የታመመችውን ርዕዮትን የቃሊቲ ማረሚያ ቤት በቀጠሮዋ መሠረት ሐኪም ቤት እንደማይወስዳት አባትዋ ለዶቼቬለ ተናግረዋል ። በሌላ በኩል ጋዜጠኛ ውብሸት ታዮ ከቅሊንጦ ማረሚያ ቤት ወደ ዝዋይ እንዲዛወር መደረጉ ቤተሰቦቹና ወዳጅ ዘመዶቹ እንዳይጎበኙት እንቅፋት መሆኑ ተሰምቷል ።
የጋዜጣ ዓምደኛ የርዕዮት ዓለሙ የጤንነት ሁኔታ እንደሚያሳስባቸው ቤተሰቦቿ አስታወቁ ። የታመመችውን ርዕዮትን የቃሊቲ ማረሚያ ቤት በቀጠሮዋ መሠረት ሐኪም ቤት እንደማይወስዳት አባትዋ ለዶቼቬለ ተናግረዋል ። በሌላ በኩል ጋዜጠኛ ውብሸት ታዮ ከቅሊንጦ ማረሚያ ቤት ወደ ዝዋይ እንዲዛወር መደረጉ ቤተሰቦቹና ወዳጅ ዘመዶቹ እንዳይጎበኙት እንቅፋት መሆኑ ተሰምቷል ። የፌደራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር የህዝብ ግንኙነት የርዕዮት ዓለሙ የህክምና ቀጠሮ እንዳልተስተጓጎለና አሁንም በጥሩ የጤና ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ ገልጾ ፣ ጋዜጠኛ ውብሸት ታዮም በማንኛውም ፍርደኛ ላይ በሚደረግ መደበኛ ዝውውር ወደ ዝዋይ ማረሚያ ቤት መወሰዱን አስታውቋል ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዝርዝር ዘገባ አለው ።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ሂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ
No comments:
Post a Comment