቴት ፖለቲካ እጅጉን ያሳዝነኛል።
አማራው ሰርቶ ከሚኖርበት ተወልዶ ካደገበት ቅዬው በግፍ እየተፈናቀለ ለድህነትና ለተረጂነት በሚደረግበት በአሁኑ ወቅት ትውልዱ ባለው የስራ አጥነት የኑሮ ውድነት የአገዛዙ አፈናና በተንሰራፋው ለከት የለሽ ኢሞራላዊ የግልሙትና ባህል ተስፋ በመቁረጥ ስደትን ብቸኛ አማራጭ በማድረግ በገፍ በሚሰደድበት ሁኔታ ላይ በትግራይ ግን የወጣው ፀሃይ የማይጠልቅ በኢትዮጽያውያን ሞት ስደት መከራና ስቃይ ላይ ስትሞሸር በህዝቦች ጉስቁልና በወገን ረሃብ ድህነትና እንግልት ላይ በመገንባት ላይ ያለች የግፍና የሃጥያት ከተማ ዘመናይቷ ባቢሎን በዘራፊ ልጆቿ በደም አፍሳሽ ሰውበላ ነጻ አውጪዎቿ ጎጆዋ የሞላላት ሰላሟ የተቃናላት ትዳሯ የሰመረላት የምስራቅ አፍሪካዊቷ ሲንጋፖር የኢንዱስትሪ ቀጠና ድርቀቷ እንደጉም ተኖ የልምላሜ ምሳሌ የተባለላት በእርሻ የበለጸገች በምርት የተሻለች ለመሆን የበቃች በረሃብ ከሚናውዘው በጥም አሩር ከነደደው በእርዛት ቁር ከሚጠብሰው የምግብ እጦት አጥወልውሎ ከሚደፋቸው ህጻናት አፍ ተነጥቆ በቀማኛ ልጆቿ ታታሪነት ሃገር እየፈረሰ የምትገነባ እናቷን በልታ የምትደልብ ጋለሞታይዩ ሙሽራ በውስጥም በውጪም ያሉ ልጆቿ ከጥቂቶች በቀር አብዛኞቿ የተያያዘችወን የግፍ መንገድ ተይ ማለት ያቃታቸው ነጻ አውጪዋ ነኝ ባዩን ጉግማንጉግ የወያኔ ጀሌ አጆሃ ባዮች የበዙባት ተቻችሎ መኖርን ሃገራዊ አንድነትን ከቁብ ያልቆጠሩ የዘረኝነት ትራኮማ አይነልቦናቸውን የጋረደባቸው ያየሉባት በሕዝብ ለቅሶ ጮቤ የሚረግጡ ለዜጎች መፈናቀል የሚደረገውን ተቃውሞ የሚያላግጡ ሃይላቸው የማይደክም እብሪታቸው የማይናድ መስሎ የሚሰማቸው የህዝብ ትግዕስትና አስተዋይነትን በፍርሃት ሂሳብ መንዝረው የመቻቻልን መንገድ ለሚዘጉ የብዙሃንን ሃያልነትና አሸናፊነት ለማስተዋል ሕሊና ያጡ የገዠው ቡድን ደጋፊ ጭፍሮች የዘነጉት የሚፈጽሙት ወንጀል ጊዜውን ጠብቆ እንደሚያስፈርድባቸው ጭምር ነው። ሌላው ወያኔና ተከታዮቹ ያላስተዋሉት አካሄዳቸው እንደ ሃገር በአብሮነት የመቀጠላችንን ሁኔታ እንዲያጠላበት የሚያደርግና ትውልድ የሚያጨራርስ አካሄድ በመሆኑ መጪውን ዘመን አደገኛ እያደረገው ይገኛል።
አንዳንድ የአገዛዙ ደጋፊ የሆኑ ድህረ ገጾች በአማራው ላይ የሚካሄደውን ግፍ ተው ከማለት ይልቅ ይደልዎ አጁሃ ይገባዋል መፈናቀል ይኖርበታል የሚል አዝማች ይዘው የሚያካሂዱት ሂትለራዊ ቅስቀሳ በቅጡ የተደራጀ ሃይል አለመኖሩ እንጂ በምዕራቡ ዓለም ሕግና ደንብ መሠረት ተገቢ ቅጣት የሚያስከትል ከባድ ወንጀል ነበር። በአንጻሩም አንዳንድ በጥቅማ ጥቅም ከዐገዛዙ ጋር ተሞዳምደው በአድርባይነት ሲያገለግሉ ከነበሩት ውስጥ በፈረስ ስሙ አባ መላ የሚባለው የቀድሞው የደርግ መንግስት ኮሚሳር የነበረ ቀንደኛ የወያኔ ቱርጁማን ሰሞኑን በጥቅም ላሽቆ የነበረ ሕሊናውን ሰንጥቆ በወጣ መልካም ተግባር ለወገንና ለሰብዐዊነት ከመቆርቆር አንጻር በአንድ የፓልቶክ መድረክ ላይ ያቀረበው ሃላፊነት የተሞላው ትንተና የወያኔን የግፍ ተግባር በተባ አንደበቱ የገለጸበት ተገቢ ቃል ምንም ግለሰቡ ከማህበረሰባችን ጋር ሆድና ጀርባ ሆኖ የቆየ ቢሆንም ያቀረበው ሂስ ላዳመጠው አስተማሪ ብቻ ሳይሆን ሁኔታውን በተገቢ መንገድ የተነተነ ፖለቲካዊ ዕይታ ነው።
ለማጠቃለል የትግሬው ወያኔ እያከሄደ ያለው የአማራውን ዘር የማዳከምና ጨርሶም የማጥፋት ዘመቻ እንዲህ በቀላሉ የሚገታ ባለመሆኑ ኢትዮጽያ እንደ ሃገር እንድትቀጥል የሚፈልግ ቅን ዜጋ በይበልጥም የአማራው ተወላጅ ለረጅም ግዜ ተቆራኝቶት ከቆየው አፍዝ አደንግዝ የህብረ ብሄር ፖለቲካ ስሌት ተላቆ አማራጭ በሆነው በዘውግ አሰላለፍ በራሱ ዙሪያ የመሰባሰብን የውይይትና የመደራጀት አላማን በማሳካት ለወገኑ አፋጣኝ ምላሽ በመስጠት ሞት የታወጀበት የአማራው ተወላጅ ያለውን አቅም እውቀት ገንዘብና ጉልበት አስተባብሮ በግፍ ፈጻሚዎቹ የትግሬ ፋሽስቶች ላይ እንዲዘምት ጥቃቱን እንዲመክት ክብሩን እንዲያስጠብቅ ማደረግ የሚቻለው ከአማራው ሕዝብ አብራክ የተፈጠረው በተለይ በውጪ ሃገራት ያለው የአማራ ህብረተሰብ ከፍተኛ አስተዋጽዖ የሚጠበቅበት በመሆኑ ይህን ወገናዊ ጥሪ አፋጣኝ ምላሽ በመስጠት በዚህ ወገናችን ላይ የሚደርሰውን እንግልት ለመታደግ ለመከላከልና ለዘለቄታውም ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ከዚህ ሕገ አራዊት የትግሬ ነጻ አውጪ የአራዊት መንጋ ለመላቀቅ የዜግነት ድርሻችንን ለመወጣት መዘጋጀት ይኖርብናል።
እግዚያብሔር ይርዳን!!!
አሜን!!!


No comments:

Post a Comment