Sunday, 14 April 2013

በዊኒፔግ፣ ካናዳ የማርያም ቤተክርስቲያን ከዛሬ ጀምሮ በውጭው ሲኖዶስ ትመራለች



ECADF – ዊኒፔግ በሀገረ ካናዳ፣ በማኒቶባ ክፍለ-ሀገር የምትገኝ በቅዝቃዜዋ ታዋቂ የሆነች ከተማ ነች። በርካታ ኢትዮጵያውያን በዊኒፔግ ይኖራሉ፣ አብዛኛዎቹ ባለፉት 10 አመታት ወደ
Ethiopian-Orthodox-Church-Holy-Synod
 ከተማዋ ያቀኑ ሲሆን ሌሎች ደግሞ ከዛም ቀደም ብለው ነው በዊኒፔግ የከተሙት።

በዊኒፔግ ያሉ ኢትዮጵያውያን እንዳሳወቁት ከሆነ በከተማዋ የምትገኘው  ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን (ማርያም ቤተክርስቲያን) ከዛሬ ጀምሮ ውጭ ባለው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሲኖዶስ ስር ትተዳደራልች።
ይህን የቤተክርስቲያኗን ውሳኔ በርካታ ምዕመናን የሚደግፉት ሲሆን፣ ዜናውን ያቀበሉን ኢትዮጵያዊም ከደስታ ብዛት ሳግ ይተናነቃቸው ነበር።

No comments:

Post a Comment