በሳንዲያጎ የወያኔ አምባሳደር ይገኝበታል ተብሎ በአባይ ግድብ ስም ቦንድ ለመሸጥ የተጠራው ስብሰባ በኢትዮጵያውያን ተቃውሞ እንዲቋረጥ ሆንዋል።
በቁጥር ከሁለት መቶ በላይ የተቆጡና በርካታ መፈክሮችን ያነገቡ ኢትዮጵያውያን ስብሰባው በሚደረግበት አዳራሽ የተገኙት ቀደም ብለው ነበር።
በርካታ ታዋቂ ሚድያዎች በቦታው ተገኝተው የተቃውሞዉን ትዕይንት የዘገቡ ሲሆን የቴሌቪዥን ጣብያዎች ዜናውን ማምሻው ላይ ለቀውታል።
ወያኔዎቹ በሌሎች ቦታዎች የገጠማቸውን ከግምት አስገብተው 3 ሰዎች በር ላይ አቁመው የራሳቸውን ሰዎች ብቻ መርጠው ለማስገባት ያደረጉት ሙከራ አልተሳካም።
ስብሰባው ሲጀመር የወያኔዎቹ ቁጥር ከ20 በታች ሲሆን ኢትዮጵያውያኑ ከሁለት መቶ በላይ ነበሩ።
ነገር አሳምራለሁ ብሎ ስብሰባውን እንግሊዝኛ ቋንቋ በመናገር የጀመረው የወያኔ ተወካይ በጥዋቱ ነበር ተቃውሞ የገጠመው፣ ኢትዮጵያውያኑ “እኛ ኢትዮጵያውያን ነን በቋንቋችን ተናገር” ብለው አስቆሙት። ተወካዩ ንግግሩን በአማርኛ ቀጠለ “እኛና እናንተ…” ብሎ ሊቀጥል ሲል አሁንም ከባድ ተቃውሞ ገጠመው “እናንተ እነማን ናችሁ? እኛስ ማን ነን? አትከፋፍለን እኛ አንድ ነን” አሉት።
አይጋ ፎረም በመባል የሚታወቀው የጎሳ ድረ-ገጽ ተቃዋሚውን ሁሉ ፎቶ እያነሳ ለአባይ ግድብ ገንዘብ ተሰበሰበ እያለ ፕሮፓጋንዳ እንደሚሰራ የተረዱት የሳንድያጎ እና አካባቢው ነዋሪዎች በነብስ-ወከፍ መፈክር አንግበው ነበር በቦታው የተገኙት፣ በመሆኑም ለወያኔ ፕሮፓጋንዳ ፎቶም አልተመቹም።
ሁኔታው እንደተበላሸ የገባቸው ወያኔዎች ፖሊስ ተቃዋሚዎቻቸውን ለይቶ እንዲያስወጣላቸው ተማጸኑ፣ ፖሊሶቹ መጠነኛ ጥረት አድርገው ነበር ይሁንና የህዝቡን ቁጣ አይተው ተውት፣ ይልቁንም ወያኔዎቹን አጅበው አስወጧቸው።
አንዳንዶቹ ወያኔዎች ህዝቡን ከመፍራታቸው የተነሳ ከፖሊሶች ጀርባ ሲከለሉ ታይተዋል።
No comments:
Post a Comment